ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

Friday, September 30, 2016

=>+*"+<+>†† መስከረም-21- ††

† መስከረም-21- እንኳን ለንጽሕተ ንጹሓን ቅድስተ ቅዱሳን
ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ግሸን ደብረከርቤ
ዳግማዊት ጎልጎታ - የግማደ መስቀሉ መገኛ ታላቅ ክብረ
በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
† ግሸን ደብረከርቤ ዳግማዊት ጎልጎታ - የግማደ መስቀሉ
መገኛ †
✔ሼር ✔ሼር
ግሸን ማርያም ደብር በወሎ ክፍለ ሀገር በአምባሰል አውራጃ
ውስጥ የምትገኝ ደብር ናት፤ ይህች ደብር በሐይቅና
በመቅደላ፤ በደላንታ፤ በየጁ መካከልና በበሸሎ ወንዝ አዋሳኝ
በርዋ አንድ ዙሪያውን በገደል የተከከበች አምባ ናት፡፡ በበርዋ
ከተገባ በኋላ ግቢዋ ከላይ ሜዳና መስቀለኛ ቦታ ነው፡፡
በትግራይ እንደ ደብረ ዳሞ በበጌምድር እንደዙር አምባ
በመንዝ እንደ አፍቅራ ናት ፡፡
ወደዚህች ደብር ለመሔድ በረሐ አቋርጦ በሸሎን በመሻገር ፫
ሰዓት መንገድ አቀበት በመውጣት አንድ ቀን ሙሉ ተጉዞ
ማታ ፲፪ ሰዓት ይገባል ፡፡ግሸን ማርያም በፊት ደብረ
እግዚአብሔር ትባል ነበር ፡፡ይህ ደብረ እግዚአብሔር
የሚለው ስያሜም በጻድቁ ንጉሥ ላሊበላ እጅ ከቋጥኝ
ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሠራ ቤተ መቅደስ በእግዚአብሔር አብ
ስም ስለነበረ ደብረ እግዚአብሔር ተብሎ የተጠራ ነው፡፡
ከዚያም በዓጼ ድግናዣን ዘመን መንግሥት የሐይቅ
እስጢፋኖስ ገዳም ሲመሠረት ሐይቅ ደብር ነጎድጓድ ተብሎ
ሲሰየም ግሸን የሐይቅ ግዛት ስለሆነች ከደብረ እግዚአብሔር
ደብረ ነጎድጓድ ተብላለች ፡፡
ከዚያም በ ፲፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ በዓጼ ዘርአ ያዕቆብ
ዘመነ መንግሥት የክርስቶስ ግማደ መስቀሉ ግሸን ገብቶ
ሲቀመጥ ከደብረ ነጎድጓድ ደብረ ከርቤ ተብላለች የደብሩ
አስተዳዳሪም መምህረ እሥራኤል ዘደብረ ከርቤ ይባል
ነበር፡፡ ከደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም ተብላለች፡፡
† የግማደ መስቀሉ መምጣት ታሪክ †
ዓለምንና በውስጡ የሚገኘውን ሁሉ ፍጡር ፈጥሮ
የሚገዛውን አምላክ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ቤተ
እሥራኤል በቀራንዮ ላይ በመስቀል ሰቀሉት ፡፡ መድኃኔዓለም
በዕለተ ዓርብ ከቀኔ በዘጠኝ ሰዓት ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት
ሥጋው በገዛ ሥልጣኑ ከለየ በኋላ በኋላ ከመስቀሉ አውርደው
ቀበሩት ፡፡በ፫ኛው ቀን ሲነሣ ተሰቅሎ የነበረው የእንጨት
መስቀል ሌት ተቀን በሙሉ ሳያቋርጥ እንደፀሐይ ሲያበራ
በተጨማሪም አጋንንት ሲያባርር ድውይ ሲፈውስ ሙት
ሲያነሣ ቤተ እሥራኤል አይሁድ ቀንተው በዓዋጅ ትልቅ
ጉድጓድ ቆፍረው በመቅበር የቤት ጥራጊና አመድ ጠቅላላ
የቆሻሻ መከማቻ እንዲሆን ወሰኑ፡፡ ከዚያ ዘመን ጀመሮ እስከ
ሦስት መቶ ዘመን ድረስ የተከማቸው ቆሻሻ እንደተራራ ሆነ፡፡
ከዚያ በኋላ የታላቁ ቆስጠንጢኖስ እናት እሌኒ ንግሥት
የተባለች ደግ ሴት የክርስቶስን መስቀል መስከረም ፲፯ ቀን
፫፻፳ ዓ.ም. ላይ በዕጣን ጢስ ምልክት ቁፋሮ አስጀምራ
መጋቢት ፲ ቀን አግኝታ በማውጣት ታላቅ ቤተ መቅደስ
ጎልጎታ ላይ ሠርታ በክብር አስቀመጠችው ይህ መስቀልም
ከዚያ ዘመን ጀምሮ እንደ ፀሐይ እያበራ ድውይ እየፈወሰ
አጋንንት እያባረረ ልዩ ልዩ ተአምራትን እየሠራ ሙት እያነሳ
ዕውር እያበራ ተአምራቱን ቀጠለ፡፡ ይህንንም ከኃያላን
ነገሥታት መካከል የፋርስ ንጉሥ መስቀሉን ማርኮ ፋርስ
ወስዶ አስቀመጠው በዚህ ጊዜ የኢየሩሳሌም ምዕመናን
የሮማውን ንጉሥ ሕርቃልን ዕርዳታ በመጠየቅ እንዲመለስ
አድርገው በኢየሩሳሌም ብዙ ዘመን ሲኖር እንደገና ኃያላን
ነገሥታት ይህን መስቀል እኔ እወስድ እኔ እወስድ እያሉ ጠብ
ፈጠሩ፡፡
በዚህ ጊዜ የኢየሩሳሌም ፤ የቁስጥንጥንያ ፤ የአንጾኪያ ፤
የኤፌሶን ፤ የአርማንያ ፤ የግሪክ ፤ የእስክንድርያ የመሳሰሉት
የሃይማኖት መሪዎች ጠቡን አበረዱት ከዚህም አያይዘው
በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የክርስቶስ መስቀል ከ፬ ከፍለው
በዕጣ አድርገው በስምምነት ተካፍለው ከሌሎቹ ታሪካዊ
ንዋያት ጋር በየሀገራቸው ወስደው በክብር አስቀመጡት፡፡
የቀኝ ክንፉ የደረሰው ለአፍሪቃ ስለነበር ከታሪካዊ ንዋያተ
ቅድሳት ጋር በግብጽ የሚገኘው የእስክንድርያ ፓትርያርክ
ተረክቦ ወስዶ በክብር አስቀመጠው፡፡
ይህ ግማደ መስቀልም ለብዙ ዘመን በእስክንድርያ ሲኖር
በግብጽ ያሉ እስላሞች እየበዙ ኃይላቸው እየጠነከረ ሔደ
በእስክንድርያ የሚኖሩትን ክርስቲያኖች ሥቃይ ያጸኑባቸው
ጀመር ክርስቲያኖቹም አንድ ሆነው መክረው ለኢትዮጵያዊ
ዓፄ ዳዊት እንዲህ የሚል መልዕክት ላኩ “ንጉሥ ሆይ! በዚህ
በግብጽ ያሉ እስላሞች መከራ አጽንተውብናልና ኃይልህን
አንሥተህ አስታግሥልን ብለው ጠየቁት” ዳግማዊ ዓፄ
ዳዊትም ለመንፈሳዊ ኃይማኖት ቀንተው የክርስቶስ ፍቅር
አስገድዶአቸው ፳ ሽህ ሠራዊት አስከትለው ወደ ግብፅ ዘመቱ
በዚህ ጊዜ በግብፅ ያሉ ኃያላን ፈሩ ተሸበሩ ንጉሡ ዳግማዊ
ዳዊትም እንዲህ የሚል መልዕክት ለእስላሞች ላኩ በተፈጥሮ
ወንድሞቻችሁ ከሆኑት ክርስቲያኖች ጋር ካልታረቃችሁ
ሀገራችሁን መጥቼ አጠፋዋለሁ የሚል ማስጠንቀቂያ ላኩ ፡፡
የንጉሡ መልዕክት ለእስላሞች እንደደረሳቸው ፈርተው
እንደጥንቱ በየሃይማኖታቸው ፀንተው በሰላም እንዲኖሩ
ከክርስቲያን ወንድሞቻቸው ጋር ታረቁ፡፡
መታረቃቸውን ዳግማዊ ዳዊት ሰሙ በዚህም ጉዳይ ንጉሡ
በጣም ደስ አላቸው እገዚአብሔርንም አመሰገኑ በግብፅ
የሚኖሩ ክርስቲያኖችም ከ፲፪ ሺህ ወቄት ወርቅ ጋር
ደስታቸውን ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ለዳግማዊ ዳዊት
በደብዳቤ አድርገው ላኩላቸው ንጉሡም የደስታውን ደብዳቤ
ተመልከተው ደስ ኣላቸው ፤ ወርቁን ግን መልሰው በመላክ
እንዲህ የሚል ደብዳቤ ፃፉ በግብፅ የምትኖሩ የክርስቶስ
ተከታዮች ሆይ እንኳን ደስ አላችሁ የላካችሁልኝን ፲፪ ሺህ
ወቄት ወርቅ መልሼ ልኬላችኋለሁ የእኔ ዓላማ ወርቅ ፍለጋ
አይደለም የክርስቶስ ፍቅር አስገድዶኝ በተቻለኝ ችግራችሁን
ሁሉ አስወገድኩላችሁ አሁንም የምለምናችሁ በሀገሬ
በኢትዮጵያ ረሀብና ቸነፈር ድርቅ ስለወረደብኝ መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎበት የነበረውን መስቀልና
የቅዱሳንን አፅም ከሌሎች ክቡራን ዕቃዎች ጋር
እንድትልኩልኝ ነው የሚል ነበር፡፡
በእስክንድርያም ያሉ ምእመናን ይህ መልዕክት እንደደረሳቸው
ከሊቃነ ጳጳሳቱና ከኤጲስ ቆጶሳቱ ጋር ውይይት በማድረግ ይህ
ንጉሥ ታላቅ ክርስቲያን ነው፡፡ ስለዚህ ልቡን ደስ እንዲለው
የፈለገውን የጌታችንን ግማደ መስቀል ከቅዱሳን አጽምና
ንዋየ ቅድሳት ጋር አሁን በመለሰው ፲፪ ወቄት ወርቅ የብርና
የንሐስ የመዳብና የወርቅ ሣጥን አዘጋጅተን እንላክለት ብለው
ተስማምተው በክብር በሥነ ሥርዓት በሠረገላና በግመል
አስጭነው ስናር ድረስ አምጥተው ባስረከቡአቸው ጊዜ
በእጃቸው እያጨበጨቡ በእግራቸው እያሸበሸቡ በግንባራቸው
እየሰገዱ በክብር በደስታ ተቀበሉት ይህም የሆነው መስከረም
፳፩ ቀን ነው፡፡ በኢትዮጵያም ታለቅ ብርሃን ሌት ተቀን ፫
ቀን ሙሉ ሲበራ ሰነበተ፡፡
ግማደ መስቀሉ ወደ መካከለኛው ኢትዮጵያ ሳይደርስ በድንገት
ዓፄ ዳዊት ስናር ላይ አረፉ፡፡ ግማደ መስቀሉም የግድ በዚያው
በስናር መቆየት አስፈለገው፡፡ ከዚህ በኋላ የሟቹ የዳግማዊ
ዳዊት ልጅ ዘርአ ያዕቆብ እንደነገሡ ወደ ሥናር ሔደው
ግማደ መስቀሉን ከሌሎቹ ንዋያተ ቅድሳት ጋር አምጥተው
በመናገሻ ከተማቸው በደብረ ብርሃን ላይ ቤተ መቅደስ
ሠርተው ለማስቀመጥ ሲደክሙ በሕልማቸው አንብር
መስቀልየ በዲበ መስቀል ወዳጄ ዘርአ ያዕቆብ ሆይ
መስቀሌን በመስቀልኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ የሚል ሕልም
አዩ ፡፡ ንጉሡም መስቀለኛ ቦታ እየፈለጉ በኢትዮጵያ
አውራጃዎች ሁሉ መስቀለኛ ቦታ በመፈለግ ከብዙ ቦታ ላይ
አስቀምጠውት ነበር ለምሳሌ በሸዋ በደርሄ ማርያም ፤
በመናገሻ ማርያም ፤ በወጨጫ መስቀሉን አሳርፈውት
ነበር፡፡ ነገር ግን የመጨረሻውን ቦታ ያላገኙ በመሆኑ በራዕይ
እየደጋገገመ መስቀሌን በመስቀልኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ እያለ
ይነግራቸው ነበር፡፡
ዓፄ ዘርአያዕቆብም ለ፯ ቀናት ያህል ሱባዔ ገቡ በዚያም
የተገለፀላቸው መስቀልኛውን ቦታ የሚመራህ ዓምድ ብርሃን
ይመጣል አላቸው እርሳቸው ከዚያ እንደወጡ መስቀለኛውን
ቦታ የሚመራ ዓምደ ብርሃን ከፊታቸው መጥቶ ቆመ በዚያ
መሪነት ወደ ወሎ ክፍለ ሀገር አምባሰል አውራጃ ውስጥ
ግሸን ከምትባል መርቶ አደረሳቸው ፡፡በርግጥም ይህች ግሽን
የተባለች አምባ ጥበበኛ ሰው እንደቀረፃት የተዋበች
መስቀልኛ ቦታ ሁና ስለአገኟት የልባቸው ስለደረሰ ደስ አላቸው
፡፡ በዚያችም አምባ ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርተው
መስቀሉንና ሌሎች ንዋያተ ቅድሳቱን በየማዕረጋቸው የክብር
ቦታ መድበው አስቀመጧቸው ዘመኑም በ፲፬ ኛው ክፍለ
ዘመን ነው፡፡
ከእስክንድርያ ሀገር ከመስቀሉ ጋር በልዩ ልዩ ሣጥን
ተቆልፈው የመጡትም ዝርዝር:
❖ጌታ በዕለተ ዓርብ ለብሶት የነበረው ቀይ ልብስ ከሮም
የመጣ ከለሜዳው
❖ከአፍርጌ ሀገር የመጣው ሐሞት የጠጣበት ሰፍነጉ
❖ዮሐንስ የሳለው የኲርዓተ ርዕሱ ስዕል
❖ቅዱስ ሉቃስ የሣላቸው የእመቤታችን ስዕሎች
❖ የበርካታ ቅዱሳን አጽምና በኢየሩሳሌም ውስጥ ከልዩ ልዩ
ቅዱሳት መካናት የተቆነጠረ የመሬት አፈር
❖የዮርዳኖስ ውሃ
❖በግብጽ ውስጥ ከሚገኙት ታላላቅ ገዳማት የተቆነጠረ አፈር
፡፡
የነዚህንም ዝርዝር ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለግሼን ካህናት
መስከረም ፳፩ ቀን ፩ ሺ ፬፻፵ ዓ.ም. ላይ ተናገሩ ፡፡
በመጀመሪያም ይህ ግማደ መስቀል ከእስክንድርያ ስናር
የገባው መስከረም ፲ ቀን ነው ወደ ኢትዮጵያም የገባው
በመስከረም ፳፩ ቀን ነው፡፡ አሁንም በመጨረሻ ግሸን አምባ
የገባው መስከረም ፳፩ ቀን ሲሆን ቤተ መቅደስ ተሠርቶ
ቅዳሴ ቤቱ የተከበረውና አፄ ዘርዓያዕቆብ ለመላው ኢትዮጵያ
በፅሑፍ በመዘርዘር የገለፁበትም መስከረም ፳፩ ቀን ነው፡፡
ስለዚህ ከዚህች በግሸን ደብር የክርስትና እምነት ያላቸው
የኢትዮጵያ ምእመናን ከበረከተ መስቀሉና ከቅዱሳን አፅም
በረከት ለማገኘት በየዓመቱ መስከረም ፳፩ ቀን እየመጡ
ያከብራሉ፡፡ በዚያም ዘመን የነበሩት የኢትዮጵያ ጳጳሳት
የነበሩት አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤል የተባሉ ከንጉሡ ከዓፄ
ዘርአ ያዕቆብ ጋር ሆነው የምህረት ቃል ኪዳን ለመቀበል
በዚህች በግሸን ደብር ሱባዔ ገቡ በሱባዔአቸውም በመጨረሻ
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾ ይህች ቦታ እኔ ተወልጄ
ያደኩባትን ኢየሩሳሌምን ትሁን የተሰቀልኩባትን ቀራንዮን
ትሁን የተቀበርኩባትንም ጎልጎታን ትሁን በዚች ቦታ እየመጣ
የሚማፀነውን ሁሉ ቸርነቴ ትጎበኘዋለች ጠለ ምህረቴንም
አይለይባትም ፤ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ መጥቶ የተቀበረ
ኢየሩሳሌም እንደተቀበረ ይሁን የሚል የምህረት ቃል ኪዳን
ተገልጾላቸው በዚህ ለተገኙት ምዕመናን ሁሉ በጽሑፍ ካሰሙ
በኋላ ጠቅላላ የግማደ መስቀሉንና የሌሎቹን ታሪካውያን
ንዋያተ ቅዱሳትንም ዝርዝር ታሪክ የያዘውን መጽሐፈ ጤፉት
ብለው ሰይመው ድንጋጌውን ሁሉ በመዘርዘር ለግሸን
እግዚአብሔር አብ ሰጡ፡፡
አፄ አርዓ ያዕቆብም በዚህ ብቻ ሳይወሰኑ እሌኒ እኅታቸው
የተሰኘችው በእመቤታችን ማርያም ስም ቤተ መቅደስ
እንድትሠራ አዘው የእመቤታችን ማርያም ቤተ ክርስቲያን
ከእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ አሳንጻ ጥር ፳፩
ቀን ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ ዓፄ ዘርአ ያዕቆብም ይህችን ደብር
ደብረ ከርቤ ብለው በመሰየም እንኳንስ ሰው የሠገረ ቆቅ ፤
የበረረ ወፍ እንዳይገደል ዳሯ እሳት መሀሏ ገነት ትሁን ብለው
ደንብና ሥርዓት በጤፉት መጽሐፍ ውስጥ አጽፈዋል፡፡ በዚህ
ምክንያት በየጊዜው የነገሡ የኢትዮጵያ ነገሥታትና የተሾሙ
ጳጳሳት መሳፍንትና መኳንንት ልዩ ልዩ ንዋያተ ቅድሳትንና
መጻሕፍትን የወርቅንና የብርን ሰን ፤ ብርና ጻሕል ጽዋን
መስቀልን የመሳሰሉትን የሰጧት ምዕመናንም በየዓመቱ
መስከረም ፳፩ ቀን በግሸን ማርያም ለመገኘት ከዓመት ወደ
ዓመት እየበረከቱ ሔደዋል፡፡
በመስከረም 10 ፤ መስከረም 17 በዓለ መስቀል እና
መስከረም 21 የግሸን በዓል ታሪክ ከረጅም በአጭሩ ይህንን
ይመስላል ፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ ምዕመናን የሆናችሁ ሁሉ
ከበረከተ መስቀሉ ለመሳተፍ ወደ ግሸን ገሥግሱ፡፡
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እና
ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን።
የጌቶች ጌታ የንጉሶች ንጉስ ልዑል እግዚአብሔር ዛሬም
ዘወትርም ስሙ የተመሰገነ ይሁን። ከበረከተ መስቀሉ
ያሳትፈን:: አሜን አሜን አሜን !!!
መልካም በዓል
ምንጭ: ትንሣኤ መጽሔት
መለከት መጽሔት

Tuesday, September 13, 2016

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: =>+*"+<+>††† መስከረም 2-መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ †††<+>+"*

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
አሜን
መስከረም 2-መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሰማዕትነት
ያረፈበት
ዕለት ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን አስቀድሞ "በመወለዱም
ብዙዎች ደስ
ይላቸዋል" (ሉቃ1:14) በማለት የመጥምቁ መወለድ ለእኛ
የደስታ
ቀናችን መሆኑን ነግሮናል፡፡ ዳግመኛም ጌታችን የመጥምቁን
ክብር
ሲገልጥለት "እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል
ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም" በማለት
መስክሮለታል፡፡
ማቴ 11:11፣ ሉቃ 7:28፡፡ በዚህም መሠረት ቅዱስ ገድሉ
ላይ
እንደተጠቀሰው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ
ለመጥምቁ ዮሐንስ ዓሥር እጅግ አስደናቂ ቃል የድኅነት
ኪዳኖችን
እንደገባለት ከቅዱስ ገድሉ ላይ ያገኘነውን ቀጥሎ
እንናገራለን፡-
ገድለ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ (በጎል ሰከበ ደብረ መንክራት
ሚጣቅ
ቅዱስ አማኑኤል ማኅበረ ሰላም አንድነት ገዳም
ያሳተመው-2003
ዓ.ም)
‹‹እግዚአብሔር ወደ በራክይ ልጅ ወደ ዘካርያስ ልጅ
እንደሚወልድ
ይነግረው ዘንድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ላከው፡፡
እርሱም
በመሠዊያው በስተቀኝ በኩል ተገልጦ ለዘካርያስ ታየው፡፡
ለሰይጣን ቀኝ
የለውምና መልአክ ግን ብርሃናዊ የማናዊ ነውና መልአክ
እንደሆነ
ለማጠየቅ በቀኝ በኩል ተገልጦ ታየው፡፡ አንድም ሰው ሁሉ
ወደ የማናዊ
ግብር የሚመለስበት ዘመን ደረሰ ሲል በቀኝ በኩል ታየው፡፡
አንድም
ሰውን ሁሉ መክሮ አስተምሮ ወደ ቀኝ ወደ መንፈስ ቅዱስ
ሥራ
የሚመልስ ልጅ ትወልዳለህ ሲለው በቀኝ በኩል ተገልጦ
ታየው፡፡››
የእግዚአብሔርን ስጦታ በልብ ብቻ በድብቅ መያዝ
እንደሚገባ፡-
‹‹የአካባቢዋ ሰዎችም ሁሉ መካን በመሆኗ አልሳቤጥን ‹ጡተ
ደረቅ፣
ማኅፀንሽም የተዘጋ፣ በረከትን ያጣሽ፣ መርገምንም
የተመላሽ፣ የበቅሎ
ዘመድ፣ ቢወልዷት እንጂ አትወልድ…› እያሉ ይሰድቧት ነበር፡፡
አልሳቤጥም ‹በዚህ ወራት መፀነሷን ባወቀች ጊዜ ስድቤን
ሁሉ ከሰው
ያርቅልኝ ዘንድ እግዚአብሔር በረድኤት በጎበኘኝ ጊዜ እንዲህ
አደረገኝን!› ብላ አምስት ወር ፅንሷን ሠወረች (ለማንም
አልተናገረችም)፡፡ እነርሱም ‹ይህቺ ሴት የበላችው ቂጣ
ቢነፋት ፀነስኩ
ትላለች› ብለው ቢሰድቧት እንጂ ሌላ ረብ (ጥቅም)
ባልነበረው ነበር፡፡
ኤልሳቤጥም ስድስት ወር በሆናት ጊዜ መልአኩ ለቅድስት
ድንግል
ማርያም አምላክን እንደምትወልድ አበሰራት፡፡ ድንግል
ማርያምም
መልአኩ ስለ ኤልሳቤጥ መፀነስ የነገራትን ለማረጋገጥ ወደ
እርሷ
ሄደች፡፡ እመቤታችንም ‹እንዴት ነሽ?› ስትላት ኤልሳቤጥ
በሰማች ጊዜ
በማኅፀኗ ያለው ፅንስ በደስታ ሰገደ፡፡››
መንፈስ ቅዱስ የተለየው ሰው የክርስቶስን አምላክነትና
የድንግል
ማርያምን አማላጅነት ማወቅ አይችልም፡- ‹‹ኤልሳቤጥም
‹እንዴት ነሽ?›
ስትላት የእመቤታችንን ድምፅ በሰማች ጊዜ የፈጠረው
አምላክ
በማርያም ማኅፀን ውስጥ መኖሩን አወቀ፡፡ የዓለሙ
መድኃኒት ፈጣሪው
በድንግል ማርያም ማኅፀን ውስጥ መኖሩን ለማየት
የመጥምቀ መለኮት
ቅዱስ ዮሐንስ ዐይኖች በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ በእናቱ ማኅፀን
ውስጥ
የተገለጡ ሆኑ፡፡ የሁለቱም የማኅፀን መጋረጃዎች ሳይገለጡ
ፈጣሪውን
ለማየት የዮሐንስ ዐይኖች በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ተገልጠው
እንደ
መስታዎት ሆኑለት፡፡ የሁለቱም የማኅፀን መጋረጃዎች
ፈጣሪውን ለማየት
የዮሐንስ ዐይኖች አልከለከሉትም፡፡ መልአኩ ለአባቱ
ለዘካርያስ ‹ከእናቱ
ማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስን የተመላ ይሆናልና› ብሎ
እንደነገረው
በእናቱ ማኅፀን ሆኖ በማርያም ማኅፀን ውስጥ ያለውን
ፈጣሪውን
አየው፡፡ ፈጣሪውንም ለመቀበል ሰገደለት፣ እንደ እንቦሳ
ጥጃም በደስታ
ፈንድቆ ዘለለ፡፡ በእርሱ ላይም የመላው መንፈስ ቅዱስ
በኤልሳቤጥም
ላይ መላባትና እንዲህ ብላ ተናረች፡- ‹ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ
አንቺ
የተባረክሽ ነሽ፣ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፡፡ የጌታዬ
እናት ወደ እኔ
ትመጪ ዘንድ እኔ ምንድነኝ?› አለቻት፡፡››
መጥምቁ ዮሐንስ ምግቡ የበረሃ አንበጣ ነበር›› የሚለው
አነጋገር
ስሕተት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በተለምዶ ሲነገር እንደምንሰማው
መጥምቁ
ዮሐንስ የበረሃ አንበጣ እየተመገበ ይኖር ነበር ይባላል፡፡ ነገር
ግን ቅዱስ
ገድሉ የሚናገረው ቅዱስ ዮሐንስ ይመገብ የነበረው ‹‹የበረሃ
አንበጣ››
ሳይሆን ‹‹አንቦጣ›› ተብላ የምትጠራ አንዲት የበረሃ
ቅጠልንና የጣዝማ
ማርን እንደነበር ነው፡፡ ቅዱስ ገድሉ ላይ የተጻፈውን እንይ፡-
‹‹ዮሐንስና
እናቱ ኤልሳቤጥ ወደ በረሃ ከገቡ አምስት ዓመት በሆናቸው
ጊዜ እርሱ
ዕድሜው ሰባት ዓመት ከመንፈቅ ከሆነው በኋላ እናቱ
ኤልሳቤጥ
ሞተችበትና ብቻውን ከበረሃ ውስጥ ተወችው፡፡ ዮሐንስም
በሰፊዋ በረሃ
ውስጥ በአራዊቶች መካክል ብቻውን ቀረ፡፡ ለዮሐንስ ግን
በእርሱ ላይ
ምንም መጥፎ ነገር ሳያደርጉ የቶራና የአንበሳ፣ የነብርም
ልጆች እንደ
ወንድምና እንደ እኅት ሆኑት፡፡ አራዊቶችም ሁሉ ወዳጅ ሆኑት
እንጂ፡፡
ምግቡም የበረሃ ቅጠል ነው፤ መጠጡም ከተቀመጠባት
ድንጋይ ሥር
የምትፈልቀው ውኃ ነበረች፡፡ ዮሐንስ ሰውነትን
አለምልመው፣ ሥጋን
አለስልሰው፣ ገጽንና ፊትን የሚያሳምሩትን የበረሃ
ቅጠሎችንም
አልተመገበም፡፡ አንቦጣ ከተባለችው ከአንዲት የበረሃ ቅጠልና
ከጣዝማ
ማር በስተቀር ከሚበሉት ምግቦች ሁሉ ዮሐንስ ሕርምተኛ
ሆኖ የተለየ
ነበር›› ይላል ቅዱስ ገድሉ፡፡ እስመ ሕሩም ውእቱ ዮሐንስ
እምኲሉ
መባልዕት ዘእንበለ አሐቲ ዕፅ እንተ ይእቲ አንቦጣ ወመዐረ
ጸደንያ
ባሕቲቱ እንዲል መጽሐፍ፡፡
ዮሐንስ ጌታችንን ሲያጠምቀው ሁለቱ ምን ብለው
እንደተነጋገሩ፡-
‹‹በዚያን ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ
በዮርዳኖስ ወንዝ
ያጠምቀው ዘንድ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወደ ዮሐንስ መጣ፡፡
ዮሐንስም
በእርሱ ላይ አድሮበት ባለው በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ጌታችን ወደ
እርሱ
ሲመጣ ባየው ጊዜ አሰምቶ ጮኸ፤ በታላቅ ቃልም እንዲህ
አለ፡- ‹እኛን
ለማዳን የመጣው የእግዚአብሔር በግ እነሆ፡፡ ነቢያትም ስለ
እርሱ
ትንቢት የተናገሩለት ንጉሠ ነገሥት ይህ ነው፡፡ በዕውነት
ቀዳሚና ተከታይ
የሌለውና ለመንግሥቱም ፍጻሜ የሌለው አምላክ ይህ ነው፡፡›
ዮሐንስም
ይህን ቃል እየተናገረ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠርቶ
እንዲህ
አለው፡- ‹ዮሐንስ ሆይ! ስለ እኔ የተጻፈውን ሕግ ሁሉ ትፈጽም
ዘንድ እነሆ
ይገባሃል፤ እነሆ በአየኸው ሁሉ ምስክር ትሆን ዘንድ በአንተ
እጅ
የምጠመቅበት ጊዜ ስለደረሰ አጥምቀኝ› አለው፡፡ ዮሐንስም
ለጌታችን
እንዲህ ብሎ መለሰለት፡- ‹ወደ አንተ መጥቼ መጠመቅ ለእኔ
ይገባኛል
እንጂ እኔ ባሪያህ ሆኜ ሳለሁ በእኔ እጅ ትጠመቅ ዘንድ
ስለምን ወደ እኔ
መጣህ? አንተ ጌታ ሆነህ ይህ ነገር ፈጽሞ አይገባም› አለው፡፡
ጌታችንም ‹ዮሐንስ ሆይ! በአንተ እጅ ስለመጠመቄ ደስ
መሰኘት
ይገባሃል፤ አትፍራም፡፡ አንተ እጅህን በራሴ ላይ ታኖራለህ፤
ሰውነቴንም
እኔ አጠምቃታለሁ፡፡ ዮሐንስ ሆይ! እንቢ አትበለኝ እነሆ
ነቢያት ስለ እኔ
የተናገሩትን ሕግና ትእዛዝን ሁሉ ልፈጽም መጥቻሁና›
አለው፡፡ ጌታችንም
ይህን ቃል ለዮሐንስ ነግሮት ከጨረሰ በኋላ ወደ ዮርዳኖስ
ውኃ ውስጥ
ገባ፡፡ ያንጊዜ ዮርዳኖስ አርባ ክንድ ወደኋላው ተመለልሶ ሸሸ፣
ውኃውም
በእሳት እንዳፈሉት ሆነ፡፡ በጸናችው የጥበቡ ኃይል አዳምን
ከነልጆቹ
ለማዳን ወደዚህ ዓለም ከመጣው ከጌታችን ፊት ዮርዳኖስ ስለ
መሸሿና
ወደ ኋላዋ ስለ መመለሷ ነቢዩ ዳዊት ትንቢት ተናግሮአል፡-
‹አቤቱ
ውኆች አዩህ፣ ውኆችም አይተውህ ፈሩ፡፡› አንቺ ባሕር
የሸሸሽው፣ አንቺ
ዮርዳኖስ ወደ ኋላ የተመለሽው ምን ሆናችኋል? ጌታችንም
ዮርዳኖስን
እንዲህ በማለት ገሠፀው፡- ‹ዮርዳኖስ ሆይ! በጥምቀቴ ጊዜ
አትሽሽ፣
ባለህበት ቦታም ተመልሰህ ቁም› አለው፡፡ ጌታችንም ይህን
ቃል
በተናገረው ጊዜ የነቢዩ ዳዊት ትንቢት ይደርስ ዘንድ ውኃው
ወደ ቦታው
ተመልሶ ቆመ፤ ከጌታችንም ፊት ሰገደ፡፡ ዮሐንስም ዮርዳኖስ
ወደ ኋላዋ
ተመልሳ መሸሿንና በጌታችን ትእዛዝ ወደ ቀድሞ ቦታዋ
ተመልሳ
ከጌታችን ፊት ስትሰግድ ባየና በተመለከተ ጊዜ ፈራ፣ ደነገጠ፣
ታላቅ
መንቀጥቀጥም አደረበት፣ በፊቱም ሰገደለት፡፡ ‹እነሆ አንተ
ጌታዬና
ፈጣሪዬና ነህ እኔ አገልጋይህ ባሪያህ ነኝ፣ አቤቱ ጌታዬ ሆይ!
ይህን ሁሉ
ደካማነቴን ተመልክተህ እጁን በራስህ ላይ ያኖር ዘንድ
ባሪያህን
አታስገድደው› አለው፡፡ ጌታችንም ለዮሐንስ እንዲህ አለው፡-
‹ይህ ለእኛ
ተድላ ደስታ ነውና እውነትን ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና
ያዘዝኩህን
አድርግ› አለው፡፡ ‹አንተም መጥምቀ መለኮት ተብለህ
ክብርህ
ይነገራልና እኔም በባሪያው እጅ ተጠመቀ ተብዬ ትሕትናዬ
ይነገራልና›
አለው፡፡ ይህንንም ሲናገረው ዮሐንስ ተወው፡፡ ዮሐንስም
እንዲህ
አለው፡- ‹የአብ ስም በአንተው አለ፣ የወልድ ስም አንተው
ነህ፣ የመንፈስ
ቅዱስም ስም በአንተው ሕልው ሆኖ አለ፡፡ ሌላውን በአንተ
ስም
አጠምቃለሁ፣ አንተን ግን በማን ስም አጠምቃለሁ?›
አለው፡፡ ጌታም
ዮሐንስን እንዲህ እያልክ አጥምቀኝ አለው፡- ‹እንደ
መልከጼዴቅ ሹመት
የዓለሙ ካህን፣ ብርሃንን የምትገልጽ፣ የአብ የባሕርይ ልጅ፣
አቤቱ ይቅር
በለን፣ የዓለምን ኃጢአት የምታስወግደው የእግዚአብሔር በግ
ይቅር
በለን እያልክ አጥምቀኝ› አለው፡፡ ያንጊዜ ዮሐንስ ጌታችን
ኢየሱስ
ክርስቶስን ጥር ዐሥራ አንድ ቀን ከሌሊቱ በአሥር ሰዓት
አጠመቀው፡፡››
አስቀድሞ መሐላ መማል ፈጽሞ ተገቢ እንደልሆነ፡-
‹‹የሄሮድያዳ ልጅ
ንጉሥ ሄሮድስን በዘፈኗ በጣም አድርጋ ስላስደሰተችው
እርሱም በተራው
ሊያስደስታት ፈለገ፡፡ ‹እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም
ቢሆን
የለመነችውን ይሰጣት ዘንድ በሕዝቦቹና በመኳንንቱ ሁሉ ፊት
እንዳይከዳት በፅኑ ቃልኪዳን ማለላት፡፡› እንዲህም እያለ
‹የፈለግሽውን
ጠይቂኝ፣ የመንግሥቴንም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁ ምን
ላድርግልሽ?›
እያለ በመሐላ ባላት ጊዜ በእናቷ ምክር የዮሐንስን አንገት
ቆርጦ
ይሰጣት ዘንድ ለመነችው፡፡ ንጉሥ ሄሮድስም ይህን ልመና
ከአፏ በሰማ
ጊዜ ‹የፈለግሽውን እሰጥሻለሁ› ብሎ በሕዝቡ ፊት ስለማለ
ለሰው
ይምሰል አዘነ፣ ተከዘ፡፡ ኃዘኑም ስለ ዮሐንስ መሞት
አይደለም፣ ዮሐንስን
ሕዝቡ ይወደው ስለነበር እነርሱን ስለ መፍራቱና መሐላ ምሎ
ከዳ
እንዳይባል ነው እንጂ፡፡ ስለ ዮሐንስ አዝኖ ቢሆን ኖሮ
ቀድሞውንም
በግፍ እንዲታሰር ባላደረገው ነበር፡፡ ወንድሞቼ እኅቶቼ ሆይ!
ከመሐላ
የተነሣ መፍራት ይገባችኋል፡፡ ‹የለመንሽውን ሁሉ
እሰጥሻለሁ› ብሎ
ስለማለ ሄሮድስ የዮሐንስን አንገት እንድትቆረጥ አደረገ፡፡
ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስም በቅዱስ ወንጌል ‹ፈጽማችሁ አትማሉ›
ብሏል፡፡
ከዚህ በኋላ ወታደሮች ሠይፍ ይዘው የዮሐንስን አንገት
ይቆርጡ ዘንድ
ወደ መኅኒ ቤት ሄዱ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሄሮድስ ጭፍሮች
ሊገድሉት
እንደመጡ በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ስላወቀ ከጨለማው ቤት
ውስጥ
አንገቱን በመስኮት አውጥቶ እንደሚመቻቸው አድርጎ
ጠበቃቸው፡፡
የሄሮድስን ቃል እንዳያቃልሉ ጭፍሮቹም የመጥምቀ
መለኮት ዮሐንስን
አንገት ስለ መሐላው ቆረጡት፡፡ በመሐላ ምክንያት ባይሆን
ኖሮ ሄሮድስ
መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን ባላስገደለው ነበር፡፡ ስለዚህ
ወንድሞቸ
እኅቶች ሆይ! እናንተም ከመሐላ የተነሣ መፍራት ይገባችኋል፣
ፈጽማችሁም መማል የለባችሁም፡፡››
ስካርና ዘፈን ከሚገኙበት ቦታ አጋንንትና ኃጢአት ከዚያ አሉ፡-
‹‹ወንድሞችና እኅቶች ሆይ! አለልክ መብላና መጠጣት ካለበት
ቦታ
እግዚአብሔርን መበደል፣ ማስቀየምና ማስቆጣት
ይገኝበታል፡፡ ስካር
ከሚገኝበት ቦታ አጋንንትና ኃጢአት ከዚያ አሉ፡፡ ስካርና ዘፈን
ከሚገኝበት
ቦታ የእግዚአብሔር መቅሰፍት የፈጣሪያችን ቁጣና በቀል
ይፈጸምበታልና፡፡ እናንተ ሕዝበ ክርስቲያኖች ሆይ! ከስካር፣
ከዘፈንና
ከዝሙት መራቅ ይገባችኋል፡፡ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን
ያስገደለው
ዘፈን፣ ስካርና የዘማ ፍቅር መሆኑን ልብ በማለት መገንዘብ
አለባችሁ፡፡››
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለመጥምቁ ዮሐንስ የተገለጠበት ልዩ
ሁኔታ፡-
‹‹ንጉሥ ሄሮድስ በሞተ ጊዜ እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ
በግብፅ አገር
ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ ታየው፡፡ እንዲህም አለው፡- ‹እነሆ
የዚህን
ሕፃን ነፍስ የሚሹ ሙተዋልና ተነሥተህ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ
ወደ
ምድረ እስራኤል ተመለስ› አለው፡፡ ዮሴፍም ተነሥቶ ሕፃኑንና
እናቱን ይዞ
ወደ ምድረ እስራኤል ገባ፡፡ ‹ልጄ ናዝራዊ ይባላል› ተብሎ
በነቢይ
የተነገረው ቃል ይደርስ ይፈዘም ዘንድ መጥቶ ናዝሬት
በምትባል አገር
ተቀመጠ፡፡ ለሞት ይፈልገው የነበረው የተረገመ ከሐዲ
ሄሮድስ ከሞተ
በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር
ከምድረ
ግብፅ ተመልሶ በናዝሬት ተቀምጦ ሳለ እነሆ የዕድሜ ባለፀጋ
የሆነችው
የዮሐንስ እናት ክብርት ኤልሳቤጥ ልጇን ዮሐንስን ይዛው ወደ
ደብረሲና
በረሃ ከገቡ ከአምስት ዓመት በኋላ ዐረፈች፡፡ ዮሐንስም በእናቱ
አስክሬን
አጠገብ ተቀምጦ በእጅጉ እያዘነ መሪር ልቅሶንም እያለቀሰ
ሳለ
የተሸሸገውን ሁሉ የሚያውቅ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ
የኤልሳቤጥን መሞት፣ እናቱም ስለሞተችበት ዮሐንስ
ብቻውን ከበረሃ
ውስጥ ተቀምጦ እያለቀሰ መሆኑን ዐወቀ፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የኤልሳቤጥን
መሞት፣ የወዳጁ
ዮሐንስ ኃዘንና ማልቀስ ባወቀ ጊዜ እርሱም በናዝሬት ሆኖ
ያለቅስ
ጀመር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ልጇ
ወዳጅዋ ሲያለቅስ
ባየችው ጊዜ ‹ልጄ ወዳጄ ሆይ! ምን ሆንክ? ስለምንስ
ታለቅሳለህ?› ብላ
ጠየቀችው፡፡ ጌታችንም ለቅድስት እናቱ እንዲህ በማለት
መለሰላት፡-
‹እነሆ ወገንሽ የሆነችው ኤልሳቤጥ ዐረፈች፤ ዮሐንስንም
ብቻውን ከበረሃ
ውስጥ ተወችው፡፡ ዮሐንስም ሕፃን ስለሆነ የሚያደርገውን
አጥቶ በእናቱ
አስክሬን አጠገብ ከፊት ለፊቷ ተቀምጦ በመረረ ኃዘን
ያለቅሳል፡፡ እናቴ
ሆይ እኔም ዘመድሽ የሆነ የዮሐንስን ልቆሶ ስላወቅሁኝና
የእርሱም ኃዘን
ስለተሰማኝ የማለቅሰው ስለዚህ ነው› አላት፡፡ በድንጋሌ ሥጋ
በድንጋሌ
ነፍስ የፀናች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም
የኤልሳቤጥን
መሞት በሰማች ጊዜ በጣም ምርር ብላ አለቀሰች፡፡
ያንጊዜም ብርሕት
ደመና መጥታ ከፊታቸው ቆመች፤ ፈጥናም ተሸከመቻቸውና
ኤልሳቤጥ
ከሞተችበት ዮሐንስም ካለበት ቦታ ከደብረሲና በረሃ ውስጥ
ወስዳ
አደረሰቻቸው፡፡ ዮሐንስም ባያቸው ጊዜ ደነገጠ፡፡ ከዚያ በፊት
ሰው አይቶ
ስለማያውቅ የእናቱን አስክሬን ብቻውን ትቶ ወደ ጫካ ሸሸ፡፡
ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስም የዮሐንስን ፍርሃት አራቀለትና እንዲህ
አለው፡- ‹እኛን
ከማየትህ የተነሣ አትፍራ፣ አትደንግጥም፤ አይዞህ እነሆ
የእናትህ
ዘመዶች ማርያምና ሰሎሜ በእናትህ አስክሬን ላይ መልካም
ነገር
ሊያደርጉ መጥተዋልና ና ወደ እኛ ቅረብ› አለው፡፡ ዮሐንስም
ይህን ቃል
ከጌታችን አንደበት በሰማ ጊዜ ወደኋላው ተመለሰ፡፡
ከመሬትም ላይ
ወድቆ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰገደለት፡፡
ጌታችንም እመቤታችን ማርያምንና ሰሎሜን እንዲህ ብሎ
አዘዛቸው፡-
‹በጠማው ጊዜ ለእርሷ ይጠጣ ዘንድ ለዮሐንስ በፈለቀችለት
ውኃ
የኤልሳቤጥን ሥጋ አጥባችሁ ገንዙ› አላቸው፡፡
እንዳዘዛቸውም
የኤልሳቤጥን አስክሬን አጥበው ገነዙት፡፡ ጌታችንም ቅዱስ
ሚካኤልንና
ቅዱስ ገብርኤልን ይመጡ ዘንድ አዘዛቸው፡፡ እነርሱም
ፈጥነው እንደ
ዐይን ጥቅሻ ከሰማይ ወርደው መጡና ከጌታችን ፊት ቆሙ፡፡
ጌታችንም
‹የኤልሳቤጥን ሥጋ የሚቀበርበትን መሬት ቆፍሩ› አላቸው፡፡
ቅዱስ
ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርኤልንም መቃብሩን ይቆፍሩ ዘንድ
ጀመሩ፡፡
ጌታችን ዘካርያስንና ስምዖንን በአካለ ነፍስ ከሰማይ መጥተው
በኤልሳቤጥ አስክሬን ላይ ጸሎተ ፍትሐቱን ያደርሱ ዘንድ
አዘዛቸው፡፡
እነርሱም የኤልሳቤጥ አስክሬን ካለበት ቦታ ላይ ቅዱስ
ሚካኤልና ቅዱስ
ገብርኤል፣ እመቤታችን ማርያምና ሰሎሜ ከጌታችን ፊት
ቆመው ሳለ
ስምዖንና ዘካርያስ በአስክሬኑ አጠገብ ቆመው ጸሎተ
ፍትሐቱን ያደርሱ
ጀመር፡፡ ጸሎተ ፍትሐቱንም በጨረሱ ጊዜ መላእክት
በቆፈሩት መቃብር
ውስጥ ቀበሩዋትና የስምዖንና የዘካርያስ ነፍስ ወደነበረችበት
ቦታዋ
ተመለሰች፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የኤልሳቤጥን
መቃብር
በትእምርተ መስቀል አምሳል ደፈነው፡፡ ኤልሳቤጥም
ያረፈችበት ዕለት
የካቲት አሥራ ስድስት ቀን ሆነ፡፡
ከዚህ በኋላ ዮሐንስን ብቻውን ከበረሃ ውስጥ ትተውት ጌታችን
ኢየሱስ
ክርስቶስ ከእመቤታችን ጋር ወደ ናዝሬት ለመመለስ
ከደመናዋ ላይ
ተሣፍሮ ተነሣ፡፡ ያንጊዜም ክብርት እመቤታችን ልጇን
እንዲህ አለችው፡-
‹ጌታዬና አምላኬ ፈጣሪዬ ሆይ! ስለምን ዮሐንስን ብቻውን
ከበረሃ
ውስጥ ትተወዋለህ? እንዴትስ ትተነው እንሄዳለን? ወደዚህ
ቦታ ይዛው
የሸሸችው እናቱ ጥላው ሞታ በመቃብር ውስጥ ተቀብራለች
ከእኛ ጋር
ይዘነው እንሂድ እንጂ› አለችው፡፡ ዳግመኛም እመቤታችን
እንዲህ
አለችው፡- ‹ነፍስ ያለወቀ ሕፃን ስላሆነ አራዊት ይበሉታልና
ይዘነው መሄድ
አለብን› አለችው፡፡ ጌታችንም ለቅድስት እናቱ እንዲህ
በማለት
መለሰላት፡- ‹በመምህርነት ወጥቶ ለእስራኤል ታይቶ
እስከሚያስተምር
ድረስ የሰማያዊው አባቴ ፈቃድ በበረሃ ውስጥ ብቻውን
እንዲኖር ነው፡፡
አንቺ ብቻውን እንዴት ከበረሃ ይኖራል ትያለሽ፤ አራዊቶች
እንዳይጣሉት
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከእርሱ አይለይም፡፡
በፈለገው ነገር ሁሉ
እንዲራዱትና እንዲታዘዙለት መላእክተ ብርሃንን አዝለታለሁ፡፡
ብርሃናዊው
መልአክ ገብርኤልም ሰማያዊ ሕብስትን ለምግቡ
ያመጣለታል፤
በጠማውም ጊዜ እንደ ወተት የነጣችውን፣ እንደ ወለላ
ማርም
የጣፈጠችውን ውኃ ከኤዶም ገነት ያመጣለታል፡፡ ይህችንም
እርሱ
ካለበት ድንጋይ ሥር የምትፈልቀውን ውኃ እንደ እናቱ ጡት
ለአፉ
የጣፈጠች አደርግለታለሁ፡፡ አንቺ ብቻውን እንዴት በበረሃ
ውስጥ ይኖራል
ትያለሽ፤ እስከ ዛሬ ድረስም የጠበቅሁት እኔ ነኝ፣ ሌላ ማን
ጠበቀው
ብለሽ ነው? እኔ አይደለሁምን? ወዳጄ ዮሐንስን ሰማያዊው
አባቴ ከዚህ
ዓለም ፍጥረት ሁሉ በጣም አብልጦ ይወደዋል፡፡ አባቱ
ዘካርያስም
በሥጋው ቢሞት በነፍሱ ሕያው ስለሆነ ዮሐንስን ለማጽናናት
በአካለ
ነፍስ ከእርሱ እንዳይለየው አደርጋለሁ፡፡ እናቱ አልሳቤጥም
በሥጋዋ
ብትሞት በነፍሷ ሕያዊት ስለሆነች ታጽናናው ዘንድ በነፍሷ
በፍጹም
ከእርሱ እንዳትለየው አደርጋለሁ፡፡ ዮሐንስን የተሸከመች
ማኅፀን ንዕድ፣
ክብርት ስለሆነች በሥጋዋ ውስጥ መጥፎ ሽታ፣ ክፉ መዓዛ
አይገኝባት፣
በመቃብሯም ውስጥ ትሎች አይገኙበት፡፡ ድንግል እናቴ ሆይ!
አንቺ እኔን
ፀንሰሽ ሳለሽ ወደ ኤልሳቤጥ በሄድሽ ጊዜ በእጇ ይዛ ጨብጣ፣
በአፏ
በሳመችሽ ጊዜ እንዲህ ብላ ትንቢት ተናግራለች፡፡ ‹አንቺ
ከሴቶች ሁሉ
ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ፤ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፤
የጌታዬ እናቱ
ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እኔ ምንድነኝ? ከእግዚአብሔር
አግኝተው
የነገሩሽን ቃል ይደረጋል ብለሽ የተቀበልሽ አንቺ ብፅዕት ነሽ፣
ክብርት ነሽ›
ብላ ስላመሰገነችሽ እንኳን ሥጋዋ ሊፈርስ ይቅርና መግነዟም
አይለወጥም፤ መቃብሯም አይጠፋም፤ ነፍሷንም ከሥጋዋ ጋር
እንድትኖር
አደርጋታለሁ፡፡› ይህን የመሰለ ነገር ስለ ወዳጁ ዮሐንስ
ለድንግል እናቱ
ነግሯት ለጨረሰ በኋላ ዮሐንስን ከበረሃ ውስጥ ትተውት
በደመና ላይ
ተጭነው ወደ ናዝሬት ተመለሱ፡፡››
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለመጥምቁ ዮሐንስ የሰጠው ልዩ
ቃልኪዳን፡-
1. ‹‹…ከሚበላውና ከሚጠጣው ከፍሎ በስምህ ለነዳያን
ለሰጠ ሥጋዬን
ደሜን እሰጠዋለሁ፤ በሃይማኖት ፀንቶ፣ በምግባር ሠፍቶ
ሥጋዬን ደሜን
እንዲቀበል አደርገዋለሁ፤ ለሥጋዬ ለደሜ የሚያበቃ ሥራ
እንዲሠራ
አደርገዋለሁ፤ እስከ ሃምሣ አምስት ትውልድም ድረስ
እምረዋለሁ፡፡››
2. ‹‹ሰው ሁሉ ወደ ሥጋዊ ተግባርም ሆነ ወደ መንፈሳዊ
ተግባርም
ቢሆን ሲሄድ ‹ይህ የመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ቤተክርስቲያን
ነው› ብሎ
ቅጽሩን፣ ገራገሩን ቢሳለም የተሳለመው ሰው ቢኖር እኔ
መንበረ
መንግሥቴን አሳልመዋለሁ፡፡ የገድልህንም መጽሐፍ
የተሳለመ ቢኖር እኔ
መንበረ መንግሥቴን አሳልመዋለሁ፡፡››
3. ‹‹ከቤተክርስቲያንህ የተቀበረውን ሰው ከመከራ ሥጋ፣
ከሲኦል እሳት
አድነዋለሁ፤ እኔ ከተቀበርኩበት ኢየሩሳሌም ሄዶ ከእኔ
መቃብር ውስጥ
እንደተቀበረ አደርገዋለሁ፡፡››
4. ‹‹ቤተክርስቲያንህ ከታነፀችበት፣ ስምህ ከሚጠራበት፣
መታሰቢያህ
ከሚደረግበት፣ የተአምርህ ዜና ከሚነገርበት፣ የገድልህ
መጽሐፍ ተነቦ
ከሚተረጎምበት፣ እኔ በረድኤት ከዚያ እገኛለሁ፤ ከዚያ ቦታ
አልለይም፡፡
የገድልህ መጽሐፍ ከሚተረጎምበት ቦታ አጋንንት አይደርሱም፤
ከዚያ ቦታ
ሰይጣናት ይርቃሉ፡፡››
5. ‹‹የገድልህ የተአምርህ መጽሐፍ የተነበበትን ውኃ እኔ
እንደተጠመቅሁበት እንደ ማየ ዮርዳኖስ አደርገዋለሁ፡፡
የገድልህ
መጽሐፍ በተነበበት ውኃ የተጠመቀበት ሰው ቢኖር የሰማንያ
ዓመት
ኃጢአቱን አስተሠርይለታለሁ፤ ወንዱን የአርባ ቀን፣ ሴቷን
የሰማንያ ቀን
ሕጻን አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ በተጠመቅሁበት ማየ ዮርዳኖስ
እንደተጠመቀ
ሆኖለት ከኃጢአቱ ይነጻል፡፡››
6. ‹‹ሰውም ሆነ እንስሳ ቢታመም በጽኑ እምነት
ይደረግልኛል ብሎ
አምኖ ያለ ጥርጥር ውኃ አቅርቦ የገድልህን መጽሐፍ በላዩ
ላይ አንብቦ
የተነበበበትን ውኃ ቢታጠብበት ወይም ቢጠጣ ያለ ጥፋት
ፈጥኖ
ከደዌው ይፈወሳል፡፡››
7. ‹‹የገድልህ መጽሐፍ የተነበበትን ማየ ጸሎት በቤቱ ውስጥ
ቢረጭ
ከዚያ ቤት በረከቴን እመላበታለሁ፤ ተድላን፣ ደስታን፣ ጥጋብን
በዚያ ቤት
አሳድራለሁ፤ እስከ ዘለዓለም ድረስ በቤቱ ውስጥ የእህል
መታጣትና
ረሀብ፣ የውኃ ጥማት፣ ተላላፊ በሽታ አይገባበትም፤ ፈጽሜም
አላመጣበትም፡፡››
8. ‹‹ደስ ብሎት በተድላ በደስታ በዓለህን ያከበረውን ሰው ሁሉ
በቅዱሳን መላእክቶቼና በሰማያዊ አባቴ በአብ ማሕያዊ
በሚሆን
በመንፈስ ቅዱስ ፊት እኔ ደስ አሰኘዋለሁ፡፡ እነሆ እኔም
ከበዓልህ ቦታ
ላይ አልለይም፤ በዓልህንም ከሚያከብሩት ጋር እኔ
አብሬያቸው
እቀመጣለሁ፤ እስከ ሃምሣ አምስት ትውልድም
እምረዋለሁ፡፡››
9. ‹‹ለቤተክርስቲያንህ ዕጣን፣ ሻማ፣ ጧፍ፣ ልብሰ ተክህኖ፣
መጎናጸፊያ፣
መጋረጃ፣ ነጭ ስንዴ የሰጠ ሰው ቢኖር እስከ ሃምሣ አምስት
ትውልድም
ድረስ እምረዋለሁ፡፡››
10. ‹‹ሥጋዬን ደሜን መቀበል ያልተቻለው ሰው ቢኖር
ለመታሰቢያህ
ዝክር ከተደረገው ፍርፋሪ ይቅመስ፣ ሥጋዬን ደሜን
እንደተቀበለ እኔ
አደርግለታለሁ፡፡ ፍርፋሪውን ባያገኝ እንጀራውና ዳቦው
የተበላበትን
ገበታ፣ ጠላው የተጠጣበትን ፅዋ በምላሱ ይላስ፣ እኔ ኢየሱስ
ቃሌ
የማያብለው ሥጋዬን ደሜን እንደተቀበለ አደርግለታለሁ፤ ስለ
እምነቱ
ሥጋዬን ደሜን ለመቀበል የሚያበቃውና እውነተኛውን
ምግባር የጽድቅ
ሥራ እንዲሠራ አደርገዋለሁ፡፡››
ጌታችን በቅዱስ ወንጌሉ ስለ ዮሐንስ ሲናገር ‹‹ዮሐንስ
የሚያበራ መብራት ነበረ›› ነው ያለው፡፡ ዮሐ 5፡35፡፡
ዳግመኛም ክብሩን ሲገልጥለት "እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች
ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም
የለም" በማለት መስክሮለታል፡፡ ማቴ 11:11፣ ሉቃ
7:28፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ
ይማረን፡፡

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: =>+*"+<+>††† መስከረም 1-ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል †††<+>+"*

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
አሜን
መስከረም 1-ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል የተሾመበት
ዕለት ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ሐዋርያው ቅዱስ በርተሎሜዎስ
ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ታላቁ አባት ጻድቁ አባ ሚልኪ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ጻዲቁ ኢዮብም ከበሽታው የዳነው በዚህች ዕለት ነው፡፡
ጻዲቁ ኢዮብ በፈሳሽ ውኃ ታጥቦ ከደዌው ሁሉ ስለተፈወሰ
ለሰዎች ልማዳቸው ሆኖ ዓመቱ ዞሮ ሲመጣ ፈሳሹ ውኃም
በመላ ጊዜ በአዲስ ውኃ ይጠመቃሉ፣ በእርሱም ይባረካሉ፡፡
ሐዋርያው በርተሎሜዎስ፡- ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ዕጣ
የደረሰው አልዋሕ በሚባል አገር ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ
ሊያደርሰው አብረው ወደ አልዋሕ ሄዱ፡፡ ወደ ከተማው
ለመግባት ምክንያት ፈለጉና ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ
በርተሎሜዎስን ‹‹አትክልተኛ ባለሙያ ነው›› ብሎ የወይኑን
ቦታ እንዲጠብቅለት ለአንድ ባለጸጋ መኰንን ባሪያ አድርጎ
ሸጠው፡፡ ባለጸጋውም በርተሎሜዎስን በ30 እስቴታር
ገዝቶት ሄደ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ገንዘቡን ደብቆ ለቅዱስ
በርተሎሜዎስ በድብቅ ሰጥቶት እንዲመጸውተው ነግሮት
ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፡፡ አልዋሕ ከገባ በኋላ ቅዱስ
በርተሎሜዎስ የወይን ቦታው አለቃ ሆኖ 40 ቀን
ተቀመጠ፡፡ ወንጌሉን ባለመስበኩ በሀዘን እያለቀሰ ጌታችንን
በጸሎት ጠየቀው፡፡ በገንዘቡ ገዝቶት ባሪያው ያደረገው
ባለጸጋውም የወይኑን ቦታ ያይ ዘንድ እንደመጣ መርዘኛ እባብ
ነድፎት ሞተ፡፡ ሕዝቡም ተሰብስቦ ሲያለቅስ በርተሎሜዎስ
ግን ወደ ጌታችን ከጸለየ በኋላ ሄዶ ባለጸጋውን ሰው ከሞት
አስነሣው፡፡ በዚህም ሕዝቡ ሁሉ አምነው ተጠምቀዋል፡፡
በርተሎሜዎስም ወደ ሌሎች አገሮች ሄዶ አስተማረ፡፡
ጌታችን ወደ በርበሮች ዘንድ ሄዶ ወንጌልን እንዲሰብክ
አዘዘው፡፡ ረዳት እንዲሆነውም እንድርያስን ከደቀ መዝሙሩ
ጋር ላከለት፡፡ የሀገሪቱ ሰዎች ግን እጅግ ክፉዎች ነበሩ፡፡
በሐዋርያቱም ፊት በአስማት አስደናቂ ተአምራት እያሳዩ
ትምህርታቸውን የማይቀበሏቸው ሁኑ፡፡ ይህን ጊዜ ጌታችን
ሰውን ከሚበሉ አገር አንዱን ገጸ ከልብ ይታዘዝላቸው ዘንድ
በሚያዙትም ነገር ሁሉ ከትእዛዛቸው እንዳይወጣ አዘዘው፡፡
ሐዋርያትም ወደ በርበሮች አገር ዳግመኛ በገቡ ሰዓት
ይበሏቸው ዘንድ ኃይለኛ አራዊትን አውጥተው ለቀቁባቸው፡፡
ያ ገጸ ከልብም በአራዊቱ ላይ ተነሥቶ እየነጠቀ በላቸው፡፡
ይህንንም የተመለከቱት በርበሮች እጅግ ፈርተው በድንጋጤ
ብቻ የሞቱ አሉ፡፡ በሐዋርያቱም እግር ሥር ወደቁ፡፡
ሐዋርያቱም አስተምረው ካሳመኗቸው በኋላ
አጥምቀዋቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ቅዱስ በርተሎሜዎስ
እግዚአብሔርን ወደማያውቁ አገሮች ሄዶ ብዙ ተአምራትን
እያደረገ አስተምሮ አጠመቃቸው፡፡ የከሃዲው ንጉሡ
የአግሪጳን ሚስትም ትምህርቱን ሰምታ በጌታችን አመነች፡፡
ንጉሡ አግሪጳም በዚህ እጅግ ተቆጥቶ ቅዱስ
በርተሎሜዎስን ብዙ ካሠቃየው በኋላ አሸዋ በተሞላ ትልቅ
ከረጢት ውስጥ ከቶ ከነሕይወቱ ባሕር ውስጥ እንዲጥሉት
አደረገ፡፡ ምእመናንም ሥጋውን አውጥተው በክብር
ቀብረውታል፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + + + + + + + + + + + + + +
አባ ሚልኪ ዘቁልዝም፡- በላይኛው ግብጽ የሚኖሩ ባለጸጋ
ወላጆቻቸው በስዕለት ወለዷቸው፣ ብሉይን ከሐዲስ አጠናቀው
ከተማሩ በኋላ የአባታቸውን ወርቅ ለድኆች ሰጥተው ገዳም
ገብተው መነኩሰው በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ፣ የአገረ ገዥውልን
ልጅ ዘንዶ ውጦት ሳለ አባ ሚልኪ ዘንዶውን ጠርቶት ልጁን
ይተፋው ዘንድ አዘዘውና ልጁ ጤነኛ እንደሆነ ከዘንዶው ውስጥ
ወጣ፣ በውስጡ ያደረ ከይሲም በኖ ጠፋ፣ ጻድቁ ቤ/ክ ሲሠሩ
የመሠረቱ ድንጋይ ራሱ በተአምራት እየተፈነቀለ ይተከል
ነበር፣ ለ300 መነኮሳትም አባት ሆነው በተአምራታቸው
የፋርስንና የሮም ሰዎችን አሳመኗቸው፣ ዋሻ ዘግተው ሊኖሩ
በማሉ ጊዜ ሰይጣን መሀላቸውን ሊያፈርስ አስቦ በሮሙ ንጉሥ
ልጅ አድሮ አሳመማትና በአባ ሚልኪ ካልሆነ በቀር
አልወጣም አለ፣ ንጉሡም ልኮባቸው በደመና ተጭነው ሄደው
ልጅቷን ፈውሰው አድሮባት የነበረውን ሰይጣን ገዝተው
አሠሩትና ከንጉሡ ቤት 14 ሰው የማይሸከመውን ድንጋይ
በአንገቱ ላይ አሳስረው አስሸክመውት ሰው ሁሉ እያየው ወደ
ገዳማቸው አስመጡትና ድንጋዩን የበዓታቸው መዝጊያ
አደረጉት፤ ጻድቁ በብርቱ ሲጋደሉ ኖረው የሚያርፉበት ቀን
ከተነገራቸው በኋላ እነ እንጦንስ፣ መቃርስ፣ ሲኖዳ፣ ብሶይ፣
ጳኩሚስ ተገልጠውላቸው ወንድማችን ና ወደ እኛ ብለዋቸው
በሰላም ዐርፈዋል፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣
በጸሎታቸው ይማረን፡፡
+ + + + + + + + + + + + + + +
ራጉኤል ሊቀ መላእክት:- ራጉኤል ማለት የብርሃናት አለቃ
ማለት ነው። የብርሃናት አለቃ ሲባል ፀሐይን፣ ጨረቃን እና
ከዋክብትን በማመላለስና ለሰው ልጆች፣ ለአዝርዕት፣
ለእንስሳት፣ ለአራዊት ሁሉ ብርሃንን የሚመግብ ነው ማለት
ነው። አንድም ራጉኤል ማለት የሚበቀል ማለት ነው።
የሚበቀል ነው ማለት በቀል የሚገባው ለጠላት ነው የሰው
ልጅ ጠላት ደግሞ ዲያብሎስ ነው፤ ስለሆነም ቅዱስ ራጉኤል
እግዚአብሔርን አምነው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው
በፍርሐተ እግዚአብሔር አምልኮቱን ለሚፈጽሙ ሁሉ ጠላት
ዲያብሎስን የሚያርቅላቸው ወደ እነርሱም ፈጥኖ በመድረስ
የሚታደጋቸው ነው ማለት ነው። ሔኖክ 6:4፡፡ አንድም
ራጉኤል ማለት የኃያላን ኃያል እግዚአብሔር ማለት ነው።
የኃያላን ኃያል ያለው የእግዚአብሔርን ኃያልነት ከምድር
ፍጥረታት ዘንድ ኃያል ከሚባሉት ሁሉ ሊገለጽ የማይችል
ኃያልነቱን ለመግለጽ ኃያልነቱም ከ እስከ የሌለው መሆኑን
ለመግለጽ የተቀመጠ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ኃያል
የኃያላን ኃያል መሆኑን የሚገልጽ ትርጉም አለው።
አንድም ራጉኤል ማለት ጽኑ እግዚአብሔር ማለት ነው።
የእግዚአብሔር አምላክን ጽኑነት ለማጉላት ሲል ጽኑ አለው።
እግዚአብሔር የማይወላውል የማይዋዥቅ የማይከዳ ነው
ለማለትም ሲል ይህ ስያሜ ተሰጠው። የእግዚአብሔርን ጽናት
የሚያሳይ ትርጉም ያለው ስያሜ ነው። የሊቀ መላእክት
የቅዱስ ራጉኤል አገልግሎት እና ስልጣን፡- እመቤታችን
ቅድስት ድንግል ማርያም ከዚህ ዓለም በ64 ዓመቷ ካረፈች
በኋላ ሥጋዋ ወደ ዕፀ ሕይወት ሲነጠቅ (ሲያርፍ) አብሮ
ለሔደው እና ስጋዋን በእጣን ሲያጥን ለነበረው ለፍቁረ እግዚ
ለቅዱስ ዮሐንስ ኅብስትን የመገበ መልአክ ነው።
በብርሃናት ሁሉ ላይ የሰለጠነ መልአክ ነው። ከአዳም ሰባተኛ
ትውልድ የሆነ በእግዚአብሔር ፊት ግሩም ያማረ ሥራው
የሰመረ እስከዛሬ የሞት ወጥመድ ያልያዘው የሞት ጥላ
ያላረፈበት ነብዩ ሔኖክ "ከቅዱሳን መላእክት አንዱ የሆነ ጸላዒ
ዲያብሎስን የሚበቀለው ራጉኤል በብርሃናት ላይ የሰለጠነ
ነው" ሲል ስለ እርሱ ተናግሯል፡፡
እግዚአብሔር ዓለምን ይቆጣጠር ዘንድ የሾመው ታላቅና
ቅዱስ መልአክ ነው። (ድርሳነ ራጉኤል ዘ ጥቅምት ገጽ 23)
አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ለመተካት ዓለምን የመለወጥ
ሥልጣን የተሰጠው ቅዱስ መልአክ ነው። ከእግዚአብሔር
የጌትነቱ አዳራሽ ይገባና ይወጣ ዘንድ ስልጣን ያለው
ከኪሩቤልና ከሱራፌል ጋር ከፈጣሪ የጌትነት ዙፋን ፊት
የሚቆም ነው። ሎጥን ሚስቱንና ልጆቹን ከእሳተ ጎመራ
ያዳነ የበለአምን እርግማን ወደ በረከት የለወጠ እርሱ ነው።
በቅዱስ ራጉኤል ስነ ሥዕል ላይ የምናየው ይህ ባለ አራት
እራስ ንስር ከአርባእቱ ኪሩቤል አንዱ ገጸ ንስር ነው።
የሥላሴን የጌትነት ዙፋን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳት
ናቸው። የሚሸከሙት ሲባል ጫማ የሰውን ልጅ
እንደሚሸከመው እንጂ ችለውትስ አይደለም። እነርሱም
የሰው ገጽ፣ የእንስሳ ገጽ፣ የንስር ገጽ እና የአንበሳ ገጽ ያላቸው
ናቸው። ይህንንም ነብዩ ሕዝቅኤል "ለእያንዳንዱ እንስሳትም
የተለያዩ አራት ገጾች ነበሩት። ይህውም በስተቀኝ በኩል
የእንስሳ መልክ፣ በስተ ግራ የላም ገጽ፣ በበስተ ኋላም የንስር
ገጽ የሚመስሉ ነበሩ" ብሏል ሕዝ 1፡6-13፡፡ ከዚህ
የምንገነዘበው ነገር ቢኖር አራት ገጽ ካላቸው ኪሩቤል
መካከል አንዱ ንስር መሆኑን ነው። ቅዱስ ራጉኤል ደግሞ
የእነዚህ ኪሩቤል አለቃቸው (የጌትነቱ ዙፋን ጠባቂ) በመሆኑ
በዚህ ምክንያት ማለትም እነርሱ ዙፋኑን ተሸካሚ እርሱ
ደግሞ አጠገባቸው መቆሙ መንበሩን ጠባቂ በመሆኑ በዚህ
አይነት የአገልግሎት ድርሻ አብረው ሊሳሉ ችለዋል። ቅዱስ
ያሬድም በድጓው "አርባእቱ እንስሳ አልቄንጥሩ እንደሚባለው
ንስር ፊት ለፊት አይታዩም አንዱም በመራቸው ይሔዳሉ
እነርሱም እያንዳንዳቸው አራት ገጽ ሲኖራቸው ሳያርፉና
ሳይደክሙ የሚያመሰግኑ ናቸው" በማለት ጽፏል። አንድም
መላእክት ነገደ ሱራፌል እና ነገደ ኪሩቤል በመባል
ይከፈላሉ። በነገደ ሱራፌል እነ ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ
ሩፋኤል ወዘተ ሲሆኑ በነገደ ኪሩቤል ደግሞ ቅዱስ ገብርኤል
ቅዱስ ራጉኤል ወዘተ ያጠቃልላል። ስለዚህ ቅዱስ ራጉኤል
ነገዱ ከነገደ ኪሩቤል ነው በዚህም ላይ የነገደ ኪሩቤል
አልቄንጡራ (አራት እራስ ንስር) አለቃቸው ቅዱስ ራጉኤል
ነው። በዚህም ምክንያት አብረው ሊሳሉ ችሏል። አንድም
መላእክትን ሁሉ እንደ እየስራቸው መለያ ስነ ሥዕላቸውን
መሳል ልማድ ነውና። ለምሳሌ ቅዱስ ሚካኤል ከቅድስት
አፎምያ ጋር፣ ቅዱስ ገብርኤል ከሠለስቱ ደቂቅ ጋር፣ ቅዱስ
ዑራኤል ከእዝራ ሱቱኤል ጋር እንደሚሳሉት ሁሉ ማለት
ነው። በዚህም መሰረት ቅዱስ ራጉኤልም ዐቃቤ መንበር
ነውና መንበሩን በሚሸከሙት ኪሩቤል ከሚመሰሉት ንስሮች
ጋር አብረው ሊሳሉ ችለዋል፡፡
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል ከአምላክ የተሰጠው ቃል
ኪዳን እግዚአብሔር አምላክ በስሙ ለታመኑት ቅዱሳን፣
ጻድቃን፣ ሰማእታት፣ ሐዋርያት፣ ዘወትር ያለማቋረጥ ስሙን
ለሚጠሩት ቅዱሳን መላእክት ሁሉ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል።
የሰጣቸውም ቃል ኪዳን ዘላለማዊ እና ሊሻር የማይችል
ነው። ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ራጉኤልም ይህን ቃል ኪዳን
ሰጥቶታል "የራጉኤል አምላክ ይቅር በለኝ በማለት አንዲት
ቃልስ እንኳን ቢናገር እንደ ወዳጄ እንደ አብርሃም፣ እንደ
ባለሟሌም እንደ ይስሐቅ፣ እንደ አከበርኩትም እንደ ያዕቆብ
ክብርን ባለሟልነትን እሰጠዋለሁ በራሱ ላይም አክሊል
አቀዳጀዋለሁ እረጅም ዘመናት ሰፊ ወራትም እሰጠዋለሁ"
ሲል ቃሉን ሰጥቶታል፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል
መስከረም 1 ቀን ከሊቃነ መላእክት በ4ተኛ ደረጃ
የተሾመበት ዕለት ነው። ግንቦት 1 ቀን ለታላቁ አባት ለሄኖክ
ምሥጢራትን የገለጸበት በዓሉ ነው፡፡ ጥበቃው አይለየን፣
በምልጃው ይማረን፡፡
የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ ሀገራችንን ይጠብቅልን፡፡

Tuesday, September 6, 2016

=>+*"+<+>††† ዻጉሜን-1 +" ወርኀ ዻጉሜን "+ †††<+>+"*

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ዻጉሜን-1
+" ወርኀ ዻጉሜን "+
=>#እግዚአብሔር አዝማናትን የፈጠራቸው ለሰው ልጆች
ጥቅም መሆኑ ይታወቃል:: እርሱ ባወቀ: በረቂቅ ሥልጣኑ
ዓለምን ፈጥሮ: ጊዜያትን እንዲከፍሉ ብርሃናትን (ፀሐይ:
ጨረቃ: ከዋክብትን) ፈጥሮልናል::
+ጊዜያትንም በደቂቃ: በሰዓት: በቀን: በሳምንት: በወር:
በዓመታት: በኢዮቤልዩ: በክፍላተ ዘመናት እንድንቆጥር
ያስማረንም እርሱ ነው:: የሰከንድ 540,000 ክፋይ
ከሆነችው 'ሳድሲት' እስከ ትልቁ ቀመር (532 ዓመት) ድረስ
እርሱ ለወደዳቸው እንዲያስተውሉት ገልጧል::
+በየዘመኑም በቅዱስ #ድሜጥሮስ: በቅዱስ #ዮሐንስ
ዘደማስቆ: በቅዱስ #አቡሻኽር እና በሌሎቹም አድሮ
መልካሙን አቆጣጠር አስተምሯል:: ሃገራችን ኢትዮዽያ
ደግሞ የ13 ወራት የፀሐይ ጸጋ (thirteen months sun
shine) ያላት: 4ቱ ወቅቶች የተስማሙላት ናት::
+ሌላው ዓለም ወሮችን 31,30,29 እያደረገ ሲጠቀም እኛ
ግን እንደ ኖኅ (ዘፍ) አቆጣጠር ወሮችን በ30 ቀናት ወስነን:
ዻጉሜንን ለብቻዋ እናስቀምጣለን:: ዻጉሜን 'ኤዻጉሚኖስ'
ከሚል የግሪክ (ጽርዕ) ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም
'ትርፍ: ጭማሪ' እንደ ማለት ነው::
+የወርኀ ዻጉሜን 5ቱ (6ቱ) ቀናትም ወደ አዲስ ዓመት
መሸጋገሪያ እንደ መሆናቸው ብዙ ምሳሌያት (ምሥጢራት)
አሏቸው:: ዋናው ግን በዚህ ጊዜ ዳግም ምጽዓት ይታሠባል::
ጊዜውንም በጾምና በጸሎት ሊያሳልፉት ይገባል:: ግን በፈቃድ
ነው እንጂ የግዴታ አይደለም::
+" ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ "+
*የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ
*በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
*በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
*እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
*የጌታችንን መንገድ የጠረገ
*ጌታውን ያጠመቀና
*ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::
*ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ:
ገዳማዊ: መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ ብላ
ታከብረዋለች::
+ቅዱሱ በዚህች ዕለት ወደ እሥር ቤት ገብቷል:: ይሕስ እንደ
ምን ነው ቢሉ:-
ንጉሡ ሔሮድስ የወንድሙን የፊልዾስን ሚስት ሔሮድያዳን
በማግባቱና በመሰል ክፋቶቹ ቅዱስ ዮሐንስ ይገስጸው ነበር::
ቅዱስ ዮሐንስ "መምሕር ወመገስጽ: ዘኢያደሉ ለገጽ - ፊት
አይቶ የማያዳላ" ነውና ገሰጸው::
+ሔሮድስ ቅዱሱን ይፈራው: ያከብረውም ነበር:: በኋላ ግን
ፈቃደ ሥጋው ስላየለበት: በተለይ ደግሞ ከ7 ቀናት በሁዋላ
ልደቱን ሲያከብር እንዳይረብሸው በመስጋት በዚህች ቀን
በወታደሮቹ አስይዞ እሥር ቤት ውስጥ ጥሎታል:: ለ7 ቀናት
በጨለማ ውስጥ አሥሮ መስከረም 2 ቀን አንገቱን እንዴት
እንዳስቆረጠው ዕለቱን ጠብቀን እንመለከታለንና የዚያ ሰው
ይበለን::
+" ቅዱስ ዑቲኮስ ሐዋርያ "+
=>ቅዱሱ ሐዋርያ ጭራሽ ከነ ስማቸው እንኩዋ እየተዘነጉ
ከሔዱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን ቁጥሩም ከ72ቱ አርድእት
ነው:: በወጣትነት ዘመኑ የጌታችን ደቀ መዝሙር መሆንን
መርጦ ለ3 ዓመታት ከ3 ወራት ምሥጢረ ወንጌልን ጠንቅቆ
ተምሯል::
+መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜም እንደ መጠኑ ተቀብሎ
ለአገልግሎት ወጥቷል:: በመጀመሪያ የወንጌላዊው ዮሐንስ
ተከታይ ሁኖ ብዙ ምሥጢራትን ተካፍሏል:: ቀጥሎም ቅዱስ
ዻውሎስን ተከትሎ ብዙ አሕጉራትን በስብከተ ወንጌል
አዳርሷል::
+በመጨረሻም በእስያ አካባቢ ለብቻው ተጉዞ: ብዙ ነፍሳትን
ማርኮ: ጣዖታትን አጥፍቷል:: ስለዚህ ፈንታም በእሳት:
በስለትና በግርፋት ብዙ መከራዎችን አሳልፏል:: በዚህች
ቀንም በበጐው እርግና (ሽምግልና) ዐርፏል::
+" ቅዱስ ብሶይ ቀሲስ "+
=>በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ካህናት አንዱ የነበረው አባ ብሶይ
ለአገልግሎት ወጥቶ ሲመለስ የቤተሰቦቹ ቤት ሰው
አልነበረበትም:: "የት ሔዱ?" ብሎ ቢጠይቅ "ወንድምህ አባ
ሖርና እናትህ ቅድስት ይድራ ወደ እስክንድርያ ሔደዋል::
በዚያም ስለ ክርስቶስ ፍቅር ተሰውተዋል" አሉት::
+በማግስቱ የኔ ብጤዎችን ጠርቶ ሃብቱን: ንብረቱን: ቤቱን
አካፈላቸው:: ለራሱ ግን አንዲት በትር እና 3 የዳቦ ቁራሾች
ይዞ ጉዞ ተነሳ:: ወደ እስክንድርያ እንደ ደረሰ አፈላልጐ
የቤተሰቦቹን መቃብር አገኘ:: ከፊታቸው ወድቆም የናፍቆት
ለቅሶን አለቀሰ::
+ወዲያውም እንዲህ አላቸው:- "ፈጥኜ ወደ እናንተ
ስለምመጣ ጠብቁኝ:: ደግሞም ጸልዩልኝ::" ከዚያ ተነስቶ
በመኮንኑ ፊት ስለ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት መሰከረ::
በዚህ ምክንያት ብዙ ተሰቃይቶ በዚህች ቀን ሰማዕት ሆኗል::
ከወገኖቹም ጋር ተቀብሯል::
=>አምላከ ቅዱሳን ተረፈ ዘመኑን ባርኮ ለአዲሱ ዘመን በቸር
ያድርሰን:: ከወዳጆቹም ጸጋ በረከትን ይክፈለን::
=>ዻጉሜን 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ (የታሠረበት)
2.ቅዱስ ዑቲኮስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
3.ቅዱስ ብሶይ ቀሲስ (ሰማዕት)
4.አባ ዻኩሚስ / ባኹም (የ3,000 ቅዱሳን አባት)
5.አባ ሰራብዮን / ሰራፕዮን (የ10,000 ቅዱሳን አባት)
=>+"+ ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ. . .
ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም
የሚበልጠውን. . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት
መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም. . .
ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ::
ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው::
የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ:: +"+ (ማቴ. 11:7-15)
<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>

=>+*"+<+>††† ጳጉሜ †††<+>+"*

ጳጉሜን
በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከነሐሴ በኋላ ጳጉሜን የምትባል
አምስት ቀን አለች፡፡ ወር እንዳትባል አቅም ያንሳታል፡፡
ሳምንት እንዳትባል አምስት ቀን ብቻ ኾናለች፡፡ ጳጉሜን
የሚለው ስያሜዋ ግን “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል
የመጣ መኾኑ በአበው ቃል ተነግሯል፡፡
“ኤፓጉሜኔ” ማለት ጭማሪ ማለት ነው ፡፡ በግእዝ
ቋንቋችን ተውሳክ ማለት ነው፡፡ ተውሳክ ማለት ተጨማሪ
ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ
የተገኘ ነው፡፡ ኤውሮፓዎች ጳጉሜን የወር ተጨማሪ
አድርገዋታል፡፡ ይኸውም ይታወቅ ዘንድ እኛ የወርን ቁጠር
ሠላሳ ስናደርግ እነርሱ ሠላሳ አንድ ብለው የሚቆጥሩት ወር
አላቸው፡፡ ይኹን እንጂ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጳጉሜን የወር
ተጨማሪ ሳያደርጉ የዓመት ተጨማሪ አድርገዋታል፡፡
የዓመቱንም ቀን ቁጥር ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ቀን ከነሱ
ብለው ደምረውታል፡፡
በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት
መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም
ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ
አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዋኑ ዘንድ የታወቀ
አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው
ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን
ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ
የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ
እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር
በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው
እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር
አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፡-2-7፡፡ እርሱም
እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ
የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ
መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ
ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋ በመድረሱ
የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡
ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም
በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ
ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ
ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ
እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ
ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ
8፡-2 ፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት
እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡
ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት
ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ
ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ
በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን
በፈቃድ ይጾማሉ፡፡
የጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡
ይህም ጳጉሜ የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት
ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ
ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ
ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው፡፡
ሊቃውንቱ እንደ ሱባኤ ቀን ቀኖና እንዲፈጽምባት ለብቻ
ለይተው አኑረውታል፡፡ “ይህ ዓለም ኑሮ፣ ኑሮ በመጨረሻ
ያልፋል፡፡ ጌታ ዓለምን ለማሳለፍ ይመጣል” ሲሉ የገታ
የመምጣቱ ነገር እንዲነገርባት፣ መሥዋዕት እንዲሠዋባት፣
ጾም እንዲያዝባት፣ ምጽዋት እንዲመጸወትባት ለይተው
መድበዋታል፡፡
ሕዝቡ ሳይቀር “ጳጉሜን ዕድሜ ትሰጠናለች፤ በኋላም
ታድነናለች” ብለው ጾም ይጾሙባታል፡፡ የዚሁም ማስረጃ
በቅዱስ መልከ ጸዴቅ ድርሳን ይገኛል፡፡ ንግሥት ዘውዲቱ
ምኒልክ የጾም ሥርዐት ይፈጽሙባት ነበር፡፡ ሌሎችም
ሽማግሌዎችና ባልቴቶች አክብረው ይጾሙባታል፡፡ ኾኖም
የጳጉሜን አቆጣጠር አንዱ ከወር ጋራ፣ ሌላውም ከዓመት
ጋራ ቢያደርገውም በሀሉም አቆጣጠር ውስጥ ሕያዊት ኾና
መገኘቷ የታወቀ ነው፡፡
የነቢዩ ኄኖክ መጽሐፍም ጳጉሜን ጨርሶ አልዘነጋትም፡፡
ክርስቲያኖች ሁሉ በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ሁሉም ተሰብስበው
ከሌሊት ጀምረው በቤተክርስቲያን ተገኝተው ጸበል
ይጠመቃሉ፡፡ ይህንን የምናደገውም እግዚአብሔር የተባረከ
ዓመት እንዲሰጠን፣ ባሳለፍነው ዓመት የሰራነውን ኃጢአት
ይቅር እንዲለን ነው፡፡ የምንጠመቀውም ንስሐ ገብተን
ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስም የተቀደሰው ጸበል ደግሞ
ከበሽታችን ያድነናል፣ የተቀደስንም ያደርገናል፣ መጪውንም
ህይወታችን የተባረከ ያደርግልናል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
መልካም የአዲስ ዓመት ዋዜማ (ጷጉሜ) ይሁንላችሁ፡፡
ተዋሕዶ ሀይማኖታችን ለዘለአለም አለም ፀንታ ትኑርልን!!!
ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስትያን!!!

=>+*"+<+>††† ጾመ ዮዲት - ጾመ ጳጉሜም †††<+>+"*

<< ጾመ ዮዲት - ጾመ ጳጉሜም >>
በቤተክርስቲያናችን የፈቃድ ጾም ተብለው የሚታወቁት ጾመ
ጽጌ እና ጾመ ዮዲት ናቸው። የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ
ስለ ጾመችው ነው፡፡ ለፋርስ ንጉሥ ለናቡከደነፆር የጦር አበጋዝ
የነበረው ሆሎፎርኒስ ፈቃድ ተሰጥቶት እስራኤልን ለመውረር
ሲመጣ በሠራዊቱ (ዮዲ2፣2-7) የእሥራኤል ልጆችም
ሆሎፎርኒስ የአሕዛብን አገር እንዳጠፋና ንብረታቸውን
እንደዘረፈ ሰምተው ስለ ቤተ መቅደሱ መፍረስና ሰለ ንዋያተ
ቅድሳት መርከሰ ማቅ ለብሰው አመድ ነስንሰው ከቤተ
መቅደሱ በር ወድቀው አለቀሱ።(ዮዲ4፡2-15)
ሆሎፎርኒስ ግን የሚጠጡትን ምንጫቸውን በመያዙ ፣
የእሥራኤል ልጆች በውኃ ጥም ከመቸገርና ከመሞት ይልቅ
እጃቸውን ለጠላት ለመስጠት ወሰኑ፡፡ ነገር ግን ዖዝያን
የአባቶቻቸው አምላክ መልስ እስኪሰጣቸውና ቸርነቱን
እስኪመልስላቸው መከራውን በትዕግሥት እንዲቀበሉ
ስለመከራቸው ጸኑ፡፡ዮዲ7 ፣10-32)
፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
በዚያም ባሏ ምናሴ የሞቶባት፣ ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን
ጠብቃ በጾም፣ በቀኖና፣ በትኅርምት፣ በኀዘን፣ በጸሎት ተወስና
የምትኖር የሜራሪ ልጅ ዮዲት ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትቢያ
ነስንሳ፣ ሱባዔ ገባች! አምላክም ሕዝቡን የሚያድንበትን
ዕውቀትና ጥበብ ግብር በገባች በሦስተኛ ቀን ገለጸላት፡፡
(ዮዲ8፡2) ከዚያም “ወዴት ትሔጃለሽ አትበሉኝ አምላክ
እሥራኤል ይከተልሽ ብሉኝ” ብላ የኀዘን ልብሷን ጣለች፡፡
ሰውነቷን ታጠበችና ሽቱ ተቀባች፣ ባሏ በሕይወት ሳለ
የምትለብሰውን የክት ልብሷን ለበሰች፣ የጠላት ሰዎች ሁሉ
እስኪወዷት ድረስ ፈጽማ አጊጣ ሄደች፡፡(ዮዲ.10፡2-3 )
እነርሱም ለእኔ ትገባለች ለእኔ ትገባለች እያሉ ተሻሙባት፡፡
የንጉሥ ጃንደረባ ጋይ የሚባል ይህችስ ለጌታዬ ትገባለች አለ፣
ለምን እንደመጣች ጠይቀዋት ለመልካም ነገር እንደመጣች
ሲረዱ ከጦር አበጋዙ አደረሷት፡፡(ዮዲ10፡12 -22)
፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
በአንዲትም ዕለት ሆሎፎርኒስ የአሽከሮች የምሣ ግብዣ
አድርጎ ሲያበላ ሲያጠጣ ያችን እብራዊት ጥሩ ብሎ አስጠርቶ
ከፊቱ አስቀምጦ ሲበላ አብዝቶ ሲጠጣ ውሎ ሰከረ፡፡(ዮዲ12፡
1-20 ) ከዚያም አሽከሮችን ከሁሉ አስወጥቶ ድንኳኑን
ቆልፎ እንደተኛ ከባድ እንቅልፍ ያዘው ዮዲትም ከፀለየች
በኋላ ከራስጌው ያለውን ሰይፍ አንስታ የራስ ጠጉሩን ይዛ
አንገቱን ቆርጣ በድኑን ከመሬት ጥላ ቸብቸቦውን በአቁማዳ
ቋጥራ ለብላቴናዋ አሸክማ ግንዱን በታች ገልብጣ ዙፋኑን
በላይ አድርጋ ወደ ሃገሯ ተመለሰች፡፡ (ዮዲ13፡1-10) ሕዝበ
እሥራኤል በዚህ ድርጊቷ እጅግ ተደነቁ፣ ጠላታቸውን
በእጃቸው የጣለላቸውን አግዚአብሔር አምላካቸውንም
አመሰገኑ፡፡ በኋላም የሆሎፎርኒስን ራስ በተራራው ላይ
ሰቅለው መዋጋት ጀመሩ፡፡ እስከዮርዳኖስም እየተከተሉ
አጥፍተዋቸዋል፡፡ ቅድስት ቤ.ክንም እግዚአብሔር የዮዲት
ጾም ተቀብሎ ከጠላት እጅ እንዳዳናቸው፣ ለእኛም ከሰይጻም
ወጥመድ እናመልስ ዘንድ ይህንን ጾም እንጾመው
ታበረታታለች ( የፈቃድ ጾም ነውና)። ለእኛም ለሃገራችን
ፍቅር ሰላምና አንድነትን፣ የመከፋፈልን አዚም
የምንቆርጥበት ጾም ያድርግልን!

=>+*"+<+>††† ጳጉሜ፦3 ቅዱስ ሩፋኤል †††<+>+"*

ጳጉሜ፦3
ቅዱስ ሩፋኤል
ሥንክሳር፦
1)የስሙ ትርጉም፦ "የእግዚአብሔር መድኃኒት"
2)ምድብ፦ ከ7ቱ ሊቃነ-መላእክት እንዱ።
3)ትውልድ፦ መላእክት የሥጋ ልደትና ሞት የለባቸውም
(ለመጠቆም ያክል ነው)
4)ዓቢይ ተልእኮ፦ ፈታሄ ማህፀን፣ ሕክምና፣ የቀንና የዓመታዊ
የሰዎችን ሥራ ለእግዚአብሔር ዘገባ ማቅረብ፣ የሌሊት
3ሰዓት ተረኛ ጥበቃ፣ ከአውሬዎች ጥበቃ፣ መንገድ መምራትና
ሌሎችም፤
5)ተኣምር፦"ከከበሩት ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ እኔ
ሩፋኤል ነኝ" እንዳለ:: ጦቢት 12፥13
እንግዲህ ከባህሪው ቅድስና ፍጥረቱን በጸጋ ቅድስና መርጦ
የሚለይ እግዚአብሔር አክብሮ እንዲህ ያለ ሰማያዊ ፀጋ
ከሰጣቸው ቅዱሳን መላእክት መካከል በስልጣኑ
ሊቀመናብርት (የመናብርት አለቃ) የሆነ በሹመት ፈታሔ
ማኅጸን (ማሕጸን የሚፈታ) ከሳቴ እውራን (የእውራንን ዓይን
የሚያበራ) ሰዳዴ አጋንንት (አጋንንትን የሚያባርር) ፈዋሴ
ዱያን (ድውያንን የሚፈውስ)፣ አቃቤ ኆኅት (የምህረትን ደጁ
የሚጠብቅ) ተብሎ የተገለጠ ከሊቃነ መላእክቱ ቅዱስ
ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ተከትሎ የሚነሳ መልአክ ራሱን
እንዲህ በማለት ገለጠ « የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ
ከበረ ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነት ከሚያገቡ ከከበሩ
ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል
ነኝ» (ጦቢ.12÷15)
ይህ የከበረ ታላቅ መልአክ ሰሙ ሩፋኤል የሚለው ከአምላክ
ለሰዎች የተሰጠ ፈውስ የሚለውን ይተካል «በሰው ቁስል
የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ሩፋኤል ነው፡» (ሄኖ.6÷3)
ይህ መልአክ እንደሌሎቹ ሊቃነ መላእክት ሁሉ የሰው ልጆችን
ይጠብቃቸዋል(ዳን.4÷13 ዘጸ. 23÷20 መዝ.
90÷11-13 )
ያማልዳል፣ ከፈጣሪ ያስታርቃቸዋል፡፡(ዘካ.1 ÷12)
በፈሪሀ እግዚአቤሔር እና በአክብሮተ መላእክት ያሉትን
ያድናቸዋል (ዘፍ.49÷15 መዝ.3÷37)
« እግዚአብሔር ሃይሉን የሚገልጥበትን ቅጣቱን ሊያሳይ
ቢወድ አስቀድሞ መርጦ በወደዳቸው ለይቅርታ የተዘጋጁ
የይቅርታ መላእክትን ያመጣል» (ሮሜ.9÷22)
የወላድ ማኅፀን እንዲፈታ ስለተሸመ ከጌታ አዋላጅ ብትኖርም
ባትኖርም ሐኪም ሩፋኤል አይታጣም በምጥ ጊዜ ሲጨነቁ
ሴቶች ሁሉ የመልአኩን መልክ አንግተው ማርያም ማርያም
ይላሉ ማየጸሎቱን ጠጥተው ቶሎ ፈጥነው ይወልዳሉ እያሉ
ደጅ ጠንተው ይማጸኑታል፡፡
ዜና ግብሩን ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ከተናገረለት በመነሳት
በቅዱሳን ላይ ድንቅ የሆነ እግዚአብሔር በመልአኩ አድሮ
ያደረጋቸውን ተግባራት አበው የበረከት ምንጭ በሆነ ድርሳኑ
ላይ አኑረው የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን ሰጥተውናል፡፡
በጉልህ ሠፍረው ከምናገኛቸው ብዙ ድንቅ ሥራዎች መሀል
ጥቂቶቹን እነሆ፦
~> በሥነ-ስዕሉ የተማጸኑ፣ በምልጃው ታምነው የጸኑ
ቴዎዶስዮስንና ዲዮናስዮስን በገሃድ ተገልጾ ለንግስናና ለጵጵስና
ክብር አብቅቷቸዋል፡፡
~> የንጉስ ቴዎዶስዮስ ልጅም ጻድቁ አኖሬዋስም በፈጣሪው
ህግ እየተመራ የሊቀ መናብርቱን መታሰቢያ ቤተ መቅደስ
አሳንጾ ሲያስመርቅ ለበለጠ ክብር ልቡን አነቃቅቶ ለታናሽ
ወንድሙ ለአርቃዴዋስ የነጋሢነት ስልጣኑን ትቶ መንኖ
በስውርና በጽሙና እዲኖር ረድቶታል፡፡
~> በሊቀጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን አባቶች ለሊቀመናብርቱ
ክብር በአሣ አንበሪ ጀርባ ላይ ያሳነጹትን መታሰቢያ ቤተ
መቅደስ በወደቡ አጠገብ በእስክንድሪያ ሳለች ጠላት ዲያቢሎስ
አነዋውጾ ለምስጋና የታደሙትን ምዕመናን ሊያጠፉ አሣ
አንበሪውን ቢያውከው ወደ ሊቀመናብርቱ ተማጽነው እርዳን
ቢሉ ፈጥኖ ደርሶ በበትረ መስቀሉ (ዘንጉ) ገሥጾ ከጥፋት
ታድጓቸዋል፡፡
በቅዱስ መጽሐፍም እንደተገለጠው
~> ሣራ ወለተ ራጉኤልን አስማንድዮስ ከተባለው የጭን
ጋንኤን ሲታደጋት የጦቢያን አባት የጦቢትን ዓይን አበራለት
(መጽሐፍ ጦቢት)
ከዚህም አልፎ የይስሐቅን እናት ሣራን፣ የሶምሶንን እናት
(እንትኩይን) ምክነታቸውን የቆረጠ ወልዶ ለመሳም
ያበቃቸው ይኸው ፈታሔማኅጸን የልዑል እግዚአብሔር
መልአክተኛ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡
የመልአኩ ጥበቃና የክንፎቹ መጋረድ ከተዋህዶ ምእመናን
ጋር! አሜን!
ለቅዱሳን ክብርን ከማይሰጥ ከተሸወደ ትውልድ ያድነን!

Thursday, August 18, 2016

=>+*"+<+>††† ምሥጢረ ደብረ ታቦር †††<+>+"*

ምሥጢረ ደብረ ታቦር!
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ .)፡- ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በፊሊጶስ ቂሳርያ ለደቀመዛሙርቱ “ሰዎች የሰውን
ልጅ ማን ይሉታል?” ብሎ ጠይቋቸው ነበር፡፡ እነርሱም
“አንዳንዶች ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ቅዱስ ነውና ኤርሚያስ
ነው ይሉሀል፤ አንዳንዶቹ ድንቅ የሆነ ልደትህንና
የምታጠምቀውን አዲስ ጥምቀት አይተው መጥምቁ ዮሐንስ
ነው ይሉሀል፤ ሌሎች ደግሞ ለአባቶችህ ቤት ያለህን ቅናት
አይተው ኤልያስ ነው ይሉሃል” እያሉ መልሰውለት ነበር፡፡
ጌታችንም መልሶ፡- “እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?” ብሎ
ጠየቃቸው፡፡ የሐዋርያት አፈጉባዔ የሚሆን ሊቀ ሐዋርያት
ቅዱስ ጴጥሮስም “አንተክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር አብ
የባሕርይ ልጅ ነህ” ብሎ መልሷል፡፡ ጌታም “የዮና ልጅ
ስምዖን ሆይ በሰማይ ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም
(ምድራዊ መምህር) ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ”
ብሎታል፡፡
ከዚህ በኋላ ጌታችን በኢየሩሳሌም ካህናት ሊቀካህናት ጸሐፍት
ፈሪሳውያን ስለሚያደርሱበት መከራ ስለሚሞተው ሞት
ይነግራቸው ጀመር፡፡ ሰይጣንም አስቀድሞ በቀዳማይቱ
ሔዋን እንዳደረገው አሁንም በስምዖን ጴጥሮስ አንደበት
ወዳጅ መስሎ “አይሆንም አይደረግም” በማለት መከራከር
ጀመር፡፡ ጌታችን ግን ጴጥሮስን አድርጎ ሰይጣንን ይገስጸው
ጀመር፡- “ጴጥሮስ ሆይ! የእኔ አመመጣጥ ለምን እንደሆነ
አታስተውልምን? የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! በቤተልሔም
ተወልጄ ከሴቶች ለሚወለዱ ሕፃናት ሁሉ ደስታ
እንደሆንኩላቸው አሁንም የእኔን እዚያ መውረድ እየተጠባበቁ
የሚገኙትን ቅዱሳን ወደ ገነት እመልስ ዘንድ ሲዖል መሄድ
አለብኝ፡፡ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን ይህን ሊያዩ ይመኛሉና፤
አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ይናፍቃልና፡፡ ስለዚህ አያቸው ዘንድ
መውረድ አለብኝ፤ እጎበኛቸው ዘንድ ልሞት ልሰቀል
ይገባኛል፡፡ በእውነት ሰይጣን ካልሆነ በቀር የእኔን መሰቀል
የሚቃወም የነፍሳትም ነፃ መውጣት የማይናፍቅ ማን ነው?
አንተ ጴጥሮስ! ይህን ሁሉ የምትለኝ ሰይጣን በአንተ ተመስሎ
አንድም አንተው ራስህ ለእኔ ካለህ ፍቅር የተነሣ መሆኑን
ብረዳም ጀሮህ ትንቢተ ነቢያትን ባይሰማ ይልቁንም ዓሣ
ማጥመድን ብቻ ስለሚያውቅ ነውና ወግድ” አለው፡፡
ይህም በሆነ በሰባተኛው ቀን ሦስቱን ደቀ መዛሙርት
ማለትም ጴጥሮስ፣ ዮሐንስንና ያዕቆብን ይዞ ወደ ታቦር
ተራራ ወጣ፡፡ ክርስቶስ ባይሞት እንዴት ያለ ክብር
እንደሚቀርባቸው ያሳያቸው ዘንድ ምስክርም እንዲሆኑ
እነዚህን ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ይዞ ወጣ፡፡ በዚያም እንደ
ዮርዳኖስ ወንዝ መድኃኔዓለም ክብረ መንግሥቱን፣ ብርሃነ
መለኮቱን ገልጠላቸው፡፡ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን ቤተ
ክርስቲያናችን ከምታከብራቸው ዘጠኙ ዐበይት የጌታ በዓላት
አንዱ የሆነው በዓለ ደብረታቦር የዚህ ታሪክ መታሰቢያ ነው ፡፡
በዚህ ዕለት ሕፃናት ጅራፋቸውን ገምደው እያስጮኹ
ይጨፍራሉ፡፡ ይኸውም ጅራፍ ሲጮህ እንደሚያስደነግጥ ሁሉ
ከጌታ ጋር የነበሩት ሦስቱ ደቀ መዛሙርትም አብ በደመና
ሆኖ ሲናገር መደንገጣቸውንና መውደቃቸውን የሚያስታውስ
ነው፡፡
ታቦር ተራራ ከገሊላ ባሕር በምዕራራባዊ ደቡብ በኵል 10
ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፣ ከናዝሬት ከተማ በስተምሥራቅ፣
ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ ተራራ
ነው፡፡ ተራራው ከባሕር ወለል በላይ 572 ከፍታ አለው፡፡
ብዙ ሰዎች ከላይ ወደታች ሲታይ ታቦር ተራራ ቅርጹ
የተገለበጠ የሻይ ስኒ ይመስላል ይላሉ ፡፡
ምሥጢረ መንግሥቱን ለምን በታቦር ተራራ ገለጸው?
መድኃኔዓለም ሌሎች ተራሮች እያሉ ክብሩን ለመግለጥ
ስለምን ደብረ ታቦርን መረጠ ቢሉ ትንቢቱንና ምሳሌውን
ለመፈጸም ነው፡፡
1. ትንቢቱን ለመፈጸም
“ታቦርና አርሞንኤም በስምህ አምነው በተደረገላቸው ነገር
ደስ ይላቸዋል፣ ስምህን ያመሰግናሉ፣ ለስምህም ምስጋና
ያቀርባሉ” እንዲል /መዝ. 88፡12/፡፡ 2. ምሳሌውን
ለመፈጸም
ይህ ተራራ ባርቅ ሲሳራን ድል አድርጎበታል /መሳ.4፡6/፡፡
ታሪኩም እንዲህ ነው፡፡ “የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር
ፊት እንደገና ክፉ ሥራ ሠሩ፡፡እግዚአብሔርም በአሶር
በነገሠው በከነዓን ንጉሥ በኢያቡስ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤
የሠራዊቱም አለቃ በአሕዛብ አሪሶት የተመረጠው ሲሣራ
ነበር፡፡… ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩትና
የእስራኤልንም ልጆች ሃያ ዓመት ያስጨንቃቸው ነበር” /
መሳ 4.1-3/፡፡ ሁሌም ቢሆን የሰውን በደል
ዐይቶእንደወጣችሁ ግቡት፣ እንደገባችኋት ውጧት የማይልና
“ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል”
የተባለለት እግዚአብሔር ከዚህ ቀንበርየሚላቀቁበትን መላ
ራሱ አመለከታቸው /1ቆሮ. 10-13/፡፡ እስራኤላውያን ወደ
ፈጣሪያቸው በጮኹ ጊዜ የለፊዶት ሚስት የሆነችውንና
እስራኤልን በነቢይነትና ዳኝነት ታገለግል የነበረችው ነቢይቱን
ዲቦራን ተጠቅሞ የማሸነፊያ መላውን አመለከታቸው፡፡
ነቢይቱ ዲቦራ ትንቢት ከመናገር አልፋ የእስራኤልን ንጉሥ
ባርቅ ከእኔ ጋር ወደ ጦርነቱ ውጪ ብሎ ባስጨነቃት ጊዜ
በጦር አዝማችነትም ተሳተፈች፡፡ እግዚአብሔር በነቢይቱ
በዲቦራ በኩል ለእስራኤል ንጉሥ “ሔደህ ወደ ታቦር ተራራ
ውጡ” ብሎ አዞት ነበርና ንጉሡ ዐሥር ሺሕ ብረት ለበስ
ያልሆነ እግረኛ ሠራዊት ይዞ ደብረ ታቦርን ተማምኖ
በተራራው ላይ መሸገ፤ ጦርነቱም ሳይጀመር አለቀ፡፡
ምክንያቱም “እግዚአብሔርም ሲሣራን ሰረገሎቹንም ሁሉ
ሠራዊቱንም ሁሉ ከባርቅ ፊት በሰይፍ ስለት አስደነገጣቸው፡፡
ሲሣራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ” /መሳ. 4.15/፡፡
እስራኤል በእግዚአብሔር አጋዥነት በታቦር ተራራ ላይ የሃያ
ዓመት የግፍና የሰቀቀን አገዛዝ ቀንበራቸውን ከትከሻቸው
አሽቀንጥረው በምትኩ የድል ካባን ደረቡ፡፡ “በጦርነት
ኃይለኞች ሆኑ የባዕድ ጭፍሮችንም አባረሩ” ተብሎም
ጀግንነታቸው ተጻፈላቸው፡፡ የታቦር ተራራ ያኔ እንደ
እግዚአብሔር ፈቃድ ባለውለታቸው ነበር /ዕብ.
11.32-34/፡፡ ጌታም በልበ ሐዋርያት ያለ ሰይጣንን ድል
ያደርግበታልና ማለትም በልባቸው ጥርጥርን እና ፍቅረ
ሢመትን( የሥልጣን ፍቅር) ያሳደረ ዲያብሎስን ድል
ነስቶላቸዋል፡፡ ከዚህም በመነሣት ነው “በዓለ ደብረታቦር
የደቀመዛሙርት ተማሪዎች በዓል ነው” የሚባለው ፡፡
ለምን ሦስቱን ሐዋርያት ብቻ ይዞ ወጣ?
1. ጌታ “እሞታለሁ፤ እሰቀላለሁ” ባለው ጊዜ ጴጥሮስ
“ልትሞት አይገባም፤ ይህ ላንተ አይገባም” ብሎ ተቃውሞት
ነበርና በአብ ቃል “እርሱ ያላችሁን ስሙት፤ ይህ ለአንተ
አይገባም አትበሉት፤ አትቃወሙት” ለማለት፡፡
2. ጌታ “እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?” ብሎ ደቀመዛሙርቱን
በጠየቃቸው ጊዜ ጴጥሮስ “አንተ የሕያው የእግዚአብሔር
ልጅ ነህ” ብሎት ነበርና አሁንም አብ “አዎ ልክ ነህ!
እመለክበት ዘንድ ለተዋሕዶ የመረጥኩት የምወደው ልጄ ይህ
ነው” ብሎ ለማረጋገጥ፡፡
3. ለፍቅሩ ስለሚሳሱ ነው፡፡ ይህም በዕብራይስጡ ኬፋ ፤
በግሪኩ ጴጥሮስ ፤ በግዕዙ ኰኲሕ (ዐለት) የተባለው የዮና
ልጅ ስምዖን ጌታችን “እሞታለሁ” እያለ ሲናገር
“አይሁንብህ” ማለቱ አስቀድመን እንደተናገርን “ለጌታ ካለው
ፍጹም ፍቅር የተነሣ ነው” ይላል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፡፡
ዮሐንስም በወንጌል “የጌታ ወዳጅ” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ያዕቆብ
ደግሞ ጌታን በእጅጉ እንደሚወደው በኋላ ታውቋል፡፡
ይኸውም “እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ?” /ማቴ.20፡
20/ ሲባሉ“አዎ” ብሎ መመለሱና በዚህም በሄሮድስ
ዘአግሪጳ ሰማዕት ሆኖ መሞቱ ምስክር ነው፡፡
4. በይሁዳ ምክንያት ነው፡፡ “ኃጥእ ሰው የእግዚአብሔርን
ክብር እንዳያይ ያርቁታል” እንዲል /ኢሳ 26:13/ እርሱን
ጥሎ አሥራ አንዱን ወደ ተራራ ይዞ ቢወጣ ከምሥጢር
ቢለየኝ በሞቱ ገባሁበት እንዳይል፡፡ ያም ባይሆን ስምንቱ ደቀ
መዛሙርት ለምን ይከለከላሉ ቢሉ አልተከለከሉም በርዕሰ
ደብር (በተራራው አናት)ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት የተገለጸው
ምስጢር በእግረ ደብር (በተራራው ግርጌ) ለነበሩት ስምንቱ
ደቀ መዛሙርት ተገልጦላቸዋል፡፡ ይህም በደብረሲና
ለሰባውሊቃናት የተገለጠ ምሥጢር በከተማ ለነበሩት
ለኤልዳድና ሙዳድ እንደተገለጠ ማለት ነው /ዘኁ.11፡26/፡፡
ኤልያስና ሙሴን ለምን አመጣቸው?
1. በአንድ ወቅት ሙሴ እግዚአብሔርን ፡- “በአንተ ዘንድ
ባለሟልነትን ማግኘቴ እውነት ከሆነስ ፊት ለፊት ተገልጸህልኝ
ልይህና በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘቴን ልወቀው” ሲል
ጠይቆት ነበር፡፡ እግዚአብሔርም “ጀርባዬን ታያለህ ፊቴን
ግን አታይም” ብሎት ነበር /ዘጸ. 33.13፣23/፡፡ የዚህ ኃይለ
ቃል ትርጓሜናሐተታ በደብረ ታቦር ተፈጽሟል፡፡ እንዲህ
ማለቱ “አምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ሰው
ሆኜ ሥጋ ለብሼ ኋላ በደብረ ታቦር እስክገለጽልህ ድረስአንተ
በመቃብር ተወስነህ ትኖራለህ” ማለቱ ነበርና፡፡ ይህን ማለቱ
እንደሆነ የታወቀው ግን በደብረ ታቦር ሙሴን ከብሔረ
ሙታን በአካለ ነፍስ አምጥቶ ባቆመው ጊዜ ነበር፡፡
2. ልዑል እግዚአብሔር ነቢዩ ኤልያስን፡- “አንተ በኋለኛው
ዘመን ምስክር ትሆነኛለህ” ብሎት ነበር፡፡ ይኸውም ኃይለ
ቃል ኤልያስ ከብሔረ ሕያዋን መጥቶ “የእኔን የኤልያስን ጌታ
ማን ኤልያስ ነው ይልሃል? እግዚአ ኤልያስ፤ አምላከ ኤልያስ
ይበሉህ እንጂ” ሲል በደብረ ታቦር ተፈጸመ፡፡ ታያለህ የተባለው
ሙሴም አየ፣ትመሰክራለህ የተባለው ኤልያስም መሰከረ፡፡ 3.
በፊልጶስ ቂሳርያ ጌታ ሐዋርያትን “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን
እንደሆነ ይሉታል?” ብሎ በጠየቃቸው ጥያቄ ሲመልሱ
“ሙሴ ነው ይሉሃል ፤ እንዲሁም የኃይልሥራህን ተመልክተው
ኤልያስ ነው ይሉሃል” ብለው ነበርና ሙሴን ከመቃብር ፤
ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ እግዚአ ሙሴ ፤ አምላከ
ሙሴ ፤ እግዚአኤልያስ ፤ አምላከ ኤልያስ መሆኑን
ለማስመስከር፡፡
4. አይሁድ ፈሪሳውያን ጌታን እንደ ሕግ ተላላፊና
የእግዚአብሔርን ክብር ለራሱ የሚወስድ አድርገው ያስቡት
ስለነበረ /ዮሐ.9፡16፣ 10፡33/ ሕግን የሰጣቸው ሙሴንና
ለሕገ እግዚአብሔር ቀናተኛ የነበረው ኤልያስን አምጥቶ ሕግ
አፍራሽ አለመሆኑን የእግዚአብሔር ተቃዋሚም አለመሆኑን
ለማስረገጥ፡፡
5. ጌታችን በሙታንና በሕያዋን ላይ ሥልጣን ያለው እንደሆነ
ይታወቅ ዘንድ ሞተው ከተቀበሩት ሙሴን ከብሔረ
ሕያዋንም አልያስን አምጥቶ ሲነጋገር ታየ፡፡
6. የሐዋርያቱን የወደፊት አገልግሎት ሲነግራቸው፡፡
ይኸውም ሙሴ እና ኤልያስ ለሕዝበ እስራኤል በጣም ታማኝ
እንደነበሩ ሁሉ እነርሱም ለሚያገለግሉት ሕዝብ ታማኝ
እረኞች እንዲሆኑ፡፡ ሆኖም ግን አገልግሎታቸው ከሙሴና
ከኤልያስ ይልቅ ጠንከር እንደሚልም አሳይቶአቸዋል፡፡
ምክንያቱም ውጊያቸው እንደ ሙሴ ከፎርዖን እንደ ኤልያስም
ከአክዓብ ጋር ሳይሆን ከክፋት መናፍስት ጋር ነውና፡፡
7. ጽድቃቸው ከእነዚህ ከሙሴና ከኤልያስ የበለጠ ሊሆን
እንደሚገባ ለማሳየት /ማቴ.5፡20/፡፡ ምክንያቱም ሙሴ
ሕዝበ እስራኤልን ቢመራ ምድረ ፍልሥጥኤምን ለማውረስ
ነው፡፡ እነዚህ ግን ሕዝቡን መርተው የሚያስገቡት መንግሥተ
ሰማያትን ነው፡፡ ኤልያስ ሰማያትን ቢለጉምም ከጊዜአዊ
ዝናም ነው፡፡ እነዚህ ግን ለዘለዓለም መንግሥተ ሰማያትንም
የመለጎም ሥልጣን አላቸውና፡፡
ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ “ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም
ነው” ሲል ተደምጧል፡፡ ይህም የተለያየ ትርጉም አለው፡፡
ቃል በቃል (Literaly)ስናየው ቅዱስጴጥሮስ ጌታ ሆይ በዚህ
መኖር ለእኛ መልካም ነው ማለቱ “አንተ እያበላኸን
እየፈወስከን፣ ሙሴ እነዚህ መከራ ያደርሱቡኛል ይገድሉኛል
ያልካቸውን ጸሐፍትና ፈሪሳውያን እንዳይመጡ በደመና
እየጋረደ፣ ቢመጡም አልያስ እሳት እያዘነመ እያባረራቸው
በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው” ማለቱ ሲሆን
ምሥጢራዊው መልእክቱ ግን “የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ
አምላክነት በሚታመንበት፣ ወልድ ዋሕድ በምትለው
ሃይማኖት መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡ ሰይጣን ድል
በተደረገባት በታቦር ተራራ ምሳሌም በምትሆን በወንጌል
ሕይወት፣ አንድም በቤተ ክርስቲያን መኖር ለእኛ መልካም
ነው” ማለቱ ነው፡፡
ታቦር ተራራ የወንጌል ምሳሌ ነው!
ተራራ ሲወጡት ያደክማል፣ ከወጡት በኋላ ግን ጭንጫውን፣
ግጫውን ሲያሳይ ደስ ያሰኛል፡፡ ወንጌልም ሲማሯት
ትከብዳለች በኋላ ግን ጽድቅን እና ኃጢአትን ለይታ ስታሳውቅ
ደስ ታሰኛለች፡፡
ታቦር ተራራ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ነው!
ሀ. በታቦር ተራራ ከብሉይ ኪዳን ነቢያት ኤልያስና ሙሴን፣
ከሐዲስ ኪዳን ሦስቱን ሐዋርያት እንደተገኙ በቤተክርስቲያን
ብሉይ ከሐዲስ እንዲነገር ያጠይቃል፤ ሐዋርያት የሰበኩት
ወንጌል አስቀድመው ነቢያት በምሳሌና በትንቢት የተናገሩት
እንደሆነ ያስረዳል፡፡ “ነቢያት በቀየሱ ሐዋርያት ገሰገሱ”
እንዲል ጳውሎስም“በሐዋርያት በነቢያት መሠረት ላይ
ታንጻችኋል” ይላልና /ኤፌ 2፣20/፡፡
ለ. በታቦር ተራራ ከመዓስባን (ባለትዳር) ሙሴን ከደናግል
ደግሞ ኤልያስ እንደተገኙ በቤተክርስቲያን በድንግልና
የሚኖሩ መናንያን መነኮሳት፣ በሕግ በሥርዓትየሚኖሩ
ባለትዳሮችም ይገኛሉና፡፡
ታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው!
1. ተራራ በብዙ ችግር እንዲወጡት ወደ እግዚአብሔር
መንግሥትም በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናልና /ሐዋ
14፡22/፡፡
2. በታቦር ተራራ የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከሐዲስ ኪዳንም
ሐዋርያት እንደተገኙ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም፣
ሐዋርያትም አንድ ሆነው ይወርሷታልና፡፡
3. በታቦር ተራራ ከመዓስባን ሙሴ ከደናግል ደግሞ ኤልያስ
እንደተገኙ መንግሥተ ሰማያትንም ደናግልም መዓስባንም
በአንድ ላይ ይወርሷታልና፡፡
4. በታቦር ተራራ ሞተው ከተቀበሩት መካከል ሙሴን
በብሔረ ሕያዋን ካሉት ደግሞ ኤልያስን እንደመጡ
መንግሥተ ሰማያትንም ሞተው የተቀበሩትም በብሔረ
ሕያዋን ያሉትም በአንድነት ይወርሷታልና፡፡
በአጠቃላይ ታቦር ተራራ የክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት
የተመሠከረበት፣ የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት የተሰጠበት፤
ፈጣሪ ከቅዱሳን ሰዎቹ ጋር የተገኘበት፤ በልበ ሐዋርያት የነበረ
ሰይጣን ድል የተደረገበት፤ የሐዋርያት በተለይም የሦስቱ
ባለሟልነት የተገለጠበት፤ አሉባልታና ተራ ወሬ የከሸፈበት፤
የቅዱሳንን ክብርለሚያናንቁ ተራራም እንኳን “ቅዱስ”
እንደሚባል የተማርንበት፤ የብሔረ ሕያዋን መኖር
የተመሰከበረበት፤ የትንሣኤ ሙታን ዋስትና የተገለጠበት
የክብር ሰገነት፣ የምሥጢር መቅደስ፣ ታላቅ ትምህርት
ቤትም ጭምር ነው፡፡
ፈጣሪያችን እግዚአብሔር እስከ መጨረሻዋ ሕቅታ ድረስ
በታቦር ተራራ በተመሰለች ቤተክርስቲያን በሃይማኖታችን
ጸንተን የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች የስሙ ቀዳሾች
እንድንሆን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም
አማላጅነት አይለየን፡፡ አሜን!!

Tuesday, June 14, 2016

=>+*"+<+>††† ወደ ምስራቅ ተመልከቱ †††<+>+"*...

"ወደ ምስራቅ ተመልከቱ ማለት ምን ማለት ነው"??
በኦርቶዶክስ። ተዋህዶ ሀይማኖታችን ቤተ ክርስቲያን
የምታንፀው ምስራቁን አቅጣጫ ጠብቃ ነው እንድሁም
ከቤተ ክርስቲያኑ ጋር አብሮ የሚሰራው ቤተለሄም። በስተ
ምስራቅ በኩል ይደረጋል በፆለት ሰአትም ወደ ምስራቅ
ዙረን ነው የምንፀልየው በስረአተ ቀብር ላይም የሞተ
ሰው ሲቀበርእራሱ ውደ ምዕራብ እግሩ ወደ ምስራቅ።
ሆኖ ይቀበራል።ሌላው ዳቆኑ በስረአተ ቅዳሴው ላይ ወደ
ምስራቅ ተመልከቱ ይላል ለምን??
፩ የአዳም አባታችን ጥንተ ርስተ ገነት በምስራቅ ናት ዘፍ
2*8 ፪÷፰ ይች እርስታችን በአዳም በደል ምክንያት
በክሩቤል ሰይፍ ተዘግታ ስትኖር ሞትን ድል አድርጎ
በደልን ክሶ ጌታችን መዲሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በሞቱ
ከፈተልን ሉቃ 23*43። ፳፫*፵፫ ወደ ምስራቅ በዞርን
ቁጥርወደ ገነት ለመግባት የተሰጠን ተስፍፋ ትዝ ይለናል
የተከፈተችውም ቤታችን ገነት በእምነት ውለል ብላ
ትታየናለች በክርስቶስ ያገኘነውን ፀጋ እናስባለን
ምድራዊያን አለመሆናችንንም እናስባለን
፪ ጌታ የተውለደው በምስራቅ ነው
ሰበአሰገል ኮኩቡን ያዩት በምስራቅ ሲሄን ያኮከብ
የምህረት እግዝያብሄር ምሳሌ ነው እርሱን ወደ
እግዝያብሄር እንዳደረሳቸው ሁሉ እኛንም ወደ ለመለመው
መስክ ይመራናል ማቴ ፳፪*፲፬ 22*14 ወደ ምስራቅ
በዞርን ቁጥር። የጌታን መውለድነ ያደረገልንን ውለታ
ይታውሰናል የምህረት ኮከብ እየመራን መሆኑን ትዝ
ይለናል
፫ ምስራቅ የእመቤታችን ምሳሌ ነው
ከምስራቅ ጨለማውን የሚገፈው።ፀሀይ እንደሚውጣ
ሁሉ ከእመቤታችን ከድንግል ማርያምም የአለም
የሀጥያት ጨለማ የሚገፍ ፀሀይ ፅድቅ እየሱስ ክርስቴስ
ውጥቷል። ተገኝቷል ለእናንተ ስሜ የምትፈሩ የፅድቅ
ፀሀይ ትወጣላችሁአለች። ሚል ፬*፩ 4*1 ህዝ ፵፬*፩÷፬
44*1-4 ነብዩ ህዝቀየልም እመቤታችንን ያያት በምስራቅ
ነው ስለዚህ ውደ ምስራቅ በዞርን ቁጥር እመቤታችንን
እናስታውሳለን የፅድቅ ፀሀይ ክርስቶስ ስለተውለደልን
በጨለማ አለመሆናችን ትዝ እያለን ከሀጥያት እንርቃለን
፬ የአለም ድህነት የተገኘው በምስራቅ ነው
ጌታ የተስቀለውና አለምን ያዳነው በምስራቅ ነው እየሩስ
አሌም ምስራቃዊት ከተማ ናት በመሆኑ ውደ ምስራቅ
በዞርን ቁጥር የተሰቀለውን ክርስቴስንና የተከፈለልንን ዋጋ
እናስባለን
፭ ክርስትናና ቤተ ክርስቲያን የተመሰረቱት በምስራቅ ነው
የመጅመሪያው ቤተ ክርስቲያን የተመስረተውበ በእየሩስ
አሌም ሲሆንውንጌል የተሰበከው ከዚህ በመነሳቱ ነው
ስለዚህ ውደ ምስራቅ ስንዞር የቤተ ክርስቲያን ጉዞ
የውንጌል መስፋፋትን የህዝብ ና የአለም መዳን ትዝ
ይለናል
፮ ምስራቅ የእግዝያብሄር ክብር መገለጫ ነው
ኢሳ ፳፰*፲፫ 28*13። እግዝያብሄር በምስራቅ
የእስራኤልንም አምላክ የእግዝያብሄርንም ስም በባህር
ደሴቶች አከበሩ ህዝ ፵፫*፪ 43*2 የእስራኤልንም
አምላክ ክብር ከምስራቅ መንገድ ውጣ ።
፯ የጌታ ዳግም ምፅአትም ከምስራቅ ነው
ዘካ ፲፬*፲፬ 14*14
ውስብሀት ለእግዝያብሄር አሜን

=>+*"+<+>††† 7 †††<+>+"*...

#ሰባት_ቁጥር_ምስጢራት
በመጽሐፍ ቅዱስና በስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮ ስባት
ቁጥር ብዙ ምሳሌ እንዳለው ይታወቃል፡፡ በዕብራዊያን
ዘንድም
ሰባት ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ምሳሌ 24፡16 እግዚአብሔር
ከሰኞ
እስከ እሑድ ያሉትን ቀናት በሰባት ቁጥሮች ወስኗል ሕዝበ
እስራኤል ከግብጽ ባርነት ወጥተው በሲና በርሀ ሲጓዙ ይመሩት
የነበሩት በ7 ደመና እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ዘዳ 13፡21 ከዚህ
ቀጥለንም ለቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮ የ7 ቁጥር
ምስጢራትን
ምሉዕነትን የሚያስረዱ ልዩ ልዩ ማስረጃዎችን በዝርዝር
እንመለከታለን፡፤
ሀ/ ሰባቱ አባቶች
1. ሰማያዊ አባታችን እግዚአብሔር
2. የነፍስ አባት
3. ወላጅ አባት
4. የክርስትና አባት
5. የጡት አባት
6. የቆብ አባት
7. የቀለም አባት
ለ ሰባቱ ዲያቆናት
1. ቅዱስ እስጢፋኖስ
2. ቅዱስ ፊልጶስ
3. ቅዱስ ጵሮክሮስ
4. ቅዱስ ጢሞና
5. ቅዱስ ኒቃሮና
6. ቅዱስ ጳርሜና
7. ቅዱስ ኒቆላዎስ
ሐ ሰባት የጌታ ቃላት /እኔ ነኝ
1. የሕይወት እንጅራ እኔ ነኝ
2. የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ
3. እኔ የበጎች በር ነኝ
4. መልካም እረኛ እኔ ነኝ
5. ትነሣዔና ሕይወት እኔ ነኝ
6. እኔ መንገድና ሕይወት ነኝ
7. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ
መ ሰባቱ ሰማያት
1. ጽርሐ አርያም
2. መንበረ መንግሥት
3. ሰማይ ውዱድ
4. ኢየሩሳሌም ሰማያዊት
5. ኢዮር
6. ራማ
7. ኤረር
ሠ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት
1. ቅዱስ ሚካኤል
2. ቅዱስ ገብርኤል
3. ቅዱስ ሩፋኤል
4. ቅዱስ ራጉኤል
5. ቅዱስ ዑራኤል
6. ቅዱስ ፋኑኤል
7. ቅዱስ ሳቁኤል
ረ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት
1. የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን
2. የሰርምኔስ ቤተ ክርስቲያን
3. የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን
4. የትያጥሮስ ቤተ ክርስቲያን
5. የሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን
6. የፊልድልፍልያ ቤተ ክርስቲያን
7. የሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን
ሰ ሰባቱ ተዐምራት
ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ
ተዐምራት
1. ፀሐይ ጨልሟል
2. ጨረቃ ደም ሆነ
3. ከዋክብት ረገፉ
4. ዐለቶች ተሠነጠቁ
5. መቃብራት ተከፈቱ
6. ሙታን ተነሡ
7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ
ሸ ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት
1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ
2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው
3. ዛሬ ከእኔ ጋራ በገነት ትሆናለህ
4. እነሆ ልጅሸ እናትህ እነሆት
5. ተጠማሁ
6. ተፈጸመ
7. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እስጥሃለሁ
ቀ ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን
1. ምሥጢረ ጥምቀት
2. ምሥጢረ ሜሮን
3. ምሥጢረ ቁርባን
4. ምሥጢረ ክህነት
5. ምሥጢረ ተክሊል
6. ምሥጢረ ንስሐ
7. ምሥጢረ ቀንዲል
በ ሰባቱ ዐበይት አጽዋማት
1. ዐቢይ ጾም
2. የሐዋርያት ጾም
3. የፍልሰታ ጾም
4. ጾመ ነቢያት
5. ጾመ ገሀድ
6. ጾመ ነነዌ
7. ጾመ ድኅነት
ተ ሰባቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ነገሮች
1. ትዕቢተኛ ዓይን ምሳ 16፡6-19
2. ሃሰተኛ ምላስ
3. ንፁህን ደም የምታፈስ እጅ
4. ክፉ ሃሳብን የምታፈልቅ ልብ
5. ለክፋት የምትፈጥን እጅ
6. የሐሰት ምስክርነት
7. በወንድሞች መካከል ጠብን የምታፈራ ምላስ
ቸ ሰባቱ ፀሎት ጊዜያት
1. ነግህ የጠዋት ጸሎት
2. ሠለስት (የ3 ሰዓት ጸሎት)
3. ቀትር (የ6 ሰዓት ጸሎት)
4. ተሰአቱ (የ9 ሰዓት ጸሎት)
5. ሰርክ (የ11 ሰዓት ጸሎት)
6. ነዋም (የምኝታ ጸሎት)
7. መንፈቀ ሌሊት (የሌሊት ጸሎት)
ኀ ሰባቱ ራሶች (2ኛ ነገ. 17፡6)
1. ኢራን
2. ኢራቅ
3. ግሪክ
4. ሚዳን
5. ግብጽ
6. ጣሊያን
7. እስራኤል
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ
ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን
ለይኩን ለይኩን፡፡

Saturday, June 11, 2016

=>+*"+<+>††† ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ †††<+>+"*+

አእምሩ ከመ ተሰብሐ እግዚአብሔር በጻድቁ =>ዘፍ19:3
እግዚአብሐር በጻድቁ እንደተገለጠ እወቁ =>መዝሙረ ዳዊት
4:3 ++++እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ
ቅዱስ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን የጻድቁ
አባታችን አቡነገብረ መንፈስ ቅዱስ ፀሎት ,ምልጃና እረድሂት
በረከታቸው በሁላችን ላይ ይደርብን አሜን !!!!!!!!
ፃድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በስመ አብ ወወልድ
ወመንፈስ ቅዱስዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ (የጸድቅ መታሰቢያ
ለዘላለም ይኖራል።) መዝ.111፡6ቅድመ ዓለም ዘሀሎ አለም
ከመፈጠሩ በፊት ለነበረ ለእግዚአብሔር አብ እና የእመቤታችን
የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ለለበሰ ለእግዚአብሔር
ወልድ እንዲሁም ከእነሱ ባለመራቅ ለሚኖር ለእግዚአብሔር
መንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፡፡ ስለ ጻድቁ አቡነ ገብረ
መንፈስ ቅዱስ በማብዛት አይደለም በማሳነስ በማስረዘም
አይደለም በማሳጠር እንድጽፍ ያነሳሳኝ እግዚአብሔር ክብርና
ምስጋና ጌትነትና ውዳሴ ይገባዋል አሜን
በእውነት፡፡“እግዚአብሔር ያፈቅሮሙ ለጻድቃን
እግዚአብሔር የዐቅቦሙ ለፈላስያን፡፡“ (እግዚአብሔር
ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር ስደተኞችን
ይጠብቃል፡፡)“” መዝ.፻፵፭፡፰ (145፡ 8)አባታችን አቡነ ገብረ
መንፈስ ቅዱስ ሀጋራቸው ንሂሳ ግብጽ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን
እናታቸው አቅሌስያ፡ ይባላሉ፡፡ ልጅ አጥተው 30 ዘመን
ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር
ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ
ከፍታ የሚበጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች፡፡
በዚሁ መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ተጸንሰው ታህሳስ 29
ተወለዱ፡፡ ዓይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ
እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ተነስተው “ስብሐት ለአብ
ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽ
ልመት ውስተ ብረሃን” ብለው በማመስገናቸው ኋላም ምድራዊ
መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው
በመኖራቸው መላዕክትን ይመስላሉ፡፡ሦስት ዓመት ሲሆናቸው
ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ
አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው፡፡
አባ ዘመደ ብርሃን አሳድጎ አስተምሮ ከመዓርገ ምንኩስና
አድርሷቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ “ሀብተ ፈውስ” ተሰቷቸዋል፡፡
በአንድ ቀን እልፍ እውራንንና አንካሳን ፈውሷል፡፡ ኋላ ግን
ኤጲስ ቆጶሳቱ ካህናቱ ዝናቸውን ሰምተው እየመቱ ግብር
የሚያስፈቷቸው ቢሆን ቅዱስ ገብርኤል በክንፉ ነጥቆ ከጌታ
ፊት አቀረባቸው፡፡ በገድልህ በትሩፋትህ ከሞተ ነፍስ ከርደተ
ገሃነም የሚድኑ ብዙ ነፍሳት አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ
ግባ፡፡ ኑሮህም ከ60 አናብስተና ከ60 አናምርት ጋር ይሁን
አላቸው፡፡ ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ? ብለው ጌታን
ጠየቁት፡፡ “ዘኬድከ ጸበለ-እገሪከ ይልህሱ ወበውእቱ ይጸግቡ…”
የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያው ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ፡፡
ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው ከአናብስትና አናምርት ጋር
ይኖሩ ጀመር፡፡ ዳንኤል በአናብስት ጉድጓድ በጣለ ጊዜ አናብርቱ
እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ የረገጡትን ትቢያ
ይልሱ ይታዘዟቸውም ነበር፡፡ በዚህ መልኩ መልአኩ 30
ዓመት ከቆዩ በኋላ ጌታ ባንድነት በሦስትነት ተገልጾ “ምን
ላድርግልህ ትሻለህ?” አላቸው፡፡ መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ
ይገባልና የምድረ ጋቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት፡፡ 3000
ሃጥአንን ከሲኦል አውጥቶ ገነት አግብቶላቸዋል፡፡ “ሑር ምድረ
ኢትዮጵያ ወበህየኒ ሀላውከ ነፍሳት ዘታወጽኦሙ ወደ ኢትዮጵያ
ሂድ” አላቸው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፋስ ጭኖ ምድረ
ከብድ አድርሷቸዋል፡፡ ዳግመኛም ወደ ዝቋላ ደብር ቅዱስ
ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጽሐ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ
ሃጢአት አይተው ከባሕሩ በራሳቸው ቆመው ይጸልዩ ጀመር፡፡
አርባ ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ “ዘገብረ ተዝካረከ
ወዘጸውዐ ስመከእምሕር ለከ ብሎሀል” አላቸው፡፡ መላ
ኢትዮጵያን ካልማረልኝ አልወጣም ብለው መቶ አመት ሲጸልዩ
ኑረዋል፡፡ ከመቶ አመት በዃላ ጌታ “ተንስእ ወጻእ መሐርኩ ለከ
ኩሎ ኢትዮጵያ ምሬለሃለሁ ውጣ” ብሏቸው ወጥተዋል፡፡ከዚህ
በኋላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች
ሆነው ሰባት ዓመት እንደ ትኩል አምድ ሆነው ዓይናቸውን
ሳይከድኑ ሰባት ዓመት ቆመው ጸልየዋል፡፡ ሰይጣንም
በምቀኝነት ተነሳስቶ ቁራን መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ
አሳወራቸው፡፡ ሁለት ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ
ገብርኤል መጥተው እፍ ብሏቸው አድነዋቸዋል፡፡ ከዚያ
ተነስተው ወደ ዝቋላ ሲሄዱ ሥላሴን በአምሳለ አረጋውያን
ከጥላ ስር አርፈው አገኟቸው፡፡ በእግዚአብሔር ዙፋን
ተማጽነናል አዝለህ አንድ አንድ ምዕራፍ ሸኘን አሏቸው፡፡
አዝለው ከሸኙአቸው በኋላ በአንድነት በሦስትነት ሆኖ ታያቸው
ደንግጠው ወደቁ፡፡ አንስተው ዝቋላ ወርደህ ጠላቶችህን
ተበቀላቸው አሏቸው፡፡ በዘባነ መብረቅ ደርሰው ሰባቱን ሊቃነ
መላእክት አጋዥ አርድገው እልፍ አዕላፍ አጋንንትን በማጭድ
አጭደዋል፡፡ እንዲህ ለሰሚዕ እፁብ በሆነ ግብር ዓመት
በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው
ያመነውን በኪዳናቸው የተማጸነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ
ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለት በዕለተ እሁድ
ዐርፈዋል፡፡መላእክት በአክናፈ እሳት ኢየሩሳሌም ወስደው
በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል፡፡ሮሜ 12፡12፣ 15፡
30፣ያዕ5፡ 16፣ መዝ.88፡3፣111፡6 ምሳ.10፡7 ማቴ10፡
40-42ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በቅዱስ ላሊበላ ዘመነ
መንግስት መሆኑ ስለሚታወቅ ከ9- 14ኛው ም/ዓ ድ/ል/ክ
መሆኑ ነው፡፡ ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኝ፣ ካለማወቅ ወደ
መረዳት ያደረሰኝ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ
ጥንት ላሌለው ቀዳማዊ ፍጻሜ ላሌለው ድህራዊ ያልኖረበት
ጊዜ የሌለ የማይኖርበት ጊዜም የማይኖር የዘላለም ንጉስ
ሁሉን ቻይ ፈጣሪ እግዚአብሔርን በራስ ፀጉሬ ቁትር
በአጥንቶቼም ልክ አመሰግናለሁ፡፡በሰማይ ያሉ መላእክት
በምድርም የሚኖሩ የአዳም ዘር ሁሉ የሚያመሰግኗት
በአማላጅነቷ ሁል ጊዜ የማትለየኝ ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ
የብርሃን እናት የሁሉ እመቤት የአምላክ እናት ከተመረጡ
የተመረጠች ከተለዩ የተለየች ከተከበሩ የተከበረች እናቴ
እመቤቴ ድንግል ማርያም በቃላት ልገልጸው ከምችለው በላይ
አመሰግናለሁ፡፡ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ
ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን
ለይኩን ለይኩን፡፡
ምንጭ፡- መዝገበ ታሪክ፣ ነገረ ቅዱሳን፣ የወርሃ ጥቅምት
ስንክሳርና ገድላቸው፡፡

Wednesday, June 8, 2016

=>+*"+<+>††† ዕርገት †††<+>+"*+

†† †† ††
#ዕርገት
††
“እግዚአብሔር” በእልልታ ጌታችንም በመለከት ድምጽ ዐረገ
ዘምሩ ለአማላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ ለንጉሳችን ዘምሩ። መዝ
45:5
+
" እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ
ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥
በመንፈስ የጸደቀ፥
ለመላእክት የታየ፥
በአሕዛብ የተሰበከ፥
በዓለም የታመነ፥
በክብር ያረገ።"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:16)
†† †† ††
እንኩዋን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የዕርገት በዓል
በሰላም አደረሳችሁ!!!
†††
ሙሴ አሮንንና ሖርምን ከተማዋን እንዲጠብቁ አድርጎ ኢያሱን
አስከትሎ
ወደ ደብረ ሲና ሔደ። ኢያሱን ከተራራው ግርጌ ትቶ ሙሴ
ብቻውን ወደ
ሲና ወጣ። በሲና ተራራም 40 ቀንና ለሊት ቆየ።
በዚህን ጊዜ እስራኤላዊያን ተስፋ ቆረጡና ማጉረምረም
ዠመሩ።
“ፀሐይ ወጣች ገባች ሙሴ ግን ቀለጠ” አሉ። አመሌ አመሌ
ሲል
በደብረ ሲና ያያት እሳት አቃጠለችው እንዴ? ሐመልማሉንስ
አላቃጠለች
ሙሴን ፈጀችው እንዴ? ይህ ባይሆንም ወደኛ ሲመጣ ባሕረ
ኤርትራን
ሲሻገር ሰጠመ እንዴ? ብለው አጉረመረሙ።
አንገተ ደንዳና የተባሉት እስራኤላዊያን በሬ አላርስ ሲል
አንገቱን
እንደሚያደነድን አንገታቸውን አደንድነው ካህኑ አሮንን ሙሴ
ስለቀረ
አምላክም ስለሌለ ጣኦት ስራልን ብለው ጮኹ። አሮን አሮን
ግበር ለነ
አማልክተ ዘይሐውሩ ቅድሜነ እያሉ ጣኦቱ ይሰራላቸው ዘንድ
ካህኑ
አሮንን አቻኮሉት አጣደፉትም። ይገርማል! እኛም አንዳንዴ
ካህናቱን
የማይገባ ሥራ ስሩ እንደምንላቸው ማለት ነው። ካህናቱን ፣
መነኮሳትን
፣ ጳጳሳትን ፤ ባሕታዊያንን ዓለማዊ ስራ ስሩ እንደምንላቸው
እስራኤላዊያንም ካህኑን ጣዖት ስራ አሉት።
አሮን ልቡ ተከፈለ። ጣኦቱን ቢሰራ ከፈጣሪ ሊጣላ ባይሰራ
እስራኤላዊያን በድንጋይ ሊወግሩት መኾኑን እያሰበ ልቡ
ተከፈለ።
በመጨረሻም ዘዴ መጣለት። አፍቃሬ ንዋይ ናቸውና
ወርቃችሁን አምጡ
ብላቸው ይሰስታሉ ብሎ አሰበ። ይኹን እንጂ በልባቸው ያደረው
ሰይጣን
እጃቸውን ፈቶ ወርቁን በአሮን እግር አስቀመጡ። ካህኑም
መሬት
ተቆፍሮ ቢቀበር ጣኦት ይኾናል አላቸው በዚያው ጠፍቶ
የሚቀር
መስሎት። ግና የተቀበረው ወርቅ በግብረ ሰይጣን አንገቱ
ወርቅ ደረቱ
ብር እግሩ ብረት የኾነ ጥጃ ኾኖ ወጣ።
†††
እስራኤላዊያንም አምላካችን እያሉ መጮኽ ዠመሩ። ቀን
ሲደርስ አንባ
ይፈርስ እንዲሉ ሙሴ ከሲና ተራራ የሚወርድበት ቀን ደረሰ።
ጽላቱን
ከእግዚአብሔር ተቀብሎ 40 ቀን ሙሉ ከሲና ተራራ ግርጌ
የነበረውን
ትዕግስተኛ ኢያሱን አስከትሎ ወደ ሕዝበ እስራኤል መጣ። ነቢዩ
ሙሴ
ከሲና ተራራ ላይ የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዞ ሲወርድ
እስራኤላዊያን ጣኦትን
ያመልኩ ነበር፤
ሙሴ ከሲና ተራራ መውረዱ .... ጌታችን ከሰማየ ሰማያት
የመውረዱ
ምሳሌ ነው።
ታቦቱ ከሙሴ እጅ ወድቆ ጣዖታቱን ሰባበረ ...... ይህም ጌታችን
የዲያቢሎስን እራስ እራሱን የመቀጥቀጡ ምሳሌ ነው።
ጌታ ስለ ኃጢአታችን በፈቃዱ ሞቶ ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ
“በክብርም
ዐረገ” ይህም ታቦቱ ከእንደገና በእግዚአብሔር ጣት ተጽፎ
ለሙሴ
የመሰጠቱ ምሳሌ ነው!!! ዘፀአት ምዕ. 31-34
ልበአምላክ ዳዊት ለምስጋና አሥሩን ቅኝት ቃኘውና በገናውን
አነሳና
የጌታን ዕርገት በትንቢት መነጽር አየነና እንዲህ አለ፦
“እግዚአብሔር”
በእልልታ ጌታችንም በመለከት ድምጽ ዐረገ ዘምሩ
ለአማላካችን ዘምሩ፤
ዘምሩ ለንጉሳችን ዘምሩ። መዝ 45:5፤ መጽሐፍ አንባቢው
ያስተውል!
ይላል። የዳዊትን መዝሙር ልብ ብለህ ስማው! ልበ አምላክ
ዳዊት
ጌታችን በዐረገ ጊዜ “እግዚአብሔር ዐረገ” ብሎ ተነበየ።
ጌታችን ሞትን
ድል አድርጎ ሲነሣ ደግሞ ምን እንዳለ አስተውል
“እግዚአብሔር
ከእንቅልፍ እንደሚነሳ ተነሣ” መዝ 77:65
አንድም ንዋየ ኅሩይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በደሙ ያፀናትን
የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ጠብቁ አለ; ደሙን በላዕለ
መስቀል ላይ
ያፈሰሰውን ጌታችንን “እግዚአብሔር” ብሎ ተናገረ
ሐዋ20:28።
††† ††† †††
" #ዕርገት_በደብረዘይት_ተራ ራ"

ጌታችን የዐረገው በደብረዘይት ተራራ ላይ ሲሆን በዚህች ተራራ
ላይ
ብዙ የወይራ ተክል ስለሚገኝ ተራራው ደብረዘይት ተብሏል።
ጌታችን ከትንሳኤ “እስከ ዕርገቱ ለ40 ቀናት” ለሐዋርያቱ
እየተገለጸ
ያስተምራቸው ነበር። [ሐዋ. 1:3] ነገር ግን ምን
እንዳስተማራቸው
አልተጻፈም; በመፅሐፈ ኪዳን ላይ ግን ተፅፏል።
ቤተክርስቲያናችን
አዋልድ መጽሐፍትን የምትጠቀመው በእንዲህ ሁኔታ ነው
ማለት ነው።
“ይህ ወደ ሰማይ ሲያርግ የአያችሁት ኢየሱስ በክብር ወደ ሰማይ
ሲወጣ እንዳያችሁት እንዲሁ በክብር ይመጣል” ሐዋ. 1:11
አምላክ በእልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ
********* ዐረገ ********* መዝ46:5
ከላይ እንዳየነው እንደ ልቤ የተባለለት ዳዊት; ብርሐነ ዓለም
የተባሉት ሐዋርያት እንዲህ ብለው የጻፉትን መናፍቃኑ ሁሌ
ባነበቡት
ቁጥር እስከ ዛሬ ድረስ እንዲሁ አይናቸው እያነበበ ያልፉታል!!
ለነገሩ
ሐዋርያው አስቀድሞ እንዲህ ብሏል፦ “እናንተ የማታስተውሉ
የገላትያ
ሰዎች ሆይ በመስቀል ላይ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንዳታዩ
ማን አዚም
አደረገባቹ” ገላትያ 3:1
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት ከመጽሐፍ ቅዱስ
ከብዙ
በጥቂቱ ፦
ብሉይ ኪዳን *** አዲስ ኪዳን
መዝ 46:5 *** ሮሜ 9:5
ኢሳያስ 9:6 *** እብራዊያን 1:10
ሚክያስ 5:2 *** ቆላስይስ 1:15
ዘካርያስ 9:9 *** ራዕ 22:12
††† ††† †††
“ #ከዕርገት_በኋላ_10ኛዋ_ ቀን”

እመቤታችን ከሐዋርያቱ ጋር በተዘጋ ደጅ ኾና በፀሎት
ትረዳቸው ነበር፤
በፀሎት ላይ እያሉም ጌታችን ከሞት በተነሣ በ50ኛው በዐረገ
በ10ኛው
ቀን መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያቱ ወረደ። ይህች ቀን ልደታ
ዘቤተክርስቲያን
በመባል ትታወቃለች፤ ምክንያቱም እነ ቅ/ጴጥሮስ በአንድ ቀን
3ሺ
ሰዎችን አጥምቀው አማኞች ስላደረጉ ነው። [የሐዋ.2:41]
በዚህች ቀን
ርደተ መንፈስ ቅዱስ [የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ኾኖ
ለሐዋርያቱ
በአውሎ ንፋስና በእሣት አምሳል ተገለፀላቸው። ጌታችን
ለኒቆዲሞስ
መንፈስ ቅዱስ በአውሎ ንፋስ መገለፁን ሲያስረዳው እንዲህ
አለው፦
ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔርን
መንግስት
አይገባም… “ንፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል ድምፁንም
ትሰማለህ” ከየት
እንደመጣና ወዴት እንደሚሔድ አታውቅም የተባለውም በዚሁ
ምክንያት
ነው፤ ዮሐ. 3:8።
ከበዓለ ዕርገት ጋር በተያያዘ ጥያቄ ልናነሳ እንችላለን፤ ብዙ
ጊዜ ሰዎች ጌታችን 40 ቀን ብቻ ጾሞ እኛ ለምን 55 ቀናት
እንፆማለን
እያሉ ይጠይቃሉ፤ ለጥያቄያቸው እራሱን የቻለ መልስ
ቢኖረውም ይህን
የሚጠይቁ ሰዎች ግን ከትንሣኤ ጀምሮ ሐዋርያቱ “መንፈስ
ቅዱስ”
እስከተቀበሉበት ቀን ድረስ ለ50 ቀናት ለምንድን ነው
የማንጾመው
ብለው አይጠይቁም፤ ሙሽራው ከሐዋርያቱ ጋር እያለ
አይጾሙም
ስለተባለ በእነዚህ ግዜያት አይፆምም አይሰገድም ለንስኃ ቀኖና
ቢሰጥም ቀኖናው በዚህ ወቅት አይፈጸምም።
[ንስኃ እንገባለን ነገር ግን ቀኖናው እስከ ጾመ ሐዋርያት ድረስ
ይቆያል ]

“ዕርገትና እግዚኦታ” ፦ በእግዚኦታ ላይ ካህኑ ሕብሥቱን
ይበልጥ ከፍ
አድርጎ ይይዘዋል ይህም “የዕርገቱ” ምሳሌ ነው። ከካህኑ ጋር
ሆነን 41
ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ እንላለን ፤ ይህም አርባው
እግዚኦታ
አይሁድ ጌታችንን 40 ግዜ እንገርፋለን ብለው እያዛቡ ብዙ ግዜ
የመግረፋቸው ምሳሌ ሲሆን በመጨረሻ ካህኑ ብቻውን
የሚላት
እግዚኦታ ደግሞ የአዳምና የሔዋን የንስሃ ምሳሌ ነው። 12
ግዜ
እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ ስንል ደግሞ ስለስምህ ብለህ ይቅር
በለን
ስንል ነው።
“አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ” የሚለውን እያንዳንዱን ፊደል
ስንቆጥር
12 ይሆናልና!!
Ascend in to haven in glory sit the right hand
of the
father & again wilt come on glory to judge
the quick
and the dead Have mercy up on us.
አቤቱ ሞትህን ልዩ የምትሆን ትንሣኤህንም እናስተምራለን፤
ዕርገትህን
ዳግመኛ መምጣትህን እናምናለን ፤ እናመሰግንሃለን፤
እናምንሃለን ፤
ፈጣሪያችን ሆይ እንማልድሃለን።
+
እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ
ነው፤
በሥጋ የተገለጠ፤
በመንፈስ የተረዳ፤
ለመላዕክት የታየ
በአሕዛብ ዘንድ የተሰበከ፤
በዓለም የታመነ፤
በክብር ዐረገ 1ኛ ጢሞ 3:16
*********
እነኾ በዓለ ዕርገትን ይህን የመሳሰሉትን እያሰብን እናከብራለን።
†††
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የሲኦል ደጆች አይችሏትም
ቤተክርስቲያን አትታደስም!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
ሰላም
እንማልዳለን!
(መጽሐፈ ሚስጢር)
የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣
የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣
የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት
አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው
ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
†† † ♥ † ††
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት
ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን
፤ አሜን!!!
†† † ♥ † ††
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን
እንደገለጽክላቸው ለእኛም ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!!
†† †♥ † ††
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክ ቡ ር

Friday, June 3, 2016

=>+*"+<+>††† ግንቦት_27_መድኃኔዓለም †††<+>+"*+

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
አሜን
#ግንቦት_27_መድኃኔዓለም _ክርስቶስ_ለመባዓ
#ጽዮን_ያደረገለት_ተአምር _ይኽ_ነው፡- ‹‹ተክለማርያም
የተባለ መባዓ ጽዮን የመድኃኔዓለምን በዓል ከሌላ ጋር
አይጨምርም ነበር፡፡ ለመድኃኔዓለም መታሰቢያ የሚሆነውን
ሁሉ ለብቻው ያስቀምጠዋል፡፡ በረሃብ እስኪሞት ድረስ
ከመድኃኔዓለም መታሰቢያ እህል ምንም አይቀምስም፡፡
ያዘጋጀውንም ኅብስትና ጽዋ ለሕዝቡ ይሰጣቸዋል፡፡ የታመሙ
ሰዎችም ለመድኃኔዓለም መታሰቢያ ከተዘጋጀው በበሉ ጊዜ
ከሕመማቸው ሁሉ ይድናሉ፡፡ አባታችን የሚያዘጋጀውን
የመድኃኔዓለምን መታሰቢያ ይበሉ ዘንድ እየተጨናነቁ
ከቅርብም ከሩቅም ሰዎች በእምነት ይመጡ ነበር፡፡ በየወሩ
በዓሉም በቀረበ ጊዜ በጾምና በጸሎት ሰባት ቀን ይማለላል፡፡
ሆዱን ሳያጠግብ ራሱን ሳያስተኛ በፍጹም ልቅሶ መከራውን
ያስባል፡፡ ምድርን እስኪያርስ ድረስ ከዓይኖቹ ዕንባውን
ያፈሳል፡፡ ከልቅሶውም ብዛት የተነሣ እስኪጠፋ ድረስ ዓይኖቹ
ታመሙ፡፡ እመቤታችን ማርያምም ብርሌ የሚመስል ጽዋን
በእጇ ይዛ መጣች፡፡ ‹ወዳጄ ተክለማርያም ሆይ! ስለ ልጄ
ፍቅር ለታመሙ ዓይኖችህ መድኃኒትን እሰጥህ ዘንድ እነሆ
መጣሁ› አለችውና ጣቶቿን ከዚያ ጽዋ ነክራ ዓይኖቹን ቀባችው፤
ከሕመሙም ዳነ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሕመም አላገኘውም፡፡
በተቀደሰች በዓርባ ጾምም የመድኃኔዓለምን ግርፋት እያሰበ
ሰውነቱን በእጅጉ ገረፈ፡፡ ደሙ ከመሬት እስኪወርድ ድረስ
ልቡንም አጥቶ ከምድር ላይ ወደቀ፡፡ የመድኃኔዓለምን
መከራውን አስቦ እንደሞተም ሆነ፡፡ መድኃኔዓለምም ወደ
እርሱ መጣና ‹ተነሥ እኔ ቁስልህን እፈውስሃለሁ› ብሎ
የጀርባውን ቁስል ዳሰሰው፡፡ ምንም ሕማም እንዳላገኘውም
ሆነ፡፡ መድኃኔዓለምም አባታችንን ‹በአንተው እጅ ትገደልን?
እኔ እንኳ የተገደልኩት በአመፀኞች በአይሁድ እጅ ነው› አለው፡፡
በዚያችም ሰዓት ጌታ የመባዓ ጽዮንን ከንፈሮቹን ይዞ አፉን
ከፍቶ ሦስት ጊዜ እፍ አለበት፡፡ ‹የከበረ ትንፋሼም ከትንፋስህ
ጋራ ይጨመር፣ ሥጋህም ከነፍስህ ጋራ የከበረ ይሁን› አለው፡፡
‹አንተ በላዩ እፍ ያልህበትም የተቀደሰና የከበረ ይሁን› አለው፡፡
ብፁዕ ተክለማርያምንም አይቶ ለሰው ፈጽሞ የሚያስደንቅ
ነገርን ነገረው፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምም ስለ ልጇ ስለ
ፍቅሩ ገናንነትም ተደሰተች፡፡ መድኃኔዓለምም አባታችንን ‹ስለ
ሕማሜ ታመሃልና ስለ ክቡር ደሜም ደምህን አፍሰሃልና ስለ
ሞቴም ሞተሃልና እንደወደድኸኝ እኔም እወድሃለሁ፣
ሁልጊዜም ከአንተ አልለይም፡፡ አንተን የወደደ እኔን ወደደ፣
አንተንም የጠላ እኔን ጠላ፣ የላከኝንም ጠላ፣ እኔን እንደጠሉኝ
እንደ አይሁድ ይሁን፡፡ ነፍስህ ከሥጋህ ተለይታ በምትወጣበት
ቀንም ለሌላ አልሰጣትም እኔ እቀበላታለሁ እንጂ› አለው፡፡
‹ወደ አንተ የደረሰ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያንህም የመጣ፣
በአንተም የተማፀነ፣ በእጅህም የተባረከውን ሁሉ
እምርልሃለሁ፡፡ በእኔና በእናቴ ማርያም ስም በማይታበል ቃሌ
ቃልኪዳን ሰጠሁህ፣ መሐላዬንም አላጎድልብህም› አለው፡፡
አባታችንም ይህን ሰምቶ ፈጽሞ ተደሰተ፡፡
‹‹በሌላም ጊዜ ዳግመኛ ጌታችን ደም ግባቱ ያማረ፣ ልብሱም
የመስቀል ምልክት የሆነ ንጹሕ አክሊል በራሱ የተቀዳጀ
ጎልማሳ ሆኖ በፊቱ ቆመ፡፡ ‹ልመናህን እፈጽምልህ ዘንድ እነሆ
ወደ አንተ መጣሁ› አለው፡፡ ‹…እንደ አንተ በዓሌን ያደረገውን
እምረዋለሁ፣ የብርሃን ልብስንም አለብሰዋለሁ…› ብሎ
ቃልኪዳን ከሰጠው በኋላ ሁለመናው በመለኮት ጨውነት
ይጣፍጥ ዘንድ አውራ ጣቱን አጠባው፡፡ ከዚህም በኋላ ከእርሱ
ተሰወረ፡፡ እንዲሁም በሌላ ጊዜ እንዲህ እያለ መለነ፡- ‹ጌታዬ
ፈጣሪዬ ሆይ! በዓልህን አድርግ አንድ አንተ የምትወደውን
ግለጥልኝ› አለ፡፡ ጌታም ‹የሞቴን መታሰቢያ ያደረገ እንደ እኔ
ነፍሳትን ከደይን ያወጣል፣ ‹በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን
ይሠራል፣ ከዚያም የበለጠ ይሠራል› ብዬ በወንጌሌ
እንደተናገርሁ› አለው፡፡›› ‹‹ክርስቲያኖች ሁሉ የፈጣሪያችንን
የመድኃኔዓለም ክርስቶስን የመታሰቢያ በዓሉን እናድርግ፡፡
የአባቶቻችን የሐዋርያት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የመላእክት
መታሰቢያቸው ባረፉበት በተሾሙበት ቀን ይከበራል፡፡ እነርሱን
የፈጠራቸው እርሱ መድኃኔዓለም ነው፣ ያከበራቸው፣ ከፍ ከፍ
ያደረጋቸው፣ ስማቸውን ለጠራ መታሰቢያቸውን ያደረገ
እንደሚድን ቃልኪዳን የሰጣቸው እርሱ ነው፡፡ የመድኃኔዓለምን
የሞቱን መታሰቢያ ያደረገ ግን የተኮነኑ ነፍሳትን ከደይን
ያወጣል፣ በሞቱም ጊዜ ሥቃይን አያያትመ፡፡›› ‹‹ጌታችንም
ለመባዓ ጽዮን እንዲህ አለው፡- ‹መታሰቢያዬንም እንደ አንተ
በየወሩ የሚያደርግ ሁሉ በዓርብ ቀን ብዙ ነፍሳትን ከሲኦል
አወጣለታለሁ፡፡ አንተ ከምታደርገው ከሞቴ መታሰቢያም
ቁራሽ የበላውን፣ ከሩቅም ወሬህን ሰምቶ በልቡ ደስ ያለውና
የወደደውን ከሞቴ መታሰቢያ መድረስ ባይቻለውም እንኳ
እምረዋለሁ፡፡› መባዓ ጽዮንም ስለተሰጠው የምሕረት
ቃልኪዳን እጅግ ደስ ብሎት እንዲህ አለ፡- ‹ያለቸርነቱ በቀር በጎ
ሥራ ለሌለኝ ለእኔ ለኃጢአተኛው ይኽን ሁሉ ስላደረገልኝ
ለእግዚአብሔር ምን እከፍለዋለሁ?› አለ፡፡ ነገር ግን ስሙ
ለዘለዓለም የተባረከ ይሁን አሜን፡፡››
+ + + + + + + + + + + + + + +
ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ከሞተ ከ4 ቀን በኋላ ጌታችን
ያስነሣው ቅዱስ አልዓዛር ዓመታዊ መታሰቢያ በዓሉ ነው፡፡
ይኸውም ቅዱስ አልዓዛር የባለ ሽቱዋ የማርያም እንተ
ዕፍረትና የማርታ ወንድም ሲሆን ጌታችን በጣም ይወደው
ስለነበር አልዓዛር መሞቱን ሲሰማ ከእኅቶቹ ጋር
አልቅሶለታል፡፡ ከሞተም ከ4 ቀን በኋላ ከመቃብር
አስተሥቶታል፡፡ ከጌታችን ዕርገት በኋላም አልዓዛርና እኅቶቹ
ቤታቸውን የወንጌል መማርያና የእንግዶች መቀበያ
አድርገውታል፡፡ እርሱ ከሞት በተነሣ በሳምንቱ ጌታችን
ተሰቅሎ በሥጋ ሞተ፡፡ ከትንሣኤውም በኋላ አልዓዛር
ከሐዋርያት ጋር ሆነ፡፡ በ50ኛውም ቀን ከሐዋርያት ጋር
መንፈስ ቅዱስን ተቀብሏል፡፡
አይሁድም ክርስቶስን ያመኑ ክርስቲያኖችን ሲያሳድዱ
አልዓዛርንና እኅቶቹን በቀዳዳ መርከብ ጭነው ወደ ባሕር
ጥለዋቸዋል፡፡ በተአምራት ከሞት ድነው የፈረንሳይ ግዛት
ወደሆነች አንዲት ከተማ ተሰደው በዚያ እየኖሩ የክርስቶስ
ምስክር ሆነዋል፡፡ ሐዋርያት በቆጵሮስ አገር ላይ በአንብሮተ
እጅ ኤጲስ ቆጶስነት ሾሙት፡፡ መንጋውንም በመልካም
አጠባበቅ እየጠበቀ በሹመቱ 40 ዓመት አገልግሏል፡፡
በከተማዋም የመጀመሪያው ጳጳስ በመሆን ወንጌልን እየሰበከ
ሲያገለግል ኖሮ መጋቢት 17 ቀን በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡
ቅዱስ አልዓዛር በሰማዕትነት ካረፈ ከብዙ ዘመን በኋላ
ከክርስቲያን ነገሥታት መካከል አንዱ የቅዱስ አልዓዛር ሥጋው
በቆጵሮስ እንዳለ በሰማ ጊዜ ከቆጵሮስ ደሴት ወደ
ቁስጥንጥንያ አፈለሰው፡፡ ሊያፈልሱትም በወደዱ ጊዜ በከበረ
የድንጋይ ሣጥን ውስጥ ሆኖ በምድር ውስጥ ተቀብሮ አገኙት፡፡
በላዩም እንዲህ የሚል ጽሑፍ ነበረ፡- ‹‹ይህ በመቃብር ውስጥ
አራት ቀን ከኖረ በኋላ ከሙታን ለይቶ ላስነሣው ክብር
ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጁ የሆነ የቅዱስ
አልዓዛር ሥጋ ነው፡፡›› ይህንንም ጽሑፍ ባነበቡ ጊዜ ደስ
ተሰኝተው ተሸክመው ወደ ቁስጥንጥንያ አገር ወሰዱት፡፡
ካህናቱም ሁሉ በዝማሬ በክብር ተቀበሉት፡፡ ባማረ ቦታ
አስቀምጠውት ጥቅምት 21 ቀን የፍልሰቱን በዓል
አደረጉለት፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
የመድኃኔዓለም ቸርነቱ የመባዓ ጽዮን አማላጅነቱ አይለየን!

=>+*"+<+>††† ግንቦት 26 †††<+>+"*+

<<< በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን :: >>>
<+> ግንቦት 26 <+>
+*" አቡነ ሃብተ ማርያም ጻድቅ "*+
=>እኒህ ጻድቅ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው:: "ጽድቅና
ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው:: ባሕር ከሆነ
ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል::
+ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን
አባታቸው ፍሬ ቡሩክ : እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና
ትባላለች:: በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ : ምጽዋትን
ወዳጅ : ቡርክት ሴት ነበረች:: እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ
በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር::
+ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ
አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች:: ጻድቁን ወልዳ
አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ
ዐርፋለች::
+ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና
ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ
መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ:: ይሕችን ጸሎት በሕጻን
አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?"
እያሉ ይሰግዱ ነበር::
+የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት
ይደንቃል:: ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም
ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ:: ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው
ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:: የፈጣሪውን ስም ያቃለውን አንድ
እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል::
+ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው :
መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል:: በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ
ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን
የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም::
*ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ::
*በየቀኑ 4ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ::
(መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው)
*በ40 ቀናት : ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ::
*ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው::
*በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ:: (ካህን ናቸውና)
*ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ : ክቡር ደሙን
ይጠጣሉ::
*በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን : መከፋትን አላሳደሩም::
+በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ
የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ
ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር:: ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም
የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን
አስከተትሎ መጥቶ አላቸው::
"1.ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ:
2.ስለ ምናኔሕ:
3.ስለ ተባረከ ምንኩስናህ:
4.ስለ ንጹሕ ድንግልናህ:
5.ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ:
6.ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ:
7.ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን
እሰጥሃለሁ::"
+"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን : 500 የእንቁ
ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ :
በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ!
በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው::
+ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ
አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ
ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ
ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: በዝማሬም ወሰዷት:: {ይህች ቀን
(ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት::}
=>አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን:
ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን::
=>+"+ እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+ (መዝ. 36:28-31)
<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>

=>+*"+<+>††† ሎሚ 26 ግንቦት እዩ †††<+>+"*+

በሰምኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሃዱ ኣምላክ ኣሜን።
††† ሎሚ 26 ግንቦት እዩ †††
††† #ዓመታዊ_በዓለ_ዕረፍት_ሓ ዋርያ_ቅዱስ #ቶማስ †††
ቶማስ ማለት ጸሓይ ማለት እዩ።ቀዳማይ ስሙ ደዲሞስ እዩ
(ማቴ 10፡30፣ ዮሓ 20፡24 ፣ግብ ሓዋ 1፡13)። ጎይታ ክብ
ምውታት ተፈሊዩ ምስ ተንሰአ ኣብ መበል ሻሙናይ መዓልቱ
ሰንበት መዓልቲ ጎድኒ ጎይታ ዳህሲሱ መለኮት ምስ ኣቃጸሎ
"ጎይታይን ኣምላኸይን "ኢሉ ትንሳኤኡ ኣመነ። ዕርገት ናይ
ኣዴና ቅድስት ድንግል ማርያም ዝርኣየ ድማ ሓዋሪያ ቶማስ
እዩ።ሃገረ ስብከቱ ሕንድኬ (ህንዲ) እዩ። ንሱ ብ 30 ቅርሺ
ተሸይጡ ምስ ናይቲ ሃገር ሃብታም ክልኩዮስ የገልግል ነበረ።
እቲ ሃብታም ካኣ "እንታይ ክትሰርሕ ትክእል ፧"ኢሊ ሓተቶ።
ሓዋሪያ ቶማስ ድማ "ህንጻ ምስራሕ ሓወልቲ ምቅራጽ
ይክእል"በሎ። በዚ ተሰማሚዖም ብዙሕ ገንዘብን ወርቕን
ሃቦ።ኣህዛብ ምኩሓት ስለ ዝኾኑ ካኣ "ጥበብ ዘለዎ ሰብ ረኺበ
"ክብል ናብ ንጉስ ከደ። ቶማስ ድማ ነቲ ገንዘብ ወርቅን
ንድካታትን ነደያትን ሂቡ፣ምሂሩ ኣእመኖም ፣ሰበይቲ ልኩዮስ
፣ምስ ደቃን ኣገልገልታን ኣሚና ተጠምቀት።ልኩዮስ ካብ
መገሽኡ ምስ ተመልሰ "ዝሃነጽካዮ ህንጻ፣ዝቀረጽካዮ ሓወልቲ
ዳኣ ኣበይ ኣሎ፧ ኢሉ ሓተቶ። ሓዋርያ ቶማስ ድማ
"ብገንዘብካን ወርቅካን ዘስራሕካዮም ህንጻታት እዚኦም
እዮም " ኢሉ ነቶም ዝኣመኑ ህዝቢ ኣርኣዮ።ልኪዮስ ድማ
"ተጻዊትለይ "ብምባል ኢዱን እግሩን ኣሲሩ ቆርቦቱ ተቀሊጡ
ክሳዕ ዝግፈፍ ገረፎ።ሑጻ ኣሰኪሙ ውን ካብ ቦታ ናብ ቦታ ኮለል
ከም ዝብል ገበሮ። ሰበይቱ ኣርሰንዋ ነዚ ርእያ ሰንቢዳ ወደቀት
ብኡ ብኡ ድማ ሞተት ። ልክዮስ ካኣ "ሰበይተት ዝሞተት
ብሰንክኽኻ እዩ፣ ስለዚ እንተድኣ ኣሕዊኻያ ኣነ ውን ብኣምላኽካ
ክኣምን እየ በሎ።ጎይታ ንቑስሊ ሓዋርያ ቶማስ ከም ማይ
ኣዝሓሎ። ቅዱስ ቶማስ ካኣ በቲ ዝተገፈ ቆርበቱ ነታ ዝሞተት
ሰበይቲ ተንከያ እሞ ንሳ ካኣ ተንሰአት። ሽዑ ልኪዮስ ብጎይታ
ኣሚኑ ተጠመቐ። ብድሕርዚ ንቆርበቱ ተሰኪሙ ካብ ቦታ ናብ
ቦታ እንዳ ተዘዋውወረ ሕሙማት ፈወሰ፣ሙዉታት
ኣተንስአ፣ንኣህዛብ ኣእሚኑ ከም ዝጥመቑ ገበረ።ሓደ ግዜ
ቀንጣፍያ ትብሃል ዓዲ ምስ በጽሐ ሓደ ሰብኣይ ሸውዓተ ደቁ
ተቀቲሎም ሓዚኑ ረኾቦ እሞ ብቆርበቱ ነቶም ደቂ እቲ ሰብኣይ
ተንኪፉ ኣተስኦም። ኣብ ኢናስም ዝተባህለ ዓዲ ውን ትምህርቱ
ሰሚዖም ተኣምሩ ርእዮም ካብ ንጉስ ክሳብ ገባር ኣሚኖም
ተጠመቁ።ዘራጊ ከሎ ጽሩይ ማይ ዘይስተ ግን ካህናተ ጥዖት
ህዝቢ ብጎይታ እናኣመነ ኽገድፎም ስለ ዝጀመረ ጥቅሞም ስለ
ዝጎደሎም ምስ ንጉስን መኻንንትን ኣባኣስዎ እሞ በዚ ዕለት
ብሰይፈ ሰማዕትነት ተቀበለ ግዚኡ ብ 72 ዓ/ም እዩ።
በረከቱ ጸሎቱ ናይ ሓዋርያ ቅዱስ ቶማስ ምስ ኩሉና ህዝበ
ክርስቲያን ይኩን ።
ኣሜን ኣሜን ኣሜን
ስብሓት ለእግዝኣብሄር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ይኩን!!!
ኣማኑኤል-ኣርኣያ
ምንጪ ምጽሓፍ መዝገበ ታሪኽ

Thursday, June 2, 2016

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: =>+*"+<+>ግንቦት 25<+>+"*+

ግንቦት 25-
እመቤታችንን በስደቷ ጊዜ አብራት ተሰዳ ድካሟን
የተካፈለቻትና ልጇን መድኃኔዓለምን በጀርባዋ አዝላ ገላውንም
አጥባ ትንከባከበው የነበረችው ቅድስት ሰሎሜ ዕረፍቷ ነው፡፡
+ በዚኽችም ዕለት ጌታችን የደረቁ በትሮችን ያለመለመበት
ዕለት ነው፡፡ ይኸውም የአረገዊ ዮሴፍን በትሮች በአረንጓዴ ቦታ
ላይ ቢተክላቸው ወዲያው ዛፎች ሆኑ፡፡
+ ከበሬዎች ጋር ተጠምደው ሰማዕትነትን የተቀበሉት አቡነ
ሕፃን ሞዐ በዓለ ፅንሰታቸው ነው፡፡
+ ከእንዴና አገር የተገኘው የከበረ ቅዱስ ኮጦሎስ በሰማዕትነት
ዐረፈ፡፡
+ ስብስጣ ከሚባል አገር የተገኘው የከበረ አባ ኄሮዳ
በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡
ቅድስት ሰሎሜ፡- ይኽችም ቅድስት የእመቤታችን የአክስት
ልጅ ናት፡፡ እርሷም የማጣት ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፣ የሚልኪ ልጅ፣
የካህን አሮን ልጅ ናት፡፡ ማጣትና ሄርሜላ ሶፍያ፣ ማርያምና
ሐና የሚባሉ ሴቶች ልጆችን ወልደዋል፡፡ ቅድስት ሐና ድንግል
ማርያምን ወለደች፣ ድንግል ማርያምም መድኃኔዓለም
ክርስቶስን ወለደች፡፡ ሶፍያ ኤልሳቤጥን ወለደች፣ ኤልሳቤጥም
መጥምቁ ዮሐንስን ወለደች፡፡ ማርያምም ሰሎሜን ወለደች፡፡
እመቤታችን ጌታችንን በወለደችው ጊዜ ቅድስት ሰሎሜ
የእመቤታችን አወላለድ እንደ ሌሎቹ ሴቶች ያለ አወላለድ
መስሏት ነበርና የእመቤታችንን ሆዷን ዳሰሰቻት፡፡ በዚህም
ጊዜ እጇ ተኮማትሮ ተቃጠለ፡፡ ሕፃኑን በዳሠሠችው ጊዜ ግን
እጇ ዳነችላት፡፡ በዚህም እመቤታችን አምላክን እንደወለደች
ዐወቀች፡፡ እመቤታችንን በስደቷ ጊዜ አብራት ተሰዳ ድካሟን
ተካፍላታለች፡፡ ጌታችንንም በጀርባዋ አዝላ፣ በክንዶቿ
ታቅፋዋለች፡፡ ገላውንም የምታጥብበትም ጊዜ ነበር፡፡ ጌታችን
ሰው በሆነበት ወራት ሁሉ ከእርሱ አልተለየችም፡፡
በመከራውም ጊዜ እያለቀሰች ተከትላዋለች፡፡ ከሙታን ተለይቶ
በተነሣም ጊዜ ወደ መቃብሩ ገስግሳ ትንሣኤውን ከሐዋርያት
ቀድማ ያየች ናት፡፡ በ50ኛም ቀን መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ
ከሌሎቹ ሴቶች ጋር ሆና ሰማያዊ ሀብትን ከተቀበለች በኋላ
ቅድስት ሰሎሜ በጌታችንም ስም ወንጌልን አስተራለች፡፡
ብዙዎችንም አሳምና ያስጠመቀች ድንቅ እናት ናት፡፡
ከአይሁድም የሚደርስባት መከራ በጸጋ ተቀብላ ግንቦት 25
ቀን ዐርፋለች፡፡ የቅድስት ሰሎሜ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣
በጸሎቷ ይማረን፡፡
+ + + + + + + + + + + + + + +
ሰማዕቱ ቅዱስ ኮጦሎስ፡- የዚኽም ቅዱስ ወላጆቹ
እግዚአብሔርን የሚፉ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸውና ጌታችንን
ልጅ እንዲሰጣቸው አጥብቀው ከለመኑትና እርሱም የተባረከ
ልጅ ከሰጣቸው በኋላ ልጃቸውን በሃይማኖት በምግባር
አሳደጉት፡፡ አባቱም የእንዴናው ገዥ መኮንን ነው፡፡
ቅዱስ ኮጦሎስም ለራሱ ሥርዓትን በመሥራት በቀን አንድ
መቶ በሌሊትም አንድ መቶ ጸሎታትን ይጸልያል፡፡ ዕድሜውም
በደረሰ ጊዜ ወላጆቹ ሊያጋቡት ሲሹ እርሱ ግን እምቢ አላቸው፡፡
ነገር ግን ወላጆቹ ታናሽ እኅቱ የሆነችውን ሴት ልጃቸውን
ከአርያኖስ ጋር አጋቧት፡፡ አባቱም ከሞት በኋላ ቅዱስ ኮጦሎስ
የስደተኞችና መጻተኞች መቀበያ ቤት ሠርቶ እንግዳን ሁሉ
የሚቀበል ሆነ፡፡ ከዚኽም በኋላ የጥበብ መጻሕፍትን ተምሮ
ሐኪም ሆነ፡፡ ሕሙማንም ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ ያለምንም
ዋጋ የሚፈውሳቸው ሆነ፡፡
ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስም ጌታችንን በካደ ጊዜ አርያኖስ
ስለሹመቱ ከንጉሡ ጋር ተስማምቶ ሰማዕታትን የሚያሠቃይ
ሆነ፡፡ በዚኽም ጊዜ ቅዱስ ኮጦሎስ ሰማዕት ይሆን ዘንድ
ተመኝቶ ወደ ሰማዕትነት አደባባይ ወጥቶ አርያኖስን፣ ንጉሡን
ዲዮቅልጥያኖስንና አለቆቹን ሁሉ ስለ ጣዖት አልኮአቸው
ሰደባቸው፣ ጣዖታቱንም ሰደበ፡፡ አርያኖስም ስለ እኅቱ ብሎ
በቅዱስ ኮጦሎስን ከእሥር ፈታው፡፡ ከአርያኖስም በኋላ ሌላ
መኮንን በተሾመ ጊዜ የቅዱስ ኮጦሎስን ዜና እና ገድል ነገሩት፡፡
ጭፍራ ልኮ ወደ እርሱ ካስመጣው በኋላ ለአማልክት
እንዲሰግድ አስገደደው፡፡ ቅዱስ ኮጦሎስም ‹‹ከዕውነተኛው
አምላክ ከክርስቶስ በቀር የሚገዙለት አምላክ የለም፣ ለእርሱ
ብቻ እሰግዳለሁ›› አለው፡፡ በዚኽም ጊዜ መኮንኑ ተቆጥቶ ልዩ
ልዩ በኾኑ ሥቃዮች አሠቃየው፡፡ ነገር ግን የታዘዘ መልአክ
እየመጣ ቅዱስ ኮጦሎስን ከቁስሉ ሁሉ ይፈውሰውና ያጽናናው
ነበር፡፡ ጌታችንም በዚኽ ቅዱስ እጆች ብዙ ድንቅ ድንቅ
ተአምራትን አደረገ፡፡
መኮንኑም ቅዱስ ኮጦሎስን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ አንገቱን
በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ፡፡ እንደትእዛዙም ሰየፉትና
የሰማዕትነት ፍጻሜው ሆነ፡፡ ከሥጋውም ብዙ ተአምራት
ተገልጠው ታዩ፡፡ የሰማዕቱ የቅዱስ ኮጦሎስ ረድኤት በረከቱ
ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + + + + + + + + + + + + + +
ሰማዕቱ አባ ኄሮዳ፡- ይኽም ቅዱስ አባ ኄሮዳ ከሕጻንነቱ
ጀምሮ በፈሪሃ እግዚአብሔር ያደገ ነው፡፡ በዘመኑም ከሃዲው
ንጉጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ነግሦ ነበርና አባ ኄሮዳ አንድ ቀን
ተኝቶ ሳለ ስለዚኽች ከንቱ አላፊ ዓለም አሰበ፡፡ ጌታችን ‹‹ይኽን
ዓለም ያልካደ ሊያገለግለኝ አይችልም›› ያለውን አስታውሶ
በስሙ ሰማዕት ይኾን ዘንድ ወደደ፡፡ ይኽንንም በልቡ ሲያስብ
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ወደ እርሱ መጥቶ ‹‹የከበርክና
የተመሰገንክ ኄሮዳ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፡፡ እግዚአብሔር
የክብር ዙፋን አዘጋጅቶልሃልና እኔም የመላእክት አለቃ
ሚካኤል ወደ ፍርድ አደባባይ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፣
ከመከራውም አጸናሃለሁና ሰማዕትነትህን በድል ትፈጽማለህ››
ብሎት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡
ከዚኽም በኋላ ቅዱስ አባ ኄሮዳ ወደ ምዕራባዊ ክፍል ወጥቶ
ከጸለየ በኋላ ወደ ፍርድ አደባባይም ሄዶ ‹‹እኔ የክብርን ባለቤት
ክርስቶስን የማመልክ ክርስቲያን ነኝ›› ብሎ በግልጥ ጮኸ፡፡
ከሃዲው መኮንን ሉክያኖስም ይዞ የመጣበትን ጠየቀው፡፡ አባ
ኄሮዳ ከብሕንሳ አውራጃ ስብስጣ ከምትባል አገር እንደሆነና
አስቀድሞም የምድራዊ ንጉሥ ባለሟል እንሆነ ነገረው፡፡
መኮንኑም ‹‹ለአማልክት ሠዋና ብዙ ገንዘብ ሰጥቼህ
ከጭፍሮቼ ሁሉ የበላይ አድርጌ ልሹምህ›› አለው፡፡ አባ ኄሮዳ
ግን ስለ አምኮተ ጣዖቱ ሉክያኖስን ገሠጸው፣ ጣዖታቱንም
ረገመበት፡፡ መኮንኑም እጅግ ተቆጥቶ እሾህ ባላቸው የብረት
ዘንጎች በጽኑ አስደበደበው፣ ከሥቃዩም የተነሣ የቅዱሱ ደሙ
እንደውኃ ፈሰሰ፡፡ ጌታችንም መልአኩን ልኮ ፈወሰውና ፍጹም
ጤነኛ አደረገው፡፡ ዳግመኛም ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮችም
አሠቃየው፡፡ ይኽንንም ተአምር ያዩ ሰዎች ‹‹በአባ ኄሮዳ
አምላክ በክርስቶስ አምነናል›› ብለው እየመሰከሩ ሰማዕትነትን
ተቀበሉ፡፡ ቁጥራቸውም ሠላሳ ሺህ አምስት መቶ ሆነ፡፡
መኮንኑም አባ ኄሮዳን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ራሱን በሰይፍ
እንዲቆርጡት አዘዘ፡፡ በዚኽም ጊዜ ጌታችን ለአባ ኄሮዳ
ተገለጠለትና ‹‹በችግርና በመከራ ውስጥ ያለ ሰው ቢኖር
በስምህ ቢማጸን ፈጥኖ ከችግሩና ከመከራው ይድናል›› የሚልና
ሌላም ብዙ ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገባለት፡፡ ከዚኽም
በኋላ አባ ኄሮዳ ወደ ሕዝቡና ወደ ሰያፊዎቹ ተመልሶ ካረፈ
በኋላ ስለ ሥጋው ነገራቸው፡፡ በታላቅ ደስታም ተመልቶ
ለሰያፊዎቹ ‹‹የታዘዛችሁትን ፈጽሙ›› ብሎ አንገቱን አውጥቶ
ሰጣቸው፡፡ በዚኽችም ዕለት ሰማዕትነቱን በድል ፈጽሞ
አስቀድሞ ጌታችን ቃል የገባለትን የድል አክሊል ተቀዳጀ፡፡ ከ3
ወርም በኋላ ቅዱስ ሥጋውን ወደ አገሩ ወስደው ያማረች ቤተ
ክርስቲያን ሠርተው በውስጧ አኖሩት፡፡ ከሥጋውም ብዙ
ተአምራት ተገልጠው ታዩ፡፡ ለሕሙማንም ፈውስ ሆነ፡፡ የአባ
ኄሮዳ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + + + + + + + + + + + + + +
አቡነ ሕፃን ሞዐ፡- በአባታቸው አርከሌድስ እናታቸው ትቤ ጽዮን
ይባላሉ፡፡ የተወለዱት ጥር 25 ነው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ እና ከእነ
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር የሥጋ ዝምድና አላቸው፡፡ ይኸውም
አባታቸው አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ወንድማማቾቸ ናቸው፡፡
አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ሌሎች ሌሎች 4 ወንድሞች አሏቸው፡፡
እነርሱም እንድርያስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ቀሲስ ዮናስ እና ቀሲስ
ዮሐንስ ናቸው፡፡ አርከሌድስ ሕፃን ሞዐን ይወልዳል፣ ጸጋ ዘአብ
ተክለ ሃይማኖትን ይወልዳል፣ እንድርያስ ሳሙኤል ዘወገግን፣
ዘርዐ አብርሃም ታላቁ አኖሬዎዮስን፣ ቀሲስ ዮናስ
ገላውዲዮስንና የፈጠጋሩን ማትያስን፣ እና ቀሲስ ዮሐንስ
ዜናማርቆስን ይወልዳሉ፡፡ እነዚህ የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን
በእናታቸውም ወገን ቢሆን እንዲሁ በዝምድና የተቆራኙ
ናቸው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ በሌላኛው ስማቸው ሕፃን ዘደብረ
በግዕ ተብለውም ይጠራሉ፡፡ ይኸውም የደብረ በግዕን ገዳም
የመሠረቱት እርሳቸው ስለሆኑ ነው፡፡ ከ47ቱ የሀገራችን
ቀደምት ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ በመንዝና በተጉለት
የሚገኙ ታላላቅ ገዳማትን አብዛኞቹን የመሠረቷቸው አቡነ
ሕፃን ሞዐ ናቸው፡፡ ጻድቁ በክፉዎች ወሬና ሴራ ምክንያት ከበሬ
ጋር ተጠምደው ሰማዕትነት የተቀበሉ አባት ናቸው፡፡ ከበሬ ጋር
ሲታረሱ ውለው በእጅጉ ከደከማቸው በኋላ በኃይል የተነፈሱባት
ምድሪቱ ዛሬም ድረስ ልክ እንደሰው የሚሞቅ ትንፋሽ
ታወጣለች፡፡ ያም በጻድቁ እስትንፋስ አምሳል ከመሬት ውስጥ
የሚወጣው እስትንፋስ ለአስም በሽታ መድኃኒት ሆኖ ብዙዎችን
እየፈወ ነው፡፡ ገዳማቸው ከደብረ ብርሃን ከተማ በእግር የ2
ሰዓት መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ይኸውም ከወንይዬ ተክለ
ሃይማኖት ገዳም አጠገብ ነው፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣
በጸሎታቸው ይማረን፡፡

Tuesday, May 31, 2016

=>+*"+<+>ግንቦት 24<+>+"*+

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
አሜን
ግንቦት 24-ጌታችን ከቅድስት ድንግል እናቱ፣ ከአረጋዊ ዮሴፍና
ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብፅ የተሰደደበት ዕለት ነው፡፡
+ በዚህችም ዕለት ጌታችን በአረጋዊ ዮሴፍ በትር ብዙ አስደናቂ
ተአምራትን አድርጓል፡፡ ዳግመኛም እመቤታችንና የተወደደ
ልጇን መድኃኔዓለምን በእጆቹ ሥራ ይመግባቸው የነበረና
እነርሱንም ከሄሮድስ ለማዳን ብዙ ሰማዕትንት የተቀበለ
ጻድቁና የ83 ዓመቱ አረጋዊ ዮሴፍ ግብፅ የገባበትና ቅዳሴ ቤቱ
የከበረበት ዕለት ነው፡፡
+ ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ የሆነው ነቢዩ ቅዱስ ዕንባቆም
ዕረፍቱ ነው፡፡ ቅዳሴ ቤቱም በዚኹ ዕለት ነው፡፡
+ የአሮን ልጅ አልዓዛር ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ከእንጽና አገር የተገኘው የከበረ አባት ቀሲስ አብቁልታ
በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡
የእመቤታችንና የልጇ የመድኃኔዓለም ስደት-ከገድለ አረጋዊ
ዮሴፍ ላይ የተገኘ፡- የእመቤታችን ስደት የመጀመሪያው የአዲስ
ኪዳን ስደት ነው፡፡ ከገነት የተሰደደውን አዳምን ወደ ቀደመ
ክብሩና መንበሩ ከዚያም ወደ ሚበልጥ ክብር ለመመለስ
የተወለደው ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገና
ከሕፃንንቱ ጀምሮ ስደትንና መከራን ተቀብሏል፡፡ ወላዲተ
አምላክ ቅድስት እናቱ እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች፣ ለእኛ
የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተርባለች፣ የሕይወትን ውሃ
ተሸክማ እርሷ ተጠምታለች፣ የሕይወት ልብስን ተሸክማ ሳለ
እርሷ ተራቁታለች፣ የሕይወት ሀሴት ደስታ ተሸክማ እርሷ
አዝናለች፡፡ እመ አምላክ ስለ ልጇ ብላ ተርባ፣ ተጠምታ፣
ታርዛለች፤ ደክማና አዝና አልቅሳለች፡፡ እግሯ ደምቷል፣ እሾህ
ወግቷት አንቁረው አውጥተውላታል፡፡ እርሷም ይህንን ሁሉ
መከራ የተቀበለችው ልጃን ለማዳንና ለእኛ ለዘላለማዊው
ድኅነት ነውና አባቶች እንዲህ ብለው አመስግነዋታል፡- «ድንግል
ሆይ ርጉም በሆነ ሄሮድስ ዘመን ከልጅሽ ጋር ከሀገር ሀገር
ስትሸሺ ከአንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ ፤ ድንግል ሆይ ከዓይንሸ
የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውንመሪር እንባ
አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ረሀቡንና ጥሙን፣ ችግሩንና ኀዘኑን፣
ከእርሱ ጋር የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ›› ቅዳሴ
ማርያም፡፡
የእመቤታችንን የስደቷን ጥንተ ነገር ስናየው እመቤታችን
በቤተ መቅደስ ሳለች ከአባቷ የሚመጣላትን የትረፈረፈ ሀብት
ለድኆችና ጦም አዳሪዎች ትመጸውት ነበር፡፡ 7 ዓመት በሆናት
ጊዜ ግን ወላጆቿ ዐረፉና እነርሱ የተውላትን ወርቅና ብዙ
ገንዘብ እግዚአብሔርና ለጦም አዳሪዎች ሰጠች እንጂ ምንም
አልወሰደችም፡፡ ካህናቱ እንደ በባሕላቸው መሠረት በቤተ
መቅደስ በብፅዓት ያደገን ሰው (ሴትም ይሁን ወንድ) ለአካለ
መጠን ሲደርስ በቤተ መቅደስ እያገለገለ እንዲኖር ወይም
ከካህናቱ ወገን መርጦ እንዲያገባና ሀብት ሰጥተው እንዲሸኙት
ሁለት ምርጫ ይሰጡታል፡፡ እመቤታችንም 12 ዓመት በሆናት
ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስይህንኑ ምርጫ ሲያቀርብላት
እመቤታችንም በልቧ የሰው ልጅ ሀሳብ የላትምና ‹‹እኔስ
በእግዚአብሔር ቤት እያገለገልኩ መኖርን እመርጣለሁ››
አለችው፡፡ ካህናቱም ‹‹ስለእርሷ ወደ ቤተ መቅደስ ገብተህ
እግዚአብሔር የሚነግርህን በጸሎት ጠይቅ›› አሉትና እርሱም
የክህነት ልብሱን ለብሶ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ገብቶ በጸሎት
ሲጠይቅ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮለት ሚስቶች
የሌሏቸውን የዳዊት ወገን የሆኑ ወንዶችን ሰብስቦ በበትራቸው
ላይ ስማቸውን ጽፎ ወደ ቅድስተቅዱሳኑ እንዲያገባው ነገረው፡፡
ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስም በአዋጅ አስነግሮ 1985 ብሮችን
ሰብስቦ ሲጸልይባቸው ቢያደር በአረጋዊ ዮሴፍ በትር ላይ
ምልክት ታየ፡፡ በትሩንም ሲሰጠው ነጭ ርግብ መጥታ በዮሴፍ
ላይ አረፈች፡፡ እርሱም ድንግልን እንዲወስዳት ሲነገረው
አለቀሰ፡፡‹‹ይቅር በሉኝ እኔ ሽማግሌ ነኝና ልጆችም አሉኝ፤
ዕድሜዬም 83 ዓመት ነውና›› እያለ አለቀሰ፡፡ ዘካርያስም
‹‹ይህ ሥራ ከእኛ ዘንድ አይደለም፣ እግዚአብሔር አዞናል
እንጂ፡፡ እነሆ እርሷን ትጠብቃት ዘንድ ሰጥቶሃልና
የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እምቢ አትበል፤ ትእዛዙን አንቀበልም
ያሉትን ፈጣሪህ እግዚአብሔር እንዴት እንዳደረጋቸው አስብ…››
እያለ አጽናናው፡፡ አገራዊ ዮሴፍም እየፈራ ድንግል ማርያምን
ወደቤቱ ወሰዳት፡፡ እቤቱወስዶም ልጆቹና ቤተሰቦቹ ይጠብቋት
ዘንድ አደራ ሰጥቷቸው ወደ ንግድ ሄደ፡፡ እመቤታችንም ወደ
ዮሴፍ ቤት በገባች ጊዜ ልጆቹ እናታቸውበልጅነታቸው
ሞታባቸዋልችና የሙት ልጆች ሆነው አገኘቻቸው፡፡ ዮሴፍ
አስቀድሞ ማርያም የምትባል ሚስት አግብቶ ነበር፡፡
ከእርሷም 3 ሴቶችና 4 ወንዶች ልጆች ነበሩት፡፡ እነርም
ስምዖን፣ ያዕቆብ፣ ይሁዳና ዮሳ ናቸው፡፡ ማቴዎስና ማርቆስም
ይህንን በወንጌላቸው ጽፈውታል፡፡
እመቤታችንም በመልአኩ ብስራት ጌታችንን ስትፀንስ ያንጊዜ
ዕድሜዋ 14 ዓመት ከ11 ወር ነበር፡፡ አረጋዊ ዮሴፍም ከ3
ወር በኋላ ሥራውን ጨርሶ ወደ ቤት ሲመለስ ደንግልን ፀንሳ
አገኛትና እጅግ ደነገጠ፡፡ በራሱም ላይ ትቢያን ነስንሶ በምድር
ላይ ወደቆ መራራ ልቅሶን አለቀሰ፡፡ ‹‹ማርያም ሆይ ካህናቱ
ስለ አንቺ ቢመረምሩኝ ምን እመልሳለሁ? በፈጣሪዬ
በእግዚአብሔር ፊትስ እንዴት እቆማለሁ? ከሚያገኘኝ ስድብም
የተነሣ ወዮልኝ፡፡ የእስራኤል ልጅ ሆይ ከማን ፀንስሽ?
ክብርሽንስ የደፈረ ማን ነው?...›› እያለ ጠየቃት፡፡ ድንግልም
‹‹እኔ ንጹሕ እንደሆንኩ እግዚአብሔር ያውቃል፤ ይህን
ያደረገው እግዚአብሔር ነው…›› እያለች ሁኔታውን በደንብ
አስረዳችው፡፡ እርሱም የሚያደርገው ግራ ገብቶት ሳለ
ይገልጥለት ዘንድ በልቅሶ ወደ እግዚአብሔር አመለከተ፡፡
እመቤታችንም ‹‹ጌታዬ ሆይ ይህን ምሥጢር ለአገልጋይህ
ለዮሴፍ ግለጥለት…›› ብላ ጸለየች፡፡ ወዲያውም እግዚአብሔር
ልአኩን ልኮ ለዮሴፍ በሕልም ተነጋገረው፡፡ በማኅፃኗ ያለው
በግብረ መንፈስ ቅዱስ ነውና አትፍራ… ሕዝቡንም ሁሉ
ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል…›› እያለ አስረዳው፡፡ ከእንቅልፉም
ነቅቶ እጅግ ደንግጦ ወደ እመቤታችን ቢሄድ ስትጸልይ አገኛትና
ሰገደላት፡፡ ከዚህም በኋላ በናዝሬት ከሚኖሩ ከካህናት ወገን
የሆነ አንድ ካህን አረጋዊ ዮሴፍን ሰላምታ ይሰጠው ዘንድ ወደ
ቤቱ መጥቶ ‹‹ምነው ወደ ቤተ መቅደስ አልመጣህም?››
ቢለው ዮሴፍም ‹‹ከመንገድ የመጣሁት ገና ትናንት ነውና አረፍ
ልበል ብዬ ነው›› አለው፡፡ እንዲህ ሲጨዋወቱ ያም ካህን ወደ
ንጽሕት ደንግል አይኖቹን አንሥቶ ተመለከተና እንደፀነሰች
ዐወቀ፡፡ ወዲያው ሮጦ በፍጥነት ወደ ካህናቱ በመሄድ ‹‹ስለ
እርሱ ምስክር የሆናችሁለት ዮሴፍ እነሆ በደለ፣ ኃጢአትንም
ሠራ፣ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የወሰዳትን፣ እናንተም
ጠባቂዋ ያደረጋችሁት ድንግል ማርያምን ዐወቃት ፀነሰችም››
ብሎ ነገራቸው፡፡
እነርሱም ወደ ዮሴፍ መልእክተኞች ልከው ‹‹ማርያም ይዘሃት
ና›› ብለው ላኩበት፡፡ የሴፍም አምጥቷት ሁሉም ቢመለከቷት
ፀንሳች፡፡ ወደ ካህናቱም ሁሉ መልአክተኞችን ልከው ሁሉም
ካህናት ተሰበሰቡና ዮሴፍንና ድንግል ማርያምን በአደባባይ
አቆሟቸው፡፡ እመቤታችንንም ‹‹በእስራኤል ደናግል ላይ
ለምን ስድብን አደረግሽ?›› እያሉ ወቀሷት፡፡ በሙሴም ሕግ
መሠረት ሆድን የሚሰነጥቅ ማየ ዘለፋ አጠጧትና
የሚያደርጋትን ለማየት ተሰበሰቡ፡፡ ነገር ግን ማየ ዘለፋው
እንኳንስ በእርሷ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይቅርና ፊቷን እንደ
ሚያዝያ ጨረቃ አደመቀው፡፡ የመንፈስ ቅዱስን ሥራ
የማያምኑትን ብዙዎችን ግን አቃጠላቸው፡፡ እነርሱም
የድንግልን ንጽሕናዋን ባዩ ጊዜ እጅግ ተደነቁ፡፡ ዮሴፍንና
እመቤታችንንም ‹‹እግዚአብሔር ካልፈረደባችሁ እኛ
አንፈርድባችሁ በሰላም ወደ ቤታችሁ ሂዱ›› ብለው
አሰናበቷቸው፡፡
በአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ መሠረት ሄሮድስ በሀገረ ይሁዳ
ሰው ሁሉ በየወገኑ፣ በየሀገሩ፣ በየአባቱ ይቆጠር ዘንድ አዘዘ፡፡
አይሁድም ለመቆጠር ብቻ ሳይሆን ሄሮድስን አይወዱትም
ነበርና ከቄሣር ጋር ያጣሉት ዘንድ ተሰበሰቡ፡፡ እመቤታችንም
የመውለጃዋ ወቅት ደርሶ ነበርና አረጋዊ ዮሴፍ ወደ ቤተልሄም
ወስዳትና ከአንዲት የእረኞች ዋሻ ውስጥ ይዟት ገባና በዚያ
አደሩ፡፡ በዚያም ከብቶች የሚያድሩበት የፈረሰ ግንብ ነበረ፡፡
ይህም በኬብሮን ትይዩ ሲሆን አቀድሞ የእሴይ ቤት ነበርና
ዳዊት በዚህ ቤት ተወልዷል፣ በዚያም በሳሙኤል እጅ
የመንግሥት ቅባት ተቀብቶበታል፡፡ ቦታው በባቢሎን ስደት ጊዜ
ፈርሶ የፈረሰው ግንብ ከሩቅ ለሚመጡ ነጋዴዎች ማደሪያ ሆኖ
ነበር፡፡ በአጠገቡም ዋሻ ነበርና ጌታችን በታኅሣሥ ወር
በመንፈቀ ሌሊት ማክሰኞ ቀን በዚያ ዋሻ ተወለደ፡፡ ጌታችንም
በተወለደ ጊዜ ዋሻው በእጅጉ ስላበራ ዮሴፍ ደንግጦና
ተንቀጥቅጦ መሬት ላይ ወደቀ፡፡ እመቤታችንም ስትወልድ
እንደሴቶች ሁሉ ልማድ ሕማም አላገኛትም፡፡ መልአኩም
ለእረኞቹ አብስሯቸው ወደ ዋሻው ሄደው የተወለደውን ሕፃን
ከእናቱና ከዮሴፍ ጋር አገኙት፡፡ ከእረኞቹም አንዱ
የቤተልሔሙና በኋላም በይሁዳ ተተካው ማትያስ ነበር፡፡
እረኞቹም የበግ ጠቦትና የላም ወተትን፣ ማርንና ቅቤን
አምጥተው እጅ መንሻ አቀረቡ፡፡ የሕፃኑንም መለኮታዊ እግር
ስመው ከሁሉም በፊት አስቀደመው ሰገዱለት፡፡
ለእመቤታችንና ከዮሴፍም ከሰገዱ በኋላ ተመልሰው ሄደው
በይሁዳ ሀገር ሁሉ ዜናውን ተናገሩ፡፡
ሰሎሜም እመቤታችን በድንግልና የበኩር ልጇን እንደወለደች
ስትሰማ መጀመሪያ ‹‹በዓይኖቼ ካላየሁ በእጆቼም ካልዳሰስኩ
አላምንም›› ብላ ወደ ዋሻው ሄደች፡፡ ወደ እመቤታችንም
ቀርባ ሰውነቷን ዳሰሰች፡፡ ወዲያውም መለኮታዊ እሳት
የወጣበትን ሰውነቷን ዳሥሣለችና እጆቿ ተቃጠሉ፤ ደረቁም፡፡
ወዲያውም በታላቅ ቃል እየጮኸችና እያለቀሰች ‹‹የአምላክ
እናት ሆይ ይቅር በይኝ የሃይማኖቴ ጉድለት ታላቅ መከራ
አመጣብኝ›› እያለች በእመቤታችን ፊት መሪር ልቅሶን
አለቀሰች፡፡ ድንግል ማርያምም ወደ ልጇ ማለደችላት፡፡
በዚህም ጊዜ መልአክ መጥቶ ሰሎሜን ‹‹እግዚአብሔር ይቅር
ብሎሻል፣ ወደ ሕፃኑ ሂጂና በተቃጠሉ እጆቺሽ ያዥውና ታቀፊው
ተድኛለሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም ትታቀፈው ዘንድ ሕፃኑን
ልጇን ሰጠቻት፡፡ ሰሎሜም ታቀፈችው ጊዜ እጇ ወዲያው
ዳነላትና የእመቤታችንን ደንግልናዋን አምና ሰገደችላት፡፡
ሰሎሜም ያየችውንና የሆነውን ሁሉ ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች
ሁሉ ለማውራት እጅግ ተቻኩላ ከዋሻው ወጥታ ስትሄድ ከሰማይ
ድምጽ መጣላትና ያየችውን ተአምር ሕፃኑ ወደ ቤተ መቅደስ
እስኪገባ ድረስ ለማንም እንዳትናገር አስጠነቀቃት፡፡ ጌታቸንም
እንደ አይሁድ ልማድ በ8ኛ ቀኑ ግዝረትን በግብረ መንፈስ
ቅዱስ ፈጽሞ በ40ኛውም ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዱት፡፡
ጌታችን ከመወለዱ ከ277 ዓመት በፊት በንጉሥ በጥሊሞስ
ትእዛዝ 72ቱ ሊቃውንት መጻሕፍቶቻቸውን ከዮናናውያን ቋንቋ
ወደ ጽርዕ ቋንቋ ሲተረጉሙ የ123 ዓመቱ ስምዖን አንዱ
ነበር፡፡ ትንቢተ ኢሳይያስን የተረጎመው እርሱ ነበርና ድንግል
ድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንደምትወልድ ይህንንም ሳያይ
እንዳይሞት እግዚአብሔር ቃል ገብቶለት ነበር፡፡ ወደ
መቅደስም ሲመጣ መልአኩ ለስምዖን ተገልጦለት ሲጠብቀው
የኖረው ተስፋው ዕውን ሆኖ ዛሬ መሢሑን በክንዶቹ
እንደሚታቀፈው ነገረው፡፡ በቤተ መቅደስም ጌታችንን
አገኘውና ታቅፎ ‹‹ጌታ ሆይ ዓይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና
ባሪያህን ሰላም አሰናብተው›› አለው፡፡ ለእመቤታችንም
‹‹ጦርና ሰይፍ በልብሽ ውስጥ ይገባል›› ብሎ በልጇ ምክንያት
የሚደርስባትን መከራ በትንቢት ነገራት፡፡ ‹‹ጦርና ሰይፍ››
ያለውም የክርስቶስን መከራ ነው፡፡ በሕማሙና በመቸንከሩ
ልቧ መሪር በሆነ የኀዘን ጦር ተወግቷልና አንጀቷም በተሳለ
የሰይፍ ኀዘን ተነዋውቷልና፡፡ ልጇ የተቀበላቸው መከራዎችንም
እንደ እርሱ በልቡናዋ እመቤታችንም ተቀብላቸዋለችና
ስለዚህም የሰማዕታት እናት ትባላለች፡፡
ከሰብዓ ሰገል አንዱ ዘሮአስተር የሚባለው ስለ ኮከብ መውጣትና
ስለ ክርስቶስ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የጥበብ
ሰዎች መጻሕፍትን ተምረው በትንቢቱም ታምነው ይኖሩ
ነበር፡፡ ስለዚህም በየዓመቱ ሁሉም አንድ ቀን ከፍ ባለ ተራራ
ላይ ይሰበሰቡና ኮከቡን ይመለከቱታል፡፡ ክርስቶስም በተወለደ
ጊዜ አዲስ ኮከብ በሕፃን መልክ ታያቸው፡፡ በላዩም የመስቀል
ምልክት አለው፡፡ ‹‹የአሕዛብ ተስፋቸውና መስፍናቸው፣
የአይሁድ ንጉሣቸው ወደ ምድር ወረደ›› የሚል ቃልም ሰሙ፡፡
‹‹እጅ ለመንሳትና ለመስገድም ፈጥናችሁ ሂዱ›› አላቸው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የጥበብ ሰዎችን ቁጥር ባይገልጸውም
አውግስጦስና ዮሐንስ አፈወርቅ 12 ናቸው ብለዋል፡፡ በሦስት
የትውልድ ቅርን መስለው ሦስት ናቸው የሚሉም አሉ፡፡
ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተናገረው በ5 ወር ደርሰው ደብረ ዘይት
እግር ሥር ከተሙ፡፡ ተጉዘውም ኢየሩሳሌም ከተማ ገብተው
‹‹የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ የት ነው?›› ብለው ሲጠይቁ
ሄሮድስና መላዋ ኢየሩሳሌም ታወኩ፡፡ ሰብዓ ሰገልም በኮከቡ
ተመርተው ወደ ቤተልሔም ዋሻ ገብተው ሕፃኑን ከእናቱና
ከዮሴፍ ጋር አገኙትና ወድቀው ሰገዱለት፡፡ እጅ መንሻቸውን
አቀረቡለት፡፡ መልአኩም ከሄሮድስ እንዲሰወሩ ነግሯቸው በሌላ
መንገድ ተመለሱ፡፡ እመቤታችንና ዮሴፍም ሥርዓቱን ሁሉ
ፈጽመው ሲጨርሱ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡ የስምዖንም
ትንቢት ይፈጸም ዘንድ የሄሮድስ ቁጣ ነደደችና 2 ዓመትና ከዚያ
በታች ያሉ ሕፃናት ሁሉ ይገደሉ ዘንድ አዘዘ፡፡ የነቢዩ
ኤርሚያስም ትንቢት ተፈጸመችና 144 ሺህ ሕፃናትም ተገደሉ፤
መቃብራቸውም በራማ ሀገር በበለስ ዛፍ ሥር ነው፡፡
መልአኩም ለዮሴፍ ተገልጦለት ‹‹ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው
ይፈልገዋልና ተነሥ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ››
አለው፡፡ እርሱም ወዲያው በሌሊት ተነሥቶ ይዟቸው ሸሸ፡፡
ከናዝሬት ጀምረው የባሕሩን ዳርቻ ይዘው እስከ ፍልስጤም
ደረሱ፡፡ በ6ኛው ቀን ደክሟቸው አንድ ዋሻ ውስጥ ገቡ፡፡
እመቤታችንም በጸሎቷ ውኃን አመነጨችና ጠጡ፡፡ ያም
ምንጭ ስሙ የማርያም ውኃ ተብሎ እስከዛሬ አለ፡፡
በሌሎችም ቦታዎች እመቤታች ስትጸልይ ውኃ እየፈለቀ
በእርሱ ልጇን ገላውን ታጥበዋለች፡፡ ዐሥር ቀን ያህል በይሁዳ
ሀገር፣ ዐሥር ቀን ያህል በምድረ በዳ እጅግ አስቸጋሪ ጉዞ
ከተጓዙ በኋላ ግብፅ ደረሱ፡፡
ጌታችንም ምድረ ግብፅ በደረሰ ጊዜ በነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት
መሠረት የግብፅ ጣዖታት ከመሠረታቸው ተነዋውጠው ምድር
አፏን ከፍታ ዋጠቻቸው፡፡ በግብፅ ኤሌዎጶሊዎስ ሀገር ገብተው
ዮሴፍ ማረፊያ ሠራ፡፡ በዚያም ባለች ተራራ ሥር ጌታችን ውኃን
አፈለቀ፡፡ ይህችውም በእኛና በቅብጥ ሰዎች ዘንድ ሰኔ 8 ቀን
የምትታሰበው ዕለት ናት፡፡ ደም ማፍሰስ የለመደ ርጉም ሄሮድስ
ሚስቱን ማርያናንም ከገደላት በኋላ ይበቀሉኛል በማለት
ከእርሷ የወለዳቸውን የገዛ ልጆቹንም ገደላቸው፡፡ ከዚህም
በኋላ በሥጋው ጽኑ መከራ መጣበትና እግዚአብሔር የደዌውን
ዘመን አስረዘመበት፡፡ ቢበላ ቢበላ ይጠግብም
ይልቁንምረሀብና ጥም ይበዛበታል፣ አንጀቱም ተቋጠረ፣
ሰውነቱም ተልቶ ሰው ሁሉ አልቀርበው አለ፡፡ ማቆ ሲያበቃ
በመጨረሻም ክፉ አሟሟት ሞተ፡፡ የእግዚአብሔርም
መልአክ ዮሴፍን ሄሮድስ ስለሞተ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ
እስራኤል እንዲመለስ ነገረው፡፡ ተመልሰውም በፍልስጤም
አልፈው ድልማጥያ ወደምትባል አንዲት ገር ደርሰው በበረሃ
ውስጥ ተቀመጡ፡፡
እመቤታችንም ከነልጇ ረሃቡ ቢጠናባት ትዕማን ወደምትባል
አንዲት ከበርቴ ባለሀብት ቤት ሄዳ ቁራሽ እንጀራንና ለልጇም
ጥቂት ወተትን ለመነቻት፡፡ ያቺ ክፉ ሴት ግን ልብን በሀዘን
የሚሰብር ክፉ ንግግርን ተነጋረቻት፡፡ ጻድቅ ዮሴፍም
‹‹እንግዳን ካለ ይሰጡታል ከሌለ በሰላም ይሸኙታል እንጂ
ለምን ክፉ ንግግርን ትናገሪያታለሽ›› እያለ ሲነጋገሩ አሽከሯ
ኮቲባ የእመቤቷን ቁጣ ሰምታ መጥታ ጌታችንን ከመሬት ላይ
ጥላ እንደ ድንጋይ አንከባለለችው፡፡ እመቤታችንም ደንግጣ
እያለቀሰች ልታነሣው ስትል ዮሴፍ ‹‹ተይው አታንሽው ኀይሉን
ያሳይ›› አላት፡፡ ያንጊዜም ምድር አፏን ከፍታ ዋጠቻት፣ ገረዷ
ኮቲባም በለምጽ ተመታች፡፡ በቤታቸውም ውስጥ በሕይወት
የቀረ የለምና ቤተሰቦቿ ጦጣ ሆነው ከተራራ ወደ ተራራ ሸሹ፡፡
እመቤታች፣ ዮሴፍና ሰሎሜም በትዕማን ቤት 6 ወር
ከተቀመጡ በኋላ መልአኩ ተገልጦ ከዚያ እንዲወጡ አዘዛቸውና
ወጡ፡፡ አርዲስ ወደምትባል ሀገርም ደርሰው የሀገሪቱ ሰዎች
በሰላም ተቀብለው አስተናገዷቸው፡፡ እመቤታችንም ከሀገረ
ገዥው ሆድ ውስጥ በጸሎቷ እባብ ላወጣችለትና ከሕመሙ
ስላደ በጣም አከበሯቸው፡፡ ዕውሮችን፣ አንካሶችን፣
ለምፃሞችንና አጋንንት ያደሩባቸውን ሁሉ እያመጡላት የልጇን
እጆች ይዛ ከሩቅ እያማተበች ፈወሰቻቸው፡፡ ሄሮድስም
እንደሚያፈላልጋቸው መልአኩ ሲነግራቸው ከአንዱ ሀገር ወደ
ሌላው ሀገር እየተዘዋወሩ ታችኛው ግብፅ ንሂሳ ድረስ ደረሱ፡፡
እመቤታችንም በዚያ ያሉ ሕመምተኞችን ፈወሰችላቸው፡፡
ከዚህም በኋላ አሁንም መልአኩ ነግሯቸው ደመናም መጥታ
ነጥቃ ወሰደቻቸውና የ38ቱን ወራት መንገድ በአንድ ጊዜ
አደረሰቻቸው፡፡ በዚያም ትንሽ ከቆዩ በኋላ ወደ ቤጎር ቆላ
ደረሱ፡፡ በዚያም ግብፃውያን እንደ ሕጋቸው ለአማልክቶቻቸው
ላሞችን አርደው ሠውላቸው፡፡ በጎሽ፣ በአውራሪስ፣ በነጭ
ዝንጀሮ የሚመሰሉ አጋንንትም መጡ፡፡ እመቤታችንም ከሩቅ
ሆና ተመልክታቸው እነዚያን አጋንንት በጸሎቷ እንደጢስ
በተነቻቸው፡፡ ግብፃውያንም ፈርተው እየጮኹ ሸሹ፡፡ በዚያም
ወራት ‹‹ረዳት አማልክቶቻችንን ጠፉብን›› ብለው እያዘኑ ሳለ
ዮሴፍን ሲጸልይ አግኝተውት አስረው በምድር ላይ አስተኝተው
40 ግርፋት ገረፉት፡፡ እርሱም በዚህ ጊዜ ‹‹እመቤቴ ሆይ ስለ
አንቺና ስለ ልጅሽ ይህ መከራ አግኝቶኛልና እርጂኝ›› ብሎ
በኀይል ጮኸ፡፡ እመቤታችንም ድምጹን ስትሰማ የሄሮድስ
ጭፍሮች የመጡ መስሏት እጅግ ደነገጠች፡፡ ቅዱስ
ገብርኤልም ተገልጦ ካረጋጋት በኋላ ዮሴፍን በኀይል ይደበድቡ
የነበሩትን በእሳት ሰይፉ ጨረሳቸው፡፡ ዮሴፍንም በእጆቹ
ዳሰሰውና ፈወሰው፡፡ እመቤታችንም ዮሴፍን ባየችው ጊዜ
‹‹ይህ ሁሉ መከራ ያገኘህ በእኔና በልጄ ምክንያት ነው››
ብላውአንገት ለአንገት ተቀቅፈው ተላቀሱ፡፡ መልአኩም ‹‹ይሄ
ሀዘናችሁ በደስታችሁ ጊዜ ይረሳል…›› እያለ አረጋጋቸውና
ዐረገ፡፡
የሀገሩ ሰዎችም ይወጓቸው ዘንድ ወጡና ክፉ ውሾችን
ለቀቁባቸው፡፡ ነገር ግን ውሾቹ በሰው አንደበት እመቤታችንን
እያነገሯት ሰግደው የእግሯን ትቢያ ልሰው በመመለስ
ባለቤቶቻቸውን መልሰው መናከስ ጀመሩ፡፡ ብዙዎቹንም
ገደሏቸው፡፡ ዮሴፍም ‹‹እመቤቴ ሆይ በዚህ ሀገር ከምንኖርስ
በዱር በበረሀ ብንኖር ይሻለናል›› ብሏት ወደለሌላ ትርጓሜዋ
የሰላም ሀገር ወደሆነች ዲርዲስ ሀገር ደረሱ፡፡ ሰዎቹም
‹‹ይህችስ የነገሥታት ወገን ትመስላለች በላያችን ላይ
ትነግሥብናለች›› ብለው በክፉ ሲነሱባቸው በማግስቱ ደመና
ነጥቃ ወስዳ ኤልሳቤጥ በሞት ካረፈችበት በረሀ አደረሰቻቸው፡፡
ዮሐንስ በእናቱ በድን ላይ ሆኖ እያለቀሰ ሳለ ዮሴፍንና ሰሎሜን
ባያቸው ጊዜ ደነገጠ፡፡ ጌታችንም አረጋጋው፡፡ እመቤታችንም
ስለ ኤልሳቤጥ ሞት እጅግ መሪር የሆነ ልቅሶን ስታለቅስ ልጇ
ድንቅ ምሥጢርን ከነገራት በኋላ አረጋጋት፡፡ እመቤታችንም
‹‹እናቱ ሞታበታለችና በዚህም በረሀ ማንም የለመውና
ዮሐንስን ከእኛ ጋር እንውሰደው›› ስትለው ጌታችን ‹‹ዕድሉ
በዚህ በረሀ ነው›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ከዚህም በኋላ ደመና ነጥቃ
ወስዳ ወደ ጋዛ ምድር አደረሰቻቸውና በዚያ አተር የሚያበራዩ
ሰዎችን አግኝታ እመቤታችን ‹‹ለልጄ አተር ስጡኝ››
አለቻቸው፡፡ እነርሱም ክፉዎች ነበሩና ‹‹ይህ አተር ሳይሆን
ድንጋይ ነው›› አሏት፡፡ ሕፃኑ ልጇም ‹‹እናቴ ሆይ እንደቃላቸው
ይሁንላቸው ተያቸው›› አላት፡፡ ያንጊዜም አተሩ ድንጋይ ሆነ፣
ይህም እስከዛሬም ድረስ አለ፡፡ ከዚህም በኋላ እመቤታችን ወደ
ተወለደችበት ሀገር ወደ ሊባኖስ ተራራ ሄደው በዚያ ያሉ
ሰዎችም በሰላም ተቀበሏቸው፡፡ እመቤታችንም ብዙ
ተአምራት አደረገችላቸው፡፡ ገዥው ደማትያኖስም ሄሮድስን
ሊወጋው ጦሩን አዘጋጅቶ ሳለ ነገር ግን ፈቃደ እግዚአብሔር
ከለከለችው፡፡ መልአክም ተገልጦለት በእርሱ ምክንያት ብዙ
ሰማዕታት ይሰየፉ ዘንድ አላቸውና ጊዜው ገና መሆኑን
አስረድቶት ሄሮድስን በጦር እንዳይገድለው ከለከለው፡፡
ደማትያኖስም ኃይሉና ጦሩ እጅግ የበረታ ነበር፡፡ ቅዱስ ጊጋርም
በዚህ ወቅት ስለ እመቤታችንና ስለልጇ ሰማዕት ሆነ፡፡ ቅዱስ
ገብርኤልም ለእመቤታችን ተገልጦ ወደ ግብፅ እንድትሄድ
ነገራት፡፡ ዳግመኛም መልአኩ ለገዥው ለደማትያኖስ
ተገልጦለት ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ እንዲያሰናብታት ነገረው፡፡
እርሱም አስቀድሞ ‹‹በዙፋኔ ተቀመጪ እኔና ሚስቴ
አገልጋይሽ እንሁን እንጂ ከዚህስ አትሄጂም›› ብሎ ግድ ብሏት
ነበርና፡፡ ከዚህም በኋላ የአንድ ቀን መንገድ ሸኝቷት እንዲህ
አላት፡- ‹‹እመቤቴ ሆይ ሄሮድስ ቢፈልግሽ ወደኔ መልእክት
ላኪብኝ ፈጥኜ እመጣለሁ፡፡ የእስራኤል አምላክ ቢፈቅድልኝ
ከዛብሎን፣ ከንፍታሌምና ከሐሴቦን ጀምሮ ይሁዳንና
ኢየሩሳሌምን ሁሉ አጠፋቸዋለሁ፡፡ ሰውን ብቻ የምገድል
አይደለሁ ዛፎቻቸውን ቆመው እንዲታዩ አልፈቅድም፡፡
ሀገሪቱንም ፍርስራሽ አደርጋታለሁ›› አላት፡፡ ይህ
የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዳልሆነ አስረድታው መርቃ
አሰናበተችውና በበነጋታው ተለያዩ፡፡
ወደ ቤተልሔምም ከደረሱ በኋላ አሁንም መልአኩ አዘዛቸውና
በሌሊት ተነሥተው ወደ ግብፅ ተጓዙ፡፡ ሄሮድስም ሀገሪቱን
መጥቶ ከበባት፡፡ እነርሱንም ቢያጣ በዚያ ያገኘውን ሁሉ ሰየፈ፡፡
2 ዓመትና ከዚያ በታች ያሉ ሕፃናትን ሁሉ ሰብስበው
እንዲያመጡአቸው አዘዘና 144 ሺህ የቤተልሔም ሕፃናትን
ከእናቶቻቸው ላይ እየቀማ ሰየፋቸው፡፡ መላእክትም እጅግ
ደንግጠው ይህ ለምን እንዲሆን ፈቀድክ ብለውም
አምላካቸውን ጠየቁ፡፡ እንዲህ የሚል ቃልም ከዙፋኑ ወጣ፡-
‹‹ኢየሩሳሌም በሰው ደም እንደምትታጠብ በነቢያት እንዲሁ
ተጽፏልና እነዚህ ሕፃናት ለመንግሥተ ሰማያት ቀድመው
ተዘጋጁ ናቸው›› እመቤታችንና እነ ዮሴፍም ግብፅ ደርሰው
በዚያ ቢቀመጡም ነገርን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም
በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን
ሕዝቡ ሁሉ በሰላም ተቀበላቸው፡፡
ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና
የኢትዮጵያ ሰዎች እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡
‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር
አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..› ብለው
እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር
ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም
አደረጉላቸው፡፡ እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን
በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን
በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር››
አለችው፡፡ ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር
ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡
በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤
የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡ ከዚህም በኋላ
ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ
ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡
እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም
ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት
ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም እጅግ
ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ
ከአብዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን
በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡
ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን
ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…››
እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለእናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ
ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት
መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡
እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትል
የተወደደ ልጇ ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም
ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡
እመቤታችን ልጇን መድኃኔዓለምን ይዛ ለምን ተሰደደች?
1ኛ.ትንቢተ ነቢያትን ለመፈጸም፡- እግዚአብሔር ሊያደርግ
ያሰበውን ፈቃዱን ሁሉ ለሰው ልጅ እየገለጠ ነቢያትን ትንቢት
እያናገረ መምህራንን እየላከ መጽሐፍትን እያጻፈ መሆኑን ልብ
ማለት ተገቢ ነው፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ለህዝቡ በመጽሐፍ
ይናገራቸዋል››፣ ‹‹በቀንና በሌሊት ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ
ልኬባቸው ነበር፣ አዎ ልኬባቸዋለሁ›› እንዲል፡፡ መዝ 87:6፣
ኤር 7፡25፡፡ ከነዚህም ትንቢታት መካከል ስለ እመቤታችንና
ስለ ልጇ ስደት ሲሆን ነቢዩ ኢሳይያስ 19፡1 ላይ ‹‹እነሆ
እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል››
በማለት ሲናገር ከሙሴና ከአሮን ጸሎት የተነሳ የግብጻውያን
የእጃቸው ሥራ መጥፋቱን፣ እግዚአብሔር በናቡከደነጾር አድሮ
ወደ ግብጽ መምጣቱን፣ ጣዖታትን ማጥፋቱን የተነበየበት
ከመሆኑ በላይ በእመቤታችን ጀርባ ታዝሎ በፈጣን ደመና
በተመሰለች ከእመቤታችን ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡ ሊቃውንት
እመቤታችንን ሲመስሏት ደመና ኢሳይያስ የሚሏትም ስለዚህ
ነው፡፡
በዚህ ትንቢት ላይ እንደተገለጸው ግብጽ በጣዖታት የተሞላች
በመሆኗ የጌታችን ስደት በግብጽ ያሉ ጣዖታትን ለማጥፋት
እንዲሆን ተጠቅሷል፡፡ ግብጻውያን ከጥንት ጀምሮ የላም፣
የፍየል፣ የአንበሳ ምስልን በመቅረጽ ያመልኩ ነበር፡፡ እነዚህን
ለማጥፋት የጌታ ስደት ወደ ግብጽ ይሆን ዘንድ ትንቢት አናገረ፡፡
ከዚህም ባሻገር በኛ ሕይወትም ውስጥ ጌታችንን ለመቀበልና
ሥራ እንዲሠራብን በቅድስና ለመኖር የልብን ጣዖታት ማጥፋት
ማጽዳት ይገባል፡፡ ጌታንና ጣዖትን በልባችን ማኖር
አንችልም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን
ኅብረት አለው? ክርስቶስ ከቤልሆር ጋር መስማማት አለው
ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው
ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም
አለው፡፡ እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና›› ያለው
ለዚሁ ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት መዝ 83፡3 ‹‹ወፍ ለእርስዋ ቤትን
አገኘች ዋኖስም ጫጭቶችዋን የምታኖርበት ቤት አገኘች››
በማለት ሲተነብይ ወፍ ለእርስዋ ቤትን አገኘች ሲል ነቢያት
የተነበዩት ፍጻሜውን በእመቤታችን ማግኘቱን አንድም
እመቤታችን በስደት ግብጽ መኖርያዋ ማድረጓን ዋኖስም
ጫጭቶችዋን የምታኖርበት ሲል ዮሴፍና ሰሎሜም
የሚኖሩበት ቤት ማግኘታቸውን ተናገረ፡፡ ለእመቤታችን
ማደሪያ ጠፍቶ ማደሪያዋን ግብጽ ማድረጓን ተንብየዋል፡፡ ነቢዩ
ሆሴዕ ‹‹እስራኤልን ሕጻን በነበረ ጊዜ ወደድኩት ልጄንም
ከግብጽ ጠራሁት›› እንዳለ (11፡1) እስራኤል በግብጽ ሳሉ
እንደተመረጡ ከዚያም አገር አውጥቶ መንግስት ይሆኑ ዘንድ
እንዳበቃቸው የተናገረበት ትንቢት ከመሆን ጋር የጌታችን ወደ
ግብጽ መሰደድ ሔሮድስ እስኪሞት በዚያ መቀመጡን ከዚያም
መመለሱን የሚያመለክት መሆኑን ቅዱስ ማቴዎስ የነቢዩን
ቃል ፍጻሜ አድርጎ ተናግሯል፡፡ ማቴ 2፡15፡፡
2ኛ. የቅዱሳንን ስደት ለመባረክ ጌታችን ከድንግል እናቱ ጋር
ተሰደደ፡-የክርስትና ሕይወት የመስቀል ላይ ጉዞ በመሆኑ
ክርስቶስን አምነው ለተከተሉት ሁሉ በመከራና በስደት
እንደሚያልፍ ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ከአለም ተመርጠው
ለተከተሉት ደቀ መዛሙርቱ ሲያስተምር ‹‹እኔን መከተል
የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ››
በማለት ተናገረ፡፡ ማቴ. 16፡24፡፡ በዚህም ቃል መሠረት
ከቅዱሳን ሐዋርያት ጀምሮ የተነሡ ክርስቲያኖች በብዙ መከራ
ውስጥ አለፉ በበረሃ ተሰደዱ፣ በዱር በገደሉ ተቅበዘበዙ በሰይፉ
ተተረተሩ፣ በድንጋይ ተወገሩ፡፡ ዛሬም ቢሆን በእምነት
የተሰደድን የተጨነቅን የምንጸልየው ስደትን ከኛ በፊት
በሕጻንነቱ በቀመሰ ስደትን በሚያውቅ አምላክ ፊት ነው፡፡
3ኛ.ጣኦታተ ግብጽን ለማጥፋት ተሰደደ፡- ግብጽ ከነገሥታቶቿ
ጀምሮ ጣኦትን የሚያመልኩ አሕዛብ የነበሩ ህዝቦች ነበሩ፡፡
እነዚህ ጣኦታት ደግሞ የእንስሳትን ምስል በማስመሰል ደንጊያ
ጠርበው እንጨት አለዝበው ማዕድን አቅልጠው የበሬ፣ የላም፣
የአንበሳ፣ የወፍ ምስል አስቀርጸው ያመልኩ ስለነበር ከተማዋ
በጣኦታት የተሞላች ነበር፡፡ ለዚህም ጌታችን ጣኦታትን
ሊያፈርስ ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡ ገና ከተማዋ ሲገባ በጣኦታቱ ላይ
ያደሩ አጋንንት ጮኸው ወጡ፣ ጣኦታቱም ተሰባበሩ፡፡
4ኛ.ጌታችን ሰው መሆኑን ለመግለጽ ተሰደደ፡- ኢየሱስ ክርስቶስ
አገሩን ሳይለቅ ከሄድሮስ ዓይን መሠወር ይችል ነበር፡፡ ነገር
ግን በአምላካዊ ጥበቡ ከሄሮድስ ዓይን ተሰውሮ ቢሆን ሥጋ
መልበሱ ሰው መሆኑን አይገለጽም ነበር፡፡ በሄሮድስ ዓይን
የማይታይ ከሆነ ሥጋ ሳይለብስ የለበሰ መስሎ የተገለጸ ሥጋና
አጥንት የሌለው (ምትሐት) ነው በተባለም ነበር፡፡ ከአዳም
አካል አንድም ያልጎደለው ሙሉ ዳግማዊ አዳም መሆኑን እና
የለበሰው ሥጋ የሚደማ የሚቆስል በሰይፍም ሆነ በጦር ቢወጋ
ጉዳት የሚደርስበት ሰብአዊ ባሕርይ ያለው መሆኑን
ለማስረዳት ስደተኛ ሆነ፡፡ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ከጠላቱ ማምለጥ
የሚችለው ከጠላቱ ፊት ዞር በማለቱ እና በመሸሹ ስለሆነ
ጌታም ከጠላቱ ከሄሮድስ ለማምለጥ ሰው እንደመሆኑ ወደ
ግብጽ ሸሸ፡፡
5ኛ. ምሳሌውን ለመፈጸም ተሰደደ፡- ጌታችን የሥጋ አባቶቹ እነ
አብርሃም፣ ያዕቆብ፣ ኤርምያስ ሁሉ አስቀድመው ወደ ግብጽ
ተሰደው ስለነበር፡፡
6ኛ.ጌታችን የግብፅና የኢትዮጵያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ
ከድንግል እናቱ ጋር ተሰደደ፡፡
7ኛ.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ጌታችን ተሰደደ፡፡
8ኛ.ዲያብሎስን ለማሳደድ ተሰደደ፡- አዳም ዕፀ በለስን በልቶ
ከፈጣሪው ጋር ተጣልቶ ከገነት ከወጣ በኋላ የእግዚአብሔርና
የሰው ግንኙነት የተራራቀ ሆነ፡፡ ይህን የፈጣሪና የፍጡር
መራራቅ ያመጣው ዲያብሎስ የአዳምን ልጆች ሁሉ
ተቆጣጠራቸው፡፡ ልባቸውን በፍቅረ ጣኦት ሸፍኖ አምልኮተ
እግዚአብሔር እንዳያዩ አደረጋቸው ብዙ የአዳም ልጆችም
የአግዚአብሔርን ፈቃድ ሳይሆን የሰይጣንን ፈቃድ ሲፈጽሙ
ኖሩ፡፡ ጌታም ‹‹አሁን የዚህ ዓለም ገዥ ወደ ውጪ
ይጣላል›› (ዮሐ12፡31) በማለት ሰይጣን ዓለሙን
ተቆጣጥሮት እንደነበረ ይገልጻል፡፡ እግዚአብሔር ወልድ
የሰውን ሥጋ በለበሰ ጊዜ የፈጣሪና የፍጡር ግንኙነት እንደገና
ተመሠረተ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ዲያብሎስን ከተቆጣጠረው
ከሰው ልቡና አስወጣው ጌታ ከሄሮድስ ፊት እየራቀ ሲሄድ
ያብሎስም ከሰው ፊት እየራቀ ሄደ፡፡ ጌታችን የሚቀበለው
መከራ ሁሉ ዲያብሎስን በርቀት የሚመታ መሣርያ ነበር፡፡
መጨረሻም በመስቀል ላይ የሆነው የጌታችን ሞት
የዲያብሎስ ሞት ሆነ፡፡