ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

Friday, March 17, 2017

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: =>+*"+<+>††መጋቢት ፯ (7)††

ስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡
አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖መጋቢት ፯ (7) ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
✞ ሰማዕትነት በቅዱስ ቴዎዶጦስ ሕይወት ✞
+*" ቅዱስ ቴዎዶጦስ "*+
=>በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ጊዜው ለክርስቲያኖች
ሁሉ ፍጹም የመከራ ከመሆኑ የተነሳ "ዘመነ-ሰማዕታት"
ሲባል በወቅቱ ከ47 ሚሊዎን በላይ ክርስቲያኖች
ተጨፍጭፈዋል::
+የዘመኑ ክርስቲያኖች ለመሞት የሚያደርጉትን
እሽቅድምድም እያዩ አሕዛብ "ወፈፌዎች" እያሉ
ይጠሯቸው ነበር:: (ዓለም እንዲህ ናትና!) እብዶቹ
ጤነኞችን "እብድ" ማለታቸውኮ ዛሬም አለ::
(ለነገሩ "ግደልና ጽደቅ" ከሚል መመሪያ በላይ ጤና
ማጣት አይኖርም)
=>ታዲያ በወቅቱ አንድ #ቴዎዶጦስ የሚሉት ወጣት
በምድረ ግብጽ ይኖር ነበር:: ወጣቱ እጅግ ብርቱ
ክርስቲያን ነበርና እንደ ዘመኑ ልማድ ተከሦ በነፍሰ
ገዳዮች ፊት ቀረ:: ክሱ አንድ ብቻ ነው:: "ክርስቶስን
አምልከሃል" የሚል::
+ከሥጋ ሞት ለማምለጥ ደግሞ መንገዱ ያው አንድ ብቻ
ነው:: ፈጣሪውን ክርስቶስን ክዶ ለአሕዛብ አማልክት
(አጋንንት) መገዛት:: #ቅዱስ_ቴዎዶጦስ በገዳዮቹ ፊት
ቆሞ ተናገረ:-
" #እኔ_ክርስቲያን_ክርስቶሳ ዊ_የክርስቶስ_ነኝ:: ምንም
ብታደርጉኝ ከክርስቶስ ፍቅር ልትለዩኝ አትችሉም"(ሮሜ.
8:35) አላቸው::
+እነሱ ግን ነገሩ እውነት አልመሰላቸውምና ሊያሰቃዩት
ጀመሩ::
*ገረፉት
*አቃጠሉት
*ደበደቡት
*ሌላም ሌላም ማሰቃያዎችን በእርሱ ላይ ተጠቀሙ::
የሚገርመው ግን እሱ ሁሉን ሲታገሥ ገዳዮቹ ግን
ደከሙ::
+በመጨረሻም ወደ ገዢው ዘንድ አቅርበው "ብዙ
አሰቃይተነዋል:: ግን ሊሳካልን አልቻለም" በሚል ሰይፍ
(ሞት) ተፈረደበት:: በአደባባይ ሊሰይፉት ሲወስዱት ግን
ትንሽ አዘኑለት መሰል ጨርቅ አምጥተው "ፊትህን ሸፍን"
አሉት:: (ያኔ ትንሽም ቢሆን ሰብአዊነት ሳይኖር አይቀርም)
+ቅዱስ ቴዎዶጦስ ግን ገዳዮቹን በመገረም
እየተመለከታቸው ተናገረ:- "እኛ ክርስቲያኖች ሞትን
አንፈራም:: ሞት ለእኛ ወደ ክርስቶስ መሸገጋገሪያ
ድልድያችን ነውና የምንፈራው ሳይሆን የምንናፍቀው
ነው::" "ኢትፍርሕዎሙ
(አትፍሯቸው)"
(ማቴ. 10:28)
+ይህን ብሎ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ጌታውን አመሰገነ::
ፊቱ ላይ ደስታ እየተነበበ ጨካኞቹ አንገቱን ሰየፉት::
በብርሃን አክሊልም ቅዱሳን መላእክት ከለሉት::
*መሠረታዊው ነገር ቅዱስ ቴዎዶጦስ ለምን አልፈራም?
ነው::
+አጭር መልስ ካስፈለገን ቅዱሱ ያልፈራው ከልቡ
ክርስቶሳዊ በመሆኑ ነው:: ትኩረት እንድንሰጠው
የሚያስፈልገው ግን የሰማዕታት ምስጢራቸው:-
1.በጽኑ የክርስትና መሠረት ላይ መመሥረታቸው
2.ዕለት ዕለት የክርስቶስን ፍቅር መለማመዳቸው
3.ከወሬ (ንግግር) ይልቅ ተግባርን መምረጣቸው
4.በንስሃ ሕይወት መመላለሳቸው
5.ሥጋ ወደሙን የሕይወታቸው ዋና አካል ማድረጋቸው
6.ከእነሱ የቀደሙ ቅዱሳንን ዜና ሕይወት ከልብ
ማንበባቸው
7.በቃለ እግዚአብሔር መታነጻቸው . . . መጠቀስ
የሚችሉ መገለጫዎቻቸው ናቸው::
<+>" ዛሬስ "<+>
=>ዓለማችን ከጠበቅነው በላይ ነፍሰ በላነቷ እየጨመረ
ነው:: ዛሬ የክርስትና ጠላቶች ከጉንዳን በዝተዋል::
*የራሳችን ማንነት
*ክርስትናችን በአፋችን ላይ ብቻ መሆኑ
*እረኞችና በጐች መለያየታቸው . . . ሁሉ እኛ ልናርማቸው
የሚገቡ ናቸው::
*አሸባሪዎች
*አሕዛብ
*የመዝናኛው ዓለም
*ሰይጣን አምላኪ ዝነኞች (Celebrities)
*ሚዲያው
*ማሕበራዊ ድረ ገጾችና መሰል ነገሮች ደግሞ
ልንጠነቀቅባቸው የሚገቡና እኛን ውስጥ ለውስጥ
በልተው የፈጁን የሰይጣን መሣሪያዎች ናቸው::
+ስለዚህም ከዛሬ ጀምረን ባለ መታወክ ክርስትናችንን
ከአፋችን ወደ ልባችን: ከብዕራችን ወደ አንጀታችን
እንድናወርደው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አደራ ትላለች::
+ዛሬ ነገሮችን ረስተን ሌሎች አላስፈላጊ ነገሮችን
ከጀመርን እጅግ አሳፋሪ መሆኑ አይቀርም:: በጐውን
ጐዳና ተከትለን በሃይማኖትና በፍቅረ ክርስቶስ ከጸናን ግን
ማንም ቢመጣም ፈጽሞ አንናወጥም::
+ይልቁኑ
"አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን:
ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው::
ስለዚህም ምድር ብትነዋወጥ: ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ
ቢወሰዱ አንፈራም::" (መዝ. 46:1) እያልን ከቅዱስ
ዳዊት ጋር እንዘምራለን::
<< ለዚህ ደግሞ ደመ ሰማዕታት ይርዳን:: በረከታቸው ይድረሰን:: የጌታ ፍቅርም አይለየን >>
+*" ጻድቁ ንጉሥ ቴዎድሮስ "*+
=>በሃገራችን ታሪክ በጣም ተወዳጅ ከነበሩ ነገሥታት
ጻድቁ ቴዎድሮስ ቅድሚያውን ይወስዳል:: በርግጥ
በርካቶቻችን የምናውቀው ስለ ሃገሩ ፍቅር ራሱን የሰዋውን
ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስን (1845-1860) ነው:: በበጎ
ሥራውና በቅድስና ሕይወቱ የተመሠከረለት ግን ዛሬ
የምናስበው ቀዳማዊው ነው::
+ቀዳማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ የደጉ ዐፄ ዳዊት (ግማደ
መስቀሉን ያመጡት) እና የተባረከችው ሚስታቸው ፅዮን
ሞገሳ ልጅና የጻድቁ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ታላቅ ወንድም
ነው:: በኢትዮዽያ ለ3 ዓመታት (ከ1396-1399) ብቻ
ነግሦ እያለ እንደ ንጉሥ ሳይሆን-
*ከጠዋት እስከ ማታ ድሃ እንዳይበደል ፍርድ
እንዳይጉዋደል ይታትር የነበር::
*ጾምና ጸሎትን የሚያዘወትር::
*ወገቡን ታጥቆ ነዳያንን የሚያበላ::
*ለአብያተ ክርስቲያናትም የሚጨነቅ ደግ ሰው ነበር::
+ስለዚህም በሕዝቡ እጅግ ተወዳጅ ነበር:: በነገሠ በ3
ዓመቱ ዐርፎ በዝማሬና በለቅሦ ሥጋውን ተሸክመው
ሲሔዱ ወንዝ ተከፍሎላቸዋል:: ከመቃብሩም ላይ ጸበል
ፈልቁዋል::
=>ዘለዓለም ሥላሴ ደግ መሪና ሰላማዊ ዘመንን ያድሉን::
=>መጋቢት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ጻድቁ ኢትዮዽያዊ ንጉሥ ዐፄ ቴዎድሮስ
2.ቅዱስ ቴዎዶጦስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ፊልሞን ሰማዕት
4.ቅዱስ አብላንዮስ ሰማዕት
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
=>+"+ ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ::
ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና::
ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው::
ስለዚህ ባ ለሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን
ሥርዓት ይቃወማል:: . . . ለሁሉ እንደሚገባው አስረክቡ::
ግብር ለሚገባው ግብርን: ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን:
መፈራት ለሚገባው መፈራትን: ክብር ለሚገባው ክብርን
ስጡ:: +"+ (ሮሜ. 13:1-8)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ:=>+*"+<+>††በቤተክርስቲያናችን ስርአት መሰረት 7 ጊዜ እንፀልያለን ። የእነሱም ትርጉም ††

~በቤተክርስቲያናችን ስርአት መሰረት 7 ጊዜ እንፀልያለን ።
የእነሱም ትርጉም
1= ጠዋት 12:00 ሰአት፡- አንድ ክርስቲያን እግዚአብሔርን
አምላክን በፀሎት የሚያመሰግንበት ምክንያት (ሚስጥር)
እግዚአብሔር አምላክ ሌሊቱንና ጨለማውን አሳልፎ ብርሀን
እንድናይ ስላበቃን በዚህ ሰአት እግዚአብሔር አምላካችንን
እንድናመሰግን ታዝዝዋል። አንድም በዚህ ሰአት ጌታችን
ለክስ ከጲላጦ ፊት ቆሞ የተወቀሰበት ሰአት ስለሆነ አንድም
በዚ ሰአት አባታችን አዳም ያልተፈቀደለትን እፅ በልቶ ከገነት
የተባረረበት ሰአት ስለሆነ ነው። አንድ ክርስቲያን ይህን ሁሉ
እያሰበ ወደ አምላኩ እንዲፀልይ ታዝዋል
2=ከጠዋቱ 3:00 ሰአት፡- አንድ ክርስቲያን እንዲፀልይ
የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር)
በዚህ ሰአት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብስራተ
ገብርኤልን የሰማችበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድም በዚህ
ሰአት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን
የፀነሰችበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድም ጌታችን መድሀኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ከ ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የተገረፈበት ሰአት
ስለሆነ ዮሐ 19 ፥1 ሐዋ ስራ 2፥15 እያንዳንዱ ክርስቲያን
ይሔንን የመሳሰሉ ሁሉ እያሰበ እግዚአብሔር አምላኩን
እንዲያመሰግን ታዝዋል
3= 6:00 ሰአት፡-አንድ ክርስቱያን እኩለ ቀን (ከ ቀኑ
6ሰአት) ሲሆን እንዲፀልይ የታዘዘበት ምክንያት ወይም
(ሚስጥር )
ጌታችን በቀራኔዎ አደባባይ በመስቀል ተሰቅሎበታልና
አንድም ልብሱን ተገፎበታል አንድም ሳዶር አላዶር ዳናት
ሮዳስ በተባሉ ችንካሮች ተቸንክሮበታል አንድ ክርስቲያን ይህን
ሁሉ እያሰበ በዚህ ሰአት እንዲፀልይ ታዞበታል
4= ከቀኑ 9:00 ሰአት፡- አንድ ክርስቲያን የሚፀልይበት
ምክንያት (ሚስጥር)
አይሁዶች ጌታችን መድሀኒታችን ኢየ�ሱስ ክርስቶስን መራራ
ሐሞት አጠጥተውበታል አንድም ቅድስት ነፍሱን ከ ክቡር
ስጋው የለየበት ሰአት ነውና አንድም በመስቀል እንዳለ 7ቱን
አፅርሀ መስቀል የተናገረበት ማር 15፥34 ማቴ 27፥50
አንድ በዚህ ሰአት ይህንን እያሰበ እንዲፀልይ ታዝዋል
5= ከቀኑ 11፡00 ሰአት፡- አንድ ክር�ቲያን እንዲፀልይበት
የታዘዘበት ምክንያት ወይም (ሚስጥር)
ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ወደ ከርሰ መቃብር
የወረደበት ሰአት ስለሆነ አንድም ቀኑን በሰላም አሳልፎ ወደ
ምሽት በሰላም ያደረሰን አምላክ ምስጋ ስለሚገባው ነው
ይህንን የመሳሰሉ ሁሉ ሕዝበ ክርስቲያን እንዲያስቡ ታዘዋል
6= ከምሽቱ 3:00 ሰአት፡- በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን
እንዲያመሰግን የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር)
በዚህ ሰአት እራሱ ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ
ስርአተ ፀሎት አሳይቶበታል አንድም በዚህ ሰአት ጌታችንን
አይሁድ በይሁዳ ጠቁዋሚነት ተረበርበው የያዙበት ሰአት
ስለሆነ ነው አንድም በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን ከመተኛቱ
በፊት በሰላም ያዋለንንና ያስመሸንን አምላክ አመስግኖ
መተኛት አለበት ይህን ሁሉ እያሰበ እንዲፀልይ ታዝዋል
7= መንፈቀ ሌሊት ከሌሊቱ 6 :00 ሰአት:- በዚህ ሰአት አንድ
ክርስቲያን እግዚአብሔር አምላኩን እንዲያመሰግንበት
የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር)
በዚህ ሰአት ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ተወልዶበታልና ነው አንድም ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ሙስና መቃብርን ድል አድርጎበታልና(ተነስቶበታ
ል) በመዝሙረ ዳዊት አመሰግንህ ዘንድ በመንፈቀ ሌሊት
እነሳለው ባለው መሰረት ጳውሎስ ሲላስ በእስር ቤት ሆነው
ወደ እግዚአብሔር የፀለዩበት ስለሆነ ነው አንድም የሰው ልጅ
የሚመጣበት ጊዜ ማታ ይሁን መንፈቀ ሌሊት ይሁን ዶሮ
ሲጮህም ይሁን ሲነጋም ቢሆን አይታወቅምና ባለው
አምላካዊ ቀል መሰረት በመንፈቀ ሌሊት አንድ ክርስቲያን
እንዲፀልይ ታዝዋል
የቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እና ምልጃ አክሊልና ጉልላት በሆነው
በእናታችን በወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም
ጸሎት ሁላችንንም ይማረን፡፡

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ:=>+*"+<+>††ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ††

ዮሐንስ ማለት ፍሰሓ ወሐሴት ሠላም ርህራሄ ወሳህል
ማለት ነው። ወልደ ነጎድጓድ፣ አቡቀለምሲስ፣ ነባቤ መለኮት፣
ታዖሎጎስ ይለዋል፡፡ “ቃዳሚሁ ቃል ውእቱ” ብሎ ምስጢረ
ሥላሴን አምልቶ አስፍቶ ይናገራልና፡፡ ፍቁረ እግዚእ
ይለዋል፡፡ “ዝኩ ካልዕ ረድዕ ዘያፈቅሮ እግዚእ ኢየሱስ”
ይለዋልና፡፡ ዮሐንስ 21፡7 መውደድንስ ሁሉንም ይወዳቸው
የለምን ቢሉ የርሱ የተለየ ነውና፡፡ ከቶማስም የሱ መወደድ
ይበልጣል፡፡ ቶማስ በጦር የተወጋ ጎኑን ቢዳስሰው እጁ ከእሳት
እንደገባ ጅማት ተኮማትሯል፡፡ እርሱን ግን በከናፍሩ ቢስመው
በጭኑ ቢያስቀምጠው ምንም ምን አልሆነም ::
ንጹህ ወድንግል ይለዋል፡፡ ጌታን ከመውደዱ የተነሳ ጌታም
እናቱን እነዃት እናትህ ሲል ድንግል ማርያምን በሱ በኩል
ተሰታናለች፡፡ እኛም ዛሬ ልጆቿ ነንና ደስ ይበለን ይበላችሁ
የድንግል ማርያም የአስራት፣ የተስፋና የስስት ልጆች፡፡ ዮሐንስ
19፡26፡፡ ዮሐንስ ሀገሩ ገሊላ አውራጃ ሲሆን ከታላቅ
ወንድሙ ከያዕቆብና ከአባቱ ከዘብድዮስ ጋር ዓሣ እያጠመደ
ይኖር ነበር። እናቱ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ስትሆን
ማርያም ትባላለች።
ዮሐንስ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን በሕይትም በኑሮም
ጌታ ስለሚመስል (ፍቁረ እግዚእ) ይባለል። ነገረ መለኮትን
በበለጠ ከሌሎች አምልቶ አስቶ በጥልቀት በማስተማሩ ነባቤ
መለኮት (ታዖሎጎስ)ተሰኝቷል። ስለጌታም ባለው ቅናት ባሳየው
የሀይል ሥራ በኦኔርጌስ (ወልደ ነጎድጓድም) ተብሏል። ፍጥሞ
በምትባል ደሴት በራዕይ መጻእያትን በመግለጡ ባለራዕይ
(በግሪክ አቡቀለምሲስ) ይባለል። በዕለተ ዓርብ በመስቀል ሥር
ተገኝቶ የጌታን መከራ መስቀል በማየቱ ፊቱ በሀዘን
ስለተቋጠረ ቁጽረ ገጽ (ፊቱ በሀዘነ የተቋጠረ) ስምም
ተሰቶታል። ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር የፋሲካን እራት ያዘጋጀ
አንካሳን የፈወሰ ታለቅ ሐዋርያ ነው። (ሊቃስ 22፡8) እስከ
መስቀል አምላኩን ተከትሎ እመቤታችንን በአደራ የተረከበ
ባለአደራ ሐዋርያ ሲሆን ከጰራቅሊጦስ በዓል በኋላ ከቅዱስ
ጴጥሮስ ጋራ በኢየሩሳሌም በአንጾኪያ በሎዶቅያ በእስያ
ከተሞች በተለይ በኤፌሶን በአሁኑ ቱርክ አስተምሯል።
(ዮሐ.19፡26) በወጣትነት ዕድሜው ተጠርቶ በዕለተ ዓርብ
የጌታን መከራ እያሰበ ያነባ የነበረ በፍቅር በታማኝነት
እስከመጨረሻ ድረስ የጸና ከጌታ ያልተለየ ወንጌላዊ ሲሆን
ወንጌልን ጨምሮ 3 መልዕክታትን የጻፈ እንዲሁም ሐዋርያው
ዩሐንስ በፍጥሞ ደሴት በዛሬቱ ቱርክ ለሰባት አመታት ታስሮ
በነበረበት ወቅት ወንጌሉንና ራዕዩን ጽፏል። አይገርምህም
ሐዋርያው ዩሐንስ በእስር እያለ ነው ራዕዩን የጻፈው!!!
ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ ደግሞ በቀዝቃዛ እስር ቤት እያለ ብዙ
መልእክታቱን ጻፈ!!! ሐዋርያቱ በእስር ቢሆኑ እንኳን
ስለቅድስት ቤተክርስቲያን አገልግሎት አብዝተው ያስቡ ነበር።
የሐዋርያቱ ብርታት ያበርታን።
ዩሐንስ ወንጌሉን በፍጥሞ ደሴት ሲጽፍ እንዲህ ብሎ ጀመረ፦
ዩሐንስ 1:1
+++ በመጀመሪያ ቃል ነበረ; ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ
ነበረ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።እኛም በቅዳሴ ላይ ሁሌ
የዩሐንስ ወንጌል ሲነበብ ቀዳሚሁ ቃል ሥጋ ኾነ ወሃደረ
ላዕሌነ ብለን እንቀበላለን። ግሩም ዜማ ከግሩም ሚስጢር
ጋር አባቶቻችን አወረሱን።
እስቲ ሚስጢሩን እንይ፦
በመጀመሪያ ቃል ነበረ፦ እንደምናውቀው ቃል ኢየሱስ
ክርስቶስ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ አልፋና ዖሜጋ መጀመሪያና
መጨረሻ ነውና ራዕ 22:12። ቃልም እግዚአብሔር ነበር፦
መጽሃፍ አንባቢው ያስተውል ይላል; ምን እንደሚል ልብ
እንበል “ቃልም እግዚአብሔር ነበር” ሐዋርያው በመጀመሪያ
ቃል ነበር ብሎን ነበር; ያ ቃል እግዚአሔር እንደሆነ
አስረዳን!!! በዚሁ ምዕራፍ ላይ ወረድ ብሎ /ዩሐንስ 1:14/
“ያ ቃል ሥጋ ሆነ ይለናል” እስቲ ጥያቄ እንጠያየቅ; ሐዋርያው
ያ ቃል ሥጋ ሆነ ብሏል ከማን? ከማን ሥጋን ነሳ?
ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ
ነፍስ ነስቶ በኤፍራታ በቤቴልሔም ተወለደ።
+++ የፍጥሞ ደሴት ታሪክ እነሆ፦ ሐዋርያው ዩሐንስ በፍጥሞ
ደሴት ወንጌሉን መጻፍ ሲጀምር የመለኮትን ነገር ጽፎ
የሚጨርስ መስሎት ብእሩን አነሳ። በመጀመሪያ ቃል ነበረ
አለና ሊጨርስ አሰበ፤ ያኔ መልአኩ ቅ/ሚካኤል ተገልጦ
በፍጥሞ ደሴት ያለችውን ባህር በእንቁላል ቅርፊት እየቀዳ
ወደ መሬት ሲያፈስ አየው; ሐዋርያው ዩሐንስም እንዴት ይህ
ታላቅ ባሕር በእንቁላል ቅርፊት ያልቃል ብሎ ጠየቀው;
መልአኩም እኔስ ብሞክር ፍጥረትን ነው አንተስ የፈጣሪን
ባሕርይ የሚያልቅ መስሎህ ትሞክር አይደለምን አለው። ያኔ
ሐዋርያው ዩሐንስ ይህን ተረድቶ ወዲያው ከእግዚአብሔር
የተላከ ስሙ ዩሐንስ የሚባል አንድ ሰው አውቃለሁ ብሎ
ስለመጥምቁ ዩሐንስ ታሪክ የቀጠለውም በዚሁ ምክንያት
ነበር። ዩሐንስ 1:19
ከሐዋርያው፣ ከዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ረድኤትና በረከት
ይክፈለን ምልጃና ጸሎት ከሁላች ጋር ይሁን አሜን !!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ
ክቡር ይቆየን አሜን።

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ:=>+*"+<+>††መጋቢት 5 ፃድቁ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ††

መጋቢት 5 ፃድቁ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ
በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ይውላል ።
በዚህ እለት እምናከብረው የእረፍት መታሰቢያቸውን ሲሆን
ከገድላቸውም እንዲህ ተፅፎ እናገኘዋለን ።
ፃድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የተወለዱት ግብፅ ንሂሳ
በምትባል ቦታ ከአባታቸው ስምዖን ከእናታው አቅሌስያ ነው።
በአጠቃላይ የኖሩበት ዕድሜ 562 አመት ሲሆን 300
ዓመቱን በግብጽ 262 ቱን በኢትዮጵያ 100 ዓመት በዝቋላ
በተጋድሎ ያሳለፉ ታላቅ አባት ናቸው።
መጋቢት 5 በገድለ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ
ዕለቱ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ሰዓቱ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት
ሆኗል፤ አሁንም ህማሙን እየታገለ እያላበው በድካም
ለፍጥረቱ ሁሉ ይለምናል፤ “አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህን
ኢትዮጰያንም ባርክ” ይላል። ህመም የጀመረው መጋቢት 3
ዓርብ ቀን ነው፤መታመሙን የሰሙ እንደርሱ ቅዱሳን የሆኑት
ዘርአ ቡሩክ፤ ፍሬ ቅዱስ፤ያዕቆብ፤ብንያምና ዮሴፍ እንዲሁም
በወቅቱ የኢትዮጰያ ንጉስ የነበረው እንድርያስ ሊጠይቁት
ተሰብስበዋል ወደ አጠገቡ መድረስ ግን አልተቻላቸውም
አባታችን ገብረመንፈስ ቅዱስ የሚጋርደው እንጨት ዛፍ
በሌለበት በርሃ እንደ አንበሳ ተኝቶ አዩት በላዩ ያረፈው
የእግዚያብሔር ጸጋ ከፊቱ የሚወጣው ብርሃን ቀይ መልኩ
ረዥም የራስ ጠጉሩ እንደ ነጭ ሐር የሚሆን ጽሕሙ
አስደነቃቸው። ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲሆን ከሰማይ ታላቅ
ነጎድጓድ ድምጽ ተሰማ ጌታችን መላአክትን አስከትሎ ወደ
አባታችን ወረደ፤ ከሰማይ ወደ ምድር ህብሩ አምሳያው ልዩ
ልዩ የሆነ እንደ ጸሐይና እንደ ጨረቃ የሚያበራ እንደ
ወንጪፍ ድንጋይ ይወረወር ነበር ከዚያ የነበሩ ሁሉ ፈሩ ወደ
ኃላም ሸሹ ምድር ራደች ተራሮች ኮረብቶች ተናወጡ ብርቱ
ጩኸት
ንውጽውጽታ ሆነ። “ወዳጄ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሰላም ላንተ
ይሁን” እነሆ የማይታበል ቃል ኪዳን እገባልኃለው ስምህን
የጠራ መታሰቢያህን ያደረገውን፤ እጣን ቋጥሮ ግብር ሰፍሮ
መባ ይዞ ቤትህ የመጣውን እምርልኃለው አንተ ከገባህበት
ገነት መንግስተ ሰማያት አገባዋለሁ አለው፤ አባታችንም
“አቤቱ ጌታ ሆይ የኢትዮጰያን ህዝብ ማርልኝ” አለው፤ እነሆ
ምሬልኃለው አስራት በኩራት አድርጌም ሰጥቼሃለው፤
ከመጋቢት አምስት ቀን ጀምሮ ዝክርህን ያድርጉ
በአማላጅነትህም ይማጸኑ አለው። ከዚህ በኃላ ሰባቱ ሊቃነ
መላእክት የአባታችንን ነፍስ ሊቀበሉ ወረዱ በታላቅ
ምስጋናም ወደ ሰማይ አሳረጉት ስጋውንም ይዘውት ሄዱ የት
እንደተቀበረ ግን እስካሁን አይታወቅም አንዳንዱ
በእየሩሳሌም ነው ይላሉ፤ ሌላው በምድረ ከብድ ነው ይላል
ግን እስካሁን ልክ እንደ ሊቀ ነብያት ሙሴ ስጋ የት
እንደተቀበረ አይታወቅም። ገድሉ ትሩፋቱ ከሰማይ ከዋክብት
ከምድር አሸዋ ይበዛል ኢትዮጰያን አብዝቶ ይወዳታል፤
ምድራዊ ምግብ አልተመገበም የእናቱን ጡት እንኳን
አልጠባም፤ ልብስ፤ መጠለያ አልፈለገም፤ የክረምት ቁር የበጋ
ሐሩር እየተፈራረቀበት በተጋድሎ 562 ዓመት ኖረ፤ በዛሬዋ
ቀን ሩጫውን ጨረሰ። ለእግዚያብሔር ምስጋና ይሁን
እኛንም ከአባታችን በረከት ያሳትፈን።
አምላከ ገ/መንፈስ ቅዱስ መንገዱን ያብራልን ። ገድሉንም
ሰሚወች ብቻ ሳንሆን እምንማርበት ያድርግልን ።