ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

Sunday, April 3, 2016

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: የቤተ ክርስቲያን ደጃፉን ለምን እንደሚሳለሙ ያውቃሉ?

የቤተ ክርስቲያን ደጃፉን ለምን እንደሚሳለሙ ያውቃሉ?
በትእምርተ መስቀል ከአማትበን በኋላ የቤተ መቅደሱን ደጃፍ
በእምነት ስንሳለም ተመልክተው የሚገርማቸው አይጠፉም
እንዲህ ያሉ ሰዎች ዐጸዱን ደጃፉን በበሩን መስኮቱን
መሳለማችን እነርሱ እንደሚያስቡት ያለ ምክንያት አይደለም፡፡
ደጃፉን የምንሳለምበት የተለያየ ምክንያት አለን፡፡
፩. ቤተ መቅደሱን እንዲሁ በውስጡና በዙሪያው ያለውን የነካ
ስለሚቀደስበት
“የቅብዐት ዘይትን ወስደህ ማደሪያውን በእርሱም ያለውን ሁሉ
ትቀድሳለህ ቅዱስም ይሆናል” ሲል ለሙሴ አዞታል ኦሪ ዘፀ
፵፥፱/40፥9/
እግዚአብሔር ቤተ መቅደሱና በዙሪያው ያሉ ሁሉ እንዲቀደሱ
አዟል፡፡ደብተራ ኦሪት ሲተከል የሰሎሞን ቤተ መቅደስ ሲሰራ
ዙሪያው በቅብዓ ቅዱስ ተቀድሷል የቤተ መቅደሱ ደጃፍ
መሳለም መሳም የሚያስፈልገው ለዚህ ነው፡፡ሕንጻ ቤተ
ክርስቲያኑ ደጃፉ በቅብዓ ሜሮን የከበረ የተቀደሰ ስለሆነ
የሚሳለመው የሚስመው የሚተባበሰው ሁሉ ይቀደሳል፡፡
፪. ቤተ መቅደስ የክርስቶስ ማደሪያ ስለሆነ
በሌላ በኩል ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረ ቤተ ክርስቲያን
የክርስቶስ አካል ዘርፉ ልብሱ መቅደሱ ናት፡፡ ኤፌ
፭፥፳፫/5፥23/፡፡ አካል ከራስ ጠጉር እስከ እግር ጥፍር ያለውን
ሁሉ እንደሚይዝ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት ሲባል
የቤተ ክርስቲያኑ አካል ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ ስለዚህ አካሉ
የሆነችው ይህች ቤተ ክርስቲያን/ቤተ መቅደስ/ መሳለም
መተባበስ የጌታችንን የልብሱን ዘርፍ በመንካቷ አስራ ሁለት
በዓመት ሙሉ ደም ሲፈሳት ኖራ እንደተፈወሰችው ሴት
የእምነት ጥንካሬ ምልክት ነው ሉቃ ፰፥፵፫-፵፰ /8፥43-48/
፡፡በእምነት ለሚሳለም በእምነት ለሚኖር ሰው
የቤተክርስቲያን ደጃፎቿ ዐጸዱ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ያለው
ጠበል አጥሩ ቅጥሩ ውስጡ ውጪው ሁሉ ፈውስና መድኃኒት
ይሆነዋል፡፡
፫. ቤተ መቅደሱ የመለኮት ማደሪያ ስለሆነ
ቤተ ክርስቲያን/ቤተ መቅደሱ/ የመለኮት ማደሪያ ነው፡፡
በሰማይ በክብር የሚኖር እግዚአብሔር በቤተ መቅደሱን
በረድኤት ያድራል፡፡ ቤተ መቅደሱን የክብሩ
መገለጫ አድርጎታልና፡፡ “አሁንም ስሜ ለዘለዓለም በዚያ
ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለው ቀድሻለውም ዐይኖቼና
ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ” ፪/2/ ዜና፯፥፲፮ /7፥16/
“ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን” መዝ ፻፴፩፥፯/131፥7/ እንዲል
ቤተ መቅደሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ስለሆነ ደጃፉ አጥሩ
ቅጥሩ ሁሉ የተቀደሰ በበረከት የተሞላ ነው፡፡ ስለዚህ ወደ ቤተ
መቅደስ የሚቀርብ ሰው ይህን እያሰበ ይሳለማል፡፡
ስለዚህ ሰው ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ደጃፏን /ደጀ ሠላሟን/
“ሠላም ለኪ ቤተ ክርስቲያን አምሳለ ኢየሩሳሌም ቅድስት” /
ቅድስት የምትሆን የሰማያዊ ኢየሩሳሌም አምሳል የሆንሽ ቤተ
ክርስቲያን ሆይ
ሠላምታ ይገባሻል/ እያልን ደጃፏን አጥሯን እንሳለም::