ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

Thursday, March 31, 2016

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ:እመቤታችን_እና_ኤልሳቤጥ

#እመቤታችን_እና_ኤልሳቤጥ
_
በመከራው ያልተለየችው ፣ በመስቀሉ ሥር ከነበሩት ቅዱሳት
አንስት ዝርዝር ውስጥ በቀዳሚነት የተጠቀሰችው
#እመቤታችን እሑድ ደርሶ ሴቶች ወደ መቃብሩ ሽቱ ይዘው
ማልደው ሲሔዱ ግን ከእነርሱ ጋር አልነበረችም፡፡ #ለምን
ይሆን? መልሱ ቀርቧልና ይነበብ...
21 21 21 21 21
21
ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ ‹‹ስለ ድንግል ማርያም ገና ማሰላሰል
ስጀምር ‹የቆምክባት ሥፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ወደዚህ
አትቅረብ›
የሚል ድምፅ ሲጮኽ ይሰማኛል›› በማለት እንደተናገረ ስለ
እመቤታችን
ልንጽፍ ብዕራችንን ባነሣን ቁጥር የኃጢአት ጫማችንን
ሳናወልቅ ወደ
እርስዋ መቅረብ እንደማይገባን ይሰማናል፡፡ ሰውና መላእክት
ተናግረው
ለመፈጸም የማይቻላቸውን ምስጋናዋን ለመናገር ስንነሣም
ድካማችንን
አውቀን እንሰቀቃለን፡፡ ‹ስለ እርስዋ መናገር የሚቻለው ምን
አንደበት
ነው? አስቦትስ ሊደርስበት የሚቻለው እንደምን ያለ ኅሊና ነው?
ነገር
ግን የሚቻለንን ያህል ከምስጋናዋ ጥቂት እንነግራችኋለን ›
ብለው
እስከመናገር የደረሱ አባቶቻችንን ስናይ ከምስጋናዋ ሰልፍ
መደመር
ያስጨንቀናል፡፡ አባቷ ዳዊት ‹በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች
ተወለዱልሽ ፣
ስምሽን ለልጅ ልጅ ያሳስባሉ› ያላትን ስናስብ ደግሞ
የአባቶቻችን ልጆች
እንደመሆናችን የእመቤታችንን ስሟን ማሳሰብ ለእኛም
እንደተሠጠን
በማሰብ እንደሰታለን፡፡ እርስዋም ‹ትውልድ ሁሉ ብፅዕት
ይሉኛል›
ብላለችና ከትውልድ እንደመቆጠራችን የተናገረችው ትንቢት
ይፈጸማል
ብለን ስለ እመቤታችን ክብር እንናገራለን፡፡ ነቢዩ "በቀንና
በሌሊት
ደጆችዋ አይዘጉም" ሲል እንደተናገረላት ቀንና ሌሊት ምስጋናን
ሲሰሙ
የማይዘጉት የጆሮዎቿን ደጆች ተስፋ አድርገን ቅድስት ሆይ
ለምኚልን
ሳንላት አናድርም፡፡ እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደ ምድር አሸዋ
በበዛው
ኃጢአታችን ምክንያት ስለ እመቤታችን መናገራችን የሚገባን
ባይሆንም
አባቷ ዳዊት በታላቅ ትሕትና ‹ልጄ ሆይ ስሚ እዪም ጆሮሽንም
አዘንብዪ›
እያለ እየተማጸነ እንዳመሰገናት እኛም ‹እናታችን ሆይ ስሚ እዪ
ጆሮሽንም አዘንብዪ› ብለን እየተማጸንን እናመሰግናታለን፡፡
ከአባ
ጊዮርጊስም ጋር ‹‹እመቤቴ ሆይ የኃጢአተኛ ሰው ምስጋና ለምኔ
ነው
አትበዪ የእኔ ኃጢአት የአንቺን ቅድስና አያረክሰውምና›
እንላለን፡፡ /
አርጋኖን/
21
ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ ማርያም ተብለው የተጠሩ አምስት
ሴቶችን በስም ጠቅሶ ሲጽፍ ለዐሥራ አራት ዓመታት በቤቱ
የኖረችውን
እመቤታችንን ግን ስምዋን ከመጥራት ይልቅ ‹የኢየሱስ እናት›
፣ ‹የጌታ
እናት› ፣ ‹እናቱ› ብሎ መጥራትን እንደመረጠ እኛም በዚህ
ጽሑፍ
እመቤታችን ብቻ ብለን እየጠራን ስለ እርስዋ ክብር
እንናገራለን፡፡ ይህ
ጽሑፍ ጥናታዊ ጽሑፍ አይደለም፡፡ የጽድቅ ፀሐይ የወጣበትን
ሰማይ ማን
አጥንቶ ይዘልቀዋል? የማይቻለውን ስለ ቻለችው ፣
የማይወሰነውን
ስለወሰነችው እመቤታችን ከምስጋና በቀር ማንም ሰው
ምሁራዊ
ትንታኔን ሊሠጥ አይችልም፡፡ ስለዚህ ስለ እመቤታችን በቅዱስ
ሉቃስ
ወንጌል ብቻ የተጻፉ አንዳንድ ነጥቦችን እናነሣለን፡፡
21 21 21
#እመቤታችን_እና_ቅዱስ_ገ ብርኤል
°
አምላክ በሰው ላይ የፈረደውን ፍትሐ ሞት በራሱ ለማድረግ
ሰው ሊሆንና ሊያድነው የገባውን ቃል ለመፈጸም በእርሱ ዘንድ
አምስት
ቀን ከግማሽ በእኛ ዘንድ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን
አስቆጥሮአል፡፡ ‹‹የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ›› ግን አምላክ
‹‹ከሴት››
ሊወለድ ፈቃዱ ሆነ፡፡ (ሊቁ ኤጲፋንዮስ እንዳብራራው እኛ
ከሴትና
ከወንድ እንደተወለድን ፤ እርሱ ግን በሁለተኛው ልደት ያለ ዘርዐ
ብእሲ
ከሴት ብቻ እንደተወለደ ልብ ይሏል) /ገላ.4/ አምላክ ይህንን
የማዳን
ሥራ ለመፈጸም የመረጣት ንጽሕት እመቤታችን ነበረች፡፡ ነገር
ግን
የሰውን ነጻ ፈቃድ /Free will/ የሚያከብር ነውና ሊወለድ
እንደወደደ
በራሱ ፈቃድ ብቻ ልወለድ ሳይል ወደ መረጣት ቅድስት
መልአኩን ላከ፡፡
ለመልእክት የተመረጠው መልአክ መላእክቱን ‹ባለንበት
እንጽና› ብሎ
ያረጋጋው መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ነበረ ፡፡ ይህ መልአክ
ሦስቱን
ወጣቶች ከእሳት መካከል ሊያወጣ እንደተላከ አሁን ደግሞ
የሰው
ልጆችን ከሲኦል እሳት መውጣት ለማብሠር ተላከ፡፡ ቅዱስ
ገብርኤል
እመቤታችን ፊት ለማብሠር ቆመ፡፡
21
የተላከው ከኃያሉ ባለ ሥልጣን ከእግዚአብሔር ዘንድ ቢሆንም
አነጋገሩ ከላይ እንደተላከ ሆኖ የተናገረው የሥልጣን ንግግር
ሳይሆን
የፍጹም ትሕትና ንግግር ነበር፡፡ ‹አምላክ ከአንቺ ሊወለድ
ወስኖአል!›
ብሎአትም አልተሠወረም፡፡ መልእክተኛ የሚያደርሰው
እንደተላከው
አድርጎ ነውና ይህችን ከፍጥረት ሁሉ የከበረች ንግሥት አደግድጎ
አመስግኖ አክብሮ አበሠራት፡፡ ‹ደስ ይበልሽ ጸጋን የሞላብሽ
ሆይ ጌታ
ከአንቺ ጋር ነው ፣ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ›
አላት፡፡ ለሰው
የተለያየ ጸጋ ይሠጠዋል፡፡ ‹‹የጸጋ ሥጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ
ግን
አንድ ነው›› ይላል ሐዋርያው፡፡ የእመቤታችን ጸጋዋ ምን
ይሆን? ሰንል
ግን ይህ ነው ብሎ መወሰን አይቻልም፡፡ እግዚአብሔር
ለእርስዋ
ያልሠጠው ሀብት የለም ቅዳሴው ‹ወሀብተ ሰማያት ለማርያም
ድንግል›
‹የሰማያት ሀብት ለማርያም ድንግል ተሠጣት› እንደሚል
እመቤታችን
ጸጋ ሁሉ የተሞላች ናት፡፡ ስለዚህ መልአኩ በታላቅ አክብሮት
አመሰገናት፡፡
21 21 21
#ከንግግሩ_በጣም_ደነገጠች
°
እርስዋም ባየችው ጊዜ ‹ከንግግሩ በጣም ደነገጠች› የሶምሶን
ቤተሰቦች ማኑሔና አንትኮዬ የእግዚአብሔርን መልአክ ባዩ ጊዜ
እጅግ
ደንግጠው ነበር፡፡ ታላቁ መስፍን ጌዴዎን ደግሞ ‹ወዮልኝ
የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቼአለሁና› ብሎ
እንዳይሞት
ፈራ፡፡ እግዚአብሔር ግን አይዞህ አትሞትም ብሎ አረጋጋው፡፡ /
መሳ. 5፡
22/ ታላቁ ነቢይ ዳንኤል ደግሞ መልአክ ባየ ጊዜ ‹‹ደም
ግባቴም ወደ
ማሸብሸብ ተለወጠብኝ፥ ኃይልም አጣሁ። …. ቀጥ ብለህም
ቁም
አለኝ። ይህንም ቃል ባለኝ ጊዜ እየተንቀጠቀጥሁ ቆምሁ።››
በማለት
እንዴት እንደፈራ ይገልጣል፡፡ እመቤታችን ቅዱስ ገብርኤልን
ስታየው ግን
የደነገጠችው መልአኩን በማየትዋ አልነበረም፡፡ ‹‹የቃሉን
አነጋገር
አይታ›› እንጂ፡፡ (አይታ ሲል ሰምታ ለማለት ነው፡፡
ትርጓሜውም ርዕያ
ቅሉ ሰሚዓ ሲል ነው ይላል፡፡) መልአኩን ስታይ ተንቀጠቀጠች
፣ መቆም
አቅቷት ተብረከረከች የሚል ቃል የለም እርስዋ የደነገጠችው
በንግግሩ
ብቻ ነበር፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ነቢያቱ ሳይቀር
የደነገጡባቸው
መላእክት እንዴት አላስደነገጡአትም? አዎ እርስዋ ያደገችው
በመላእክቱ እቅፍ ስለሆነ ነው፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ
በአንድ ክንፉ
አቅፎ በአንድ ክንፉ ደግፎ ሰማያዊ ምግብ እየመገበ ያሳደጋት
እመቤታችን እንዴት መልአክ አይታ ትደነግጣለች? ነገሩን አልን
እንጂ
ራሳቸው መላእክት ሊያዩት የማይቻላቸውን አምላክ በማኅጸኗ
የምትይዘው እርስዋ እንዴት መላእክቱን ትፈራለች? ለእስዋ
እንግዳ
የሆነባት መልአክ መሆኑ ሳይሆን ሰላምታው ነበር፡፡
21 21 21
‹‹ #ይህ_እንዴት_ያለ_ሰላምታ _ነው; #ብላ_አሰበች››
°
አንዳንዶች እመቤታችን ስላደረገችው ነገር ብዙ አልተጻፈም
ብለው በመናገር ስለ እመቤታችን ለመናገር ስንነሣ ሊያሳቅቁን
ይሞክራሉ፡፡ ይህችን ጥቅስ ልብ ስንላት ግን ሐሴት
እናደርጋለን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ እመቤታችን ያደረገችውን ብቻ ሳይሆን
‹ያሰበችውንም›
ጭምር ጽፎልናል፡፡ ቅዱስ ሉቃስ መንፈስ ቅዱስ ገልጦለት
የእመቤታችንን ሃሳቧን ጻፈ! ሐዋርያቱ ሐሳቧን ሳይቀር ከጻፉ
እኛ
ተአምሯን ብንጽፍ ምን ጥፋት አለብን? ሃሳብ ከተጻፈ እንዴት
ተግባር
አይጻፍም?
እዚህ ላይ የምንማረው ታላቅ ትምህርት ልጅዋ ‹እኔ የዋህ
በልቤም ትሑት ነኝ› እንዳለው የእርስዋም ትሕትና የልብ
መሆኑን ነው፡፡
ሰው ሲመሰገን ‹ኸረ ለእኔ ይህ አይገባኝም› እያለ ላይ ላዩን በአፉ
ይቃወማል፡፡ በውስጡ ግን በምስጋናው ደስ ይለዋል፡፡
እመቤታችን ግን
ምስጋናን ስትሰማ ‹አይገባኝም› የሚል የአንደበት ንግግር
አልተናገረችም፡፡ ትሕትናዋ የልብ ነበርና ‹እንዴት ያለ ሰላምታ
ነው ብላ
አሰበች› መልአከ እግዚአብሔር ከፊቱ ቆሞ እያነጋገረው
የመልአኩን
ሰላምታ የሚመረምር ማን ነው; መልአክ ተገልጾ አመሰገነኝ
ብሎ
ሳይደነቅና ሳይደሰት ስለ ሰላምታው ምንነት ‹ይህ እንዴት ያለ
ሰላምታ
ነው;› ብሎ የሚያገናዝብስ ከሰው ልጅ መካከል ከእመቤታችን
በቀር
ማን ይገኛል;
21
መልአኩም ‹‹መልአኩም እንዲህ አላት፦ እርሱ ታላቅ ይሆናል
የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን
ዙፋን
ይሰጠዋል፤ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥
ለመንግሥቱም
መጨረሻ የለውም።›› አላት፡፡
እመቤታችን ሔዋንን ያሳተው የዲያቢሎስ ሽንገላ ወደ እርስዋ
የመጣ ይሆንን ስትል ከመልአኩ የቀረበላት ሰላምታ
አስደንግጦአት
ነበር፡፡ ምስጋና ከሆነ ዘንድ ብላ ጆሮዋን የምትሠጥ
ስላልነበረች ‹ጸጋን
የተመላሽ› ፣ ‹ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ› ያላትን ምስጋናም
ከደስታ ይልቅ
በፍርሃት ተመለከተችው፡፡ ግእዙ እንዲያውም ‹‹እፎኑ ዘከመዝ
እንጋ
አምኃ ይትአምኁ›› ‹‹እንዲህ ያለውን ሰላምታ እንደምን
ይቀበሉታል››
ብላ አሰበች ይላል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ‹‹ማርያም ሆይ፥
በእግዚአብሔር
ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።›› በማለት ‹ጸጋን የተሞላሽ›
ያላት
በእግዚአብሔር ፊት ያገኘችው ጸጋ እንደሆነ ነገራት፡፡ ከዚያም
‹‹እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም
ኢየሱስ
ትዪዋለሽ።›› በማለት አበሠራት፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ‹ኢየሱስ›
የሚለውን
ስም ለዓለም አስታወቀ፡፡ ክርስትናም በገብርኤል አንደበት ወደ
እኛ
መጣ፡፡
21 21 21
‹ #ወንድ_ስለማላውቅ_ይህ_እ ንዴት_ይሆናል?›
°
አንዲት በጋብቻ ለመኖር ፍላጎትና ዕቅድ ያላት ድንግል
‹ትወልጂያለሽ› ተብሎ /ያውም በመልአክ አንደበት/ ቢነገራት
ማንን
እንደምታገባ ፣ ነገሩ መቼ እንደሚፈጸም ወዘተ ትጠይቅ
ይሆናል እንጂ
ሊሆን እንደሚችል ስለምታውቅ ‹‹ወንድ ስለማላውቅ ይህ
እንዴት
ይሆናል?›› አትልም፡፡ ሣራ ትወልጂአለሽ መባሉን ስትሰማ
‹‹እንዴት
ይሆናል?›› ያለችው አርጅቼአለሁ ብላ ነበር፡፡ እመቤታችን ግን
ገና
የዐሥራ አምስት ዓመት ብላቴና ሆና ሳለ የከበረ መልአክ
ትወልጂያለሽ
ሲላት ‹እንዴት ይሆናል?› ማለትዋ ለምንድር ነው? ሊቃውንቱ
‹‹ዘንተ ትቤ
ድንግል በእንተ ዘኢዓርገ ሕሊና እጓለ እመሕያው ውስተ ልባ››
ሲሉ
ይመልሳሉ ‹‹ድንግል የሰው ልጆች ሃሳብ ወደ እርስዋ ልብ
ስላልደረሰ
ይህንን አለች›› ማለት ነው፡፡ እመቤታችን ‹እርሱ ታላቅ
ይሆናል የልዑል
ልጅም ይባላል ፤ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን
ይሠጠዋል ፤
በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለሙ ይነግሣል ለመንግሥቱ ፍጻሜ
የለውም›› ብሎ ስለምትወልደው ልጅ እየነገራት እንኳን
‹ወንድ
ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?› ብላ የምትጠይቅ የደናግል
መመኪያ
ናት፡፡ እግዚአብሔርም ነጻ ፈቃድዋን ሳይነካ ማኅተመ
ድንግልናዋን
ሳይለውጥ ከእርስዋ በኅቱም ድንግልና ተወለደ፡፡
21
በእስራኤል ብዙ ደናግል መሲሑን እንወልደዋለን ብለው
ድንግልናቸውን ጠብቀው የኖሩ አሉ፡፡ የቅዱስ ገብርኤል
ብሥራት
ከእነዚህ ደናግል ለአንዲቱ የተነገረ ቢሆን ኖሮ ‹ምኞቴ
ተፈጸመልኝ› ብላ
በተደሰተች ነበር፡፡ እመቤታችን ግን ራስዋን ለእግዚአብሔር
በንጽሕና
ስታቀርብ ለዚህ ክብር ራስዋን አስባ አታውቅም፡፡ ‹የባሪያዪቱን
ትሕትና
አይቶ› አምላክ ሲመርጣት እንዴት ይሆናል ያለችውም ለዚህ
ነበር፡፡
ቅዱስ ገብርኤል በእመቤታችን ፊት ቆሞ በጥያቄ ተያዘ፡፡
‹ቃሌን
ስላላመንህ ይህ ነገር እስከሚሆን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ› ብሎ
ከስድስት
ወራት በፊት የካህኑ ዘካርያስን አንደበት የዘጋው መልአክ
በአምላኩ እናት
ፊት ግን የተግሣጽን ቃል እንኳን አልተናገረም፡፡ ‹‹መንፈስ
ቅዱስ በአንቺ
ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ
ከአንቺ
የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።›› ብሎ
ጽንሰቱም
ልደቱም በረቂቅ አምላካዊ ጥበብ በግብረ መንፈስ ቅዱስ
እንደሚፈጸም
ነገራት ፤ በዘር በሩካቤ የተፈጸመ በመሆኑ በቂ ማስረጃ
ባይሆንም
የኤልሳቤጥን ከእርጅና ወዲያ መጽነስ ነገራት፡፡ በመጨረሻም
‹‹ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም›› አላት፡፡ እመቤታችን
የማይናወጥ እምነት አላትና ለእግዚአብሔር የሚሣነው ነገር
የለም
ስትባል በእርሱ ክሂሎት ላይ አንድም ቃል አልተናገረችም፡፡
12 21 2
‹‹#እነሆኝ_የጌታ_ባሪያ_እን ደቃልህ_ይደረግልኝ››
°
‹እነሆኝ› የሚለው ንግግር ራስን የማቅረብ ንግግር ነው፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ በአብዛኛዎቹ ቦታዎች ይህ ቃል የተቀመጠው
የተጠሩ
ሎሌዎች በጌቶቻቸው ፊት ሲቀርቡ በሚሠጡት መልስ ላይ ፣
እግዚአብሔር በቀጥታ የጠራቸው እንደ ሳሙኤል ያሉ ነቢያትና
ቅዱሳን
ያቀረቡት ራሴን አቅርቤአለሁ የሚል የትሕትና ንግግር ነው፡፡
እመቤታችንም ራስዋን ለአምላክ ማደሪያነት ‹እነሆኝ› ብላ
አቀረበች፡፡
ሌላው አስደናቂ ነገር ደግሞ ‹የጌታ ባሪያ› ብላ ራስዋን
መጥራትዋ
ነው፡፡ ‹የአምላክ እናት› ትሆኚ ዘንድ ተመርጠሻል ተብላ እንኳን
በትሕትና
የምትናገረዋ ተራራ እመቤታችን ‹የጌታ ባሪያ› ብላ ራስዋን
ጠራች፡፡
እንደ ቃልህ ይደረግልኝ ስትል አምላክ በማኅጸንዋ አደረ፡፡
ምሥጢረ ተዋሕዶ ተከናወነ፡፡ የማይታየው ታየ ፤ የማይወሰነው
ተወሰነ፡፡
የአምላክ የማዳን ሥራ የእመቤታችንን የይሁንልኝ ንግግር
ተከትሎ
ተወጠነ፡፡ እመቤታችን ‹ይሁንልኝ› እስክትል ድረስ የተጀመረ
የማዳን
ሥራ አልነበረም፡፡ ሁሉ የሚቻለው አምላክ እንኳን የከበረ
መልአኩን ልኮ
‹ይሁንልኝ› ስትል ጠብቆ ነው ሥራውን የጀመረው፡፡
21
ምናልባት እዚህ ላይ አንድ ሰው ተነሥቶ የእመቤታችንን ድርሻ
አልታየኝም ሊል ይችላል፡፡ ሌላውን እንተወውና እመቤታችን
ይሁንልኝ
የሚለውን ቃል ሳትናገር ለጥቂት ደቂቃዎች ብትዘገይ እንኳን
የሰው ልጅ
መዳን የዚያኑ ያህል ይዘገይ ነበር፡፡ አንድ ቀን ሙሉ ዝም
ብትልም አንድ
ቀን ይዘገይ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤል እንደሆን ተልዕኮውን
ሳይፈጽም
አይሔድም ፤ በግድ እሺ ሊያሠኛትም አይችልም፡፡
እግዚአብሔር ነጻ
ፈቃድዋን ጠብቋል፡፡ እንኳን ከእርስዋ ሊወለድ ለመረጣት
ቅድስት ቀርቶ
ከሕመሙ ሊፈውሰው ያሰበውንም ድውይ ፈቃድ የሚጠይቅ
የነጻነት
አምላክ ነው፡፡ ስለዚህ የእመቤታችን ‹ይሁንልኝ› ማለት ለእኛ
ድኅነት
ወሳኝ ነበር፡፡ የእመቤታችን ንግግር በሲኦል ያሉ ነፍሳት ሳይቀር
‹እሺ
በይ› ብለው የሚጮኹበት የተስፋቸው መጀመሪያ ነው፡፡
እመቤታችንም
ሙሉ ፈቃደኛ ነበረች፡፡ ‹‹ይሁንልኝ›› እንጂ ‹‹ይሁንብኝ››
አላለችም፡፡
ይሁንልኝ የሚለው ቃል በሙሉ ደስታ መቀበልን ያሳያል፡፡
ንግግርዋ
‹መቼስ ከታዘዘብኝ› የሚል ዓይነት በቅሬታ መቀበል
አልነበረም፡፡ በሙሉ
ደስታ ‹‹ይሁንልኝ›› ብላ ተቀበለች እንጂ፡፡
21 2
#እመቤታችን_እና_ኤልሳቤ ጥ
‹‹ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች … ኤልሳቤጥንም
ተሳለመቻት››
°
እመቤታችን በብሥራተ መልአክ በፈቃደ አምላክ ጌታን
ከጸነሰች
በኋላ በቀጥታ በመልአኩ አንደበት መጽነስዋ ወደተነገረላት
ዘመድዋ
ወደ ኤልሳቤጥ ለጉዞ ተነሣች፡፡ ይህ ጉዞ ላይ ላዩን ስናየው
ከአንድ ቦታ
ወደ ሌላ ቦታ መሔድ ይምሰል እንጂ በውስጡ እጅግ ትልቅ
ትምህርት
አለው፡፡ ኤልሳቤጥን ለመጠየቅ መሔድዋ ፣ ፈጥና መሔድዋ
እመቤታችን እንደምን ያለ ትሕትና ቢኖራት ነው የሚያሰኝ እና
በትዕቢት
ለተሞላው ዓለም እጅግ ትሕትናን የሚያስተምር ነው፡፡
ሰማያዊ መልአክ መጥቶ አመስግኖ አምላክን እንደምትወልድ
ነግሯት ፣ ከሴቶች ሁሉ የተባረከች እንደሆነች በእግዚአብሔር
ፊትም
ጸጋን እንዳገኘች ነግሯት ፣ ከተነገራትም በላይ ደግሞ ሰማይን
ያለ ባላ
ምድርን ያለ ካስማ ያቆመን አምላክ በማኅጸንዋ ይዛ
እመቤታችን
ዘመድዋን ኤልሳቤጥን ልትጠይቅ ሔደች፡፡ ይህን ማን
ያደርገዋል?
21
ሰው ችግርን ማጣትን ረሃብ ወዘተ መቋቋም እየቻለ ክብርን
ግን መቋቋም አይችልም፡፡ ከፍ ከፍ ባለ ቁጥር ብዙ ሰው
በትዕቢት
ይፈተናል፡፡ ሥልጣን ሲሠጠው የብዙ ሰው መልካምነት
ይጠፋል፡፡
መንፈሳዊ ጸጋ ሲሠጠው ደግሞ የበለጠ ይፈተናል፡፡ በሥልጣን ፣
በዕውቀት ፣ በጸጋ ወዘተ ብዙዎች ማንነታቸውን አጥተዋል፡፡
እመቤታችን
ከፍጥረት ሁሉ በላይ ናት፡፡ ሰው ምንም ዓይነት የቅድስና ደረጃ
ላይ
ሊደርስ ይችላል ፤ ከእመቤታችን ክብር ግን ማንም
አይደርስም፡፡ ሰማዕት
መሆን ፣ ጻድቅ መሆን ይቻላል፡፡ የአምላክን እናት መሆን ግን
አይቻልም፡፡
(ንግሥት ዕሌኒ ‹የክርስቲያኖች እመቤት አንቺ ትሆኚ;› ብለው
ሲጠይቋት
‹‹የእግርዋን እጣቢ እንኳን አላህልም›› እንዳለችው ነው)
እመቤታችን
በሥልጣን ቢባል ከፍጥረት ሁሉ በላይ ናት እንኳን ስለ እርስዋ
ስለ ስሟ
እንኳን ‹‹ስምሽም በእግዚአብሔር ዘንድ የሠለጠነ ነው››
ብሏል ሊቁ፡፡
በዕውቀት ቢባል ብትናገረው ሰማይና ምድር የማይሸከሙት
እርስዋ ግን
በልብዋ የጠበቀችው ከሰው አእምሮ በላይ የሆነ የጥበብ
መዝገብ ናት
፤ እኛ ተምረን የማንጨርሰው ምሥጢረ ሥጋዌ የተፈጸመው
በእርስዋ
ሰውነት ነው፡፡ በጸጋም ለእርስዋ ያልተሠጣት ምንም የለም፡፡
ሆኖም
በትሕትና ዘመድዋን ልትጠይቅ ተነሣች፡፡ አካሔድዋም
የንግሥትነት
የኩራት አልነበረም፡፡ ይልቁንም ‹ፈጥና ወጣች› ነው
የሚለው፡፡ መቅደስ
ሆና ሳለ ፍጥረት ሊሳለማት የሚገባት ሆና ሳለ ‹‹ኤልሳቤጥን
ተሳለመቻት›› አምላክን በማኅጸንዋ ይዛ ፍጥረት የሚሳለማት
እመቤታችን በትሕትና ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት፡፡
ሰዎች /እውነትነቱ ያልተረጋገጠ/ ራእይ አይተናል ፣
ተገልጦልናል ፣ እንፈውሳለን ወዘተ ብለው ራሳቸውን ክበው
በሚኖሩበት
፣ በሀብታቸው በዝናቸው በእውቀታቸው ምክንያት ጠባያቸው
በሚከፋበት
፣ ወዳጅነታቸው በሚለወጥበት ዓለም ላይ ሆነን እመቤታችንን
ስናስባት
ምን ይሰማን ይሆን?
21 21
#የጌታዬ_እናት_ወደ_እኔ_ ትመጣ_ዘንድ_እንዴት_ይሆ ንልኛል
?
°
ሕገ ኦሪት ሲሠራ እንደነበረችው የካህኑ አሮን ሚስት ኤልሳቤጥ
ሁሉ ሕገ ወንጌል ስትሠራ ለመመስከር የታደለችው ሁለተኛዋ
ኤልሳቤጥ
ወደ እርስዋ የመጣችውን የዐሥራ አምስት ዓመት ብላቴና
እናትዋ
ልትሆን የምትጅልበት እድሜ ላይ ብትሆንም እንደ ታናሽ ልጅ
አልተቀበለቻትም፡፡ እመቤታችን በትሕትና ብትሳለማትም
ዝም ብላ
አልተመለከተቻትም፡፡ ገና የእመቤታችንን ሰላምታ በሰማች
ጊዜ መንፈስ
ቅዱስ ሞላባት፡፡ የእመቤታችን ሰላምታ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ
እምዲመላብን ያደርጋልና ኤልሳቤጥን መንፈስ ቅዱስ
አናገራት፡፡
በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። ‹‹አንቺ ከሴቶች
መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።
የጌታዬ እናት
ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ፥ የሰላምታሽ
ድምጽ
በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና። ከጌታ፤
የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።››
የዕድሜ ባለጸጋዋ ኤልሳቤጥ ኃይል አግኝታ ታላቅ ድምፅ
አሰማች፡፡ ኤልሳቤጥ ውዳሴ ማርያም ነው የጮኸችው፡፡
መንፈስ ቅዱስ
የሞላበት ሰው ንግግሩ እመቤታችንን ከነልጅዋ ምስጋና
ማቅረብ ነው፡፡
ኤልሳቤጥ ‹አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማኅጸንሽም ፍሬ የተባረከ
ነው› ብላ
ጌታን ከእናቱ ጋር እንዳመሰገነች እኛም አባታችን ሆይ ብለን
እመቤታችን
ሆይን እናስከትላለን፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ‹አንቺ ሴቶች ተለይተሸ
የተባረክሽ
ነሽ› ሲል ኤልሳቤጥ ‹የማኅጸንሽም ፍሬ ቡሩክ ነው› ብላ
እንደጨመረችበት እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ እየተቀባበልን
እናመሰግናታለን፡፡
ኤልሳቤጥ እመቤታችንን ‹የጌታዬ እናት› አለቻት ወላዲተ
አምላክ ፣ እመ አምላክ ፣ እመ ብርሃን የምንለው እንግዲህ
ከዚያ
ወዲህ ነው፡፡ የካህን ሚስት ናትና መቅደስ እመቤታችንን
እንደምን
መጥራት እንዲገባን አስተማረችን፡፡ አስከትላም አንዳች
አስደናቂ
ምስክርነት ሠጠች፡፡ ‹የሰላምታሽ ድምፅ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ
ጽንሱ
በማኅጸኔ በደስታ ዘሎአል› አለች፡፡
መቼም ሳይንስ አዋቂ እንደሚረዳው ያም ባይሆን እናቶቻችን
እንደሚያውቁት የስድስት ወር ጽንስ በማኅጸን ሳለ መዝለሉ
የተለመደ
ተፈጥአዊ ክስተት ነው፡፡ እርግጥ አንድ ክስተት ሲደጋገም ድንቅ
መሆኑ
ስለሚቀር ነው እንጂ እንኳን የጽንስ መዝለል የጽንስ መፈጠር
ራሱ እጅግ
አስደናቂ ነበር፡፡ ግን አንዱ ተነሥቶ ‹‹ማንኛዋም ተራ ሴት
ልታውቀው
የምትችለውን ነገር ለምንድን ነው ተአምር አድርጋችሁ
የምታወሩት?››
ሊለን ይችላል፡፡ አዎ ማንኛዋም ጻድቅት ያልሆነች ወይም
እንደ
ኤልሳቤጥ መንፈስ ቅዱስ ያልሞላባት ሴት ጽንስ በማኅጸንዋ
መዝለሉን
ልታውቅ ትችላለች፡፡ ማንኛዋም ሴት ግን ጽንሱ በማኅጸንዋ
የዘለለው
በደስታ ይሁን በኀዘን ልታውቅ አትችልም፡፡ ልብ አድርጉ
ኤልሳቤጥ
ያለችው ‹‹ጽንሱ በማኅጸኔ ዘለለ›› ሳይሆን ‹‹ጽንሱ በማኅጸኔ
በደስታ
ዘለለ›› ነው፡፡
21
እኛ ኢትዮጵያውያን ምዕመናን መቼም ‹ማርያም ማርያም›
ተብለን ተወልደን ፣ ‹እንኳን ማርያም ማረችሽ› ‹ማርያም
ታኑርህ/ሽ›
ተባብለን ነው የኖርነው፡፡ በብዙ ሆስፒታሎች የማዋለጃ ክፍል
ውስጥ
የእመቤታችንን ሥዕል ማኖር የተለመደ ነው፡፡ አንዳንዶች
ታዲያ ‹ድንግል
ማርያምን ከጽንስ ጋር ምን ያገናኛታል?› ብለው ይንገሸገሻሉ፡፡
መጽሐፍ
ቅዱስን የሚያውቅ ሰው እንዴት ይኼን የሚያስገምተውን
ጥያቄ
ይጠይቃል? በመጽሐፍ ቅዱስ ባሕር ሲዋኙ ለኖሩና ባሕላችንን
በመጽሐፍ ቅዱስ ቃኝተው ላስረከቡን አበው ሊቃውንት ምስጋና
ይሁንና
ጽንስና እመቤታችንን ምን ያገናኛቸዋል የሚለውን ጥያቄ
እንግዲህ
‹የሰላምታሽ ድምፅ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ጽንሱ በማኅጸኔ
በደስታ
ዘሎአል› ያለችውን ኤልሳቤጥን መጠየቅ ነው፡፡ እኛ
የእመቤታችንን
ድምጽ ለጸነሱ ሴቶች ማሰማት ባንችል ስሟን እንዲሠሙ
ብናደርግ ማን
ይከለክለናል?
ቅዱስ ዮሐንስ ገና በእናቱ ማኅጸን ሳለ የእመቤታችንን ድምፅ
ሰምቶ
ዘለለ፡፡ ሐዋርያት በሲኖዶስ ፣ ቅዱስ ያሬድም እንዲሁ ሰገደ
ብለው
ተርጉመወታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ተፈጥሮ ገድቦት ነው እንጂ
ከእናቱ
ማኅጸን ወጥቶ ቢሆን ኖሮ ‹የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ
ዘንድ እንዴት
ይሆንልኛል?›› ይል እንደነበር ጥርጥር የለውም፡፡ ይህን
እንዴት
አወቃችሁ ብንባል የመጥምቁን ጠባይ መች አጣነውና ጌታ
ሊጠመቅ
ወደ እርሱ ሲሔድ ‹‹እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም
ወደ እኔ
ትመጣለህን?›› ብሎ ሲናገር አየነው አይደል? በእናቱ ወጥቶ
ይሆን?
ለነገሩ የወጣው እንኳን በሁለቱም ነው፡፡ እናቱ ‹‹አንቺ ከሴቶች
ተለይተሸ
የተባረክሽ ነሽ የማኅጸንሽ ፍሬ ቡሩክ ነው›› ስትል ሰማን ፣
አባቱ ደግሞ
አንደበቱ ሲከፈትለት ‹‹የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ›› አለ
(ሉቃ.
፩፥፰፰) በወላጆቹ የወጣው ዮሐንስም አምላኩን ሲያጠምቅ
‹የቡሩክ
ልጅ ብርሃንን የምትገልጥ ይቅር በለን…› ብሎ አጠመቀው፡፡
የተባረከ
ቤተሰብ!
ከዚህ በኋላ እመቤታችን ‹ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ
ታደርገዋለች› የሚለውን ጸሎት ተናገረች፡፡ ይህ የእመቤታችን
ጸሎት ሰፊ
ምሥጢር ያለው ነው፡፡ ሁለት ነገሮች ብቻ ግን እናነሣለን፡፡
የመጀመሪያው አስደናቂ ነገር ለነቅዱስ ኤፍሬም ለነአባ
ሕርያቆስ
ምሥጢር ገልጣ ‹የጸጋህን ማዕበል ያዝ› እስኪሉ ድረስ እንግዳ
ድርሰት
እንዲደርሱ ያደረገች እመቤታችን ራስዋ በጸለየችው ጸሎት ግን
አብዛኛው ክፍል የአባቶቿ ነቢያት ጸሎት መሆኑ የእመቤታችንን
ትሕትና
ሲያስደንቀን ይኖራል፡፡
ሁለተኛው ነገር ‹ከእንግዲህስ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል
እርሱ ታላቅ ሥራን ለእኔ አድርጓልና› ያለችው ነው፡፡
እመቤታችን ሥጋዊ
የመመስገን ፍላጎት ኖሯት ‹ብፅዕት ይበሉኝ› የሚል ትእዛዝ
አልሠጠችም፡፡ የተናገረችው ትንቢት ነው እንጂ፡፡ ‹‹ትንቢት
ከቶ በሰው
ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን
ሰዎች
በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።›› ይላል መጽሐፉ (፪ጴጥ.
፩፥፳፩)
እመቤታችንን ማመስገን ሰዎች ሊያስቆሙት የማይችሉት
ከመላእክት
የተቀበልነው ፣ ከኤልሳቤጥ የተማርነው በትንቢት የጸና አደራ
መሆኑን
እናስታውሳለን፡፡
21 21 21
#እመቤታችን_ለምን_አልመጣ ችም?
°
በሉቃስ ወንጌል የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እና በሌሎቹም
ወንጌላት ጌታችን በመቃብር ባደረ ጊዜ የነበረውን ሁኔታ
እናነባለን፡፡
በተለይም በተነሣበት ሌሊት ሴቶች ሽቱ ይዘው ሥጋውን ሊቀቡ
መጥተው
ነበር፡፡ ሆኖም መቃብሩ ባዶ ሆኖ አገኙት ፤ በመላእክትም
አንደበት ስለ
ጌታችን ትንሣኤ ተነገራቸው፡፡ ለሐዋርያትም ተናገሩ፡፡ ይህ ሁሉ
ሆኖ ግን
ቅዠት መስሎ የታያቸው ይበዙ ነበር፡፡
ጌታችን በመስቀል መከራ ተቀብሎ በሞተ ጊዜ ልብዋ በኀዘን
የቆሰለው እመቤታችን ነበረች፡፡ ምንም እንኳን የመሰቀሉን
ዓላማ
ብታውቅም የተቀበለው ለኅሊና የሚከብድ መከራ ግን እንኳን
አቅፋ
ያሳደገችውን ቅድስት እናቱን ለሚሰማው ሁሉ የሚያስለቅስ
ነበር፡፡
እመቤታችን እስከመጨረሻው ድረስ በመከራው አብራው
ነበረች፡፡ እንደ
ቅዱስ ጴጥሮስ ‹አይሁንብህ!› ብላ ከማዳን ሥራው ወደ ኋላ
ያልጎተተችው የፍቅርዋ ጽናት ጎድሎ አይደለም፡፡ ያለ እሱ ሞት
የዓለም
ድኅነት እንደማይሆን ተረድታ እንጂ፡፡
21
በመከራው ያልተለየችው ፣ በመስቀሉ ሥር ከነበሩት ቅዱሳት
አንስት ዝርዝር ውስጥ በቀዳሚነት የተጠቀሰችው እመቤታችን
እሑድ
ደርሶ ሴቶች ወደ መቃብሩ ሽቱ ይዘው ማልደው ሲሔዱ ግን
ከእነርሱ
ጋር አልነበረችም፡፡ ለምን? ከእርስዋ በላይ የልጅዋ ሥጋ ሽቱ
እንዲቀባ
ማን ሊያስብ ይገባል? እንደምንስ አስቻላት? ነገሩ ወዲህ ነው!
እመቤታችን ልጅዋ ሞትን ድል አድርጎ እንደሚነሣ ታውቅና
ታምን ነበር፡፡
ስለዚህ ሕያዉን ከሙታን መካከል ልትፈልግ አልተነሣችም፡፡
አባቷ
አብርሃም ልጁን ይስሐቅ እንዲሞት ሲፈቅድ እግዚአብሔር
ልጄን ከሞት
ያስነሣልኛል ብሎ እንዳመነ እመቤታችንም የተወደደ ልጅዋን
እግዚአብሔርነቱ ‹ከሙታን እንኳን ሊያስነሣው እንዲቻለው
አስባለች፡፡› (ዕብ. ፲፩፥፲፱)
21
ምንጭ:-
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ነሐሴ 2005
የዚህን ጽሑፍ የትግርኛ ትርጉም ማንበብ ለምትችሉ ወይም
የምትፈልጉ https:// www.facebook.com /
photo.php?
fbid=8933399507 28526&set=a.363
600530369140.84 551.10000157588
2711&type=1&pnr ef=story
21
የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣
የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣
የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት
አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው
ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
†† † † ††
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት
ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን
፤ አሜን!!!
†† † † ††
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን
እንደገለጽክላቸው ለእኛም ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!!
†† † † ††
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክ ቡ ር

Wednesday, March 30, 2016

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: ©ኦርቶዶክስተዋህዶነኝ®™ “ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ፡፡” መ/ዕዝ. ሱቱ. 2፡1

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::
በፍጹም መጠበቅን ጠብቆ ለዚህ ያደረሰን አምላካችን ክብርና
ምስጋን አምልኮትና ውዳሴ ይድረሰውና ይህን ታላቅ መልአክ
በችሎታችን መጠን እንድናመሰግን እግዚአብሔር ይርዳን፤
አምላክ ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን፤ ምስጢሩን ይግለጥልን
አሜን፡፡
“ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ፡፡” መ/ዕዝ. ሱቱ. 2፡1
በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ
ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው
ያነሡሃል።
በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን
ትረግጣለህ ::
በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና
እጋርደዋለሁ። ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም
ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውለሁ። ረጅምን
ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ። መዝ.
90/91/፡11-16
አፈቅሮ ፈድፋደ፡- ዑራኤል ሆይ፣ ከመልኮች ሁሉ ይልቅ ያንተን
መልክአ ጸሎት እወዳለሁ፡፡ የመልክህ ስነ ጸዳል በደመ ወልድ
እግዚአብሔር የታተመ ነውና፡፡
ዑራኤል ሆይ፣ እግዚአብሔር ሀይሉን የሚገልጽብን መልአከ
ብርሃናት አንተ ነህ፡፡ በዐለተ ሥቅለት በደመ ወልድ ዓለምን
ለመቀደስ ከሁሉ ይልቅ አንተ ተሰይመሃልና፡፡ ስለክብርህ
የሰማይ መላእክት አደነቁ፡፡
ለተፈጥሮትከ፡-
ዑራኤል ሆይ፡- ያለ መናገር በጥንት አርምሞ ከነፋስና ከእሳት
ለተፈጠረ ተፈጥሮህ ሰላም እላለሁ፡፡ ዑራኤል ሆይ የተፈጥሮና
የይቅርታና የቸርነት ክቡር መልአክ ነህና ስለኛ ስለሰው ልጆች
ወደ ልዑል እግዚአብሔር ማልድ አማላጅነትህ ዘወትር ከጥፋት
ያድናልና፡፡
ለዝክረ ስምከ፡-
ዑራኤል ሆይ፡- ከማርና ከወተት ይልቅ ለሚጥመው ስም
አጠራርህ ሰላም እላለሁ፡፡
ዑራኤል ሆይ፡- ክፍልህ /ክንፍህ/ በደመ ወልድ እግዚአብሔር
የተከበረ /የታለለ/ ነውና፡፡ ለዓለሙ ሁሉ መድሃኒት ትሆን ዘንድ
ግሩም የሚሆን የእግዚአብሔር ሥልጣን በክብር ከፍ ከፍ
አደረገ፡፡ (መልክአ ዑራኤል)
“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥
ያድናቸውማል።” መዝ.33/34/፡7 የሊቀ መልአኩ የክዱስ
ዑራኤል ረድኤቱ በረከቱ ፍጹም አማላጅነቱ ከሁላችን ጋር
ይሁን፡፡
ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኝ፣ ካለማወቅ ወደ መረዳት
ያደረሰኝ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ጥንት
ላሌለው ቀዳማዊ ፍጻሜ ላሌለው ድህራዊ ያልኖረበት ጊዜ
የሌለ የማይኖርበት ጊዜም የማይኖር የዘላለም ንጉስ ሁሉን
ቻይ ፈጣሪ እግዚአብሔርን በራስ ፀጉሬ ቁትር በአጥንቶቼም
ልክ አመሰግናለሁ፡፡
በሰማይ ያሉ መላእክት በምድርም የሚኖሩ የአዳም ዘር ሁሉ
የሚያመሰግኗት በአማላጅነቷ ሁል ጊዜ የማትለየኝ ከፀሐይ
ሰባት እጅ የምታበራ የብርሃን እናት የሁሉ እመቤት የአምላክ
እናት ከተመረጡ የተመረጠች ከተለዩ የተለየች ከተከበሩ
የተከበረች እናቴ እመቤቴ ድንግል ማርያም በቃላት ልገልጸው
ከምችለው በላይ አመሰግናለሁ፡፡ ሌሊትና ቀን ቅዱስ ቅዱስ
ቅዱስ እያሉ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑና
ሳይሰለቹ የሚጠብቁን ሊቀነ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ
ገብርኤል ቅዱስ ሩፋኤል ቅዱስ ዑራኤል ቅዱስ ራጉኤል ቅዱስ
ፋኑኤል እልፍ አእላፋት የሆኑ ጠባቂ መላእክት ሳመሰግን
በደስታ ነው፡፡
በጸሎታቸው ያልተለዩኝን ጻድቃን አባቶቼን አቡነ
ተክለሃይማኖትን አቡነ ገብረምንፈስ ቅዱስን አቡነ
ሀብተማርያምን አቡነ አረጋዊን አቡነ ኪሮስንና ሌሎች ቅዱሳን
አባቶቼን እንዲሁም እናቶቼን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራን
ቅድስት አርሴማን ብዙ ያልጠቀስኳቸው ቅዱሳንን ለማመስገን
ቃላት የለኝም፡፡
በሰማኝትነታቸው የጥንካሬ ምሳሌ የሆኑልኝ በጸሎታቸው
የረዱኝን ቅዱሳን ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ቅዱስ
እስጢፋኖን መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስንና ሌሎችን
ቅዱሳን ሰማዕታትን ሁሉ በእጅጉ አመሰግናለሁ ለዘላለሙ
አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ
ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: 21

21 21 21 21 21 21 21
# ራእየ_ማርያም
21 21 21 21 21 21 21
# እመቤታችን_በጎልጎታ_ስጸ
ልይ_ልጇ_ፈጣሪዋ_ጌታችን
_አምላካችንና_መድኃኒታች ን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_የገ
ለጸላት_ምሥጢር_ራእየ_ማ ርያም ቀርቧልና ይነበብ...
21 21 21 21 21 21 21
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ንዌጥን
በረድኤተ እግዚአብሔር ሕያው ራእየ ማርያም ወላዲተ
አምላክ ጸሎታ ወበረከታ የሃሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም
አሜን።
21
ማርያም ለዮሐንስ እንዲህ አለችው ረቂቅ ምሥጢር በልቡናየ
የማይታወቅ ጌታዬ ፈጣሪዬ ልጄ የገለጸልኝ ምሥጢር በጎልጎታ
ስጸልይ ዐርብ ቀን በቀትር ብሩህ ደመና መጥቶ ከ፫ቱ ሰማያት
አውጥቶ አስቀመጠኝ ሁሉንም አሳየኝ ከአንቺ ከፈለገ ሰማይ
ተወልጃለሁና አንቺም ሰላምታ ይገባሻል እኔም ዕጹብ ድንቅ
ምሥጢርን እገልጽልሻለሁ አለኝ። እኔም መለስኩለት ጌታዬ
ፈጣሪዬ እንዳልህ ይሁን አልሁት ወደታች እይ አለኝ ወደ ታች
ስመለከት ዓለምን ሁሉ አየሁ ሰብእሰ ከንቶ የመሰል
መውዋዕሊሁኒ ከመ ጽላሎት የኃልፍ ሰው ከንቱ ነገርን
ይመስላል ዘመኑም እንደ ጥላ ያልፋል ይጠፋል ነፍሱም
ከሥጋው ትለያለች ለዘለዓለም አትኖርም የምትኖርበትም
አይታወቅም መዝሙር ፻፵፫:፬
21
እንግዲህ ሰው ሁሉ በከንቱ ነውን አልሁት እሱም መልሶ ዳዊት
ያለውን አልሰማሽምን አለኝ ሰው ሁሉ በከንቱ ለምን ይኮራል
ዕለት ዕለትስ ለምን ኃጢአት ይሠራል ዳግመኛስ ጢስ ታይቶ
እንደሚጠፋ የሰውም አኗኗር እንዲሁ ነው አለኝ መዝሙር
፶፩:፩። እኔም መለስሁለት የጻድቃን ነፍስ ከሥጋዋ ስትለይ
አሳየኝ አልሁት። መለሰልኝ ጥቂት ቆዪ አሳይሻለሁ አለኝ።
ከዚህ በኋላ ፲፪ መላእክተ ብርሃን በእጃቸው የወርቅ መስቀል
የወርቅ ጥና ይዘው በደረታቸው የእግዚአብሔርን ምልክት
አድርገው የጻድቃንን ነፍስ ለመቀበል ሲወርዱ አየሁ።
ወደዚያች ነፍስ መላእክተ ጽልመትም መጥተው መረመሯት
ምክንያትም አጥተው ሄዱ መላእክተ ብርሃን ግን ፫ ጊዜ
ጋርደው ከሥጋዋ ስትለይ እንዲህ አሏት ደስ ሲያሰኛት
ሲመክሩዋት አንቺ ንጽሕትና ብርሕት ነፍስ ሆይ ደስ ይበልሽ
ዕፅፍ ድርብ ደስታ ይገባሻል ነይ ውጪ ወደ አገርሽ እንሂድ አሏት
አንቺ ንጽሕት ብርህት ነፍስ ሆይ ቅዱስ ዳዊት የዕድሜዬን
መጠኑን ንገረኝ በእኩሌታው ዕድሜዬ አትውሰደኝ ያለውን
አስተውለሻልና። መዝሙር ፻፩:፳፬።
21
ዳግመኛም ጳውሎስ ዛሬ የሚገዙ የሚነዱ ኋላ እንዳልገዙ
እንዳልነዱ ይሆናሉ ዛሬ የሚበሉ የሚጠጡ ኋላ እንዳልበሉ
እንዳልጠጡ ይሆናሉ። የዚህም ዓለም ንብረት ብልጽግና ኃላፊ
ጠፊ መሆኑን አስበሽ ዲያብሎስን ድል ነስተሽዋልና ዓለምንም
ንቀሽ ጉዱፍ እንደሆነ እንደመርገም ጨርቅ ጥለሽዋልና
የማያረጀውን የማይጠፋውን መርጠሻልና ለዘለዓለም የሚኖር
መንግሥተ ሰማያትን ወደሻልና ነይ ወደ ፈጣሪሽ እንሂድ አሏት
የዚያን ጊዜ ሌሎች መላእክተ ብርሃን ወረዱ የወርቅ ዝርግፍ
ዕንቁ የብርሃን ቀጸላ ፲፪ የብርሃን መብራት ይዘው ከብርሃን
አክሊሎች ጋር ወረዱ ብርሃናቸውም ከፀሐይ ከጨረቃ ፯ እጅ
ያበራል ክርስቶስም ከ፭ኛው ሰማይ ድረስ መጣ እኔም ያችን
ነፍስ ለመገናኘት ሄድኩ መላእክተ ብርሃን ዕልል አሉ እኔም
ከእርሳቸው ጋር ዕልል አልኩ ምእመናን ሁሉ በእጃቸው
አጨበጭበው በቃላቸው ዕልል ብለው ለእግዚአብሔር
ምሥጋና አቀረቡ ዳግመኛ ክብር ሞቱ ለጻድቃን በቅድመ
እግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው እንዳለ መዝሙር ፻፲፭:፮።
21
ያችን ነፍስ ወደ እግዚአብሔር አቀረቧት ነፍስ ሆይ ደስ ይበልሽ
ደስታ ይገባሻልና ወደ ፈጣሪሽም እጅ ንሺ ስገጂ አሏት እርሷም
ሰገደች ፈጣሪዋንም እጅ ነሳች አስቀድሞ ይጠብቃት የነበረው
መልአክ እግዚአብሔርን እንዲህ አለው አቤቱ የዚያች ነፍስ
ምግባሯን ነገርኩት እንደ አውነተኛነቷ አክብራት አለው
በእውነት የሚፈርድ ጌታም እንደፈጠርኩሽ ንጽሕት ሆነሽ
የኖርሽ ነፍስ ሆይ እንዴት ነሽ ቃሌን ያላቃለልሽብኝ
ያላበላሸሽብኝ እኔም አላበላሽሽም ሥጋሽንም በጊዜ ምጽአት
አነሣዋለሁ በክብር ከእኔ ዘንድ ትኖሪያለሽ ብሎ በሰው እጅ
ያልተፈተለ ከወተት የነፃ ነጭ ልብሽ ሰጣት ከፀሐይ ከጨረቃ ፯
እጅ የሚያበራ ፫ አክሊለ ብረሃን አቀዳጃት ሚካኤልን ጠርቶ
ንሳ ወደ ገነት ውሰዳት በአብርሃም በይስሐቅ በያዕቆብ አጠገብ
ተቀምጣ በደስታ ትኑር ዳግመኛ እስክመጣ ድረስ ያንጊዜ
ዋጋዋን እከፍላታለሁ ከቅዱሳን ጋር ትቆየኝ አለው፡፡
21
መላእክተ እግዚአብሔርም ይህን ፍርድ በሰሙ ጊዜ አቤቱ
ጌታችን ፍርድህ የተቃና አገዛዝህም በእውነት ነው ብለው ደስ
አላቸው እኔም እንደነሳቸው ደስ አለኝ ያችንም ነፍስ ሸኙዋት
ወደ ገነትም አደረሷት ጻድቃን ሰማዕታት አብርሃምና ይስሐቅ
ያዕቆብ አባቶቻችን እናቶቻችን ባሉበት ቅዱስ ዳዊት
በመካከላቸው በገናውን እየመታ ተቀበሏት እንዲህም አሉዋት
ንጽህትና ብርሕት ነፍስ ሆይ ለዘለዓለም የሚኖር ደስታ ሕይወት
ወደ አለበት ነይ ውጪ አሏት ያችም ነፍስ ከነሱ ጋራ ሄደች፡፡
21
እኛም ከዚህ በኃላ ተመለስን እነኛም እንዲህ እያሉ ሃሌ ሉያ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ፀባኦት ፍጹም ምሉዕ
ሰማያት ወምድር ቅዱሳተ ስብሐቲከ ዳግመኛም ስብሐት ለአብ
ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ እያሉ ፈጣሪያቸውን
አመሰገኑ እኔም ልጄን እንዲህ ስል መለስሁለት የኃጥአን ነፍስ
ከሥጋዋ ስትለይ አሳየኝ አልሁት ጥቂት ቆዬ አሳይሻለሁ አለኝ
ወደታችም አየሁ መላእክተ ብርሃንና መላእክተ ጽልመት ወደ
ኃጥእ ነፍስ ሄዱ መላእክት ብርሃን ቀርበው ያቺን የኃጥእ ነፍስ
መረመሩዋት መልካም ነገር አጥተው ሄዱ ያን ጊዜውን
መንፈስ ቅዱስ ተለያት የገሃነም እሳት ሹም ቆሞ ከሆዷ ገባ ያቺ
ነፍስ በብዙ ጭንቅ ከሥጋዋ ተለየች ሞቱ ለኃጥእ ጽዋግ የኃጥእ
ሞት የከፋ ነው እንዳለ መዝሙር ፴፫:፳፩
21
በክፋቷ በእሳት በትር በእሳት አለንጋ እየደበደቡ እያገረፉ ከሥጋዋ
ለይተው ወሰዷት አንቺ ነፍስ ወደ ማን ትሄጂ እግዚአብሔርን
አታውቂ እያሉ ሲደፏት ሲያዳፏት ወሰዷት ያቺም ነፍስ ኩነኔ
መኖሩን አላውቅም ነበር አውቄ ቢሆን ልልበስ ልብላ ልጠጣ
አልልም ነበር አሁንም ስለእግዚአብሔር ስለእግዝእትነ
ማርያም ደከመኝ አሳርፉኝ አለች ፈጣሪሽንና ማርያምን የካድሽ
ወንጀለኛ አናሳርፍሽም አሏት ሁለተኛም ስለ እግዝእትነ
ማርያም ደከመኝ አሳርፉኝ አለች ማርያም ወዴት
ታውቂያታለሽ እያሉ ሲወስዷት አይቼ ብዙ አለቀስኩ ብዙም
አዘንኩ ልጄን እንዲህ አልኩት ሰው ሆኖ የማይበድል እንጨት
ሆኖ የማይጤስ የለምና እባክህ ማርልኝ አልኩት፡፡
21
ልጄም መለሰልኝ አትዘኝ እናቴ ሆይ ሰው በምድር መልካም
ግብር ካልሰራ መማር አይገባውም አለኝ፡፡ ያን ጊዜ ልቅሶ
አበዛች ይህች ነፍስ ስለእግዝእትነ ማርያም ጥቂት አሳርፉኝ
እያለች ጩኸቷን ማብዛቷን በሰማሁ ጊዜ መሪር ዕንባ
አለቀስሁ ልቅሶዬንም ልጄ በሰማ ጊዜ ስለ እናቴ ስለ ማርያም
ብላችሁ ጥቂት አሳርፏት ይህቺን ነፍስ አለ ያቺንም ነፍስ ጥቂት
አሳረፏት፡፡ ከዚያም በኃላ አንቺ ጎስቋላ ነፍስ ወዴት ትሄጃለሽ
መግቢያሽ ወዴት ነው ወዮለሽ ወዮታ አለብሽ እያሉ ወሰዷት
ከኃጥእም ቦታ አደረሷት አቡሃ ለሐሰት የሐሰት አባት ሐሰት
የሚያናግር ሰው የሚያሳማ ዝሙት የሚያሰራ ወደ መሸታ ቤት
የሚያኬድ ዘፈን የሚያስወድድ ነፍስ የሚያስገድል ሰይጣን ወደ
እርስዋ ከጭፍሮቹ ከመላእክተ ጽልመት ጋር ተሸቀዳደመው
ሄዱ መረመሯትም ወገናቸው ሆና አገኙዋት አንቺ ጎስቋላ ነፈስ
ወደ ማን ትሄጂ ወደ መንግሥተ ሰማያት ትገቢ ትወጃለሽን
እያሉ ተዘባበቱባት ሠራዊተ መላእክት ካሉበት አደረሷት
በመካከላቸው ብትቆም ይህቺን የተረገመች ነፍስ ውሰዱልን
አሉ ሽታዋ አስቸገረን ብለው ጮሁ፡፡
21
ከዚህም በኃላ አንቺ ርግምት ነፍስ ወዮልሽ ወዮታ አለብሽ እያሉ
ወደ ሰማይ አወጧት ከእግዚአብሔር ፊት አደረሷት የፈጠረሽ
እግዚአብሔር ይህ ነው ስገጂ እጅ ንሺ አሏት ያችም ነፍስ
ሰገደች እጅም ነሳች ቀድሞ ይጠብቃት የነበረው መልአክ
ውቃቢ እቤቱ ጠብቅ ያልከኝ ነፍስ ይህቺው ብሎ ለጌታ
አቀረባት ጌታም መልሶ ነፍስ ሆይ ለምን በደልሽኝ ፀሐይና
ጨረቃን እያፈራረቅሁ ሳወጣ ከጻድቃን አለየሁሽ እህልን
ለምግብ ወሀን ለመጠጥ ዕፅዋትን አትክልትን ፈጠርኩልሽ
የነፍስሽን መድኃኒት መልካም ግብር መሥራት ለምን እረሳሽ
ቢላት እኔ ኩነኔ መኖሩን አላወቅም ነበር አውቄ ቢሆን ልብላ
ልጠጣ ልልበስ አልልም ነበር፡፡ ጌታም ካህናትና መጻሕፍት
ካንቺ ዘንድ አልነበሩምን ለምን አልሰማሻቸውም ለነፍስሽ
ስንቅ መልካም ግብር ለምን አልሰራሽም ብሎ ቢጠይቃት
እርሷም የምትመልሰው ብታጣ ዝም አለች፡፡ ከዚህ በኃላ ጌታ
በምድር መልካም ግብር ያልሰራ መማር አይገባውምና ንሱ
ወደ አባቷ ወደ ሰይጣን ውሰዷት ለገሃነመ እሳት ሹም
ለጥልምያኮስ ስጧት አለ ዳግመኛም እስክመጣ ድረስ በሲኦል
በጨላማ ቤት ትኑር አለ ይሀንንም በሰማች ጊዜ ጮኸች ወይኔ
ሳልፈጠር በቀረሁት ይሻለኝ ነበር የተወለድኩባት ቀን ርጉም
ትሁን ብላ አለቀሰች ያች ነፍስ ብታለቅስ ሁላችንም አለቀስን
መላእክትም አክሊላቸውን አውርደው አለቀሱ፡፡
21
ቅዱስ ዳዊትም ቦኑ ለከንቱ ፈጠርኮ ለሰብእ በውኑ የሰውን ልጅ
ለከንቱ ፈጥረኸዋልን እንዳለ መዝሙር ፹፰፡ ፵፯ ጌታም
ወምንት ይበቁዖ ለሰብእ ለእመ ኩሎ ዓለመ ረብሀ ወነፍሶ ኅጎለ
ሰው ሁሉ ዓለምን ቢገዛ ቢነዳ ነፍሱን ካጣ ምን ይጠቅመዋል
እንዳለ ማርቆስ ፰፡፴፮ ለዚያች ነፍስ ሁላችንም አለቀስን፡፡
21
ከዚህ በኃላ ልጄ እንዲህ አለኝ ወደ ገነት እንሂድ አለኝ ሂጄም
ጻድቃን ሰማዕታት ደናግል መነኮሳት መልካም ሰዎች
የሚኖሩበትን አየሁ ወደላይ አወጣኝ ሥሩ የማይታይ ከትልቅ
ገደል አደረሰኝ ከዚያው ፯ ብርሃናትን ከፀሐይ ከጨረቃ ፲፪ እጅ
የሚያበሩ አየሁ ፩ አረጋዊ (ሽማግሌ) ሰው መጥቶ ማርያም
ሆይ አንቺ የከበርሽ የማኀፀንሽም ፍሬ የከበረ ነው አንቺን ያዩ
ዓይኖቼ የከበሩ ናቸው ብሎ እጅ ነሳኝ ልጄን ይህ ሰው ማነው
ብየ ጠየቅሁት ሄኖክ ነው አለኝ፡፡
21
ዳግመኛም እንደሱ አንድ ሰው መጥቶ እጅ ነሳኝ ልጄን ይህስ
ሰው ማነው አልሁት ኤልያስ ነው አለኝ ከዚህ በኃላ ከታች አስከ
ላይ በወርቅ ቀለም የተጻፈ ዓምድ ወርቅ አየሁ ቁመቱ
በመላኩ ክንድ ፲፭ ይሆናል ጽሕፈቱም ረቂቅ ነው እኔም
ይኸንን አይቼ ልጄን ጠየቅሁት ይህ ረቂቅ ጽሕፈት የተጻፈበት
ዓምድ ወርቅ ምንድነው አልሁት የጻድቃን ስማቸው ነው አለኝ
የፊታቸው መልክ ብቻ ነው የተጻፈው ብዬ ብጥይቅ አይደለም
ሁለንተናቸውም ተጽፏል እንጂ አለኝ ሳይወለዱ ነው ከተወለዱ
በኃላ ብለው ካባታቸው ከአዳም በፊት ተጽፈዋል አለኝ፡፡
21
ዳግኛም በዓምደ ወርቅ ከተጻፈው ጽሕፈት የሚበልጥ
የተጻፈበት የእሳት ዓምድ ወርቅ አየሁ በዚያ በእሳት ዓምድ ላይ
የተጻፉ እነማን ናቸው ብለው ኃጥአን ናቸው አለኝ ሳይፈጠሩ ነው
ከተፈጠሩ በኃላ የተጻፈው ብለው ለዚህ ለሥቃይ አስቀድመው
የተጻፉ ናቸው ብሎ አለኝ መጽሐፍ ያለውን አልሰማሽምን አለኝ
ቦ እለ ተሐርዩ እምከርሠ እሞሙ እመሂ ለሢመት ወእመሂ
ለነዲ ከእናታቸው ማኀፀን የተመረጡ ለሹመትም ሆነ ለድኀነት
አሉ እንዳለ ቅዳሴ አትናቴዎስ ቁ. ፻፲፫።
21
ከዚህ በኃላ ወደሌላ ቦታ ወሰደኝ ከፀሐይ ከጨረቃ ፲፪ እጅ
የምታበራ አገር አየሁ በየሰዓቱ ፼ ፼ የሚያፈራ ብዙ ፍሬ ያለው
ብዙ አትክልትም አየሁ ዳግመኛም ተምር ገውዝ ለውዝ ሎሚ
ትርንጎ ፬፼ ከ፷፯ አትክልት መዓዛቸው ልቦና የሚመስጥ በዚያ
ቦታ አየሁ ልጄንም ጠየቅሁት ይህ ቦታ ለማን ይሆናል አልሁት
ወንድ በ፩ሴት ሴት በ፩ ወንድ ተወስነው በንጽሕና ቢኖሩ በሞቱ
ጊዜ መኖሪያቸው ይህ ነው በልቡናቸው ንጹሕ የሆኑ ሰዎች
እግዚአብሔርን ያዩታል ወደ እግዚአብሔርም ይወስዱዋቸዋል
እንዳለ ማቴዎስ ፭:፰።
21
ከዚህ በኃላ በዚህ ቦታ አንፃር የወይን ወንዝ ወደአለበት ቦታ
ወሰደኝ በዚያም ቦታ ደጋጎች አባቶቻችን አዳም አቤል ሴት
መላልኤል ቃይናን ያሬድ አልፋስክድ የቀደሙ አባቶቻችን ሁሉ
አሉበት መጀመሪያ አባታችን አዳም መጥቶ ማርያም ሆይ
እንዴት ነሽ አለኝ አንቺን ያዩ ዓይኖቼ ንዑዳት ክቡራት ናቸው
አለኝ አቤልም መጥቶ አንዴት ነሽ አለኝ የቀደሙ አባቶቻችን
ሁሉ እየመጡ መልካሚቱ ርግብ ማርያም ሆይ እንዴት ነሽ
አንቺን ያዩ ዓይኖቻችን ንዑዳት ክቡራት ናቸው ብለው እጅ ነሡኝ
ሰገዱልኝ ከዚህ በኃላ የመዓር ወንዝ ወዳለበት ወሰደኝ በዚያው
ቦታ ሙሴ አሮን አሞጽ ኢሳይያስ ናሆም ኤርሚያስ ሶፎንያስ
ነቢያት ሁሉ ኤልሳቤጥ ራሔል ሣራ ርብቃ የጸደቁ ሴቶች ሁሉ
አሉ የነቢያት አለቃ ሙሴ መጥቶ እጅ ነሣኝ ሰገደልኝ ፀምር
ፀዐዳ ማርያም ሆይ እነዴት ነሽ አለኝ አንቺን ያዩ ዓይኖች
ንዑዳት ክቡራት ናቸው አለኝ ነቢያትም ሁሉ መጥተው እጅ
ነሡኝ ሰገዱልኝ ጽርሕ ንጽሕት ማርያም ሆይ አንቺን ያዩ
ዓይኖቻችን ንዑዳት ክቡራት ናቸው ብለው እጅ ነሡኝ ሰገዱልኝ
እናቴ ሔዋን መጥታ እንዴት ነሽ አለችኝ ጽርሕት ንጽሕት
እንዴት ነሽ አለችኝ ጽርሕት ንጽሕት ማርያም ሆይ አንቺን ያዩ
ዓይኖቼ ንዑዳት ክቡራት ይሁኑ አለችኝ ክቡራት ቅዱሳት
አንስትም ሁሉ መጥተው እጅ ነሡኝ ሰገዱልኝ የእግዚአብሔር
ማደርያ እንዴት ነሽ አሉኝ ከዚህ በኃላ የወተት ወንዝ ወደአለነት
ቦታ ወሰደኝ በዚያ ቦታ ሄሮድስ የገደላቸው ፲፬፼ ከ፬፻ ሕፃናት
አሉ እነሱም ባዩኝ ጊዜ መጥተው እጅ ነሡኝ ሰገዱልኝ የደናግል
መመኪያቸው ማርያም ሆይ አንቺ ከሁሉ ይልቅ የከበርሽ ነሽ
አንቺን ያዩ ዓይኖቻችን የከበሩ ይሁኑ ብለው እጅ ነሡኝ
ሰገዱልኝ፡፡
21
ከዚህ በኃላ የወይን ወንዝ ወደአለበት ቦታ የሚኖሩ እነማናቸው
አልሁት ባልንጀራቸውን እንደራሳቸው ማለት እንደ ነፍሳቸው
የሚወዱ ለተራበ ያበሉ ለተጠማ ያጠጡ ለታረዘ ያለበሱ ሰዎች
በሞቱ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይወስዳቸዋል እጅ ለመንሳት
ለመስገድ ወደፈለገ ሰማይ ሲወስዳቸው ቅዱሳን መጥተው
ይቀበሏቸዋል ዓለምን ድል ነሥተዋልና ዲያብሎስን
አሸንፈዋልና መልካም ግብር በመሥራት በእውነት ጎልማሶች
ናቸውና አገራችሁ ግቡ እንደኛ ደስ ይበላችሁ ይሏቸዋል አለኝ፡፡
21
ዳግመኛም ልጄን የማር ወንዝ ወደአለበት ቦታ እነማን
ይኖራሉ አልሁት ለችግረኛና ለምስኪን አስቦ የሚሰጥ እሱ
ምስጉን ነው እግዚአብሔር ከክፉ ቀን ያድነዋል ይጠብቀዋልም
ሕያውም ያደርገዋል፡፡ በምድር ላይ በሕይወት ሥጋ
በሚኖርበር ጊዜ ያስመሰግነዋል በጠላቶቹም እጅ አሳልፎ
አይሰጠውም ታምሞ በአልጋው ላይ ይረዳዋል፡፡ መልካሙን
ምንጣፍ ያነጥፍለታል እንዳለ ቅዱስ ዳዊት መዝሙር ፵፡፩ ፡፡
ዳግመኛም እግዚአብሔር ይራራላቸዋል ደካማውን ከብርቱ
ረዳት የሌለውን ከቀማኛ እጅ ያድናቸዋል ከግፍና ከነፍስ
ጭንቀት ይሠውራቸዋል፡፡ ለሰው የሚራሩ ሰዎች ከቡራን
ናቸው፡፡ መዝሙር ፸፩፡፳ የተበደሉ ሰዎች መንግሥተ
ሰማያትን እጅ ያደርጓታልና ለተበደለ የሚራራ እናት አባት
ለሌለው እናት አባት የሚሆን ክርስቲያንም አረመኔም ቢሆን
ሁሉም የእግዚአብሔር ፍጥረት ነውና ለድኃ ሁሉ የሰጠ በቅንነት
የሚሄድ ጽድቅንም የሚያደርግ ልቦናው ተንኮል የሌለበት
በአንደበቱ ዕውነትን የሚናገር በሰውነቱ ክፋት በቃሉ ሐሰት
የማይገኝበት በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ ወገኖቹን
የማይዘልፍ የማይሳደብ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውን
የሚያከብር ባልንጀራውን የማይከዳ ገንዘቡን በአራጣ
የማያበድር ከንጹሑ ላይ መማለጃን ጉቦን የማይቀበል ፍርድን
የማያጓድል ድሀን የማይበድል የከበረ ነው እንዳለ ሮሜ. ፩፡፲፫
ለመስጠት እጃቸውን የዘረጉ ሰዎች በሞቱ ጊዜ ከእግዚአብሔር
ዘንድ ያቀርቧቸዋል እጅ ነሥተው ሰግደው ወደዚህ ያመጧቸዋል
ዋጋቸውንም ያሰጣቸዋል በዚህ ቦታ ለዘለዓለም ደስ ብሎአቸው
ይኖራሉ አለኝ፡፡
21
ዳግመኛም የወተት ወንዝ ወዳለበት ቦታ እነማን ይኖራሉ
አልሁት፤ ከዝሙት ሰውነታቸውን ንጹሕ ያደረጉ ሴቶቸም
በድንግልና የኖሩ በሞቱ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይወስዳቸዋል
ዋጋቸውንም ይሰጣቸዋል፤ በዚያው ቦታ ደስ ብሏቸው ይኖራሉ
አለኝ፤ ከዚህ በኋላ በወርቅ በዕንቁ የተሸለመች ከፀሐይ
ከጨረቃ ፪ እጅ የምታበራ ምድር አሳየኝ፤ ይህ ቦታ ለማን
ይሆናል ብዬ ልጄን ጠየቅሁት መለሰልኝ፤ አንደበቱን ከሐሜት
የጠበቀ ኩራት የሌለበት ባልንጀራውን የማያዋርድ ምክንያተ
ሐኬት የሌለበት፤ በልቡናው ቂም በቀል የማያኖር የዋህ የሆነ
እነዚህ ሁሉ በሞቱ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይወስዱዋቸዋል
እጅ ነሥተው ሰግደው ያመጧቸዋል፤ የዋሃንስ ይወርስዋ
ለምድር፡፡ የዋሃን መንግሥተ ሰማይትን ወርሰው በውስጧ
ይኖራሉ፡፡ እንዳለ መዝሙር ፲፬:፪-፭ ዋጋቸውን ይህንን
ይሰጣቸዋል አለኝ፡፡
21
ዳግመኛም በዚህ ቦታ አንፃር ብዙ ሰዎች ተበትነው አየሁ በገነት
በር ብዙ ፍሬ ያለው የሚመስል ትልቅ ዛፍ አለ እነዚያ ሰዎች
ፍሬ ያለው መስሎአቸው በተራቡ ጊዜ ለመብላት ወደ ላይ
ሲወጣ ይወጣሉ፤ ወደታች ሲወርድ ይወርዳሉ ፍሬውን
አያገኙትም ይኸንን ባየሁ ጊዜ መሪር ዕንባ አለቀስኩ ልጄንም
ጠየቅሁት እሊህ ሰዎች ምንድር ናቸው፡፡ አልሁት፤ ይህስ ዕጽ
ምንድር ነው እኔ ዛፉ ፍሬ ያለው መስሎኝ ነበር እነዚህ የተራቡ
ሰዎች ፍሬውን ለመብላት ወደታች ሲወርዱ ይወርዳሉ፡፡
ወደላይ ሲወጣ ይወጣሉ ፍሬውን አላገኙትም ነገሩ ምንድር ነው
አልሁት እረሱም የነዚህን ሰዎች ኃጢአት እነግርሻለሁ አለኝ
በጾም በጸሎት የተጸመዱና በትዕግሥት ፍጹማን ቢሆኑ ለተራቡ
አላበሉም ለተጠማ አላጠጡም ለታረዘ አላለበሱም እንግዳ
አልተቀበሉም ትዕቢተኞች ኩራተኞች ናቸው አለኝ እነዚህ ቃላት
ሰውን ያስኮንናሉን ብዬ ልጄን ጠየቅሁት መለሰልኝ ከነዚህ
ከ፫ቱ ኃጢአት የበለጠ የለም ዲያብሎስም በትዕቢቱና በኩራቱ
ተዋርዷልና አለኝ፡፡ እንዲህም ብዬ ልጄን ጠየቅሁት አስከ መቼ
ድረስ ይኮነናሉ አልሁት ጻድቃን ስለእነርሳቸው
ስለሚለምኑላቸው ዳግመኛ እስከመጣ ድረስ ነው እኔም
እምራቸዋለሁ አልጥላቸውም ወደመንግሥተ ሰማያት ይገባሉ
አለኝ፡፡ ይኸንን በሰማሁ ጊዜ ልጄን አመሰገንኩት፡፡
21
ከዚህም በኃላ ወደሌላ ቦታ ወሰደኝ ከወርቅ መርከብ ላይም
አወጣኝ ወስዶም ከቤት አገባኝ ያች ቤትም ከፀሐይ ከጨረቃ
ይልቅ ታበራለች በውስጧም ብርሃኑን የሚያንፀባርቅ የግምጃ
ምንጣፍ ወሳንሳ ተነጥፎባታል የወርቅ የብርሃን አልጋ
ተዘርግቶባታል ይህች ቦታ ለማን ትሆናለች ብዬ ልጄን
ጠየቅሁት እግዚአብሔር እንድ ያደረጋቸው ባልና ሚስት
አይለያዩም ባልና ሚስት አንድ አካል ናቸው እንዳለ ማቴ. ፲፱፡፯

21
ወንድ በአንድ ሴት ሴት በአንድ ወንድ ተጠብቀው ቢኖሩ በሞቱ
ጊዜ ከዚህ ቦታ ያገባቸዋል ለዘለዓለምም ደስ ብሎአቸው
ይኖራሉ አለኝ፡፡ ከዚህ በኋላ ፬ሺ ከ፬፻ እንደ ፀሐይ የሚያበሩ
መናብርተ ብርሃን አየሁ እሊህ ማናብርት ለማን ይሆናሉ ብዬ
ልጄን ጠየቅሁት በስሜ ስለማመን የሚያስተምሩ ናቸው
አለኝ፡፡ ሁሉም ይጠሏቸዋል ሁሉም ይደበድቧቸዋል
ይገድሏቸዋል ኋላ ግን ከራሳቸው ፀጉር አንዲት አትጠፋም፡፡
በመቻላችሁ ነፍሳችሁን ታድኗታላችሁ እንዳለ ማቴዎስ ፲፡፳፪
፡፡
21
ሲርባቸው ሲጠማቸው ከሀገር ወደ ሀገር ሲሰደዱ ዓለምን የናቁ
ስለሃይማኖት ሰውነታቸውን ለሞት አሳልፈው የሰጡ ፲፪
ሐዋርያት ፸፪ አርድእት እነዚህ ሁሉ ይቀበሏቸዋል አለኝ፡፡
የቅዱሳን ሠራዊት ሁሉ የእግዚአብሔር ማደሪያው ማርያም
ሆይ እንዴት ነሽ ብለው እጅ ነሡኝ ሰገዱልኝ ከዚህ በኋላ
ወደሌላ ቦታ ወሰደኝ ከፀሐይ ከጨረቃ ይልቅ የሚያበሩ ፪፻
ቤተ ክርስቲያን አየሁ እነዚህ ለማን ይሆናሉ ብዬ ልጄን
ጠየቅሁት ለጳጳሳት ለኤጲስ ቆጶሳት ለቀሳውስት ለዲያቆናት
ለአናጎንስጢስ ለመዘምራን ይሆናሉ አለኝ ሁሉም ይገባሉ ብዬ
ጠየቅሁት አይገቡም ጥቂት ናቸው የሚገቡት አለኝ እግዚኦ
እግዚኦ እያሉ የሚዘባበቱብኝ ሁሉ ከመንግሥተ ሰማያት
አይገቡም የአባቴን ፍቃድ የፈጸሙ ይገባሉ ብዬ የተናገርኩትን
አልሰማሽምን አለኝ ማቴዎስ ፲፭:፬ ፡፡
21
ሰውነታቸውን ከዝሙት ንጹሕ ያደረጉ ከሰው ሚስት ያልሄዱ
ኩራት የሌለባቸው ትእቢት ምቀኝነት የሌለባቸው ቂም
በልቦናቸው ያላኖሩ ከአንድ ሴት ወደ አንድ ሴት ከአንድ ወንድ
ወደ አንድ ወንድ የማይሉ ቁጡና ሰካራም ያልሆኑ ለጣኦት
ያልሰገዱ በአምልኮ ባዕድ ያላመለኩ በሐሰት ያልማሉ ቤተ
ክርስቲያን የሚያዘወትሩ በንጹሕ ሆነው ሥጋዬን ደሜን
የሚቀበሉም የሚያቀብሉ ሰዎች እነዚህ ናቸው ከመንግስሥተ
ሰማያት የሚገቡ እነዚህን የነገርኩሽን ቃላት ያልፈጸሙ
መንግሥተ ሰማያት አይገቡም አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት አደረሰኝ የእሳት
መጋረጃ ያለበት የብርሃን ቤተ መቅደስ አየሁ በእጁ መሰንቆ
በገና ይዞ እየመታ እንደ ፀሐይ የሚያበራ አንድ ሰው አየሁ ያም
ሰው መሰንቆ በገና ሲመታ ምድሯን ያናውጻታል ከኢየሩሳሌም
ደጁ ቆሟል እኔም በገባሁ ጊዜ ወደእኔ መጣ ማርያም ሆይ
ከሁሉ ይልቅ አንቺ የከበርሽ ነሽ ብሎ እጅ ነሳኝ ሰገደልኝ የዚህ
ሰው ስሙ ማነው፤ ብዬ ልጄን ጠየቅሁት ቅዱስ ዳዊት ነው
አለኝ ሃሌ ሉያ ብሎ ሲያመሰግን ሰምቼው፡፡ ሃሌ ሉያ ሲሉ
የሰማኋቸው በዳዊት ቃል ምስጋና ሁሉ ተነግሯልን ብዬ ልጄን
ጠየቅሁት አዎን ምስጋና ሁሉ በዳዊት ቃል ተነግሯል አለኝ
እኔም መልሼ ሃሌ ሉያ ማለት ምን ማለት ነው ብዬ ልጄን
ጠየቅሁት ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር
አምላክ የተመሰገነ አምላክ ማለት ነው አለኝ ሃሌ ሉያ ቢል
ለሰው ምስጋና ይሆንለታልን ብዬ ጠየቅሁት አወን በጥቡዕ
ልቡና ሆኖ ሃሌ ሉያ ብሎ ቢያመሰግን ምስጋናው እንደ
መላእክት ይሆንለታል አለኝ ዳግመኛም መለስሁለት ሰው
የታመመ እንደ ሆነ ተኝቶ ቢጸልይ ኃጢአት ይሆንበታልን
አልሁት ለድውይ አይሆንበትም አለኝ፡፡ ከዚህ በኋላ ወደሌላ ቦታ
ወሰደኝ የወርቅ ልብስ ያለበት ዳርቻው የማይታወቅ እንደ
ፀሐይ የሚያበራ አገር አሳየኝ ይህ ቦታ ለማን ይሆናል ብዬ
ልጄን ጠየቅሁት ንብረታቸውን ትተው ዓለመን ንቀው ለመነኑ
ሰዎች ይሆናል አለኝ ይህችን ሀገር የሚያውቃት የለም፡፡ ካህናተ
ሰማይ አይገቡም ከበር ይቆማሉ እንጂ የባሕርይ አባቴ አብ
የሕይወት መንፈስ ቅዱስ እነገባለን አንቺም ግቢ ሀገር
ይሁንልሽ አልኝ ፫ሺ መላእክት ያገልግሉሽ አለኝ መነኮሳት ሁሉ
ይጋባሉን ብዬ ጠየቅሁት ሁሉም አይገቡም አለኝ ሰውነታቸውን
ከዝሙት ንጹሕ ያደረጉት ዓለምን ንቀው የመነኑ ደስታን
ተድላን የጠሉ ቁጡ ያልሆኑ ትዕቢት ኩራት የሌለባቸው ቂም
በልቦናቸው ያላኖሩ ሰውን ከሰው የማያጣሉ ንዝኅላል ያልሆኑ
በየጊዜው በየሰዓቱ ጸሎት የሚያደርጉ ይገባሉ አለኝ በጾም
ተጸምዶ የሚኖር መነኩሴ የሚበልጠው የለም ብሎ መጽሐፍ
የተናገረውን አልሰማሽምን ዳግመኛም ገንዘብ አግኝቶ
ከሚመጸውት መነኩሴ ገንዘብ የሌለው በትምህርትና በጸሎት
ተጸምዶ የሚኖር መነኩሴ ይበልጣል ዳግመኛም ጳውሎስ እኔ
በዓለም ዘንድ ምውት ነኝ ዓለምም በኔ ዘንድ ምውት ናት
እንዳለ፡፡
21
ይኸንን ሁሉ የፈጸመ መነኩሴ ከመንግሥተ ሰማያት ይገባልን
ብዬ ብጠይቀው የማይገቡትን እነግርሻለሁ አለኝ ትዕቢተኞች
ኩራተኞች ሴሰኞች ባልንጀሮቻቸውን የሚጠሉ ባንደበታቸው
እራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ መነኮሳትም ሆነው ተሾመው
የሚገዙ የሚነዱ በፈረስ በበቅሎ የሚሄዱ ከቆብ በኋላ
የሚሰስኑ ለሆዳቸው የሚገዙ አለልክ የሚበሉ የሚጠጡ ሁል
ጊዜ ዛሬ ዓመት በዓል ነው እያሉ ለመብል የሚዘጋጁ እነዚህ
መንግሥተ ሰማያት አይገቡም አለኝ ዳግመኛም ነይ ወደ
ምዕራብ እንሂድ የኃጥአን ነፍስ የሚኖሩበትን አሳይሻለሁ አለኝ
ወስዶ በሰማይና በምድር ዳር ከባሕር ዳርቻ አደረሰኝ የእሳት
ባሕር ያለበት የገሃነም ቦታ አሳየኝ ይህ ቦታ ለማን ይሆናል ብዬ
ልጄን ጠየቅሁት በመልካም ግብር ያልተገኙ በኃጢአት የኖሩ
ቦታቸው ይህ ነው አለኝ በዚያ በባሕር ውስጥ ብዙ ሰዎች
ከጉልበታቸው ድረስ ከእንብረታቸው ድረስ ከደረታቸው ድረስ
ከአንገታቸው ድረስ ከከንፈራቸው ድረስ ከእራሳችው ድረስ
የእሳት ባሕር ያጠለቃቸው አየሁ ከጉልበታቸው ድረስ
ያጠለቃቸው እነማን ናቸው ብለው በ፫ ጊዜያት ጸሎት የማይዙ
ናቸው አለኝ፡፡ ከእንብረታቸው ድረስ ያጠለቃቸው እነማን ናቸው
አልሁት ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዋዛ ፈዛዛ የሚጫወቱ ናቸው
አለኝ ከደረታቸው ድረስ ያጠለቃቸው እነማን ናቸው ብለው
ከቆረቡ በኋላ እህል ውሀ ሳይቀምሱ የሚናገሩ ናቸው አለኝ
ከአንገታቸው ድረስ ያጠለቃቸው እነማን ናቸው ብለው
ባልንጀሮቻቸውን የሚያሙ ናቸው አለኝ ከከንፈራቸው ድረስ
ያጠለቃቸው እነማን ናቸው ብለው ባልንጀራውን እንግደል
የሚሉ ናቸው አለኝ፡፡ ከራሳቸው ድረስ ያጠለቃቸው እነማን
ናቸው ብለው ከጽቅረ ቤተ ክርስቲያን ሴት የሚተኙ ናቸው
አለኝ፡፡ ከዚህም በኋላ ከሥር እስከ ጫፍ ከጫፍ እስከ ሥር
ድረስ በ፭ ሺህ ዓመት የማይደረስ ትልቅ ገደል አሳየኝ ያንዱ
ነፍስ ባንዱ ነፍስ ላይ ሲወድቅ አየሁ እኔም ምንድር ናቸው ብዬ
ልጄን ጠየቅሁት ባባታቸው በወንድማቸው በልጃቸው
በባልንጀራቸው ሚስት የሚሰስኑ ናቸው አለኝ ሴት አራስ ሆና
ወይም መርገሟ በመጣ ጊዜ በሩካቤ ሥጋ የሚገናኙና እንስሳን
ምድርን ሰንጥቀው የሚያወስቡ ወንዱንም በግብረ ሰዶም
የሚያመነዝሩ ካህን ሆኖ ከሌላ ሴት የካህኑም ሚስት ከሌላ
ወንድ ቢሄዱ እነዚህ ሁሉ የኩነኔ ቦታቸው ይህ ነው አለኝ ከዚህ
በኋላ ሌላ ቦታ አሳየኝ ፬ መላእክተ ጽልመት ተሸክመው
ወስደው በእሳት አልጋ አስቀመጠው በእሳት ፍላፃ ሲነድፉት
የእሳት ውሀ ሲአፈሱበት ፩ ሽማግሌ ሰው አየሁ ባየሁትም ጊዜ
ብዙ አለቀስሁ ይህ ሰው ማነው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት ጳጳስ ነው
አለኝ ኃጢአቱንም እነግርሻለሁ አለኝ፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ሥነ
ሥርዓት አልተከተለም በሕጌ ተጠብቆ አልኖረም ሥጋዬን
ደሜን ያረከሰ ነው ዘመኑንም በዝሙት የፈጸመ ነው ዳግመኛ
እንግዳ አልተቀበለም ለተራቡ አላበላም ለተጠማ አላጠጣም
ለታረዘ አላለበሰም የታመመ አልጠየቀም ያዘኑትን አላረጋጋም
የታሠሩትን አላስፈታም ስለዚህ የዘለዓለም ቦታው ይህ ነው
አለኝ፡፡ ከዚህ በኋላ ፬ መላእክተ ጽልመት በእሳት መንዶ
እየደበደቡ ከእሳት ባሕር ሲጨምሩት ፩ ታላቅ ሰው አየሁ፡፡ ይህ
ሰው ማነው ኃጢአቱስ ምንድር ነው ብዬ ጠየቅሁት፡፡ ሊቀጳጳስ
ነው ኃጢአቱን እነግርሻለሁ አለኝ ፩ነቴን ፫ነቴን ለሕዝብ
አላስተማረም እራሱን ወዳድ የግል ጥቅሙን ፈላጊ ነገሥታትን
መኳንንትን አይመክርም ፍርድ ሲጓደል ድሀ ሲበደል ዳኞችን
አይገሥጽም አያስተምርም ስለዚህ የዘለዓለም ኩነኔው ይህ ነው
አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ የመለኮትን ሥጋ ስትበላ ትራባለህን የመለኮትን ደም
ስትጠጣ ትጠማለህን ብለው በአፉ እሳት ሲያጎርሱት እሳት
ሲያጠጡት መላእክተ ጽልመት ሲጎትቱት አንድ ሰው አየሁ ይህ
ሰው ማነው ኃጢአቱስ ምንድር ነው አልሁት ቄስ ነው
ኃጢአቱንም እነግርሻለሁ አለኝ በክህነት ሥራ አልኖረም
ሰውነቱንም ንጹሕ አላደረገም ዘመኑንም በሳቅ በጨዋታ
የፈጸመ ነው የዘለዓለም ኩነኔው ይህ ነው አለኝ፡፡
21
ዳግመኛም መላእከተ ጽልመት ፊት ፊቱን እየደበደቡ በግምባሩ
ሲያዳፉት መላሱን በእሳት ምላጭ ቆርጠው በአፉ ደም ሲዘነብ
ወደ እሳት ባሕርም ሲጨምሩት አንድ ሰው አየሁ ይህ ሰው
ማነው ኃጢአቱስ ምንድር ነው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት መለሰልኝ
ዲያቆን ነው አለኝ ኃጢአቱስ ምንድር ነው ብዬ ጠየቅሁት
ኃጢአቱንም እነግርሻለሁ አለኝ በሕጌ አልኖረም ሥጋዬን ደሜን
በንጹሕ አላዘጋጀም ቤተ ክርስቲያን አልወደደም ለግብረ
ተልእኮ አልተፋጠነም ድሀ ቢሞት አልቀበረም ኩሩ ትዕቢተኛ
ነው አለኝ ከዚህ በኋላ ብዙ የተበታተኑ ሰዎች በእሳት መካከል
አየሁ እነዚህ እነማናቸው ብለው በፀሐይ በጨረቃ በከዋክብት
በዕንጨት በድንጋይ የሚያመልኩ ለዛር ለቃልቻ ለጠንቋይ
የሚደግዱ ናቸው ስለዚህ ኩነኔያቸው ለዘለዓለም ይህ ነው አለኝ
ከዚህ በኋላ በእሳት ዛፍ ላይ የተሰቀሉ ብዙ ሰዎች አየሁ ምንድር
ናቸው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት (ብዕልን) ክብርን የወደዱ ሀብት
ገንዘብ እያለቸው ለተራበ የማይሰጡ የማይመፀውቱ ድሆቸን
የሚበድሉ ባለጠጎች ናቸው ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይድቃሉ
ስለዚህ ለዘለዓለምም ቦታቸው ይህ ነው አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋለ በእሳት ሰንሰለት አንገታቸውን ታስረው ጨለማ
የለበሱ ሴቶች አየሁ እነማን ናቸው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት እናት
አባቶቻቸው በሕግ ሳያጋቧቸው ድንግልናቸውን ለማንም በዱር
በጫካ የሚሰጡ የሚሰስኑ ክብረ ንጽሕናቸውን የሚያጎድፉ
ናቸው ስለዚህ ኩነኔአቸውም ለዘለዓለም ይህ ነው አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ ልቅሶ ጥርስ ማፋጨት ከአለበት ገሃነመ እሳት
እጃቸውን እግራቸውን ታስረው በእሳት ግንድ ተሰቅለው ብዙ
ሰዎች አየሁ እነማናቸው ብዬ ጠየቅሁት የሰው ገንዘብ የሚበሉ
እንደልባቸው የሚናገሩ በዚህ ዓለም ያላግባብ የከበሩ ወይም
የበለጸጉ የሚገዙ የሚነዱ ብዑላን ነገሥታት መኳንንት ናቸው
ለዘለዓለም የኩነኔያቸው ቦታ ይህ ነው አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ የእሳት ውሾች የእሳት እባቦች የእሳት አንበሶች
እግራቸውን እጃቸውን ሲሰብራቸው በእሳት ዛፍ ላይ ተሰቅለው
ብዙ ሰዎች አየሁ እነማናቸው ብዬ ብጠይቀው ከቆብ በኋላ
የሚሰስኑ መነኮሳት ናቸው ሴቶችም በፀነሱ ጊዜ መድኃኒት
እየጠጡ የሚያስወርዱ ናቸው እነኛም ሕፃናት መልካምም ሆነ
ክፉ ብንሠራ ምነው ባደግን አለጊዜያችን አጠፉን ብለው አቤት
አቤት እያሉ ይጮሁባቸዋል አባቴ ግን መልአኩን ሕፃናቶቹን
ወደ መልካም ቦታ ውሰዳቸው ይለዋል እናቶቻቸውም
ለዘለዓለም ኩነኔያቸው ይህ ነው አለኝ በጥቡዕ ልቦና ነስሓ ቢገቡ
አትምራቸውምን አልሁት እምራቸዋለሁ አለኝ ቀሳውስቱም
የነፍስ ልጆቻቸውን መክርው ተቆጥተው ንስሓ ግቡ
አይሏቸውም እነደ ፈሌ እንደ (ፈላ) ይሆናሉ አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ እህል እንዳይበሉ ውሀ እንዳይጠጡ ተክልክለው
በእሳት ግንድ ታስረው ብዙ ሰዎች አየሁ እነማን ናቸው ብዬ
ብጠይቀው እንዲህ አለኝ ሴት በመርገም ጊዜዋ ሆና በሩካቤ
ሥጋ የተገናኙ ዓርብ ረቡን ፵ ጾም ሁዳዴን የማይጾሙ የኩነኔ
ቦታቸው ይህ ነው አለኝ ንስሓ ቢገቡ አትምራቸውም ብለው
እምራቸዋለሁ አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኃላ በእሳት መካከል እጃቸውን እግራቸውን የተቆረጡ
ሰዎች አየሁ ምንድር ናቸው ብዬ ጠየቅሁት ለሰው ክፉ የሚጥሩ
የሚጽፉም የሰው ገንዘብ የሚሰርቁ የሚነጥቁ የሚዘርፉ
ጉልበት እያላቸው ሠርተው የማይበሉ አታላዮች ኪስ
አውላቂዎች የሰው ቤት በቀን መዝጊያ የሚሰብሩ ሌሊት
ግድግዳ የሚሠረሥሩ ለሰው ነፍስ የማይሳሱ ርኀራኄ የሌላቸው
በገንዘብ እየተገዙ የሰው ነፍስ የሚያጠፉ ዓይናቸውን በስው
ሀብት ላይ የሚያሳርፉ በጧት ወደ መሸታ ቤት የሚገሠግሡ
በብዙ ድካም ያገኙትን ገንዘብ ቤተሰባቸውን በድለው ለመሸታና
ለዝሙት የሚያጠፉ ሰካራሞች አጭበርባሪዎች ናቸው የኩነኔ
ቦታቸውም ለዘለዓለም ይህ ነው አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ በእሳት ልጓም ተለጉመው በእሳት ሜንዶ ፊት
ፊታቸውን ሲደበድቧቸው አየሁ ምንድር ናቸው ብዬ ልጄን
ጠየቅሁት ባልንጀራቸውን የሚሰድቡ የሚያዋርዱ ምቀኞች
ተንኮለኞች ሟርተኞች ሰላቢዎች ተዕቢተኞች ሰውን
አሽሟጣጮች ናቸው አለኝ፡፡
21
ዲያብሎስም አዳምን በሰደበ ከማዕረጉ ተዋርዷልና ዳግመኛም
ጨው ባሩድ የሞላበት ጨለማ ጉድጓድ አየሁ በዚያው ውስጥ
እግራቸውን እጃቸውን የተቆረጡ ብዙ ሰዎች አየሁ፤ ምንደር
ናቸው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት አንድነቴን ሦስትነቴን ቅድመ
ዓለም ከአብ ያለ እናት መወለዴን ድኀረ ዓለም ከሰማየ ሰማያት
ወርጄ ከድንግል ማርየም ያለ አባት ወወለዴን በሄሮደስ ቅንዓት
ከሀገር ወደ ሀገር መሰደዴን መጠመቄን መገረፌን
በመልዕልተ መስቀል መስቀሌን በቀኖት መቸንከሬን ሞቼ
መነሣቴን ከትንሣኤዬም በኋላ በ፵ኛው ቀን ወደሰማይ ማረጌን
በኃላም ይህን ዓለም ለማሳለፍ በጌትነትና በታለቅ ግርማ
መምጣቴን የማያውቁ አረመኔዎች ናቸው ለዘለዓለም
የሚኖሩበት የኩነኔ ቦታቸው ይህ ነው አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ የእሳት እባብ በአንገታቸው በአፋቸው
ተጠምጥሞባቸው ከአፋቸው የእሳት ዲኝ ሲወጣ ብዙ ሰዎች
አየሁ ምንደር ናቸው አልሁት ብዙ ክርስቲያን ሂደው ያላገለገሉ
ካህናት ናቸው ለዘለዓለም የኩነኔ ቦታቸው ይህ ነው አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ በእሳት ገመድ አስረው ራሱን ወደታች እግሩን
ወደላይ አድርገው ሰቅለው አንድ ሰው አየሁ ዳግመኛ በእሳት
ጦር ፊት ፊቱን እየወጉ ከእሳት ላይ ሲጥሉት አየሁ ይህ ሰው
ማነው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት ቄስ ነው ኃጢአቱንም እነግርሻለሁ
አለኝ በሰንበት ዕጣን አያጥንም ንዝኅላል ትዕቢተኛ ኩራተኛ ነው
ጸሎት አያደርስም የዘለዓለም የኩነኔ ቦታው ይህ ነው አለኝ
ልጄን እንዲህ ስል ጠየቅሁት ቁርባን ምን ጊዜ ይቁረብ እሁድ
በነግህ ቀዳሚት በ፫ ሰዓት ሊቀደስ ይገባል ኦሪት ነቢያትን
ልፈጽማቸው ነው እንጂ ላሳልፋቸውና ልሽራቸው አልመጣሁም
ብሎ መጽሐፍ የተናገረውን አልሰማሽምን አለኝ፡፡
21
ቀዳሚትንም ካንዲት ቀን በቀር አልሻርኳትም ሌሎችን
ሰንበታት እንደ እሁድ ያክብሯቸው አለኝ ማለትም እንደ እሁድ
ያክብሯት ማለት ነው፡፡
21
ከዚህ በኋላ በእሳት ፍላፃ ሲነድፉት አንድ ሰው አየሁ ይህ ሰው
ማነው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት ዲያቆን ነው አለኝ ኃጢአቱስ
ምንድር ነው ብዬ ብጠይቀው እነግርሻለሁ አለኝ፡፡
21
መሥዋዕቱን በንጹሕ አላቀረበም በሰዓቱም አላዘጋጀም
ሰውነቱንም ከኃጢአት አላነፃም ለዘለዓለም የኩነኔ ቦታው ይህ
ነው አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ ከሌላ ቦታ ወሰደኝ የእሳት ጉድጓድ አየሁ ከውስጡ
ብዙ ሰዎች ሞልተው በአንገታቸው የእሳት እባቦች
ተጠምጥሞባቸው አራት መላእክተ ጽልመት የእሳት ጦር
ሲወረውሩባቸው አየሁ ባየኋቸውም ጊዜ ብዙ አለቀስኩ እሊህ
እናማናቸው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት መነኮሳት ናቸው በሕጌ
አልኖሩም ሥራዓቱንም አልጠበቁም መነኮሳት ነን ሲሉ
የመነኮሳትን ሥራ አይሠሩም የማይረባቸውን
የማይጠቅማቸውን ሥጋዊና ዓለማዊ ሹመት ይፈልጋሉ
ዘመናቸውንም በኃጢአት የፈጸሙ ናቸው ለዘለዓለሙ የኩነኔ
ቤታቸው ይህ ነው አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ የተዘጋጀ ታላቅ ገሃነም አየሁ ልጄም እናቴም
ማርያም ታየዋለችና ክፈቱ ብሎ የገሃነመ እሳት በር ጠባቂውን
ጠርቶ አስከፍቶ በሮቹ በተከፈቱ ጊዜ አይቼ ፈራሁ ተንቀጠቀጥኩ
ይህ ቦታ ስሙ ማነው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት ገሃነመ እሳት ነው
አለኝ በዚህስ ውስጥ የሚኖሩ ምንድን ናቸው ኃጢአታቸውስ
ምንድ ነው አልኩት ሰው ከውሀና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ
በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይገባ ዘንድ አይቻለውምና
ስለዚህ ያልተጠመቁ አረመኔዎች ናቸው የዘለዓለም ቦታቸወም
ይህ ነው አለኝ፡፡ ዮሐንስ ፫፡፭፡፡ እነዚህም በስቃይ ያሉ ሁሉ
ባዩኝ ጊዜ ማርያም አንቺ ከሁሉ ይልቅ የከበርሽ ነሽ
የማኀፀንሽም ፍሬ የከበረ ነው አንቺን ያዩ ዓይኖቻቸን የከበሩ
ይሁኑ ብለው ጮሁ እኔም ሰው ሆኖ ኃጢአት የማይሠራ የለምና
ልጄን እባክህን ማርልኝ አልሁት እርሱም ዓርብ በሠርክ
መጥተው እስከ ሰኞ ድረስ ስለአንቺ በገነት ያሳርፏቸው አለኝ፡፡
21
ይህንም በሰማሁ ጊዜ ልጄን ፈጣሪዬን አመሰገንኩት
እመቤታችን ድንግል ማርያም ይህንን ከዚህ ቀጥሎ ያለውን
ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች እወቁ ተጠንቀቁ ሴት አራስ ሆና
በሩካቤ ሥጋ የተገናኘ በመርገሟም ሰዓት ወንድ ከሴቷ ሴቷም
ከወንድ ፈቃደኛ ሆነው ቢገናኙ ኃጢአት ይሆንባቸዋል በልቡ
ክፋት ያለበት ሰው ይህች መጽሐፍ ካለችበት ቦታ አይድረስ
መጽሐፉንም ከእንደዚህ ካለው መጥፎ ቦታ አታኑሩ ብላ
ተናግራለች፡፡
21
ዳግመኛም ስለ በዓላት አከባበር ቢቻላችሁ ፴፫ቱን ባይቻላችሁ
፭ቱን የጥር ማርያምን የየካቲት ኪዳነ ምሕረትን የግንቦት
ልደታን የሰኔ ማርያም የነሐሴ ፲፮ ፍስለታን እነዚሀን በዓላቴን
ያከበረ ይህን መጽሐፍ የፃፈ ያጻፈ ያነበበ የተረጎመ የሰማ ያሰማ
እነዚህን ሁሉ የፈጸሙ በሞቱ ጊዜ እኔ እቆምላቸዋለሁ ብላ
ለዮሐንስ ነገረቸው፡፡
21
የአምላክ ልጅ ወልደ አምላክ ለችግር አማላጅቱ እመቤታችን
ማርያም የገለጸላት ራእይ ባጭሩ እዚህ ላይ ተፈጸመ፡፡ የልጅዋ
የወዳጅዋ ቸርነት ለሁላችን ይደረግልን የእመቤታችን ረድኤት
በረከት እስከ ዘለዓለሙ ይደርብን አሜን አቡነ ዘበሰማያት፡፡
°°°°°°°
ምንጭ: መዝገበ ጸሎት ወመጽሐፈ ጸሎት ባለ ሰባ ስምንት
ከተሰኘው የጸሎት መጽሐፍ ላይ ከገጽ 591 እስከ 636
የተወሰደ ነው። በዘሪሁን እሸቱ የተዘጋጀ 20/4/2008 ዓ.ም
†† †† † † †† ††
ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ
ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች ዕመቤታችን እኛንም በበረከት እና
በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ
ታማልደን ፤ አሜን!!!
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሄ ር

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: 21

21 21 21 21 21 21 21
# ራእየ_ማርያም
21 21 21 21 21 21 21
# እመቤታችን_በጎልጎታ_ስጸ
ልይ_ልጇ_ፈጣሪዋ_ጌታችን
_አምላካችንና_መድኃኒታች ን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_የገ
ለጸላት_ምሥጢር_ራእየ_ማ ርያም ቀርቧልና ይነበብ...
21 21 21 21 21 21 21
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ንዌጥን
በረድኤተ እግዚአብሔር ሕያው ራእየ ማርያም ወላዲተ
አምላክ ጸሎታ ወበረከታ የሃሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም
አሜን።
21
ማርያም ለዮሐንስ እንዲህ አለችው ረቂቅ ምሥጢር በልቡናየ
የማይታወቅ ጌታዬ ፈጣሪዬ ልጄ የገለጸልኝ ምሥጢር በጎልጎታ
ስጸልይ ዐርብ ቀን በቀትር ብሩህ ደመና መጥቶ ከ፫ቱ ሰማያት
አውጥቶ አስቀመጠኝ ሁሉንም አሳየኝ ከአንቺ ከፈለገ ሰማይ
ተወልጃለሁና አንቺም ሰላምታ ይገባሻል እኔም ዕጹብ ድንቅ
ምሥጢርን እገልጽልሻለሁ አለኝ። እኔም መለስኩለት ጌታዬ
ፈጣሪዬ እንዳልህ ይሁን አልሁት ወደታች እይ አለኝ ወደ ታች
ስመለከት ዓለምን ሁሉ አየሁ ሰብእሰ ከንቶ የመሰል
መውዋዕሊሁኒ ከመ ጽላሎት የኃልፍ ሰው ከንቱ ነገርን
ይመስላል ዘመኑም እንደ ጥላ ያልፋል ይጠፋል ነፍሱም
ከሥጋው ትለያለች ለዘለዓለም አትኖርም የምትኖርበትም
አይታወቅም መዝሙር ፻፵፫:፬
21
እንግዲህ ሰው ሁሉ በከንቱ ነውን አልሁት እሱም መልሶ ዳዊት
ያለውን አልሰማሽምን አለኝ ሰው ሁሉ በከንቱ ለምን ይኮራል
ዕለት ዕለትስ ለምን ኃጢአት ይሠራል ዳግመኛስ ጢስ ታይቶ
እንደሚጠፋ የሰውም አኗኗር እንዲሁ ነው አለኝ መዝሙር
፶፩:፩። እኔም መለስሁለት የጻድቃን ነፍስ ከሥጋዋ ስትለይ
አሳየኝ አልሁት። መለሰልኝ ጥቂት ቆዪ አሳይሻለሁ አለኝ።
ከዚህ በኋላ ፲፪ መላእክተ ብርሃን በእጃቸው የወርቅ መስቀል
የወርቅ ጥና ይዘው በደረታቸው የእግዚአብሔርን ምልክት
አድርገው የጻድቃንን ነፍስ ለመቀበል ሲወርዱ አየሁ።
ወደዚያች ነፍስ መላእክተ ጽልመትም መጥተው መረመሯት
ምክንያትም አጥተው ሄዱ መላእክተ ብርሃን ግን ፫ ጊዜ
ጋርደው ከሥጋዋ ስትለይ እንዲህ አሏት ደስ ሲያሰኛት
ሲመክሩዋት አንቺ ንጽሕትና ብርሕት ነፍስ ሆይ ደስ ይበልሽ
ዕፅፍ ድርብ ደስታ ይገባሻል ነይ ውጪ ወደ አገርሽ እንሂድ አሏት
አንቺ ንጽሕት ብርህት ነፍስ ሆይ ቅዱስ ዳዊት የዕድሜዬን
መጠኑን ንገረኝ በእኩሌታው ዕድሜዬ አትውሰደኝ ያለውን
አስተውለሻልና። መዝሙር ፻፩:፳፬።
21
ዳግመኛም ጳውሎስ ዛሬ የሚገዙ የሚነዱ ኋላ እንዳልገዙ
እንዳልነዱ ይሆናሉ ዛሬ የሚበሉ የሚጠጡ ኋላ እንዳልበሉ
እንዳልጠጡ ይሆናሉ። የዚህም ዓለም ንብረት ብልጽግና ኃላፊ
ጠፊ መሆኑን አስበሽ ዲያብሎስን ድል ነስተሽዋልና ዓለምንም
ንቀሽ ጉዱፍ እንደሆነ እንደመርገም ጨርቅ ጥለሽዋልና
የማያረጀውን የማይጠፋውን መርጠሻልና ለዘለዓለም የሚኖር
መንግሥተ ሰማያትን ወደሻልና ነይ ወደ ፈጣሪሽ እንሂድ አሏት
የዚያን ጊዜ ሌሎች መላእክተ ብርሃን ወረዱ የወርቅ ዝርግፍ
ዕንቁ የብርሃን ቀጸላ ፲፪ የብርሃን መብራት ይዘው ከብርሃን
አክሊሎች ጋር ወረዱ ብርሃናቸውም ከፀሐይ ከጨረቃ ፯ እጅ
ያበራል ክርስቶስም ከ፭ኛው ሰማይ ድረስ መጣ እኔም ያችን
ነፍስ ለመገናኘት ሄድኩ መላእክተ ብርሃን ዕልል አሉ እኔም
ከእርሳቸው ጋር ዕልል አልኩ ምእመናን ሁሉ በእጃቸው
አጨበጭበው በቃላቸው ዕልል ብለው ለእግዚአብሔር
ምሥጋና አቀረቡ ዳግመኛ ክብር ሞቱ ለጻድቃን በቅድመ
እግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው እንዳለ መዝሙር ፻፲፭:፮።
21
ያችን ነፍስ ወደ እግዚአብሔር አቀረቧት ነፍስ ሆይ ደስ ይበልሽ
ደስታ ይገባሻልና ወደ ፈጣሪሽም እጅ ንሺ ስገጂ አሏት እርሷም
ሰገደች ፈጣሪዋንም እጅ ነሳች አስቀድሞ ይጠብቃት የነበረው
መልአክ እግዚአብሔርን እንዲህ አለው አቤቱ የዚያች ነፍስ
ምግባሯን ነገርኩት እንደ አውነተኛነቷ አክብራት አለው
በእውነት የሚፈርድ ጌታም እንደፈጠርኩሽ ንጽሕት ሆነሽ
የኖርሽ ነፍስ ሆይ እንዴት ነሽ ቃሌን ያላቃለልሽብኝ
ያላበላሸሽብኝ እኔም አላበላሽሽም ሥጋሽንም በጊዜ ምጽአት
አነሣዋለሁ በክብር ከእኔ ዘንድ ትኖሪያለሽ ብሎ በሰው እጅ
ያልተፈተለ ከወተት የነፃ ነጭ ልብሽ ሰጣት ከፀሐይ ከጨረቃ ፯
እጅ የሚያበራ ፫ አክሊለ ብረሃን አቀዳጃት ሚካኤልን ጠርቶ
ንሳ ወደ ገነት ውሰዳት በአብርሃም በይስሐቅ በያዕቆብ አጠገብ
ተቀምጣ በደስታ ትኑር ዳግመኛ እስክመጣ ድረስ ያንጊዜ
ዋጋዋን እከፍላታለሁ ከቅዱሳን ጋር ትቆየኝ አለው፡፡
21
መላእክተ እግዚአብሔርም ይህን ፍርድ በሰሙ ጊዜ አቤቱ
ጌታችን ፍርድህ የተቃና አገዛዝህም በእውነት ነው ብለው ደስ
አላቸው እኔም እንደነሳቸው ደስ አለኝ ያችንም ነፍስ ሸኙዋት
ወደ ገነትም አደረሷት ጻድቃን ሰማዕታት አብርሃምና ይስሐቅ
ያዕቆብ አባቶቻችን እናቶቻችን ባሉበት ቅዱስ ዳዊት
በመካከላቸው በገናውን እየመታ ተቀበሏት እንዲህም አሉዋት
ንጽህትና ብርሕት ነፍስ ሆይ ለዘለዓለም የሚኖር ደስታ ሕይወት
ወደ አለበት ነይ ውጪ አሏት ያችም ነፍስ ከነሱ ጋራ ሄደች፡፡
21
እኛም ከዚህ በኃላ ተመለስን እነኛም እንዲህ እያሉ ሃሌ ሉያ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ፀባኦት ፍጹም ምሉዕ
ሰማያት ወምድር ቅዱሳተ ስብሐቲከ ዳግመኛም ስብሐት ለአብ
ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ እያሉ ፈጣሪያቸውን
አመሰገኑ እኔም ልጄን እንዲህ ስል መለስሁለት የኃጥአን ነፍስ
ከሥጋዋ ስትለይ አሳየኝ አልሁት ጥቂት ቆዬ አሳይሻለሁ አለኝ
ወደታችም አየሁ መላእክተ ብርሃንና መላእክተ ጽልመት ወደ
ኃጥእ ነፍስ ሄዱ መላእክት ብርሃን ቀርበው ያቺን የኃጥእ ነፍስ
መረመሩዋት መልካም ነገር አጥተው ሄዱ ያን ጊዜውን
መንፈስ ቅዱስ ተለያት የገሃነም እሳት ሹም ቆሞ ከሆዷ ገባ ያቺ
ነፍስ በብዙ ጭንቅ ከሥጋዋ ተለየች ሞቱ ለኃጥእ ጽዋግ የኃጥእ
ሞት የከፋ ነው እንዳለ መዝሙር ፴፫:፳፩
21
በክፋቷ በእሳት በትር በእሳት አለንጋ እየደበደቡ እያገረፉ ከሥጋዋ
ለይተው ወሰዷት አንቺ ነፍስ ወደ ማን ትሄጂ እግዚአብሔርን
አታውቂ እያሉ ሲደፏት ሲያዳፏት ወሰዷት ያቺም ነፍስ ኩነኔ
መኖሩን አላውቅም ነበር አውቄ ቢሆን ልልበስ ልብላ ልጠጣ
አልልም ነበር አሁንም ስለእግዚአብሔር ስለእግዝእትነ
ማርያም ደከመኝ አሳርፉኝ አለች ፈጣሪሽንና ማርያምን የካድሽ
ወንጀለኛ አናሳርፍሽም አሏት ሁለተኛም ስለ እግዝእትነ
ማርያም ደከመኝ አሳርፉኝ አለች ማርያም ወዴት
ታውቂያታለሽ እያሉ ሲወስዷት አይቼ ብዙ አለቀስኩ ብዙም
አዘንኩ ልጄን እንዲህ አልኩት ሰው ሆኖ የማይበድል እንጨት
ሆኖ የማይጤስ የለምና እባክህ ማርልኝ አልኩት፡፡
21
ልጄም መለሰልኝ አትዘኝ እናቴ ሆይ ሰው በምድር መልካም
ግብር ካልሰራ መማር አይገባውም አለኝ፡፡ ያን ጊዜ ልቅሶ
አበዛች ይህች ነፍስ ስለእግዝእትነ ማርያም ጥቂት አሳርፉኝ
እያለች ጩኸቷን ማብዛቷን በሰማሁ ጊዜ መሪር ዕንባ
አለቀስሁ ልቅሶዬንም ልጄ በሰማ ጊዜ ስለ እናቴ ስለ ማርያም
ብላችሁ ጥቂት አሳርፏት ይህቺን ነፍስ አለ ያቺንም ነፍስ ጥቂት
አሳረፏት፡፡ ከዚያም በኃላ አንቺ ጎስቋላ ነፍስ ወዴት ትሄጃለሽ
መግቢያሽ ወዴት ነው ወዮለሽ ወዮታ አለብሽ እያሉ ወሰዷት
ከኃጥእም ቦታ አደረሷት አቡሃ ለሐሰት የሐሰት አባት ሐሰት
የሚያናግር ሰው የሚያሳማ ዝሙት የሚያሰራ ወደ መሸታ ቤት
የሚያኬድ ዘፈን የሚያስወድድ ነፍስ የሚያስገድል ሰይጣን ወደ
እርስዋ ከጭፍሮቹ ከመላእክተ ጽልመት ጋር ተሸቀዳደመው
ሄዱ መረመሯትም ወገናቸው ሆና አገኙዋት አንቺ ጎስቋላ ነፈስ
ወደ ማን ትሄጂ ወደ መንግሥተ ሰማያት ትገቢ ትወጃለሽን
እያሉ ተዘባበቱባት ሠራዊተ መላእክት ካሉበት አደረሷት
በመካከላቸው ብትቆም ይህቺን የተረገመች ነፍስ ውሰዱልን
አሉ ሽታዋ አስቸገረን ብለው ጮሁ፡፡
21
ከዚህም በኃላ አንቺ ርግምት ነፍስ ወዮልሽ ወዮታ አለብሽ እያሉ
ወደ ሰማይ አወጧት ከእግዚአብሔር ፊት አደረሷት የፈጠረሽ
እግዚአብሔር ይህ ነው ስገጂ እጅ ንሺ አሏት ያችም ነፍስ
ሰገደች እጅም ነሳች ቀድሞ ይጠብቃት የነበረው መልአክ
ውቃቢ እቤቱ ጠብቅ ያልከኝ ነፍስ ይህቺው ብሎ ለጌታ
አቀረባት ጌታም መልሶ ነፍስ ሆይ ለምን በደልሽኝ ፀሐይና
ጨረቃን እያፈራረቅሁ ሳወጣ ከጻድቃን አለየሁሽ እህልን
ለምግብ ወሀን ለመጠጥ ዕፅዋትን አትክልትን ፈጠርኩልሽ
የነፍስሽን መድኃኒት መልካም ግብር መሥራት ለምን እረሳሽ
ቢላት እኔ ኩነኔ መኖሩን አላወቅም ነበር አውቄ ቢሆን ልብላ
ልጠጣ ልልበስ አልልም ነበር፡፡ ጌታም ካህናትና መጻሕፍት
ካንቺ ዘንድ አልነበሩምን ለምን አልሰማሻቸውም ለነፍስሽ
ስንቅ መልካም ግብር ለምን አልሰራሽም ብሎ ቢጠይቃት
እርሷም የምትመልሰው ብታጣ ዝም አለች፡፡ ከዚህ በኃላ ጌታ
በምድር መልካም ግብር ያልሰራ መማር አይገባውምና ንሱ
ወደ አባቷ ወደ ሰይጣን ውሰዷት ለገሃነመ እሳት ሹም
ለጥልምያኮስ ስጧት አለ ዳግመኛም እስክመጣ ድረስ በሲኦል
በጨላማ ቤት ትኑር አለ ይሀንንም በሰማች ጊዜ ጮኸች ወይኔ
ሳልፈጠር በቀረሁት ይሻለኝ ነበር የተወለድኩባት ቀን ርጉም
ትሁን ብላ አለቀሰች ያች ነፍስ ብታለቅስ ሁላችንም አለቀስን
መላእክትም አክሊላቸውን አውርደው አለቀሱ፡፡
21
ቅዱስ ዳዊትም ቦኑ ለከንቱ ፈጠርኮ ለሰብእ በውኑ የሰውን ልጅ
ለከንቱ ፈጥረኸዋልን እንዳለ መዝሙር ፹፰፡ ፵፯ ጌታም
ወምንት ይበቁዖ ለሰብእ ለእመ ኩሎ ዓለመ ረብሀ ወነፍሶ ኅጎለ
ሰው ሁሉ ዓለምን ቢገዛ ቢነዳ ነፍሱን ካጣ ምን ይጠቅመዋል
እንዳለ ማርቆስ ፰፡፴፮ ለዚያች ነፍስ ሁላችንም አለቀስን፡፡
21
ከዚህ በኃላ ልጄ እንዲህ አለኝ ወደ ገነት እንሂድ አለኝ ሂጄም
ጻድቃን ሰማዕታት ደናግል መነኮሳት መልካም ሰዎች
የሚኖሩበትን አየሁ ወደላይ አወጣኝ ሥሩ የማይታይ ከትልቅ
ገደል አደረሰኝ ከዚያው ፯ ብርሃናትን ከፀሐይ ከጨረቃ ፲፪ እጅ
የሚያበሩ አየሁ ፩ አረጋዊ (ሽማግሌ) ሰው መጥቶ ማርያም
ሆይ አንቺ የከበርሽ የማኀፀንሽም ፍሬ የከበረ ነው አንቺን ያዩ
ዓይኖቼ የከበሩ ናቸው ብሎ እጅ ነሳኝ ልጄን ይህ ሰው ማነው
ብየ ጠየቅሁት ሄኖክ ነው አለኝ፡፡
21
ዳግመኛም እንደሱ አንድ ሰው መጥቶ እጅ ነሳኝ ልጄን ይህስ
ሰው ማነው አልሁት ኤልያስ ነው አለኝ ከዚህ በኃላ ከታች አስከ
ላይ በወርቅ ቀለም የተጻፈ ዓምድ ወርቅ አየሁ ቁመቱ
በመላኩ ክንድ ፲፭ ይሆናል ጽሕፈቱም ረቂቅ ነው እኔም
ይኸንን አይቼ ልጄን ጠየቅሁት ይህ ረቂቅ ጽሕፈት የተጻፈበት
ዓምድ ወርቅ ምንድነው አልሁት የጻድቃን ስማቸው ነው አለኝ
የፊታቸው መልክ ብቻ ነው የተጻፈው ብዬ ብጥይቅ አይደለም
ሁለንተናቸውም ተጽፏል እንጂ አለኝ ሳይወለዱ ነው ከተወለዱ
በኃላ ብለው ካባታቸው ከአዳም በፊት ተጽፈዋል አለኝ፡፡
21
ዳግኛም በዓምደ ወርቅ ከተጻፈው ጽሕፈት የሚበልጥ
የተጻፈበት የእሳት ዓምድ ወርቅ አየሁ በዚያ በእሳት ዓምድ ላይ
የተጻፉ እነማን ናቸው ብለው ኃጥአን ናቸው አለኝ ሳይፈጠሩ ነው
ከተፈጠሩ በኃላ የተጻፈው ብለው ለዚህ ለሥቃይ አስቀድመው
የተጻፉ ናቸው ብሎ አለኝ መጽሐፍ ያለውን አልሰማሽምን አለኝ
ቦ እለ ተሐርዩ እምከርሠ እሞሙ እመሂ ለሢመት ወእመሂ
ለነዲ ከእናታቸው ማኀፀን የተመረጡ ለሹመትም ሆነ ለድኀነት
አሉ እንዳለ ቅዳሴ አትናቴዎስ ቁ. ፻፲፫።
21
ከዚህ በኃላ ወደሌላ ቦታ ወሰደኝ ከፀሐይ ከጨረቃ ፲፪ እጅ
የምታበራ አገር አየሁ በየሰዓቱ ፼ ፼ የሚያፈራ ብዙ ፍሬ ያለው
ብዙ አትክልትም አየሁ ዳግመኛም ተምር ገውዝ ለውዝ ሎሚ
ትርንጎ ፬፼ ከ፷፯ አትክልት መዓዛቸው ልቦና የሚመስጥ በዚያ
ቦታ አየሁ ልጄንም ጠየቅሁት ይህ ቦታ ለማን ይሆናል አልሁት
ወንድ በ፩ሴት ሴት በ፩ ወንድ ተወስነው በንጽሕና ቢኖሩ በሞቱ
ጊዜ መኖሪያቸው ይህ ነው በልቡናቸው ንጹሕ የሆኑ ሰዎች
እግዚአብሔርን ያዩታል ወደ እግዚአብሔርም ይወስዱዋቸዋል
እንዳለ ማቴዎስ ፭:፰።
21
ከዚህ በኃላ በዚህ ቦታ አንፃር የወይን ወንዝ ወደአለበት ቦታ
ወሰደኝ በዚያም ቦታ ደጋጎች አባቶቻችን አዳም አቤል ሴት
መላልኤል ቃይናን ያሬድ አልፋስክድ የቀደሙ አባቶቻችን ሁሉ
አሉበት መጀመሪያ አባታችን አዳም መጥቶ ማርያም ሆይ
እንዴት ነሽ አለኝ አንቺን ያዩ ዓይኖቼ ንዑዳት ክቡራት ናቸው
አለኝ አቤልም መጥቶ አንዴት ነሽ አለኝ የቀደሙ አባቶቻችን
ሁሉ እየመጡ መልካሚቱ ርግብ ማርያም ሆይ እንዴት ነሽ
አንቺን ያዩ ዓይኖቻችን ንዑዳት ክቡራት ናቸው ብለው እጅ ነሡኝ
ሰገዱልኝ ከዚህ በኃላ የመዓር ወንዝ ወዳለበት ወሰደኝ በዚያው
ቦታ ሙሴ አሮን አሞጽ ኢሳይያስ ናሆም ኤርሚያስ ሶፎንያስ
ነቢያት ሁሉ ኤልሳቤጥ ራሔል ሣራ ርብቃ የጸደቁ ሴቶች ሁሉ
አሉ የነቢያት አለቃ ሙሴ መጥቶ እጅ ነሣኝ ሰገደልኝ ፀምር
ፀዐዳ ማርያም ሆይ እነዴት ነሽ አለኝ አንቺን ያዩ ዓይኖች
ንዑዳት ክቡራት ናቸው አለኝ ነቢያትም ሁሉ መጥተው እጅ
ነሡኝ ሰገዱልኝ ጽርሕ ንጽሕት ማርያም ሆይ አንቺን ያዩ
ዓይኖቻችን ንዑዳት ክቡራት ናቸው ብለው እጅ ነሡኝ ሰገዱልኝ
እናቴ ሔዋን መጥታ እንዴት ነሽ አለችኝ ጽርሕት ንጽሕት
እንዴት ነሽ አለችኝ ጽርሕት ንጽሕት ማርያም ሆይ አንቺን ያዩ
ዓይኖቼ ንዑዳት ክቡራት ይሁኑ አለችኝ ክቡራት ቅዱሳት
አንስትም ሁሉ መጥተው እጅ ነሡኝ ሰገዱልኝ የእግዚአብሔር
ማደርያ እንዴት ነሽ አሉኝ ከዚህ በኃላ የወተት ወንዝ ወደአለነት
ቦታ ወሰደኝ በዚያ ቦታ ሄሮድስ የገደላቸው ፲፬፼ ከ፬፻ ሕፃናት
አሉ እነሱም ባዩኝ ጊዜ መጥተው እጅ ነሡኝ ሰገዱልኝ የደናግል
መመኪያቸው ማርያም ሆይ አንቺ ከሁሉ ይልቅ የከበርሽ ነሽ
አንቺን ያዩ ዓይኖቻችን የከበሩ ይሁኑ ብለው እጅ ነሡኝ
ሰገዱልኝ፡፡
21
ከዚህ በኃላ የወይን ወንዝ ወደአለበት ቦታ የሚኖሩ እነማናቸው
አልሁት ባልንጀራቸውን እንደራሳቸው ማለት እንደ ነፍሳቸው
የሚወዱ ለተራበ ያበሉ ለተጠማ ያጠጡ ለታረዘ ያለበሱ ሰዎች
በሞቱ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይወስዳቸዋል እጅ ለመንሳት
ለመስገድ ወደፈለገ ሰማይ ሲወስዳቸው ቅዱሳን መጥተው
ይቀበሏቸዋል ዓለምን ድል ነሥተዋልና ዲያብሎስን
አሸንፈዋልና መልካም ግብር በመሥራት በእውነት ጎልማሶች
ናቸውና አገራችሁ ግቡ እንደኛ ደስ ይበላችሁ ይሏቸዋል አለኝ፡፡
21
ዳግመኛም ልጄን የማር ወንዝ ወደአለበት ቦታ እነማን
ይኖራሉ አልሁት ለችግረኛና ለምስኪን አስቦ የሚሰጥ እሱ
ምስጉን ነው እግዚአብሔር ከክፉ ቀን ያድነዋል ይጠብቀዋልም
ሕያውም ያደርገዋል፡፡ በምድር ላይ በሕይወት ሥጋ
በሚኖርበር ጊዜ ያስመሰግነዋል በጠላቶቹም እጅ አሳልፎ
አይሰጠውም ታምሞ በአልጋው ላይ ይረዳዋል፡፡ መልካሙን
ምንጣፍ ያነጥፍለታል እንዳለ ቅዱስ ዳዊት መዝሙር ፵፡፩ ፡፡
ዳግመኛም እግዚአብሔር ይራራላቸዋል ደካማውን ከብርቱ
ረዳት የሌለውን ከቀማኛ እጅ ያድናቸዋል ከግፍና ከነፍስ
ጭንቀት ይሠውራቸዋል፡፡ ለሰው የሚራሩ ሰዎች ከቡራን
ናቸው፡፡ መዝሙር ፸፩፡፳ የተበደሉ ሰዎች መንግሥተ
ሰማያትን እጅ ያደርጓታልና ለተበደለ የሚራራ እናት አባት
ለሌለው እናት አባት የሚሆን ክርስቲያንም አረመኔም ቢሆን
ሁሉም የእግዚአብሔር ፍጥረት ነውና ለድኃ ሁሉ የሰጠ በቅንነት
የሚሄድ ጽድቅንም የሚያደርግ ልቦናው ተንኮል የሌለበት
በአንደበቱ ዕውነትን የሚናገር በሰውነቱ ክፋት በቃሉ ሐሰት
የማይገኝበት በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ ወገኖቹን
የማይዘልፍ የማይሳደብ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውን
የሚያከብር ባልንጀራውን የማይከዳ ገንዘቡን በአራጣ
የማያበድር ከንጹሑ ላይ መማለጃን ጉቦን የማይቀበል ፍርድን
የማያጓድል ድሀን የማይበድል የከበረ ነው እንዳለ ሮሜ. ፩፡፲፫
ለመስጠት እጃቸውን የዘረጉ ሰዎች በሞቱ ጊዜ ከእግዚአብሔር
ዘንድ ያቀርቧቸዋል እጅ ነሥተው ሰግደው ወደዚህ ያመጧቸዋል
ዋጋቸውንም ያሰጣቸዋል በዚህ ቦታ ለዘለዓለም ደስ ብሎአቸው
ይኖራሉ አለኝ፡፡
21
ዳግመኛም የወተት ወንዝ ወዳለበት ቦታ እነማን ይኖራሉ
አልሁት፤ ከዝሙት ሰውነታቸውን ንጹሕ ያደረጉ ሴቶቸም
በድንግልና የኖሩ በሞቱ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይወስዳቸዋል
ዋጋቸውንም ይሰጣቸዋል፤ በዚያው ቦታ ደስ ብሏቸው ይኖራሉ
አለኝ፤ ከዚህ በኋላ በወርቅ በዕንቁ የተሸለመች ከፀሐይ
ከጨረቃ ፪ እጅ የምታበራ ምድር አሳየኝ፤ ይህ ቦታ ለማን
ይሆናል ብዬ ልጄን ጠየቅሁት መለሰልኝ፤ አንደበቱን ከሐሜት
የጠበቀ ኩራት የሌለበት ባልንጀራውን የማያዋርድ ምክንያተ
ሐኬት የሌለበት፤ በልቡናው ቂም በቀል የማያኖር የዋህ የሆነ
እነዚህ ሁሉ በሞቱ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይወስዱዋቸዋል
እጅ ነሥተው ሰግደው ያመጧቸዋል፤ የዋሃንስ ይወርስዋ
ለምድር፡፡ የዋሃን መንግሥተ ሰማይትን ወርሰው በውስጧ
ይኖራሉ፡፡ እንዳለ መዝሙር ፲፬:፪-፭ ዋጋቸውን ይህንን
ይሰጣቸዋል አለኝ፡፡
21
ዳግመኛም በዚህ ቦታ አንፃር ብዙ ሰዎች ተበትነው አየሁ በገነት
በር ብዙ ፍሬ ያለው የሚመስል ትልቅ ዛፍ አለ እነዚያ ሰዎች
ፍሬ ያለው መስሎአቸው በተራቡ ጊዜ ለመብላት ወደ ላይ
ሲወጣ ይወጣሉ፤ ወደታች ሲወርድ ይወርዳሉ ፍሬውን
አያገኙትም ይኸንን ባየሁ ጊዜ መሪር ዕንባ አለቀስኩ ልጄንም
ጠየቅሁት እሊህ ሰዎች ምንድር ናቸው፡፡ አልሁት፤ ይህስ ዕጽ
ምንድር ነው እኔ ዛፉ ፍሬ ያለው መስሎኝ ነበር እነዚህ የተራቡ
ሰዎች ፍሬውን ለመብላት ወደታች ሲወርዱ ይወርዳሉ፡፡
ወደላይ ሲወጣ ይወጣሉ ፍሬውን አላገኙትም ነገሩ ምንድር ነው
አልሁት እረሱም የነዚህን ሰዎች ኃጢአት እነግርሻለሁ አለኝ
በጾም በጸሎት የተጸመዱና በትዕግሥት ፍጹማን ቢሆኑ ለተራቡ
አላበሉም ለተጠማ አላጠጡም ለታረዘ አላለበሱም እንግዳ
አልተቀበሉም ትዕቢተኞች ኩራተኞች ናቸው አለኝ እነዚህ ቃላት
ሰውን ያስኮንናሉን ብዬ ልጄን ጠየቅሁት መለሰልኝ ከነዚህ
ከ፫ቱ ኃጢአት የበለጠ የለም ዲያብሎስም በትዕቢቱና በኩራቱ
ተዋርዷልና አለኝ፡፡ እንዲህም ብዬ ልጄን ጠየቅሁት አስከ መቼ
ድረስ ይኮነናሉ አልሁት ጻድቃን ስለእነርሳቸው
ስለሚለምኑላቸው ዳግመኛ እስከመጣ ድረስ ነው እኔም
እምራቸዋለሁ አልጥላቸውም ወደመንግሥተ ሰማያት ይገባሉ
አለኝ፡፡ ይኸንን በሰማሁ ጊዜ ልጄን አመሰገንኩት፡፡
21
ከዚህም በኃላ ወደሌላ ቦታ ወሰደኝ ከወርቅ መርከብ ላይም
አወጣኝ ወስዶም ከቤት አገባኝ ያች ቤትም ከፀሐይ ከጨረቃ
ይልቅ ታበራለች በውስጧም ብርሃኑን የሚያንፀባርቅ የግምጃ
ምንጣፍ ወሳንሳ ተነጥፎባታል የወርቅ የብርሃን አልጋ
ተዘርግቶባታል ይህች ቦታ ለማን ትሆናለች ብዬ ልጄን
ጠየቅሁት እግዚአብሔር እንድ ያደረጋቸው ባልና ሚስት
አይለያዩም ባልና ሚስት አንድ አካል ናቸው እንዳለ ማቴ. ፲፱፡፯

21
ወንድ በአንድ ሴት ሴት በአንድ ወንድ ተጠብቀው ቢኖሩ በሞቱ
ጊዜ ከዚህ ቦታ ያገባቸዋል ለዘለዓለምም ደስ ብሎአቸው
ይኖራሉ አለኝ፡፡ ከዚህ በኋላ ፬ሺ ከ፬፻ እንደ ፀሐይ የሚያበሩ
መናብርተ ብርሃን አየሁ እሊህ ማናብርት ለማን ይሆናሉ ብዬ
ልጄን ጠየቅሁት በስሜ ስለማመን የሚያስተምሩ ናቸው
አለኝ፡፡ ሁሉም ይጠሏቸዋል ሁሉም ይደበድቧቸዋል
ይገድሏቸዋል ኋላ ግን ከራሳቸው ፀጉር አንዲት አትጠፋም፡፡
በመቻላችሁ ነፍሳችሁን ታድኗታላችሁ እንዳለ ማቴዎስ ፲፡፳፪
፡፡
21
ሲርባቸው ሲጠማቸው ከሀገር ወደ ሀገር ሲሰደዱ ዓለምን የናቁ
ስለሃይማኖት ሰውነታቸውን ለሞት አሳልፈው የሰጡ ፲፪
ሐዋርያት ፸፪ አርድእት እነዚህ ሁሉ ይቀበሏቸዋል አለኝ፡፡
የቅዱሳን ሠራዊት ሁሉ የእግዚአብሔር ማደሪያው ማርያም
ሆይ እንዴት ነሽ ብለው እጅ ነሡኝ ሰገዱልኝ ከዚህ በኋላ
ወደሌላ ቦታ ወሰደኝ ከፀሐይ ከጨረቃ ይልቅ የሚያበሩ ፪፻
ቤተ ክርስቲያን አየሁ እነዚህ ለማን ይሆናሉ ብዬ ልጄን
ጠየቅሁት ለጳጳሳት ለኤጲስ ቆጶሳት ለቀሳውስት ለዲያቆናት
ለአናጎንስጢስ ለመዘምራን ይሆናሉ አለኝ ሁሉም ይገባሉ ብዬ
ጠየቅሁት አይገቡም ጥቂት ናቸው የሚገቡት አለኝ እግዚኦ
እግዚኦ እያሉ የሚዘባበቱብኝ ሁሉ ከመንግሥተ ሰማያት
አይገቡም የአባቴን ፍቃድ የፈጸሙ ይገባሉ ብዬ የተናገርኩትን
አልሰማሽምን አለኝ ማቴዎስ ፲፭:፬ ፡፡
21
ሰውነታቸውን ከዝሙት ንጹሕ ያደረጉ ከሰው ሚስት ያልሄዱ
ኩራት የሌለባቸው ትእቢት ምቀኝነት የሌለባቸው ቂም
በልቦናቸው ያላኖሩ ከአንድ ሴት ወደ አንድ ሴት ከአንድ ወንድ
ወደ አንድ ወንድ የማይሉ ቁጡና ሰካራም ያልሆኑ ለጣኦት
ያልሰገዱ በአምልኮ ባዕድ ያላመለኩ በሐሰት ያልማሉ ቤተ
ክርስቲያን የሚያዘወትሩ በንጹሕ ሆነው ሥጋዬን ደሜን
የሚቀበሉም የሚያቀብሉ ሰዎች እነዚህ ናቸው ከመንግስሥተ
ሰማያት የሚገቡ እነዚህን የነገርኩሽን ቃላት ያልፈጸሙ
መንግሥተ ሰማያት አይገቡም አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት አደረሰኝ የእሳት
መጋረጃ ያለበት የብርሃን ቤተ መቅደስ አየሁ በእጁ መሰንቆ
በገና ይዞ እየመታ እንደ ፀሐይ የሚያበራ አንድ ሰው አየሁ ያም
ሰው መሰንቆ በገና ሲመታ ምድሯን ያናውጻታል ከኢየሩሳሌም
ደጁ ቆሟል እኔም በገባሁ ጊዜ ወደእኔ መጣ ማርያም ሆይ
ከሁሉ ይልቅ አንቺ የከበርሽ ነሽ ብሎ እጅ ነሳኝ ሰገደልኝ የዚህ
ሰው ስሙ ማነው፤ ብዬ ልጄን ጠየቅሁት ቅዱስ ዳዊት ነው
አለኝ ሃሌ ሉያ ብሎ ሲያመሰግን ሰምቼው፡፡ ሃሌ ሉያ ሲሉ
የሰማኋቸው በዳዊት ቃል ምስጋና ሁሉ ተነግሯልን ብዬ ልጄን
ጠየቅሁት አዎን ምስጋና ሁሉ በዳዊት ቃል ተነግሯል አለኝ
እኔም መልሼ ሃሌ ሉያ ማለት ምን ማለት ነው ብዬ ልጄን
ጠየቅሁት ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር
አምላክ የተመሰገነ አምላክ ማለት ነው አለኝ ሃሌ ሉያ ቢል
ለሰው ምስጋና ይሆንለታልን ብዬ ጠየቅሁት አወን በጥቡዕ
ልቡና ሆኖ ሃሌ ሉያ ብሎ ቢያመሰግን ምስጋናው እንደ
መላእክት ይሆንለታል አለኝ ዳግመኛም መለስሁለት ሰው
የታመመ እንደ ሆነ ተኝቶ ቢጸልይ ኃጢአት ይሆንበታልን
አልሁት ለድውይ አይሆንበትም አለኝ፡፡ ከዚህ በኋላ ወደሌላ ቦታ
ወሰደኝ የወርቅ ልብስ ያለበት ዳርቻው የማይታወቅ እንደ
ፀሐይ የሚያበራ አገር አሳየኝ ይህ ቦታ ለማን ይሆናል ብዬ
ልጄን ጠየቅሁት ንብረታቸውን ትተው ዓለመን ንቀው ለመነኑ
ሰዎች ይሆናል አለኝ ይህችን ሀገር የሚያውቃት የለም፡፡ ካህናተ
ሰማይ አይገቡም ከበር ይቆማሉ እንጂ የባሕርይ አባቴ አብ
የሕይወት መንፈስ ቅዱስ እነገባለን አንቺም ግቢ ሀገር
ይሁንልሽ አልኝ ፫ሺ መላእክት ያገልግሉሽ አለኝ መነኮሳት ሁሉ
ይጋባሉን ብዬ ጠየቅሁት ሁሉም አይገቡም አለኝ ሰውነታቸውን
ከዝሙት ንጹሕ ያደረጉት ዓለምን ንቀው የመነኑ ደስታን
ተድላን የጠሉ ቁጡ ያልሆኑ ትዕቢት ኩራት የሌለባቸው ቂም
በልቦናቸው ያላኖሩ ሰውን ከሰው የማያጣሉ ንዝኅላል ያልሆኑ
በየጊዜው በየሰዓቱ ጸሎት የሚያደርጉ ይገባሉ አለኝ በጾም
ተጸምዶ የሚኖር መነኩሴ የሚበልጠው የለም ብሎ መጽሐፍ
የተናገረውን አልሰማሽምን ዳግመኛም ገንዘብ አግኝቶ
ከሚመጸውት መነኩሴ ገንዘብ የሌለው በትምህርትና በጸሎት
ተጸምዶ የሚኖር መነኩሴ ይበልጣል ዳግመኛም ጳውሎስ እኔ
በዓለም ዘንድ ምውት ነኝ ዓለምም በኔ ዘንድ ምውት ናት
እንዳለ፡፡
21
ይኸንን ሁሉ የፈጸመ መነኩሴ ከመንግሥተ ሰማያት ይገባልን
ብዬ ብጠይቀው የማይገቡትን እነግርሻለሁ አለኝ ትዕቢተኞች
ኩራተኞች ሴሰኞች ባልንጀሮቻቸውን የሚጠሉ ባንደበታቸው
እራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ መነኮሳትም ሆነው ተሾመው
የሚገዙ የሚነዱ በፈረስ በበቅሎ የሚሄዱ ከቆብ በኋላ
የሚሰስኑ ለሆዳቸው የሚገዙ አለልክ የሚበሉ የሚጠጡ ሁል
ጊዜ ዛሬ ዓመት በዓል ነው እያሉ ለመብል የሚዘጋጁ እነዚህ
መንግሥተ ሰማያት አይገቡም አለኝ ዳግመኛም ነይ ወደ
ምዕራብ እንሂድ የኃጥአን ነፍስ የሚኖሩበትን አሳይሻለሁ አለኝ
ወስዶ በሰማይና በምድር ዳር ከባሕር ዳርቻ አደረሰኝ የእሳት
ባሕር ያለበት የገሃነም ቦታ አሳየኝ ይህ ቦታ ለማን ይሆናል ብዬ
ልጄን ጠየቅሁት በመልካም ግብር ያልተገኙ በኃጢአት የኖሩ
ቦታቸው ይህ ነው አለኝ በዚያ በባሕር ውስጥ ብዙ ሰዎች
ከጉልበታቸው ድረስ ከእንብረታቸው ድረስ ከደረታቸው ድረስ
ከአንገታቸው ድረስ ከከንፈራቸው ድረስ ከእራሳችው ድረስ
የእሳት ባሕር ያጠለቃቸው አየሁ ከጉልበታቸው ድረስ
ያጠለቃቸው እነማን ናቸው ብለው በ፫ ጊዜያት ጸሎት የማይዙ
ናቸው አለኝ፡፡ ከእንብረታቸው ድረስ ያጠለቃቸው እነማን ናቸው
አልሁት ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዋዛ ፈዛዛ የሚጫወቱ ናቸው
አለኝ ከደረታቸው ድረስ ያጠለቃቸው እነማን ናቸው ብለው
ከቆረቡ በኋላ እህል ውሀ ሳይቀምሱ የሚናገሩ ናቸው አለኝ
ከአንገታቸው ድረስ ያጠለቃቸው እነማን ናቸው ብለው
ባልንጀሮቻቸውን የሚያሙ ናቸው አለኝ ከከንፈራቸው ድረስ
ያጠለቃቸው እነማን ናቸው ብለው ባልንጀራውን እንግደል
የሚሉ ናቸው አለኝ፡፡ ከራሳቸው ድረስ ያጠለቃቸው እነማን
ናቸው ብለው ከጽቅረ ቤተ ክርስቲያን ሴት የሚተኙ ናቸው
አለኝ፡፡ ከዚህም በኋላ ከሥር እስከ ጫፍ ከጫፍ እስከ ሥር
ድረስ በ፭ ሺህ ዓመት የማይደረስ ትልቅ ገደል አሳየኝ ያንዱ
ነፍስ ባንዱ ነፍስ ላይ ሲወድቅ አየሁ እኔም ምንድር ናቸው ብዬ
ልጄን ጠየቅሁት ባባታቸው በወንድማቸው በልጃቸው
በባልንጀራቸው ሚስት የሚሰስኑ ናቸው አለኝ ሴት አራስ ሆና
ወይም መርገሟ በመጣ ጊዜ በሩካቤ ሥጋ የሚገናኙና እንስሳን
ምድርን ሰንጥቀው የሚያወስቡ ወንዱንም በግብረ ሰዶም
የሚያመነዝሩ ካህን ሆኖ ከሌላ ሴት የካህኑም ሚስት ከሌላ
ወንድ ቢሄዱ እነዚህ ሁሉ የኩነኔ ቦታቸው ይህ ነው አለኝ ከዚህ
በኋላ ሌላ ቦታ አሳየኝ ፬ መላእክተ ጽልመት ተሸክመው
ወስደው በእሳት አልጋ አስቀመጠው በእሳት ፍላፃ ሲነድፉት
የእሳት ውሀ ሲአፈሱበት ፩ ሽማግሌ ሰው አየሁ ባየሁትም ጊዜ
ብዙ አለቀስሁ ይህ ሰው ማነው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት ጳጳስ ነው
አለኝ ኃጢአቱንም እነግርሻለሁ አለኝ፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ሥነ
ሥርዓት አልተከተለም በሕጌ ተጠብቆ አልኖረም ሥጋዬን
ደሜን ያረከሰ ነው ዘመኑንም በዝሙት የፈጸመ ነው ዳግመኛ
እንግዳ አልተቀበለም ለተራቡ አላበላም ለተጠማ አላጠጣም
ለታረዘ አላለበሰም የታመመ አልጠየቀም ያዘኑትን አላረጋጋም
የታሠሩትን አላስፈታም ስለዚህ የዘለዓለም ቦታው ይህ ነው
አለኝ፡፡ ከዚህ በኋላ ፬ መላእክተ ጽልመት በእሳት መንዶ
እየደበደቡ ከእሳት ባሕር ሲጨምሩት ፩ ታላቅ ሰው አየሁ፡፡ ይህ
ሰው ማነው ኃጢአቱስ ምንድር ነው ብዬ ጠየቅሁት፡፡ ሊቀጳጳስ
ነው ኃጢአቱን እነግርሻለሁ አለኝ ፩ነቴን ፫ነቴን ለሕዝብ
አላስተማረም እራሱን ወዳድ የግል ጥቅሙን ፈላጊ ነገሥታትን
መኳንንትን አይመክርም ፍርድ ሲጓደል ድሀ ሲበደል ዳኞችን
አይገሥጽም አያስተምርም ስለዚህ የዘለዓለም ኩነኔው ይህ ነው
አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ የመለኮትን ሥጋ ስትበላ ትራባለህን የመለኮትን ደም
ስትጠጣ ትጠማለህን ብለው በአፉ እሳት ሲያጎርሱት እሳት
ሲያጠጡት መላእክተ ጽልመት ሲጎትቱት አንድ ሰው አየሁ ይህ
ሰው ማነው ኃጢአቱስ ምንድር ነው አልሁት ቄስ ነው
ኃጢአቱንም እነግርሻለሁ አለኝ በክህነት ሥራ አልኖረም
ሰውነቱንም ንጹሕ አላደረገም ዘመኑንም በሳቅ በጨዋታ
የፈጸመ ነው የዘለዓለም ኩነኔው ይህ ነው አለኝ፡፡
21
ዳግመኛም መላእከተ ጽልመት ፊት ፊቱን እየደበደቡ በግምባሩ
ሲያዳፉት መላሱን በእሳት ምላጭ ቆርጠው በአፉ ደም ሲዘነብ
ወደ እሳት ባሕርም ሲጨምሩት አንድ ሰው አየሁ ይህ ሰው
ማነው ኃጢአቱስ ምንድር ነው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት መለሰልኝ
ዲያቆን ነው አለኝ ኃጢአቱስ ምንድር ነው ብዬ ጠየቅሁት
ኃጢአቱንም እነግርሻለሁ አለኝ በሕጌ አልኖረም ሥጋዬን ደሜን
በንጹሕ አላዘጋጀም ቤተ ክርስቲያን አልወደደም ለግብረ
ተልእኮ አልተፋጠነም ድሀ ቢሞት አልቀበረም ኩሩ ትዕቢተኛ
ነው አለኝ ከዚህ በኋላ ብዙ የተበታተኑ ሰዎች በእሳት መካከል
አየሁ እነዚህ እነማናቸው ብለው በፀሐይ በጨረቃ በከዋክብት
በዕንጨት በድንጋይ የሚያመልኩ ለዛር ለቃልቻ ለጠንቋይ
የሚደግዱ ናቸው ስለዚህ ኩነኔያቸው ለዘለዓለም ይህ ነው አለኝ
ከዚህ በኋላ በእሳት ዛፍ ላይ የተሰቀሉ ብዙ ሰዎች አየሁ ምንድር
ናቸው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት (ብዕልን) ክብርን የወደዱ ሀብት
ገንዘብ እያለቸው ለተራበ የማይሰጡ የማይመፀውቱ ድሆቸን
የሚበድሉ ባለጠጎች ናቸው ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይድቃሉ
ስለዚህ ለዘለዓለምም ቦታቸው ይህ ነው አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋለ በእሳት ሰንሰለት አንገታቸውን ታስረው ጨለማ
የለበሱ ሴቶች አየሁ እነማን ናቸው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት እናት
አባቶቻቸው በሕግ ሳያጋቧቸው ድንግልናቸውን ለማንም በዱር
በጫካ የሚሰጡ የሚሰስኑ ክብረ ንጽሕናቸውን የሚያጎድፉ
ናቸው ስለዚህ ኩነኔአቸውም ለዘለዓለም ይህ ነው አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ ልቅሶ ጥርስ ማፋጨት ከአለበት ገሃነመ እሳት
እጃቸውን እግራቸውን ታስረው በእሳት ግንድ ተሰቅለው ብዙ
ሰዎች አየሁ እነማናቸው ብዬ ጠየቅሁት የሰው ገንዘብ የሚበሉ
እንደልባቸው የሚናገሩ በዚህ ዓለም ያላግባብ የከበሩ ወይም
የበለጸጉ የሚገዙ የሚነዱ ብዑላን ነገሥታት መኳንንት ናቸው
ለዘለዓለም የኩነኔያቸው ቦታ ይህ ነው አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ የእሳት ውሾች የእሳት እባቦች የእሳት አንበሶች
እግራቸውን እጃቸውን ሲሰብራቸው በእሳት ዛፍ ላይ ተሰቅለው
ብዙ ሰዎች አየሁ እነማናቸው ብዬ ብጠይቀው ከቆብ በኋላ
የሚሰስኑ መነኮሳት ናቸው ሴቶችም በፀነሱ ጊዜ መድኃኒት
እየጠጡ የሚያስወርዱ ናቸው እነኛም ሕፃናት መልካምም ሆነ
ክፉ ብንሠራ ምነው ባደግን አለጊዜያችን አጠፉን ብለው አቤት
አቤት እያሉ ይጮሁባቸዋል አባቴ ግን መልአኩን ሕፃናቶቹን
ወደ መልካም ቦታ ውሰዳቸው ይለዋል እናቶቻቸውም
ለዘለዓለም ኩነኔያቸው ይህ ነው አለኝ በጥቡዕ ልቦና ነስሓ ቢገቡ
አትምራቸውምን አልሁት እምራቸዋለሁ አለኝ ቀሳውስቱም
የነፍስ ልጆቻቸውን መክርው ተቆጥተው ንስሓ ግቡ
አይሏቸውም እነደ ፈሌ እንደ (ፈላ) ይሆናሉ አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ እህል እንዳይበሉ ውሀ እንዳይጠጡ ተክልክለው
በእሳት ግንድ ታስረው ብዙ ሰዎች አየሁ እነማን ናቸው ብዬ
ብጠይቀው እንዲህ አለኝ ሴት በመርገም ጊዜዋ ሆና በሩካቤ
ሥጋ የተገናኙ ዓርብ ረቡን ፵ ጾም ሁዳዴን የማይጾሙ የኩነኔ
ቦታቸው ይህ ነው አለኝ ንስሓ ቢገቡ አትምራቸውም ብለው
እምራቸዋለሁ አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኃላ በእሳት መካከል እጃቸውን እግራቸውን የተቆረጡ
ሰዎች አየሁ ምንድር ናቸው ብዬ ጠየቅሁት ለሰው ክፉ የሚጥሩ
የሚጽፉም የሰው ገንዘብ የሚሰርቁ የሚነጥቁ የሚዘርፉ
ጉልበት እያላቸው ሠርተው የማይበሉ አታላዮች ኪስ
አውላቂዎች የሰው ቤት በቀን መዝጊያ የሚሰብሩ ሌሊት
ግድግዳ የሚሠረሥሩ ለሰው ነፍስ የማይሳሱ ርኀራኄ የሌላቸው
በገንዘብ እየተገዙ የሰው ነፍስ የሚያጠፉ ዓይናቸውን በስው
ሀብት ላይ የሚያሳርፉ በጧት ወደ መሸታ ቤት የሚገሠግሡ
በብዙ ድካም ያገኙትን ገንዘብ ቤተሰባቸውን በድለው ለመሸታና
ለዝሙት የሚያጠፉ ሰካራሞች አጭበርባሪዎች ናቸው የኩነኔ
ቦታቸውም ለዘለዓለም ይህ ነው አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ በእሳት ልጓም ተለጉመው በእሳት ሜንዶ ፊት
ፊታቸውን ሲደበድቧቸው አየሁ ምንድር ናቸው ብዬ ልጄን
ጠየቅሁት ባልንጀራቸውን የሚሰድቡ የሚያዋርዱ ምቀኞች
ተንኮለኞች ሟርተኞች ሰላቢዎች ተዕቢተኞች ሰውን
አሽሟጣጮች ናቸው አለኝ፡፡
21
ዲያብሎስም አዳምን በሰደበ ከማዕረጉ ተዋርዷልና ዳግመኛም
ጨው ባሩድ የሞላበት ጨለማ ጉድጓድ አየሁ በዚያው ውስጥ
እግራቸውን እጃቸውን የተቆረጡ ብዙ ሰዎች አየሁ፤ ምንደር
ናቸው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት አንድነቴን ሦስትነቴን ቅድመ
ዓለም ከአብ ያለ እናት መወለዴን ድኀረ ዓለም ከሰማየ ሰማያት
ወርጄ ከድንግል ማርየም ያለ አባት ወወለዴን በሄሮደስ ቅንዓት
ከሀገር ወደ ሀገር መሰደዴን መጠመቄን መገረፌን
በመልዕልተ መስቀል መስቀሌን በቀኖት መቸንከሬን ሞቼ
መነሣቴን ከትንሣኤዬም በኋላ በ፵ኛው ቀን ወደሰማይ ማረጌን
በኃላም ይህን ዓለም ለማሳለፍ በጌትነትና በታለቅ ግርማ
መምጣቴን የማያውቁ አረመኔዎች ናቸው ለዘለዓለም
የሚኖሩበት የኩነኔ ቦታቸው ይህ ነው አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ የእሳት እባብ በአንገታቸው በአፋቸው
ተጠምጥሞባቸው ከአፋቸው የእሳት ዲኝ ሲወጣ ብዙ ሰዎች
አየሁ ምንደር ናቸው አልሁት ብዙ ክርስቲያን ሂደው ያላገለገሉ
ካህናት ናቸው ለዘለዓለም የኩነኔ ቦታቸው ይህ ነው አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ በእሳት ገመድ አስረው ራሱን ወደታች እግሩን
ወደላይ አድርገው ሰቅለው አንድ ሰው አየሁ ዳግመኛ በእሳት
ጦር ፊት ፊቱን እየወጉ ከእሳት ላይ ሲጥሉት አየሁ ይህ ሰው
ማነው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት ቄስ ነው ኃጢአቱንም እነግርሻለሁ
አለኝ በሰንበት ዕጣን አያጥንም ንዝኅላል ትዕቢተኛ ኩራተኛ ነው
ጸሎት አያደርስም የዘለዓለም የኩነኔ ቦታው ይህ ነው አለኝ
ልጄን እንዲህ ስል ጠየቅሁት ቁርባን ምን ጊዜ ይቁረብ እሁድ
በነግህ ቀዳሚት በ፫ ሰዓት ሊቀደስ ይገባል ኦሪት ነቢያትን
ልፈጽማቸው ነው እንጂ ላሳልፋቸውና ልሽራቸው አልመጣሁም
ብሎ መጽሐፍ የተናገረውን አልሰማሽምን አለኝ፡፡
21
ቀዳሚትንም ካንዲት ቀን በቀር አልሻርኳትም ሌሎችን
ሰንበታት እንደ እሁድ ያክብሯቸው አለኝ ማለትም እንደ እሁድ
ያክብሯት ማለት ነው፡፡
21
ከዚህ በኋላ በእሳት ፍላፃ ሲነድፉት አንድ ሰው አየሁ ይህ ሰው
ማነው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት ዲያቆን ነው አለኝ ኃጢአቱስ
ምንድር ነው ብዬ ብጠይቀው እነግርሻለሁ አለኝ፡፡
21
መሥዋዕቱን በንጹሕ አላቀረበም በሰዓቱም አላዘጋጀም
ሰውነቱንም ከኃጢአት አላነፃም ለዘለዓለም የኩነኔ ቦታው ይህ
ነው አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ ከሌላ ቦታ ወሰደኝ የእሳት ጉድጓድ አየሁ ከውስጡ
ብዙ ሰዎች ሞልተው በአንገታቸው የእሳት እባቦች
ተጠምጥሞባቸው አራት መላእክተ ጽልመት የእሳት ጦር
ሲወረውሩባቸው አየሁ ባየኋቸውም ጊዜ ብዙ አለቀስኩ እሊህ
እናማናቸው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት መነኮሳት ናቸው በሕጌ
አልኖሩም ሥራዓቱንም አልጠበቁም መነኮሳት ነን ሲሉ
የመነኮሳትን ሥራ አይሠሩም የማይረባቸውን
የማይጠቅማቸውን ሥጋዊና ዓለማዊ ሹመት ይፈልጋሉ
ዘመናቸውንም በኃጢአት የፈጸሙ ናቸው ለዘለዓለሙ የኩነኔ
ቤታቸው ይህ ነው አለኝ፡፡
21
ከዚህ በኋላ የተዘጋጀ ታላቅ ገሃነም አየሁ ልጄም እናቴም
ማርያም ታየዋለችና ክፈቱ ብሎ የገሃነመ እሳት በር ጠባቂውን
ጠርቶ አስከፍቶ በሮቹ በተከፈቱ ጊዜ አይቼ ፈራሁ ተንቀጠቀጥኩ
ይህ ቦታ ስሙ ማነው ብዬ ልጄን ጠየቅሁት ገሃነመ እሳት ነው
አለኝ በዚህስ ውስጥ የሚኖሩ ምንድን ናቸው ኃጢአታቸውስ
ምንድ ነው አልኩት ሰው ከውሀና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ
በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይገባ ዘንድ አይቻለውምና
ስለዚህ ያልተጠመቁ አረመኔዎች ናቸው የዘለዓለም ቦታቸወም
ይህ ነው አለኝ፡፡ ዮሐንስ ፫፡፭፡፡ እነዚህም በስቃይ ያሉ ሁሉ
ባዩኝ ጊዜ ማርያም አንቺ ከሁሉ ይልቅ የከበርሽ ነሽ
የማኀፀንሽም ፍሬ የከበረ ነው አንቺን ያዩ ዓይኖቻቸን የከበሩ
ይሁኑ ብለው ጮሁ እኔም ሰው ሆኖ ኃጢአት የማይሠራ የለምና
ልጄን እባክህን ማርልኝ አልሁት እርሱም ዓርብ በሠርክ
መጥተው እስከ ሰኞ ድረስ ስለአንቺ በገነት ያሳርፏቸው አለኝ፡፡
21
ይህንም በሰማሁ ጊዜ ልጄን ፈጣሪዬን አመሰገንኩት
እመቤታችን ድንግል ማርያም ይህንን ከዚህ ቀጥሎ ያለውን
ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች እወቁ ተጠንቀቁ ሴት አራስ ሆና
በሩካቤ ሥጋ የተገናኘ በመርገሟም ሰዓት ወንድ ከሴቷ ሴቷም
ከወንድ ፈቃደኛ ሆነው ቢገናኙ ኃጢአት ይሆንባቸዋል በልቡ
ክፋት ያለበት ሰው ይህች መጽሐፍ ካለችበት ቦታ አይድረስ
መጽሐፉንም ከእንደዚህ ካለው መጥፎ ቦታ አታኑሩ ብላ
ተናግራለች፡፡
21
ዳግመኛም ስለ በዓላት አከባበር ቢቻላችሁ ፴፫ቱን ባይቻላችሁ
፭ቱን የጥር ማርያምን የየካቲት ኪዳነ ምሕረትን የግንቦት
ልደታን የሰኔ ማርያም የነሐሴ ፲፮ ፍስለታን እነዚሀን በዓላቴን
ያከበረ ይህን መጽሐፍ የፃፈ ያጻፈ ያነበበ የተረጎመ የሰማ ያሰማ
እነዚህን ሁሉ የፈጸሙ በሞቱ ጊዜ እኔ እቆምላቸዋለሁ ብላ
ለዮሐንስ ነገረቸው፡፡
21
የአምላክ ልጅ ወልደ አምላክ ለችግር አማላጅቱ እመቤታችን
ማርያም የገለጸላት ራእይ ባጭሩ እዚህ ላይ ተፈጸመ፡፡ የልጅዋ
የወዳጅዋ ቸርነት ለሁላችን ይደረግልን የእመቤታችን ረድኤት
በረከት እስከ ዘለዓለሙ ይደርብን አሜን አቡነ ዘበሰማያት፡፡
°°°°°°°
ምንጭ: መዝገበ ጸሎት ወመጽሐፈ ጸሎት ባለ ሰባ ስምንት
ከተሰኘው የጸሎት መጽሐፍ ላይ ከገጽ 591 እስከ 636
የተወሰደ ነው። በዘሪሁን እሸቱ የተዘጋጀ 20/4/2008 ዓ.ም
†† †† † † †† ††
ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ
ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች ዕመቤታችን እኛንም በበረከት እና
በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ
ታማልደን ፤ አሜን!!!
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሄ ር

Sunday, March 27, 2016

©ኦርቶዶክስተዋህዶነኝ®™ ቅዱስ ገብርኤል

ነቢዩ ዳንኤል “ዐይኖቼንም አነሣሁ” አለና አስከትሎ
“እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ
ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል
ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም
እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣
የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡… ይህንም
ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ
ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ
ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ
በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡(ዳን.10፡5-9)
ነቢዩ ዳንኤል እንዲህ ብሎ የተናገረው የመላእክት አለቃ
የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ ነበር፡፡
የዚህ መልአክ ግርማ የአምላክን ግርማ ይመስላል፡፡ ይህን
ለመረዳት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ
መለኮቱ ለወንጌላዊው ዮሐንስ የተገለጠበትን መገለጥ
መመልከት በቂ ነው፡፡ ወንጌላዊው ዮሐንስ በራእይ
ስለተመለከተው የክርስቶስ ግርማ ሲናገር፡- “ከኋላዬም እንደ
መለከት ድምፅ ያለ ታላቅ ድምፅን ሰማሁ፡፡ …የሰው ልጅ
የሚመስልን አየሁ፤ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ የሚደርስ ልብስ
የለበሰ ፣ ወገቡንም በወርቅ ዝናር የታጠቀ ነበር፡፡ ራሱና የራስ
ጠጉሩም እንደ ነጭ የበግ ጠጉር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፤
ዐይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፡፡ እግሮቹም በእሳት
የነጠረና የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፤ ድምፁም እንደ ብዙህ ውኃ
ድምፅ ነበረ፡፡”… ባየሁትም ጊዜ ከእግሩ ሥር ወደቅሁ አንደ
ሞተ ሰው ሆነሁ” አለ፡፡(ራእይ.1፡2-17 ) በእነዚህ ሁለት
ጥቅሶች ቅዱስ ገብርኤል በግርማው አምላኩን እንደሚመስል
አንረዳለን፡፡ የስሙም ትርጓሜ የሚያስዳው ይህን እውነታ
ነው፡፡ ገብርኤል ማለት አምላክ ወሰብእ ማለት ነውና፡፡
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል “እነሆ ከዋነኞቹ አለቆች”
አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ”(ዳን.10፡13) ብሎ በተናገረው
ንግግሩ በመላእክት ላይ የተሾሙ ሌሎች አለቆች እንዳሉ
ማስተዋል እንችላለን፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በቅዱሳን መላእክት
ዘንድ ስላሉት ነገዶች ሲገልጽ “… በሰማይ ያለውን በምደር
ያለውን የሚታየውንምና የማይታየውን መናብርትም ቢሆኑ
አጋእዝትም ቢሆኑ መኳንንትም ቢሆኑ ቀደምትም ቢሆኑ
ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእርሱ ለእርሱ ተፈጠረ” (ቈላ.1፡
16)በማለት ይዘረዝራቸዋል፡፡ ከዚህ ተነሥተን መላእክት
በተለያዩ ዐበይት ነገዶች የተከፈሉና ለእያንዳንዱም ነገድ የራሱ
የሆነ አለቃ እንዳለው ማስተዋል እንችላለን፡፡ ቅዱስ
ገብርኤልም ከእነዚህ ዐበይት የመላእክት ነገዶች መካከል አንዱ
በሆነው አርባብ (አጋእዝት ወይም ጌቶች) /አለቃ ኪዳነ ወልድ
ክፍሌ/ በሚባለው ዐቢይ ነገድ ላይ የተሾመ ሲሆን ከበታቹም
የሚመራቸው ዐሥር ነገደ መላእክት አሉ፡፡
ቅዱሳን መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ፊት አውራሪነት የሰው
ልጆች ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ተዋግተው ድል
ከመንሳታቸው አስቀድሞ ቅዱስ ገብርኤል እንደ አምላክ
ሊመለክ የወደደውን ሳጥናኤልን በመቃወም“አይዞአችሁ
ፈጣሪያችን ፈጥሮ አይጥለንምና አስክናገኘው፣ እስክናውቀው
ድረስ በያለንበት እንቁም፡፡” (አክሲማሮስ ገጽ.35) በማለት
መላእክት ያረጋጋ መልአክ ነው፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ በሰማያት
የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን
“አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ
ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት
እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ፡- ወደ ሰማይ
ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ
አደረጋለሁ፤… በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ
ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምደር ጥልቅም
ትወርዳለህ”(ኢሳ.14-1 6)በማለት ገለጠልን፡፡ ወደ ምድር
የጣሉት በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት እነ ቅዱስ
ገብርኤል ነበሩ፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ገብርኤል “እነሆ ከዋነኞቹ
አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ” እንዲሁም “ከሚካኤል
በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም” አለ፡፡(ዳን.10፡13፣2 1)
ቅዱስ ገብርኤል በብሉይ ኪዳን በቅድስና ሕይወት ለተጋውና
በገዢዎች ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያደረበት ሰው
(ዳን.5፡11)ተብሎ ለተመሰገነው ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና
ጥበብን የሰጠ መልአክ ነበር፡፡ ለዚህ ነቢይ እግዚአብሔር
አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ
ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆንና ሰማይንና ምድርን አሳልፎ
በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው
መልአክ ነው፡፡(ዳን.9፡21-22 ) አሁንም ነቢዩ ዳዊት “አቤቱ
እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት በልቡም የላይኛውን መንገድ
የሚያስብ ሰው ብፁዕ ነው፡፡ በልቅሶ ሸለቆ በወሰንኸቸው ስፍራ
የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና፡፡”(መዝ.83፡
5-6)እንዳለው በቅድስና ሕይወት በመጽናታቸው ምክንያት
ቅዱስ ገብርኤል መምህር የሆናቸው ቅዱሳን ብዙዎች ናቸው፡፡
የእኛ እውቀት በሰማያት ከትመው ካሉት ቅዱሳን መላእክት
እውቀት ጋር ሲነጻጸር እኛን እንደ ሕፃናት ያደርገናል፡፡ እኛ
የእነርሱን እውቀት ገንዘባችን የምናደርገው በትንሣኤ ነው፡፡
ስለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ “ዛሬ በመስታወት በድንግዝግዝ
እንደምናይ ነን ያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፡፡ አሁን በከፊል
ኋላ ግን እንደተገለጠልኝ መጠን ሁሉን አውቃለሁ”(1ቆሮ.13፡
1 2)ብሎ አስተማረን፡፡ ስለዚህም እውቀታችን የተሟላ
እንዲሆንና ሰይጣንን ለመቃወም እንድንበቃ የቅዱሳን
መላእክት የእውቀት ድጋፍ በእጅጉ ያስፈልገናል፤ ምክንያቱም
ከእኛ ይልቅ ሳጥናኤልን የሚያውቁት እነርሱ ናቸውና፡፡
እንዲህም ስለሆነ ጌታችን በእውቀታቸው እኛን እንዲረዱን
ለእያንዳንዳችን ጠባቂ መልአክትን ሰጠን፡፡(ማቴ.18፡10፤
ሉቃ.13፡6-9)
ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ይሆኑ ዘንድ ለተጠሩት መንፈሳዊ
እውቀቱን የሚያካፍላቸው መልአክ ብቻ አይደለም፤
ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች
ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡
የፋርስ ንጉሥ የነበረው ናብከደነፆር እግዚአብሔር አምላክ
ምድሪቱን ሁሉ ሲያስገዛለት በትዕቢት ተሞልቶ “በኃይሌ
አደርጋለሁ፣ በማስተዋል ጥበቤም የአሕዛብን ድንበሮች
አርቃለሁ፣ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፣ የሚቀመጡባቸውንም
ከተሞች አናውጣለሁ፣ በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት
እሰበስባለሁ፣ እንደ ተተወ እንቁላልም አወስዳቸዋለሁ፤ከእኔም
የሚያመልጥ የለም የሚቃወመኝም የለም፡፡”(ኢሳ.10፡13
-14) ብሎ በመታበይ የወርቅ ጣዖትን አሠርቶ ዱራ(አዱራን)
በሚባል ስፍራ ላይ አቆመው፡፡ በግዛቱ በልዩ ልዩ የሥልጣን
እርከን ላይ ያሉትን ሹማምንቱንና ገዢዎችን ሰበሰባቸው፤
“የመለከትና የእንቢልታ የመሰንቆና የክራር የበገናና የዋሽንትን
የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ወድቃችሁ ንጉሥ
ናብከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል ስገዱ፡፡ ወድቆም
ለማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣል”
ብሎ አዋጅ አስነገረ፡፡ ይህን አዋጅ የሰሙ የንጉሥ ሹማምንት
ሁሉ የመለከቱና የእንቢልታው እንዲህም የዘፈን ድምፅ በተሰማ
ጊዜ ተደፍተው ለወርቁ ምስል ሰገዱ፡፡
በባቢሎን አውራጃዎች ላይ የተሾሙ አዛርያ(ሲድራቅ)፣ አናንያና
(ሚሳቅ) ሚሳኤል(አብደናጎ) ግን ንጉሥ ላቆመው ምስል
አልሰገዱም፡፡ ነገር ሠሪዎችም ይህንን ወሬ ለንጉሥ ነገሩት፤
ንጉሥም እጅግ ተቆጥቶ ወደ እርሱ አስጠራቸው፡፡ እርሱ
ላቆመው ለወርቅ ምስል ያልሰገዱ እንደሆነ እጅና እግራቸውን
ታስረው ወደ እቶን እሳቱ እንደሚጣሉ አስጠነቀቃቸው፡፡
ሠልስቱ ደቂቅ ግን “ናብከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር
እንመልስልህ ዘንድ አንፈልግም፡፡ ንጉሥ ሆይ! እኛ
የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፣ ከሚነደውም ከእሳቱ
እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፤ ንጉሥ ሆይ!
ይህም ባይሆን አማልክትህን አንዳናመልክ፣ ላቆምኸውም
ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ” ብለው መለሱለት፡፡
የንጉሥ ናብከደነፆር ቁጣ ከፊት ይልቅ እጅግ ነደደ እሳቱንም
ሰባት እጥፍ እንዲያቀጣጥሉና እነዚህን ሦስት ብላቴኖች እጅና
እግራቸውን አስረው ከእነ ማዕረግ ልብሳቸው ከእቶን እሳት
ውስጥ እንዲጨምሩአቸው ትእዛዝን አስተላለፈ፡፡ ትእዛዙ
አስቸኳይ ነበርና እነርሱን ወደ እሳቱ የጣሏቸውም ኃያላን
በእሳቱ ወላፈን ተገርፈው ሞቱ፡፡ እንዲህ ሲሆን ሳለ ግን
ሠልስቱ ደቂቅ ወደ አምላካቸው “በፍጹም ልባችን
እናምንሃለን፣ እንፈራሃለን፣ አታሳፍረን እንጂ ገጸ ረድኤትህንም
እንፈልጋለን፡፡” እያሉ ይጸልዩ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክ
ጸሎታቸውን ተቀበለ፤ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልንም
ከመጣባቸው መከራ ይታደጋቸው ዘንድ ላከው፡፡ ቅዱስ
ገብርኤልም እስራታቸውን ፈታ፤ እሳቱን እንደ ውኃ
አቀዘቀዘው፡፡ ሠልስቱ ደቂቅም መልአኩን ልኮ ከዚህ እቶን
እሳት ያዳናቸውን አምላክ “የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር
ይክበር ስምህም ለዘለዓለም የተመሰገነና የከበረ ነው” በማለት
አመሰገኑት፡፡
ንጉሥ ናብከደነፆርም ሠልስቱ ደቂቅ እሳቱ አንዳች ጉዳት
ሳያደርስባቸው በእሳት ውስጥ ሲመላለሱ ከእነርሱ ጋር የሰው
መልክ ያለው ነገር ግን አምላክን የሚመስል መልአክ
ተመለከተ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሊቀ ካህናቱን ቀያፋን ፊቱን ጸፍቶ
አፉን ከፍቶ “ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለሕዝቡ ይሞት
ዘንድ እንዲሻለን አታስቡምን”(ዮሐ.11፡4 9) ብሎ
እንዳናገረው እንዲሁ ናብከደነፆርንም “እነሆ እኔ የተፈቱ
በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎችን በዚያ አያለሁ
ምንም የነካቸው የለም፤የአራተኛውም መልክ
የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል” ብሎ እንዲናገር አደረገው፡፡
የእግዚአብሔር ልጅን መልክ ያለው ያለው በኋላም መልአክ
ብሎ የተናገረለት ቅዱስ ገብርኤልን ነበር፡፡ እርሱ ስለመሆኑ
ለነቢዩ ዳንኤል በተገለጠበት ግርማ ማረጋገጥ እንችላለን፡፡
ናብከደነፆርም ወደ እሳቱ እቶን በመቅረብ እነዚህ ብላቴኖችን
“እናንተ የልዑል አምላክ ባሮች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ኑ
ውጡ ብሎ ተናገራቸው፡፡” እነርሱም ከእሳቱ ወጡ ሹማምንቱና
መኳንንቱ፣ አማካሪዎችና የአገር ገዢዎች ሁሉ እሳቱ በእነዚህ
ብላቴኖች ላይ አንዳች አቅም እንዳልነበረው፣ ከጠጉራቸው
ቅንጣት አንዱን እንኳ እንዳላቃጠለው፣ ሰናፊናቸውም
እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው ተመለከቱ፡፡
ንጉሥ ናብከደነፆርም መልአኩን ልኮ ያዳናቸውን የእነዚህን
ቅዱሳንን አምላክ አመሰገነ፡፡ በእነርሱ አምላክ ላይም የስድብን
ቃል የሚናገር ሰው እንደሚገደልና ቤቱም የጉድፍ መጣያ
እንዲሆን አዋጅ አስነገረ፡፡ አዛርያ አናንያ ሚሳኤልም በንጉሡና
በሹማምነቱ ዘንድ ሞገስ አገኙ በክብርም ከፍ ከፍ አሉ፡፡(ዳን.3
በሙሉ)
ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን መንጎቹዋ የእምነትን ፍሬ ከእነዚህ
ብላቴኖች ተምረው እግዚአብሔርን በማምለክ እንዲጸኑና
የመልአኩን የቅዱስ ገብርኤልን ተራዳኢነት እንዲረዱ
በታኅሣሥ 19 ቀን ይህን ዕለት ትዘክራለች፤ በታላቅ
ድምቀትም ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ
እምነት በድርጊት ሊታይ የሚገባው ክርስቲያናዊ ተግባር ነው፡፡
በክርስቶስ ኢየሱስ አምናለሁ የሚል ሁሉ ካመነበት ጊዜ አንስቶ
ክርስቶስን መስሎ ለመኖር ሊተጋና መስሎ ሊመላለስ
ይገባዋል፡፡ በሠልስቱ ደቂቅ የታየው እምነት በአንድ ጀምበር
የተገነባ እምነት ሳይሆን ከልጅነታቸው ጀምሮ በአንድ
እግዚአብሔር ታምነው በቅድስና ሕይወት በመመላለስ የመጣ
እምነት ነው፡፡ እነዚህ ብላቴኖች በእግዚአብሔር ዘንድ
የሚያገኙትን የድል አክሊል ተስፋ አድርገዋልና አርባ ዘጠኝ
ክንድ ያህል የነደደውን የእሳት እቶን አላስፈራቸውም፤
በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው ጽኑ እምነት በእሳት ተቃጥለው
ለመሞት እንኳ አስጨከናቸው፡፡ እንዲህም ሆነው
በመገኘታቸው በእምነታቸው እግዚአብሔርን ደስ አሰኙት፤
ስለዚህም እግዚአብሔር ባለሟሉን ቅዱስ ገብርኤልን በመላክ
ከእሳቱ እቶን ታደጋቸው፡፡ ይህ ታላቅ የሆነ እምነት ሰዶማውያን
ገዢዎች በተነሡባት በአሁኑዋ ዓለም በእኛ ክርስቲያኖች ላይ
ሊታይ የሚገባው እምነት ነው፡፡ እነዚህ ገዢዎች ኢኮኖሚያዊ
ጡንቻቸውን ታምነው፣ ነፍሳችን በእነርሱ እጅ የተያዘች
መስሎአቸው፣ በእኛ ላይ ሰይጣናዊ ሕግጋትን ሊጭኑብን ደፋ
ቀና ይላሉ፡፡ ስለዚህም እኛ ክርስቲያኖች የምድሪቱ ገዢዎች
እኛን ለማስፈራራት ሲሉ በእኛ ላይ ያነደዱትን እሳት በመልአኩ
በቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት እንደሚያጠፋልን በእግዚአብሔር
ታምነን በእምነት ልንቃወማቸው ይገባናል፡፡ እግዚአብሔር
አምላክ ከእነዚህ ከክፉ ሰዶማውያን ገዢዎች ጥፋት ምድራችንን
ይታደጋት፤ የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጸሎት
ይጠብቀን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

Saturday, March 26, 2016

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: ሰንበት

#ሰንበት !
‹‹ስድስት ቀን ስራ፣ተግባርህም ሁሉ አድርግ በሰባተኛው ቀን
ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፡፡
እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን አርፏልና ስለዚህ
እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታል፡፡ ›› (ዘጸ
20፡10-11)
ሰንበት ማለት ምን ማለት ነው ?
ሰንበት ማለት አቆመ፣አረፈ ማለት ነው፡፡ይህ ቀን የጌታ ዕረፍት
የተባረከም ቀን ነው፡፡ከማንኛውም ሥጋዊ ሥራ ተቆጥበን
የእግዚአብሔርን ውለታ የምናስብበት ቀን ነው፡፡ ሰው እረፍት
ያስፈልገዋል፡፡ የሰንበት ቀንም የተፈጠረው ለዚህ ነው፡፡ (ዘዳ
5፡14)፣(ማር 2፡38)
ከሳምንቱ ሰባት ቀናት መካከል ለእረፍት የተቀደሰው
የተባረከው ዕለት ሰንበት ብቻ ነው፡፡ ስለሌሎች ቀናት
የተነገረው ‹‹ ያ መልካም እንደሆነ አየ››የተባለው ብቻ ነው፡፡
ሰንበትን ግን ባርኮታል ቀድሶታል፡፡ (ዘፍ 1፡12፣ 18፡ 20፣
25፡31)
በሐዲስ ኪዳን ለክርስቲያን ሁለት ሰንበት አለ ቀዳሚት ሰንበት
(ቅዳሜ) እና ሰንበተ ክርስቲያን(እሑድ)
1. ቀዳሚት ሰንበት (ቅዳሜ) ጌታ ያረፈባት ለእስራኤል ዘሥጋ
የታዘዘው ሰንበት ነው፡፡
ይህ ቀን እስራኤላውያንን እግዚአብሔር አምላክ ከግብፅ
ባርነት ወደ እረፍት እንዳወጣቸው ያመለክታል፡፡(ዘዳ
5-2-16) በእግዚአብሔር እና በህዝቡ መካከል ምልክት ነበረ
ሰንበትን አለማክበር ግን ከባድ ቅጣት ያስከትል ነበር፡፡ (ዘጸ 3፡
17) ፣ (ሕዝ 20፡12) ፣ (ዘኁ 15፡32-36)
ፈሪሳውያን በነበራቸው የተሳሳተ አመለካከት በሰንበት ቀን
እንኳን መልካም ሥራን አይሰሩም ነበር፡፡ስለዚህም በጌታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ ተወቅሰዋል፡፡ (ማቴ 12፡14) ፣ (ሉቃ 4፡
16)
በዘመነ ሐዲስ የክርስቲያኖች የቀዳሚት ሰንበት አከባበር እንደ
አይሁድ ለሰው የሚከብድ እንዳይሆን በፍትሐ ነገሥት አንቀጽ
19 ላይ ተገልጿል፡፡
2. ሰንበተ ክርስቲያን (እሑድ)
እሑድ ማለት ‹‹አሐደ›› ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን
ትርጉሙም የመጀመሪያ ማለት ነው፡፡ ይህቺ ዕለት በመጽሐፍ
ቅዱስ ‹‹ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን›› በመባል ትታወቃለች፡፡
ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹የጌታ ቀን›› ያላት ናት (ራእይ 1፤10) ፡፡
ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ ‹‹ዕለተ እግዚአብሔር›› የሚላት
ዕለተ እሑድ ናት፡፡
ዕለተ እሑድ እንደ ሰንበት የሚከበርበት ምክንያቶች፡-
- እግዚአብሔር ሥራውን የጀመረባት ለሥነፍጥረት መጀመሪያ
ዕለተ (ጥንተ ዕለት) ናትና
- ዕለተ ሥጋዌ ናት፡፡ ጌታ የተፀነሰባትና እርቅ የተወጠነባት
የፍሰሐ ቀን፡፡
- ዕለተ ትንሣኤ ናት፡፡ ጌታ ከሙታን ተለይቶ የተነሳባት ዕለት
- የቤተ/ክ የልደት ቅን ናት፡፡መንፈስ ቅዱስ ለሐዋሪያት
የወረደባት ኃይልና ፅናትን ያኙባት ዕለት
-ጌታ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም በቅዱሳን
መላእክቱ ታጅቦ በጌትነቱ ለፍርድ የሚመጣባት ታላቅ የፍርድ
ቀን ናትና የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚካሄዱባት ዕለት
ናት (1ኛ ቆሮ 16፤1)
-የሐዋሪያት ዘመንም በጤሮዓዳ ያሉ ክርስቲያኖች እሑድ ቀን
ይሰበሰቡ ነበር (የሐዋ. 20፤7)
በቤተክርስቲያን ታሪክ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ
የክርስቲያኖች ሰንበት ናት በማለት ሥራ እንዳይሰራባት አዋጅ
አስነግሮ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ይህቺ ዕለት በሐዲስ ኪዳን
መከበር የጀመረ ቢሆንም በብሉይ ኪዳን ከፋሲካ በፊት የሰንበት
(የቀዳሚት) ማግስት በመባል በኩራት እና ቀዳሚያት
የሚያቀርቡበት ቀን ነበር፡፡ (ራዕ 1፡10)
በቀዳሚት ሰንበት ቅዱስ እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ አርፎ
ሥጋዊ እረፍትን ለሰው እንዳስተማረ በእሑድ ቀን (በሰንበተ
ክርስቲያን) በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት
የተገኘውን የዘላለማዊ የነፍስ ዕረፍት የምናስብበት ነው፡፡ (ዕብ
4፡1-10)
ከሰንበት ረድኤት በረከት ይክፈለን!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: የእመቤታችን 5ቱ ሀዘናት

የእመቤታችን 5ቱ ሀዘናት
◆ ◆ "ስምዖንም ባረካቸው እናቱን ማርያምንም። እነሆ፥
የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ በእስራኤል ላሉት
ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም
ምልክት ተሾሞአል፥ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል
አላት።" ሉቃስ 2:33-34
◆ ◆ "የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ፥ እንደ በዓሉ
ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤ ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ፥
ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥
ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር። ከመንገደኞች ጋር የነበረ
ስለ መሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ሄዱ፥ ከዘመዶቻቸውም
ከሚያውቋቸውም ዘንድ ፈለጉት፤ ባጡትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ
ኢየሩሳሌም ተመለሱ። ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን
መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም በመቅደስ
አገኙት፤ የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ።
ባዩትም ጊዜ ተገረሙ፥ እናቱም። ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ
አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ
ነበርን አለችው። እርሱም። ስለ ምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት
እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን? አላቸው።" ሉቃስ
2:41-48
◆ ◆"በዚያን ጊዜም ጲላጦስ ኢየሱስን ይዞ ገረፈው።
ወታደሮችም ከእሾህ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ አኖሩ ቀይ
ልብስም አለበሱት፤ እየቀረቡም። የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም
ለአንተ ይሁን ይሉት ነበር፤ በጥፊም ይመቱት ነበር። ጲላጦስም
ደግሞ ወደ ውጭ ወጥቶ። እነሆ፥ አንዲት በደል ስንኳ
እንዳላገኘሁበት ታውቁ ዘንድ እርሱን ወደ ውጭ
አወጣላችኋለሁ አላቸው። ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ ቀይ
ልብስም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ። ጲላጦስም። እነሆ ሰውዬው
አላቸው። የካህናት አለቆችና ሎሌዎች ባዩትም ጊዜ። ስቀለው
ስቀለው እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም። እኔስ አንዲት በደል ስንኳ
አላገኘሁበትምና እናንተ ወስዳችሁ ስቀሉት አላቸው።" ዮሐንስ
19:1-6
◆ ◆ "ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀሉንም ተሸክሞ
በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት
ወጣ። በዚያም ሰቀሉት፥ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት፥ አንዱን
በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ።
ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤
ጽሕፈቱም። የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ የሚል ነበረ።"
ዮሐንስ 19:17-19
◆ ◆ "ከዚህም በኋላ አይሁድን ስለ ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ
መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ
ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህም መጥቶ
የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ። ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ
ኢየሱስ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል
የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ። የኢየሱስንም ሥጋ
ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር
ልብስ ከፈኑት። በተሰቀለበትም ስፍራ አትክልት ነበረ፥
በአትክልቱም ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ።
ስለዚህ መቃብሩ ቅርብ ነበረና ስለ አይሁድ ማዘጋጀት ቀን
ኢየሱስን በዚያ አኖሩት።" ዮሐንስ 19:38-42
የእመቤታችን 5 ቱ ሀዘናት
◆ ◆ " ስምዖንም ባረካቸው እናቱን ማርያምንም ። እነሆ ፥
የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ ፥ ይህ በእስራኤል ላሉት
ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም
ምልክት ተሾሞአል በአንቺም ደግሞ ፥ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል
አላት ።" ሉቃስ 2:33-34
◆ ◆ " የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ ፥ እንደ በዓሉ
ሥርዓት ወጡ ፤ ወደ ኢየሩሳሌም ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ ፥
ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር ፥
ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር ። ከመንገደኞች የነበረ ጋር
ስለ መሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ሄዱ ከዘመዶቻቸውም
ከሚያውቋቸውም ዘንድ ፥ ፈለጉት ባጡትም ፤ ጊዜ ወደ
ኢየሩሳሌም እየፈለጉት ተመለሱ ። ከሦስት ቀንም በኋላ
በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም
በመቅደስ አገኙት የሰሙትም ሁሉ ፤ በማስተዋሉና በመልሱ
ተገረሙ ። ባዩትም ጊዜ ፥ እናቱም ተገረሙ ። ልጄ ሆይ ፥
ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን
ስንፈልግህ ነበርን አለችው ። እርሱም ። ስለ ምን ፈለጋችሁኝ?
በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን? አላቸው
።" ሉቃስ 2:41-48
◆ ◆ " በዚያን ጊዜም ጲላጦስ ኢየሱስን ይዞ ገረፈው ።
ወታደሮችም ከእሾህ አክሊል ጐንጕነው አኖሩ ቀይ በራሱ ላይ ፤
ልብስም አለበሱት እየቀረቡም የአይሁድ ። ሰላም ንጉሥ ሆይ ፥
ለአንተ ይሉት ነበር ፤ ይሁን በጥፊም ይመቱት ነበር ። ደግሞ
ጲላጦስም ወጥቶ ወደ ውጭ ። እነሆ ፥ አንዲት በደል ስንኳ
እንዳላገኘሁበት ዘንድ ታውቁ እርሱን ወደ ውጭ
አወጣላችኋለሁ አላቸው ። ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ ቀይ
ልብስም ለብሶ ወደ ውጭ ጲላጦስም ወጣ ። ። ሰውዬው
አላቸው ። እነሆ የካህናት አለቆችና ሎሌዎች ባዩትም ጊዜ
ስቀለው ስቀለው እያሉ ። ። ። ጮኹ ጲላጦስም እኔስ አንዲት
በደል ስንኳ አላገኘሁበትምና እናንተ ወስዳችሁ ስቀሉት አላቸው
።" ዮሐንስ 19:1-6
◆ ◆ " ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት መስቀሉንም ፤ ወደ
ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ተባለው የራስ ቅል ወጣ ። ስፍራ
ወደሚሉት ሰቀሉት ፥ በዚያም ከእርሱም ጋር ፥ ሌሎች ሁለት
አንዱን በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ
ጲላጦስም ። ደግሞ ጽሕፈት በመስቀሉ ላይ ጽፎ አኖረው ፤
ጽሕፈቱም የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ። ኢየሱስ የሚል ነበረ ።"
ዮሐንስ 19:17-19
◆ ◆ " ከዚህም በኋላ ስለ አይሁድን ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ
መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ
ጲላጦስን ለመነ ጲላጦስም ፈቀደለት ። ፤ ስለዚህም መጥቶ
የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ ። አስቀድሞ በሌሊት ደግሞም ኢየሱስ
ወደ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና
የእሬት ቅልቅል ይዞ የኢየሱስንም ሥጋ መጣ ። እንደ አይሁድ
ወስደው አገናነዝ ልማድ ከሽቱ በተልባ እግር ልብስ ጋር ።
ስፍራ ከፈኑት በተሰቀለበትም አትክልት ነበረ ፥ በአትክልቱም
ማንም ያልተቀበረበት ገና አዲስ መቃብር ነበረ ። ስለዚህ ስለ
መቃብሩ ቅርብ ነበረና አይሁድ ማዘጋጀት ቀን ኢየሱስን በዚያ
አኖሩት ።" ዮሐንስ 19:38-42

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: ያለእመቤታችን አማላጅነት አለም አይድንም

ያለእመቤታችን አማላጅነት አለም አይድንም" - - - ይህ
ለሚያምን እንጂ ለማያምን የሚነገር አይደለም!! በስመ አብ
ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፡፡ ስለዚህ ቃል
ሰወች ምን ይላሉ? በእውኑ ያለክርስቶስ መዳን አለን? መዳን
በማንም የለም ተብሎ ተፅፏልና፡፡ ነገር ግን ከእናንተ ውስጥ
የቅዱሳንን የፀጋ መጠን የሚያውቅ ማን ነው? ለአንዳንዶቹ
የፀጋ አማልክትነትን እንዲሁ ተቀብለዋልና፡፡ እንግዲህስ
አምላክ ከሆኑ ማዳንም መግደልም እንደሚችሉ አናውቅምን?
ወይንስ ለሃዋርያት የተሰጠ ፀጋ ምንድን ነው? በምድር ሆነው
ሳሉ የመፍታትም የማሰርም ስልጣን የተሰጣቸው አይደለምን?
መፍታትና ማሰርስ ማዳንና መኮነን ማለት አይደለምን? ታዲያ
እኒህ ሃዋርያት ፍጥረትን ያስሩና ይፈቱ ዘንድ ስልጣን ያላቸው
የክርስቶስን የማዳን ሃይል ተጋፉትን? ወይንስ ሙሴ በፈርኦን
ላይ አምላክ ሲሆን የእግዚአብሄርን አምላክነት ተሻማ ይሆን?
አይደለም ሙሴስ የፀጋ አምላክ እንጂ የባህሪ አምላክ ሆኖ
አልተገኝም ደግሞም ፀጋውን ከእግዚአብሄር የተቀበለው ነውና
ሰጭ በፈቃዱ ለተቀባይ ስጦታ ቢሰጥና ተቀባይ ስጦታውን
ቢጠቀምበት ሰጭውን የሚያናድድ አንድም የሚጋፋ
እንዳልሆነ ግልፅ ነው፡፡ ወይንስ በፍርድ ቀን ሃዋርያት በፍርድ
ዙፋን ተቀምጠው እንደሚፈርዱ ተጠቅሷልና ፍርድ
የእግዚአብሄር ሲሆን እኒህ ሃዋርያት ስለምን በእግዚአብሄር
ስራ ገባችሁ የሚል ማነው? የመፍረዱን ስልጣን ከሰጭው
በፀጋ ተለግሰዋልና ሰጭውን እያመሰገኑ በፀጋው ሃሴትን
ቢያደርጉ ነውንጂ እነርሱስ እግዚአብሄር እንደሆኑ የሚያስቡ
አይደለም፡፡ ወይንስ ሲፈርዱ አንዱንም ለሞት አንዱንም
ለህይወት ሲያደርጉ የማዳንና የመኮነን ስራ እየሰሩ አይደለምን?
አልያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሹመዋልና በእውነት ነገር ግን
እንደወደዱ ይፈርዳሉ እንጂ ስለመፍረዳቸው ነፃ ፈቃድ
የላቸውምን? ነፃ ፈቃድ ከሌላቸውስ በዚህ ሰው ላይ ፍረዱ
በዚህኛው ግን እንዳትፈርዱ እየተባሉ ሊሰሩ በፍርድ ወንበር
የሚቀመጡ ከሆነ ከቶ የተሰጣቸው ክብር ምን ይሰራላቸዋል?
ሁሉን ትተው ክርስቶስን ስለ መከተላቸውስ ክርስቶስ የገባላቸው
ቃል ለከንቱ ነበርን? የሚያስተውል ያስተውላል፡፡ እንግዲህስ
ለቅዱሳን የተሰጠውን የፀጋ መጠን የሚያውቅ ከሌለ ከቅዱሳን
ሁሉ የምትበልጥ የእመቤታችንን ፀጋ ጠንቅቆ ማወቅ
የሚችል ማነው? ድንግልንስ ይህን ታደርጊያለሽ ፡ ይህንን ግን
ማድረግ አትችይም የሚላት ከፍጥረት ወገን ማን ነው?
እንግዲህ የእግዚአብሄር ቃል የመጣላቸውን እነዚያን አማልክት
ይባሉ ዘንድ የወደደ አምላክ አማልክት ያላቸው እንዲሁ ለከንቱ
ነውን? ቅዱስ ገብርኤልስ ድንግልን ፀጋን የተሞላሽ ሆይ ሲላት
በእውነት ከፀጋ የጎደለባት አንዳች ነገር አለን? እንዲህስ የምንል
ከሆነ ቅዱስ ገብርኤልን ሃሰተኛ እናደርገዋለን፡፡ እመቤታችን
ፀጋወችን ሁሉ ከተሞላች ለአንዳንዶች የተሰጠ የፀጋ አምላክነት
ከእርሷ የተለየ ነውን? ሙሴን የፀጋ አምላክ ያደረገ
እግዚአብሄር ሙሴ የሚታዘዝላትን እመቤት እንደምን አብልጦ
አያደርጋት? የፀጋ አምላክ ከሆነችስ ማዳን ይህ ከባድ ነውን?
ለእመቤታችንስ ከፀጋወች ሁሉ የሚበልጥ ፀጋን ይሄውም
እግዚአብሄርን መውለድ ገንዘቧ ያደረገች አይደለምን? እንግዲህ
መዳን በማን ነው? ያለክርስቶስ መዳን አለን? በፍፁም ሁሉ
ይድኑ ዘንድ የተዘጋጀ መዳኛ ክርስቶስ ነው ፡ ይህም ማዳኑ
የባህርይው ነው፡፡ ነገር ግን ደግሞ እንጠይቃለን ከቶ ሃዋርያት
ሙትን ሲያስነሱ እያዳኑ አይደለምን? ይህንን እንዴት አደረጉ?
ከራሳቸው ስልጣን ነውን? አይደለም ይልቅስ በፀጋ በተሰጣቸው
የማዳን አገልግሎትን ከክርስቶስ ተቀብለው በክርስቶስ ስም
ይፈፅማሉ እንጂ፡፡ እኔ ግን “ያለእመቤታችን አማላጅነት አለም
አይድንም” የሚለውን ሃይለ ቃል ባየ ጊዜ ይህ ሊባል አይገባም
የሚልን ሰው አንድ ጥያቄ እጠይቀዋለሁ ፦ ወንድሜ ሆይ
የድንግልን የፀጋ ስጦታ ሁሉ ታውቃለህን? አልያም ድንግል
ማርያም ይህን ይህን ማድረግ ትችላለች ፡ ይህን ይህን ደግሞ
ማድረግ አትችልም ማለት ትችላለህን? እኔ አንተን ብሆን ግን
ዝም ማለትን እመርጣለሁ ወይንም ምናልባት የቀደሙ
ኦርቶዶክሳውያን ቅዱሳን አባቶችን በመንፈስ እጠይቅ ዘንድ
ልቤን አነሳሳለሁ፡፡ በአንድ ነገር ግን እስማማለሁ እንዲህ ያለ
ቃል ለሚያምኑ የሚነገር እንጂ ለማያምኑ ደግሞም
ለመናፍቃን ይነገር ዘንድ የሚገባ እንዳልሆነ፡፡ እንደኔ ግን ይህን
ቃል ማንም ይናገረው ማንም በአለም እየኖረ አንድም አለም
ብሏልና አለማዊ ሆኖ መልካም ስራን እንኳን ሳይሰራ የሚል
ትርጓሜ ቢኖረው የእመቤታችንን ክብር ያላወቀ ፡ አውቆም
የተሳለቀ ፡ አፉንም በእርሷ ላይ በሽንገላ የከፈተ አይድንም ብየ
እመሰክራለሁ፡፡ አንድም ክብሯን አውቆም ቢሆን ለክብሯ
ራሱን ዘንበል ያላደረገ ፡ አክብሮትን ያልሰጠ ፡ የእግዚአብሄርን
አማናዊ ታቦት ባየ ጊዜ ለጥ ብሎ ያልሰገደ (አማንዊ ታቦት
ስንል እመቤታችንን እንደሆነ ይታወቃል) ፡ ምንም ያክል
በክርስቶስ አምናለሁ ቢል ደግሞም ስጋውን በልቻለሁ ደሙን
ጠጥቻለሁ ቢል ከአማውናዊና ሃዋርያዊት ቤተክርስቲያን
ምስጢረ ቁርባንን አላገኝምና ያገኝ እንኳን ቢመስለው መዳን
እንደማይችል እመሰክራለሁ፡፡ ነገር ግን ይህን እኔ ከራሴ
አመንጭቼ ይህን እላለሁ እንጂ ምን መልካም ነገር ተገኝብኝና
ትርጓሜ ውስጥ ራሴን አስገባለሁ፡፡ አሁን ግን ስለዚህ ጉዳይ
የአባ ጊዮርጊስን አስተምሮ እናጤን ዘንድ እንጀምር ፦ እስኪ
የተወደደ አባት ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ስለእመቤታችን
ክብር እያደነቀ የተናገረውን እንመልከት ፦ አባ ጊዮርጊስ
እመቤታችንን የቤተክርስቲያን መሰረት አንቺ ነሽ ይላታል ፦“
እመቤቴ ማርያም ሆይ ፦ ከልጅሽ ከወዳጅሽ አንደበት
የሃይማኖት አለት ተብሎ ጴጥሮስ የተጠራባት አለት አንቺ ነሽ ፤
የሃዋርያት ጉባኤ የምትሆን ቅድስት ቤተክርስቲያን ባንቺ
ተመሰተች ፤ የንጉሱም ሙሽራ ባንቺ ተጌጠች ፤ - -- ባንቺም
ምሶሶች ቆሙ ፡ ሕንፃዋ ባንቺ ፀና ፡ግድግዳዋም ባንቺ ተሰራ ፡
ጠፈሯም ባንቺ ተጠፈረ ፡ ዋልታዋም ባንቺ ተዋቀረ ፡
ጭምጭሟም ባንቺ ተጨመጨመ ፤ ደጆቿም ባንቺ ተከፈቱ
፤ መቃን መድረኳም በልጅሽ ደም ተረጨ ፤ “ እስኪ እንግዲህ
አባታችንን እንጠይቀው ፦ አባታችን ሆይ የቤተክርስቲያን
መሰረት ክርስቶስ እንደሆነ አላስተማርከንምን ታዲያ ስለምን
አሁን የቤተክርስቲያን መሰረቷ እመቤታችን ነች አልከን ብለን፡፡
አባታችን ግን ይህን ሲናገር አላዋቂ ሆኖ አይደለም ፡
ስህተትንም ሰርቶ አይደለም ድንግልን በጠራ ጊዜ ልጇን
እየጠራ እንጂ ልጇን የባህርይ መሰረት ሲያደርገው ድንግልን
ደግሞ የፀጋ መሰረት ሲያደርጋት እንጂ ፡ ክርስቶስ የለበሰው ስጋ
የነሳው ነፍስ የድንግል ማርያም እንደሆነ ይናገር ዘንድ ይህን
አለ እንጂ ቤተክርስቲያንን በደሙ የመሰረታት ክርስቶስ
እንደሆነ አጥቶት አልነበረም፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ ራሱ
ጴጥሮስን አንተ ደንጋይ ነህ በአንተ አለትነት ቤተክርስቲያኔን
እሰራለሁ ባለ ጊዜ በደሙ የተመሰረተችውን ቤተክርስቲያን
ጴጥሮስን እንኳን የፀጋ መሰረቷ እንዲሆን ወደደ፡፡ አባታችን
አባ ጊዮርጊስ አሁንም ይቀጥላል ፦ “የእውነተኛ ፀሃይ እናት
ድንግል ማርያም ሆይ ላንቺ እገዛለሁ ፤ ፍጥረት ሁሉ ላንቺ
ይገዛልና ፤ የልጅሽ ስም በሁሉ ከተነገረ ዘንዳ ያንቺ ስም ከዚያ
ይነገራልና፡፡ የአለም ሁሉ ክብር የነገስታትም ብእላቸው ድንግል
ሆይ ነገስታትና መኳንንት አለምም ሁሉ ከእግርሽ በታች
ከጫማሽ ወድቀው ይገዛሉ፡፡” አባታችን ይህን ባለ ጊዜ ድንግል
ማርያምን የፍጥረታት ሁሉ ገዥ አደረጋት፡፡ እንግዲህ ምን
እንላለን ስለእምነታችን መድከም አባታችን ሆይ ይህ እንዴት
ነው? የፍጥረታት ሁሉ ገዥ እግዚአብሄር አይደለምን? ብለን
ብንጠይቀው እግዚአብሄርን የባህርይ ገዥ ከፍጥረት ሁሉ በላይ
የሆነች እናታችን ማርያምን ግን የፀጋ ገዥ ያደርጋታል፡፡ ታዲያ
ለምን የፀጋስ ገዥ ያደርጋታል የሚል አለን? እንዲህ የሚለውን
ግን እኛ ደግሞ ለምን የፀጋ ገዥ አያደርጋትም ብለን ደግሞ
መልሰን እንጠይቀዋለን፡፡ እርሷ በልጇ ቀኝ የምትቆም ንግስት
ናትና ይህ ለእርሷ ምኗ ነው? ለእርሷ የሁሉ ንጉስ የባህርይ ገዥ
ልጇ ነውና የንጉሱ እናትን የሚናገር ማነው? ታዲያ አባታችን
የፀጋ ገዥ ካደረጋት ገዥ ደግሞ አይፈርድምን? ፈራጅስ አንዱን
ሊኮንን አንዱን ሊያፀድቅ የሚቀመጥ አይደለምን? የማይፈርድ
ከሆነስ ገዥነቱ ለምልክት ነውን? ከቶ ይህስ ከሆነ ምን
ይሰራለታል? አባታችን ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ለማያምኑ
ከባድ የሚመስል ቃልን በአርጋኖን መፅሃፉ ያስነብበናል እንዲህ
ሲል ፦“ ድንግል ሆይ ፦ አዳም ከልጆቹ ጋር ያመሰግንሻል በሱ
የተፈረደ መርገመ ስጋ ባንቺ ጠፍቷልና ፡ እግዚአብሄር ሔዋንን
የረገማት ርግማን ባንቺ ተሽሯልና፡፡ “ ይህ ነገር እንዴት ነው?
የአዳም መርገም በድንግል ጠፋ ይለናልና፡፡ አባታችን ሆይ
ይህንን ስትል የአዳም ዘር ሁሉ መርገም በክርስቶስ የጠፋ
እንደሆነ አስቀድመህ ያስተማርከን አይደለምን? አሁን ይህንን
ለእመቤታችን ማድረግህ ስለምን ነው ብለን በእምነትና
በየዋህነት ብንጠይቀው ምን ብሎ ይመልስልን ይሆን?
አስቀድሞ አርዮስን በዘለፈበት የመፅሃፈ ምስጢር ድርሳኑ ላይ
አርዮስ ሆይ ክርስቶስን ፍጡር ነው ያልክ በፍጡር ደም
እንደምን የሰው ልጅ ይድናል እያለ የክርስቶስን አምላክነት
እየመሰከረ መዳንም በፍጡር ደም ሳይሆን በፈጣሪ እንደሆነ
እያስረዳ አሳፍሮት አይተናልና አሁን ራሱ ድንግል ፍጡር
መሆኗን ስናውቅ አርዮስን በዘለፈበት ቃል እርሱ ወደቀን?
አይደለም በተዋህዶ የከበረው የክርስቶስ ስጋና ደም ከድንግል
የነሳው መሆኑን ሲያጠይቅ ነው እንጂ ፡ አንድም የባህርይ
አዳኝና ርግማን አስወጋጅ ክርስቶስ ሲሆን ድንግል ግን በፀጋ
የተሞላች ፡ በቅድስና የተዋበች ፡ ከመርገም የራቀች ፡
ከሃጢአት የተጠበቀች የአዳም ተስፋው እንደሆነች ሲነግረን ነው
እንጂ ፡ አንድም በወንድ ዘር ምክንያት የሰውን ዘር ሁሉ
ሲቆራኝ የነበረው የባርነት ቀንበር ፡ የዲያቢሎስም ፀሃረኝነት
አንቺ ላይ ሲደርስ ተቁርጧልና ሲለን ነው ፤ እንግዲህ
አባታችንን ይህን ባልክ ጊዜ ሰው ልቡናው ተከፈለበት ብንለው
ምን ይለን ይሆን?እርሱ ግን አስቀድሞ በመፅሃፍ እንዳለው ይህ
ለሚያምን እንጂ ለማያምን የሚነገር አይደለም ይለናል፡፡
ይህንንም የሚመስል ሌላ ደግሞ ይናገራል “ቀድሜ
እንደተናገርሁት አሁንም ደግሞ መልሼ እንገራለሁ ፡ እንዲህ
ስል ኪሩብ የያዘው ዙፋን የረባኝ የጠቀመኝ የለም ፡ ሰማያትም
የረቡኝ የጠቀሙኝ የለም፡፡ እመቤቴ ሆይ አንቺ ግን ከሞት
ባርነት አዳንሽኝ ፡ የአብ በኩር ልጅ ካንቺ ስጋ በመልበሱ
ነው፡፡” ይህንም ሲል ለምን እንዳለ ደግሞ መልሶ ይናገረናል -
ድንግል ሆይ ከሞት ባርነት አዳንሺኝ ስለምን አልኩ ቢል ይህም
የአብ የበኩር ልጅ ክርስቶስ ካንቺ ስጋ በመልበሱ ነው ይለናል፡፡
እንግዲህ የምታስተውሉ መልሱልኝ ድንግል ሆይ ከሞት ባርነት
አዳንሺኝ ከሚል ቃልና ያለ ድንግል ማርያም አማላጅነት አለም
አይድንም ማለት የትኛው የሚልቅ የክብር ቃል ነው?
የትኛውስ ከፍ ያለ ክብር ይሰጣል? ቅዱስ አባታችን ሆይ ይህን
ሁሉ ስለድንግል ትናገር ዘንድ የወደድክ ደግሞም ድንግልን
በዚህ ሁሉ ክብር ያከበርካት ስለምንድን ነው ብንለው
የድንግልን ምስጋናዋን ለመግለፅ ታተርኩ ስለገናንነቷ ግን
ልፈፅመው አልቻልኩም እያለ እንዲህ ይለናል ፦ “ድንግል ሆይ
ባማረ በተወደደ ነገር ሁሉ መሰልሁሽ ምስጋናሽን ግን
ለመፈፀም አልቻልኩም፡፡እግዚአብሄር ን ባመሰገንሁ ጊዜ
ባንቺ ለስሙ ምስጋና አቀርባለሁ ፤ በስምሽም ፀሎቴን
በፀለይሁ ጊዜ ፀሎቴን ለልጅሽ አቀረብሁ፤ዳግመኛም
ውዳሴሽን ወደማወቅ ባህር ልዋኝ ወደድሁ ፡ ወደ ክብርሽ
ገናንነት ወደብ እደርስ ዘንድ ደከምሁ ፡ ያንዲቷን ማእበል
ሞገድ ያህል ስንኳን አላለፍሁም፡፡ ወደ ፅርሀ አርያም ጠፈር
ለመድረስ የሚቻለው ማነው? ከምድር በታች ወዳለው ባህር
መሰረትስ መዋኘት ማን ይችላል? ድንግል ሆይ ክብርሽን
ገናንነትሽን ጠንቅቆ መናገር የሚቻለው ማነው?”፡፡ እኛስ
የአባቶቻችን ልጆች ነንና በእምነት ሆነን ድንግል ሆይ ክብርሽን
ማን ይናገር ዘንድ ይችላል? ገናንነትሽን ማን መመጠን
ይችላል? እንላለለን፡፡ እንግዲህ ለቅዱስ አባታችን ያልተደረሰ
የምስጋናን ባህር ዋኝቶ የጨረሰ የድንግልንም የፀጋ ሙላት
መጨረሻ አይቶ ክብሯ እስከዚህ ድረስ ነው የሚል ማነው?
ለድንግል የተሰጣት ፀጋ ይህን ያክል ነው ይህንን ማድረግ
ትችላለች ፡ ይህንን ማድረግ ግን አትችልም የሚል ማነው?
ቅዱስ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሆይ እስኪ መልስልን
አለም የድንግልን ስም ሳይጠራ ክብርን ያገኛልን? ደግሞስ
ሳያከብራት ይከብራልን? ወይንስ ሳይወዳት ይወደዳልን?
ወይንስ የተከበረ ማንም ቢኖር የተከበረች እናትን አላውቃትም
ሊል ይችላልን? ወይንስ ፃድቅ ማንም ቢኖር የፃድቃን ሁሉ
እናት ድንግል ማርያምን የማይደገፍ አለን? እስኪ ተናገረን
አለም ለዚያውም በሃጢአት ርኩሰት የወደቀ አለም ፡
እግዚአብሄርን የተሳደበ አለም ፡ ለዲያቢሎስ የሰገደ አለም ፡
ለዚያውም የድንግልን ክብር ያናናቀ አለም ቅዱስ ሊሆን
ይችላልን? ወይንስ በአባታችን እዮብ ላይ ሃዘንን ያመጡ እነዚያ
ሰወች ያለ እዮብ ፀሎት በእግዚአብሄር ዘንድ ተሰሙን?
እንግዲህስ ድንግልን ያላከበሩ ፡ በንቀትም የተናገሩ ያለፀሎቷ
ክርስቶስ ፊት በፅድቅ ሊቀርቡ ይቻላቸዋልን? እያልን
በጠየቅነው ጊዜ እንዲህ እያለ ድንግልን ባመሰገነ ጊዜ
በምስጋናው ውስጥ ይመልስልናል ፦ “ ድንግል ሆይ
የማያከብርሽ ለልእልናሽም የማይሰግድ ለዘላለሙ ርጉም
ነው፡፡ በፍፁም ልቦናው የማይወድሽ ፡ ከትልቅ ሃሳቡም
የማያከብርሽ ርጉም ነው ፤ በከንፈሮቹ የማያመሰግንሽ ፡
ባንደበቱም የማይመርቅሽ ርጉም ነው ፤ ለክብርሽ የማይሰግድ
ለገናንነትሽም የማይገዛ እድል ፈንታው ፀዋ ተርታው ገሃነመ
እሳት ነው፡፡” ይህንን ባለ ጊዜ ለድንግል የሚገባ ክብርን
ያልሰጠ በሰማይ በገነት ቦታ እንደሌለው ገለፀ፡፡ ማዳን
የከበዳችሁ ወንድሞች ሆይ አባ ጊዮርጊስን ስሙት ስለድንግል
ማዳን እንዲህ ይለናል ፦ “አቤቱ ክርስቶስ ሆይ ፦ ላንደበቴ ሃይለ
ቃሉን ስጥ የእመቤቴን የማህፀኗን መክበር የድንግልናዋን ነገር
አወራ ዘንድ ፤ እርሷም ደግሞ እኔን ለማዳን የታመነች ናት ፤
ለድንቁርናየም ልቡና ለአይኔም ብርሃኗ ለጆሮየም የበጎ
ምስራች ወሬ ናት፡፡” እርሷም ደግሞ እኔን ለማዳን የተጋች ናት
ባለ ጊዜ በተሰጣት የፀጋ ስጦታ ታድነኛለች ብሎ በድፍረት
መሰከረ ፡ ይህንም ሲል አዳኝ ክርስቶስ መሆኑን አጥቶት
መስሏችሁ እናንተ የምድር ሃጥአን በልባችሁ አታጉረምርሙ
የባህርይ አዳኝ ጌታችን ሲሆን የፀጋ አዳኝ ድንግልን እንዳደረጋት
አስተውሉ እንጂ፡፡ ወንድሞች ሆይ ሰው ምንም ፍጡር ቢሆን
አምላክ ፍጡርን ፈጣሪ ያደረገበትን ጥበብ ተረዱት ቃል ስጋ
በሆነ ጊዜ ሰው አምላክ ሆኗልና በኪሩቤልም ዙፋን
ተቀምጧልና ደግሞም ይህ ስጋ ከድንግል ያለወንድ ዘር የተገኝ
እንደሆነ አስተውሉና ለሰው የተሰጠው የፀጋ ብዛት ምን ያክል
እንደሆነ አድንቁ እንጂ ፡ እንግዲህስ ሰው አምላክ ከሆነ
ከእንግዲህ ለሰው ልጅ የጎደለበት ምን ፀጋ አለ? ስለቅዱሳንስ
የእግዚአብሄር ልጆች እንደሆኑ የተመሰከረላቸው አይደሉምን?
ልጆች ከሆኑ ደግሞ ወራሾቹ ናቸው ፡ ወራሾች ከሆኑ ደግሞ
ከአባታቸው በፀጋ እየተቀበሉ ሲያድኑ ብናይ ይህ አዲስ ነገር
አይደለም፡፡ እንግዲህስ ቅዱሳንን የእግዚአብሄር ልጆች ያደረግን
ድንግል ማርያምን ልጅ አይደለሽም እንላታለንን? አንላትም
ይልቅስ እሷ የእግዚአብሄር ልጅ ብቻ አይደለችም እናቱም
ደግሞ ሆነች እንጂ፡፡ ስለዚህም አባታችን ጊዮርጊስ ክብሯን
እያሰበ እየደጋገመ እንዲህ አላት፦”እመቤቴ ማርያም ሆይ
በሁሉ ተመሰልሽ ፡ በሁሉም መሰሉሽ ፡ አንቺን ግን
የሚመስልሽ የለም፡፡ - - - የአለም ሁሉ መድሃኒት የምትሆን
ብላቴና እግሯ የተመላለሰበቱን ምድር እስም ዘንድ ማን
በከፈለኝ ፤ ይቅርታን የምታሰጥ ብላቴና ጥላዋ ይነካኝ ዘንድ
ማን በከፈለኝ፡፡ የብርሃን ልጅ ወደሄደችበት እከተላት ዘንድ ማን
በከፈለኝ የእግሯንም ጫማ እሽከም ዘንድ ማን በከፈለኝ”
አባቴ ጊዮርጊስ ሆይ እኔስ ካንተ ጋር እመቤቴን አመሰግናት
ዘንድ ማን በከፈለኝ እላለሁ፡፡ አባታችን ሆይ ድንግልን የአለም
ሁሉ መድሃኒት የምትሆን አልካት ፡ ይህ ቃል እንዴት ነው?
የአለም መድሃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ስታውቅ
እንዲህም እያልክ አስተምረኅን ሳለህ ይህ እንደምን ያለ ምስጋና
ነው? ለእግዚአብሄር የሚሰጠውን ምስጋና ለሰው ሰጠህን?
ይህንስ እንዳላደረክ እኛ እናውቃለን ነገር ግን ክርስቶስን
የባህርይ መድሃኒት ስታደርግ ድንግልን ደግሞ የፀጋ መድሃኒት
አደረግህ ፡ አማናዊ መድሃኒትን ወልዳልናለችና ፡ ቅዱስ ስጋውን
በበላን ክቡር ደሙንም በጠጣን ጊዜ አማናዊ መድሃኒት
የሚሆነን ጌታ ስጋውን ደሙንም ከድንግል ወስዷልና እንዲህ
አለ ፡ ደግሞም እኔ የአለም ብርሃን ነኝ ያለ አምላክ
ለሃዋርያቶቹ እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ ባለ ጊዜ የሱን
ብርሃንነት እንዳልሻረ ድንግልንም ስለተሰጣት ክብር ይህን
በተናገረ ጊዜ የክርስቶስን መድሃኒትነት አልሻረም ፡ ደግሞም
ስለፀሎቷ ሃይልና ስለቅድስናዋ ሙላት ይህንን ተናገረ፡፡
እንግዲህ እናንተ የምታስተውሉ ድንግልን የአለም መድሃኒት
የምትሆኝ ከማለት ይልቅ የአለም አማላጅ ማርያም ማለት
የቱ በክብር ይልቃል? አባታችንም ስለድንግል የፀሎቷ ሃይል
ሲናገር እንዲህ አለ ፦ “ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ
ከፀሎትሽ ረዳትነት በቀር ሊረዳኝ የሚችል እንደሌለ አወቅሁ፡፡
ከልመናሽም በቀር የሚያድን እንደሌለ ያለበኩርሽም የሚበጀኝ
እንደሌለ አወቅሁ፡፡ --- ድንግል ሆይ ፦ ወዳንቺ ተጠጋሁ
በልጅሽም አመንሁ እርሱንም አመለክሁ ፡ ቸርነቱንም ተስፋ
አደረግሁ፡፡” ወንድሞች ሆይ እንግዲህ ምን እንላለን? አባታችን
አሁን የሚነግረን ከእስካሁኑ ይልቅ የሚበልጥ ነውና ፤ አሁንም
ግን ደግመን የአባታችንን ምክር እንናገራለን ፡ ይህ ለሚያምን
እንጂ ለማያምን አይደለም የሚለውን፡፡ አባታችን አባ ጊዮርጊስ
ዘጋስጫ ግን የድንግልን የክብር ሙላት ባሰበ ጊዜ እየተደነቀ
እንዲህ አለ፦ “በእብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ እመቤታችን
ድንግል ማርያም ሆይ ሁሉ ላንቺ ሆነ ፡ ሁሉም ስላንቺ ተፈጠረ
፡ አዳም ከህቱም ምድር ተፈጠረ አንቺን ያፈራ ዘንድ ነው ፡
ሔዋንም ከአዳም ከግራ ጎኑ ተፈጠረች አንቺን ትወልድ ዘንድ ፤
ምድርም ተፈጠረች አዳም አባትሽን ታስገኝ ዘንድ ፡፡
ለምግቡም ቡቃያውን ታወጣ ዘንድ ሰማይም ስለርሱ ተሰቀለ ፤
ፀሃይና ጨረቃም ከዋክብትም እንዲያበሩለት በመውጣትና
በመግባታቸው የዘመኑ ቁጥር እንዲታወቅ ተፈጠረ ፤ -- -
መላእክትም እንዲያገለግሉት ተፈጠሩ ፤ - -- ድንግል ሆይ
ክብርሽን ገናንነትሽን ለመናገር የሚቻለው ማነው? ምስጋናሽን
መናገር ማን ይችላል? “ ይህ ምስጋና እንዴት ያለ ምስጋና
ነው? እንደኔ በሃጢአት ለደከመ ሰው የሚከብድ ነውና ፤
ስለክርስቶስ ሁሉ በእርሱ ለእርሱ ተፈጠረ የሚልን ቃል መፅሃፍ
እየነገረን ሳለ ሁሉ ስለማርያም ተፈጠረ ይለን ዘንድ የወደደ ይህ
ቅዱስ አባት ይህ ነገር እንዴት ነው? ሁሉ ሲል ክርስቶስንስ
ይጨምራልን? አይደለም የተፈጠረው ሁሉ ሲልስ ሁሉን
ከፈጠረው ውጭ ማለቱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሁሉን የፈጠረ
ክርስቶስ ነውና ይህን ተናገረ፡፡ ነገር ግን ስለምን ድንግልን ሁሉ
ላንቺ ሆነ አላት ብንል አንድም የአዳም ዘር ሁሉ በሃጢአት
ወድቆ ሳለ ሰውን የሚወድ አምላክ አዳም ከውድቀት እንዲነሳ
አስቀድሞ ያሰባት ስለሷም ትንቢት ያስነገረላት ፡ በልዩ ልዩ
ምሳሌ የገለጣት ቅድስት እናት የአዳም የውድቀት መነሻ
ድንግል መሆኗን ሲያጠይቅ ነው፡፡ አንድም አዳም የተፈጠረው
አንቺን ሊያስገኝ ነው ሔዋንም የተፈጠረችው አንቺን ትወልድ
ዘንድ ነው እያለ ይናገርና ሃሳቡን ቢገታ አንቺም የምትወለጂው
ሰውን አምላክ የሚያደርገውን ንጉስ ክርስቶስን ልትወልጂ ነው
ሲል ነው ፡ ይህም ማለቱ ክርስቶስን ከሁሉ በላይ ማድረጉ
ነው፡፡ ደግሞም ሁሉ ስላንቺ ተፈጠረ ማለቱ አንደኛ በሰማይ
በምድር ያሉ ፍጥረታት ሁሉ ሰውን ሊያገለግሉ መፈጠራቸውን
ሲናገር ፡ መላእክት እንኳን ሰውን ሊረዱ እንደተፈጠሩ
ማስታወሱና እመቤታችንን ከፍጥረት ሁሉ የበላይ ሲያደርጋት
ነው ፤ እመቤታችንንም ከሁሉ በላይ ቢያደርጋት ከእርሷ
የተወለደውን ክርስቶስን ከሁሉ በላይ ሊያደርግ ቢወድ ነው፡፡
እንግዲህ ወንድሞች ሆይ “ሁሉ ስለ ድንግል ተፈጠረ ከሚለውና
ያለእመቤታችን አማላጅነት አለም አይድንም ከሚለው የትኛው
የበለጠ ክብር አለው? ድንግል ሆይ ክብርሽን ገናንነትሽን
ለመናገር የሚቻለው ማነው? ምስጋናሽን መናገር ማን
ይችላል? የአብ ፍቅር ፡ የወልድ ቸርነት ፡ የመንፈስ ቅዱስ
አንድነት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ አሜን፡

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: የማዕተብ ሥርዓት

ሃይማኖት የልብ ብቻ አይደለም!!
አንዳንድ ሰዎች የማዕተብ ሥርዓትን ለመቃወምና
ዘመናውያን መስለው ለመታየት ‹‹እምነት በልብ ነው››
ይላሉ፤ ተሳስተዋል!
ሃይማኖት የልብ ብቻ አይደለም፤ የጠቅላላው ሕዋሳት ሁሉ
ናት፡፡ እግዚአብሔርን ስንወደውና ስናመልከው በልባችን ብቻ
ሳይሆን በአፋችንም በአንገታችንም በጠቅላላው ሰብአዊ
ተፈጥሯችን ሁሉ መሆን ይገባዋል፤ ምክንያቱም
እግዚአብሔር የጠቅላላው ሰውነታችን አምላክና ፈጣሪ
ስለሆነ ነው፡፡ ‹‹ስለዚህ በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ
ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው
ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ
ፊት እክደዋለሁ፡፡›› (ማቴ.10÷32÷33)
በዚህ ቃለ ወንጌል መሠረት በኢ-አማንያን ዘንድ ክርስቲያን
መሆናችንን የምንገልፀው በልባችን ብቻ ሳይሆን በቃላችንና
በሥራችንም ጭምር ነው፡፡ በአንገታችንስ እንዳንመሰክርለት
ማን ያግደናል? በአንገታችን ባለው ማዕተብም
ለእግዚአብሔር እንመሰክራለን፡፡
የስሙን ምልክት በአንገታችን እናኖራለን፤ አናፍርበትም!!
የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ በጥምቀታችን እንደምንመሰክር
የጥምቀታችንንም ዓርማ በማተባችን እናረጋግጣለን፡፡
(ሮሜ 16÷13፤ ኢዩኤ. 2÷32፤ ሮሜ 6÷1-5፤
ማቴ.5÷11-12፤ 1ኛጴጥ.3÷21-22፤ 4÷12-16)

Friday, March 25, 2016

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: ምስጢረ ሥላሴ የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት ምስጢር

ምስጢረ ሥላሴ
የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት ምስጢር
ምስጢር የሚለው ቃል አመሰጠረ፣ ሰወረ፣ አረቀቀ ከሚለው
የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ፍቺውም ረቂቅ፣ ስውር፣ ኅቡዕ
ማለት ነው፡፡ ምስጢር መባሉም የሥላሴን ባሕርይ ፍጡር
መርምሮ የማይደርስበት በመሆኑ፣ በፍጡር ባሕርይ መወሰን፣
መጨረሻውን ማወቅ የማይቻልና ከፍጡር እውቀት አቅም
በላይ በመሆኑ ነው፡፡ ሥላሴ የሚለው ቃል ደግሞ ሠለሰ ሦስት
አደረገ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሦስትነት
ማለት ነው፡፡ ቅድስት ሥላሴ: - ለሥላሴ ቅድስት ብለን
እንቀጽላለን፡፡ ቅድስት ሥላሴ ማለት ልዩ ሦስትነት ማለት
ነው፡፡ ይህም ሦስት ሲሆን አንድ፣ አንድ ሲሆኑ ሦስት ስለሚሆኑ
ልዩ ሦስትነት ተብሏል፡፡
ስለዚህ ነገር መጽሐፈ ቅዳሴያችን ሥላሴ ሦስት ናቸው ስንል
እንደ አብርሃም እንደ ይስሐቅ እንደ ያዕቆብ ማለታችን
አይደለም ሦስት ሲሆኑ አንድ ናቸው እንጂ፣ አንድ ናቸውም
ስንል ቀዳሚ ሆኖ እንደተፈጠረው እንደ አዳም ማለታችን
አይደለም አንድ ሲሆኑ ሦስት ናቸው እንጂ፡፡ /ቅዳሴ
ማርያም/፡፡ ቅድስት ተብሎ በሴት አንቀጽ መጠራቱ ደግሞ
እናት ለልጇ ስለምታዝንና ስለምትራራ ሥላሴም ለፍጥረታቸው
ምሕረታቸው ዘለዓለማዊ ነውና ቅድስት ይባላሉ፡፡
በዚህ መሠረት ምሥጢረ ሥላሴ ማለት የአንድነት የሦስትነት
ምስጢር ማለት ነው፡፡
ይኸውም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም፣ በአካል፣ በግብር
ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ በሕልውና፣ በመለኮት ደግሞ አንድ
ናቸው፡፡ እንደዚህ ባለ ድንቅ ነገር አንድ ሲሆኑ ሦስት፣ ሦስት
ሲሆኑ አንድ ይባላሉና፣ ይህም ልዩ ሦስትነት ረቂቅ እና በሰው
አእምሮ የማይመረመር ስለሆነ ምስጢር ይባላል፡፡
የሰው ልጅ ሁሉን የመመርመርና የመረዳት መብትና ሥልጣን
ከአምላኩ የተሰጠው መሆኑ ቢታወቅም የፈጣሪን ባሕርይና
ጠባዮቹን ለመገንዘብ ውሱን ከሆነው አቅሙ በላይ
ስለሚሆንበት በእምነት ከመቀበል በቀር ሌላ አማራጭ
መንገድ ሊኖረውም አይችልም፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት በማድረግና ከቅዱሳን አባቶች
በተላለፈልን ትምህርት መሠረት ኃያሉ እግዚአብሔርን
በአንድነትና በሦስትነት እናምነዋለን፡፡ እግዚአብሔር አንድ
ሲሆን ሦስት፣ ሦስት ሲሆን አንድ መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት
ያስረዳሉ፡፡
የእግዚአብሔርን አንድነት የምናምነው፡- በፈጣሪነት፣
በአምላክነት፣ በአገዛዝ፣ በፈቃድ፣ በሥልጣን እነዚህን
በመሳሰሉት የመለኮት ባሕርያት ነው፡ /መለኮት ወይም
ማለኹት/ በዕብራይስጥ ቋንቋ መንግሥት ማለት ነው፡፡
በግዕዝ ግን ባሕርይ፣ አገዛዝ፣ ሥልጣን ማለት ነው፡፡ ሦስትነቱን
የምናምነው ደግሞ በስም፣ በግብር /በኩነት/ በአካል ነው፡፡
«እንዘ አሐዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ፣ ይሤለሱ በአካላት
ወይትዋሐዱ በመለኮት» እንዳለ /ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ/፡፡
ሀ/ እግዚአብሔር በአንድነቱ የሚታወቅበት ስሞች
1. ፈጣሪ
2. አምላክ
3. ጌታ
4. መለኮት
5. እግዚአብሔር
6. ጸባኦት
7. አዶናይ
8. ኤልሻዳይ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ለ/ እግዚአብሔር በሦስትነቱ የሚታወቅባቸው ስሞች ደግሞ
1. አብ
2. ወልድ
3.መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡
ሐ/ እግዚአብሔር በግብር ሦስትነቱ የሚታወቀው
1. አብ ወላዲ፣ አሥራፂ በመባል፣
2. ወልድ ተወላዲ በመባል፣
3. መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ በመባል ነው፡፡
የአብ ግብሩ መውለድ፣ ማስረጽ ሲሆን የወልድ ግብሩ መወለድ፣
የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መስረጽ ነው፡፡ አብ ወላዲ፣ ወልድ
ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ /የወጣ፣ የተገኘ/ ነው፡፡ አብ
አባት ነው፣ ወልድ ልጅ ነው፣ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ የሠረፀ
ነው፡፡ /ዮሐ.14-26/፡፡ ሦስቱ አካላት አንድ መለኮት ናቸው፡፡
ሠለስቱ ስም አሐዱ እግዚአብሔር እንዳለ /አባ ሕርያቆስ
በቅዳሴው/፡፡
የአካል ሦስትነታቸውም ለአብ ፍጹም አካል፣ ፍጹም መልክ፣
ፍጹም ገጽ አለው፤ ለወልድም ፍጹም አካል፣ ፍጹም መልክ፣
ፍጹም ገጽ አለው፤ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል፣ ፍጹም
መልክ፣ ፍጹም ገጽ አለው፡፡ እንዲህ ሲባል ግን የሥላሴ አካል
አንደ ሰው አካል ውሱን፣ ግዙፍ፣ ጠባብ አይደለም፡፡ ምሉዕ፣
ስፉሕ፣ ረቂቅ ነው እንጂ፡፡ ምሉዕነታቸውና ስፋታቸው እንዴት
ነው? ቢሉ ከአርያም በላይ ቁመቱ፣ ከበርባኖስ በታች መሠረቱ፣
ከአድማስ እስከ አድማስ ስፋቱ ተብሎ አይነገርም፣
አይመረመርም፡፡ ምክንያቱም ሥላሴ ዓለሙን ይወስኑታል
እንጂ ዓለሙ ሥላሴን አይወስናቸውምና፡፡
ርቀታቸውስ እንዴት ነው? ቢሉ ከሁሉ ነፋስ ይረቃል፡፡ ከነፋስ
መላእክት ይረቃሉ፡፡ ከነፍሳትና ከመላእክት ደግሞ ኅሊናቸው
ይረቃል፡፡ ይህ የኅሊናቸው ርቀት በሥላሴ ዘንድ እንደ አምባ
እንደ ተራራ ነው፡፡ በዚህም ርቀታቸው በፍጥረት ሁሉ ምሉዓን፣
ኅዱራን ናቸው፡፡ ባሕርያቸውም የማይራብ፣ የማይጠማ፣
የማይደክም፣ የማይታመም፣ የማይሞት ሕያው ነው፡፡ «ስምከ
ሕያው ዘኢይመውት ትጉህ ዘኢይዴቅስ ፈጣሪ ዘኢይደክም»
እንዳለ /ቅዲስ ባስልዮስ በማክሰኞ ሊጦን/፡፡
መ/ የኩነት /የሁኔታ/ ሦስትነት
ኩነት በህልውና /በአኗኗር/ እያገናዘቡ በአንድ መለኮት የነበሩ፣
ያሉ፣ የሚኖሩ ናቸው፡፡ እነርሱም፡-
1. ልብነት፡- በአብ መሠረትነት ለራሱ ለባዊ /አዋቂ/ ሆኖ
ለወልድ፣ ለመንፈስ ቅዱስ ልብ፣ ዕውቀት መሆን ነው፡፡
2. ቃልነት፡- በአብ መሠረትነት ለራሱ ነባቢ /ቃል/ ሆኖ ለአብ፣
ለመንፈስ ቅዱስ ቃል መሆን ነው፡፡
3. እስትንፋስነት፡- በአብ መሠረትነት ለራሱ ሕያው ሆኖ ለአብ፣
ለወልድ ሕይወት መሆን ነው፡፡
ስለዚህ በአብ ልብነት ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ህልዋን ናቸው
ያስቡበታል፤ በወልድ ቃልነት አብ፣ መንፈስ ቅዱስ ህልዋን
ናቸው ይናገሩበታል፤ በመንፈስ ቅዱስ አስትንፋስነት አብ፣ ወልድ
ህልዋን ናቸው ሕያዋን ሆነው ይኖሩበታል፡፡
ታላቁ ሐዋርያ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ 1ዐ-17
ላይ «እምነት ከመስማት ነው፣ መስማትም ከእግዚአብሔር
ቃል ነው» ብሎ እንደተናገረው ከላይ የተጠቀሱትን መጠነኛ
ማስረጃዎች በሙሉ ለመገንዘብ እንዲቻል የእግዚአብሔር
እስትንፋስ የሆኑትን የቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃዎችን
መመልከት ያስፈልጋል፡፡ ሥላሴ የሚለው ስም እንዲያው
የመጣ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በአንድነቱና በሦስትነቱ
የሚጠራበት የከበረና ከስም ሁሉ በላይ የሆነ ስም ነው፡፡
ለዚህም የመጽሐፍ ቅዱስ /ዐሥራው ቅዱሳት መጻሕፍት/
ማስረጃዎችን በዝርዝር እንመለከታለን፡፡
ምስጢረ ሥላሴ በብሉይ ኪዳን
1. እግዚአብሔርም አለ፡- «ሰውን በመልካችን
እንደምሳሌአችን እንፍጠር» ዘፍ.1-26 እዚህ ላይ
«እግዚአብሔርም አለ» ሲል አንድነቱ፣ «እንፍጠር» ሲል
ከአንድ በላይ መሆኑን ግሱ /ቃሉ/ ያመለክታል፡፡ ሦስት
መሆኑን ግን በዚህ ቃለ አልወሰነም፡፡
2. እግዚአብሔር አምላክ አለ፡- «እነሆ አዳም መልካሙንና
ክፉውን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ» ዘፍ.3-22 በማለት
ባለቤቱን አንቀጽን አንድ፣ አሳቡን ዝርዝሩን የብዙ አድርጐ
ይናገራል፡፡ «እግዚአብሔር አለ » ሲል አንድነቱን፣ «ከእኛ እንደ
አንዱ ሆነ» ሲል ደግሞ ከአንድ በላይ መሆኑን ያመለክታል፡፡
በዚህ ቃል ግን ሦስትነቱን አልወሰነም፡፡
3. እግዚአብሔርም አለ፡- «ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር
እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው፡፡»
ዘፍ.11.6-8፡፡ «እግዚአብሔር አለ» ብሎ አንድነቱ፣ «ኑ
እንውረድ» ብሎ ደግሞ ከአንድ በላይ መሆኑን ያመለክታል፡፡
4. «በቀትርም ጊዜ እግዚአብሔር ለአብርሃም ተገለጠለት
አብርሃም ሦስት ሰዎችን በፊቱ ቆመው አየ» ዘፍ.18.1-15
በማለት እግዚአብሔር አንድ መሆኑንና ሦስት አካል ያለው
መሆኑን ወስኖ ያስረዳናል፡፡
5. «እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅም አምላክ፣
የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር ነኝ» ዘጸ.3-6 ሲል
«አምላክ፣ አምላክ፣ አምላክ» ብሎ ሦስትነቱን፣ «እኔ
እግዚአብሔር ነኝ» ብሎ ደግሞ አንድነቱን ገልጾ ተናግሯል፡፡
6. «የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች፣
በእግዚአበሔርም ቃል ሰማዮች ጸኑ፣ ሠራዊታቸውም ሁሉ
በአፉ እስትንፋስ» መዝ.32-6፡፡
7. ነቢዩ ኢሳይያስም «ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት
እግዚአብሔርን በልዑል ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ አየሁት...
ሱራፌልም ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር
ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያሉ ይጨሁ ነበር፡፡»
ኢሳ.6.1-8 በማለት ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ብሎ ሦስትነቱን፣
የሠራዊት ጌታ እግዚአበሔር ብሎ ደግሞ አንድነቱን አይቶ
መስክሯል፡፡
ምስጢረ ሥላሴ በሐዲስ ኪዳን
በአዲስ ኪዳንም የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት /ምስጢረ
ሥላሴ/ በምስጢረ ሥጋዌ በሚገባ ታውቋል፡፡ ይኸውም
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተለየ አካሉ /ሰው
ሆኖ/ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ፣ አብ በደመና ሆኖ «የምወደው
ልጄ ይህ ነው የሚላችሁን ስሙት» ሲል፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ
በራሱ ላይ በርግብ አምሳል ሲወድቅበት ታይቶአል፡፡ /
ማቴ.3.16-17፣ ማር.1.9-11፣ ሉቃ.3.21-22፣
ሉቃ.1.32-34/ በዚህም እግዚአብሔር በአካል ሦስት
እንደሆነ ተገልጿል፡፡
መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤልም እመቤታችንን ባበሠራት
ጊዜ «መንፈስ ቅዱስ በአንች ላይ ይመጣለ፣ የልዑልም ኃይል
ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንች የሚለደው ቅዱሱ
የአግዚአብሔር ልጅ ይባላል፡፡» ብሎ የሥላሴን ሦስትነት
በግልጽ ተናግሯል፡፡ሉቃ.1-35፡ ፡
እራሱ ባለቤቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የማዳን ሥራውን
ፈጽሞ ከማረጉ በፊት ለደቀመዛሙርቱ ቋሚ ትዕዛዝ ሲሰጥ
«እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ
ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ... ደቀመዛሙርት አድርጓቸው»
ብሏል ማቴ.28.19-20፡፡
«ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ
የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለ እኔ
ይመሰክራል፡፡» ብሏል ዮሐ.15.26፣ 14.16-17፣ 25-26፡፡
ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች
በጻፈው መልእክቱ የሥላሴን ሦስትነት ገልጾ ተናግሮአል፡፡
«የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔርም ፍቅር፣
የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን» 2ኛ
ቆሮ.13-14፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በጻፈው መልእክቱ «በሰማይ
የሚመሰክሩ ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም አብ፣ ልጁም፣ መንፈስ
ቅዱስም ናቸው፡፡ 1ኛ.ዮሐ.5-7፡፡ እነዚህ ሦስቱም አንድ
ናቸው፡፡» በማለት የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት በግልጽ
ያስረዳናል፡፡ /ይህንን ቃለ በ1886 ዓ.ም ከታተመው
የአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ እትም ይመልከቱ/፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ ደግሞ የኪንግ ጀምስ የእንግሊዝኛውን መጽሐፍ
ቅዱስ እትም ብንመለከት ይህነን አማናዊ የሥላሴን ምስጢር
በትክክል ይመሰክራል/፡፡
ወንጌላዊው ቅድስ ዮሐንስም «በራእዩ እነሆም በጉ በጽዮን
ተራራ ቆሞ ነበር፣ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱም ስም
የመንፈስ ቅዱስም ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ
አርባ አራት ሺህ ነበሩ» ራእ.14-1፡፡ በማለት በገጸ-ልቡናቸው
ስመ ወላዲ፣ ስመ ሠራፂ የተጻፈባቸውን የሥላሴን ልጆች
አይቷል፡፡ በዚህም የሥላሴን ልዩ ሦስትነት በግልጽ መስክሯል፡፡
ከላይ በዝርዝር የተገለጹትና እነዚህን የመሳሰሉት ሁሉ
እግዚአብሔር አንድነቱንና ሦስትነቱን የገለጸባቸው ምስክሮች
ናቸው፡፡
የምስጢረ ሥላሴ ትምህርት/ምስክርነት በሊቃውንት
ምስጢረ ሥላሴ በሊቃውንትም ትምህርት የአብ መላዲነት፣
የወልድ ተወላዲነትና የመንፈስ ቅዱስ ሠራፂነት ነው፡፡ አብ
ተወላዲ አይባልም፣ ወልድ ወላዲ አይባልም፡፡ ወላዲ፣ ተወላዲ፣
ሠራፂ የሚባሉት ቃላት ሦስት አካላት ለየብቻ የሚታወቁባቸው
የግብር ስሞች ናቸው፡፡ ሊቃውንት አባቶቻችን በሃይማኖተ
አበው ምሳሌ ሲመስሉ ምሳሌ ሠይሐጽጽ /ጎደሎ ምሳሌ/
በማለት አንዳንድ ምሳሌዎችን ያቀርባሉ፡፡ ምሳሌውንም
ጎደሎ የሚሉበት ምክንያት ለምስጢረ ሥላሴ ሙሉ በሙሉ
ምሳሌ የሚሆን ሲያጡ ነው፡፡ ይህንንም የሥላሴን ሦስትነትና
አንድነት ሐዋርያት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በተማሩት
መሠረት በሚከተሉት ሦስት ምስሌዎች በሚገባ ገልጸውታል፡፡
የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በነፋስ፣ በፀሐይ፣ በአሳት
ይመሰላል፡፡
1. የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በሰው ምሳሌ ይገለጻል፡፡ ሰው
በነፍሱ ሦስትነት አለውና ነው፡፡ የኸውም ልብነት፣ ቃልነት፣
ሕይወትነት ነው፡፡
ስለዚህ በሰው ነፍስ፡- በልብነቷ አብ፣ በቃልነቷ ወልድ፣
በሕይወትነቷ መንፈስ ቅዱስ ይመስላሉ፡፡ የነፍስ ልብነቷ፣
ቃልነቷን፣ ሕይወትነቷን ከራሷ ታስገኛለችና፡፡ ቃልና ሕይወት
ከአንዷ ልብ ስለተገኙ በከዊን /በመሆን/ ልዩ እንደሆኑ
በመናገርም ይለያሉ፡፡ እንዲሁም አብ ወልድን በቃል አምሳል
ወለደው፣ መንፈስ ቅዱስንም በእስትንፋስ አንጻር አሰረጸው፡፡
ነፋስ ስትገኝ በሦስትነቷ በአንድ ጊዜ ተገኘች አንዷ ልብነቷ
ቀድሞ ቃልነቷና እስትንፋስነቷ በኋላ አልተገኙም፡፡ ሰው በዚህ
አኳኋን በነፍሱ የሚመስለው ስለሆነ እግዚአብሔር «ሰውን
በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር» ዘፍ.1-26 ብሎ
ተናገረ፡፡ ስለዚህ ነፍስ ልብ፣ ቃል፣ እስትንፋስ /ሕይወት/ መሆን
የከዊን /የመሆን/ ሦስትነትን ነገር በተናገረበት ድርሳን እንዲህ
አለ፡፡
«አምላክ ውእቱ አብ፣ ወአምላክ ውእቱ ወልድ፣ በአምላክ
ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ወኢትበሀሉ ሠለስተ አማልእክተ አላ
አሐዱ አምላክ ብሏል፡፡ ይህም ማለት አብ አምላክ ነው፣
ወልድም አምላክ ነው፣ መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው ነገር
ግን ሦስቱ አማልክት አይባሉም፣ አንድ አምላክ እንጂ፡፡»
ማለት ነው፡፡
ሥላሴ በፀሐይ ይመሰላሉ፣ ፀሐይ አንድ ሲሆን ሦስትነት
አለው፡፡ ይኼውም ክበቡ ብርሃኑ፣ ሙቀቱ ነው፡፡ ክበቡ አብ፣
ብርሃኑ ወልድ፣ ሙቀቱ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ «አብ
ፀሐይ፣ ወልድ ፀሐይ፣ መንፈስ ቅዱስ ፀሐይ አሐዱ ውእቱ ፀሐየ
ጽድቅ ዘላዕለ ኩሉ» እንዳለ /ቅዱስ አባ ሕርያቆስ/፡፡
ሥላሴ በእሳት ይመሰላሉ፡፡ እሳት አንድ ሲሆን ሦስትነት አለው፡፡
ይኼውም አካሉ፣ ብርሃኑ፣ ዋዕዩ /ሙቀቱ/ ነው፡፡ በአካሉ አብ፣
በብርሃኑ ወልድ፣ በዋዕዩ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ «አብ
እሳት ወልድ እሳት ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ እሳተ
ሕይወት ዘእምአርያም፡፡» እንዳለ /አባ ሕርያቆስ/ «አምላክህ
እግዚአብሔር የሚባላ እሳት ቀናተኛም አምላክ ነው፡፡» ዘዲ.
4-24፡፡
ሥላሴ በፀሐይና በእሳት መመሰላቸውንም ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ራሱ ለሐዋርያት «እኔና አባቴ መንፈስ ቅዱስም
እሳትና ነበልባል ፍሕምም ነን» በማለት አስተምሮአቸዋል፡፡
ሐዋርያትም ይህንን ጽፈውት ቀሌመንጦስ በተባለው መጽሐፍ
ይገኛል፡፡ /ቅዳሴ ሠለስቱ ምእትን/ ይመልከቱ፡፡ ነገር ግን
እነዚህ ሁሉ አንድ ነፍስ፣ አንድ ፀሐይ፣ አንድ እሳት፣ እንጂ ሦስት
ነፍስ፣ ሦስት እሳት፣ ሦስት ፀሐይ አይባሉም፡፡ ሥላሴም በአካል፣
በስም፣ በግብር ሦስት ቢባሉ በባሕርይ፣ በሕልውና፣ በፈቃድ፣
በመለኮት አንድ ናቸው አንጂ እማልክት አይባሉም፡፡
የቂሣርያው ሊጳጳስ ቅዱስ ባስልዮስ «እንዘ አሐዱ ሠለስቱ
ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ ይሤለሱ በአካላት ወይትዋሐዱ
በመለኮት» እንዳለ፡፡ ይህም ማለት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ
አንድ ሲሆኑ ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ ናቸው፡፡ በአካል ሦስት
ሲሆኑ በመለኮት አንድ ናቸው፡፡ ማለት ነው፡፡ ይህም ሰው
በሚረዳው መጠን ለመግለጽ ያህል ነው እንጂ ከፍጥረት ወገን
ለሥላሴ የሚሆን በቂ ምሳሌ የለም፡፡ የተመሰለ ቢመስል
ሕጸጽ /ጎደሎ/ ምሳሌ ነው፡፡