ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

Monday, April 25, 2016

የየዕለታቱ ሰሙነ ሕማማት

፨፨፨ "የየዕለታቱ ሰሙነ ሕማማት"፨፨፨
፨፨፨ ሰኞ:-ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ፤ ቅጠል ያለባትን
በለስ ከሩቅ አይቶ
በለሲቱን ቀረባት፤ ነገረ ግን ከቅጠል በቀር ምንም
አልተገኘባትም፡፡ ከአሁን
ጀምሮ ማንም ከአንች ፍሬን አይብላ ብሎ እረገማት በለስ
የተባሉአ እስራኤላዊ
ናቸው፡፡ ጌታም በዕለተ ሠኞ ሁለት ነገሮችን አድረጓል ፩
ማቴ.21÷18 ቅጠል
ብቻ የተገኘባትን ዕፀበለስ እረግሟል፡፡" ፪…
ሉቃ.19÷45-46" ወደ ቤተ
መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትን የሚለውጡትን "ቤቴ የፀሎት ቤት
ናት እንጅ
የነጋደዎች ዋሻ አይደለችም" ብሎ ያንን ነጋደወቹ የያዙትን
በሙሉ
እየገለባበጠ ቤተ መቅደሱን የፀሎት ቤት አድረጓል፡፡ # ፨፨፨
ማክሰኞ:-
ሻጮቹንና ለዋጮቹን ከቤተ መቅደስ ባወጣ ጊዜ ይሔንን
በማን ኃይል
እንዳደረገው፡ የአይሁድ መምህራን ጠይቀዉት ነበር።
ማቴ.21፥13
ስለመሆኑም የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡
፨፨፨ ረቡዕ:-ምክረ አይሁድ ይባላል። ምክንያቱም የአይሁድ
ሊቃነ ካህናት እና
ጸሐፍት ፈርሳዊያን ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ምክር
ያጠናቀቁበት ቀን
ነው፡፡
፨፨፨ ሐሙስ:-በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያላቸው
በርካታ፡
ድርጊቶች የተፈፀመበት ነው፡፡
ፀሎት ሐሙስ ይባላል፡፡ ጌታ ኢየሱስ አይሁድ መጥተው
እስኪይዙት ድረስ
ሲፀልይ ያደረበት ነውና ፀሎት ሐሙስ ተባለ። ሕጽበት ሐሙስ
ይባላል፡፡
ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር ጎንተስ ብሎ
በታላቅ ትኅትና
አጥቧልና፤ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል። ምክንያቱም የኦሪት
መስዋዕት
የሆነውን የእንሥሣት ደም ማብቃቃቱን ገልጦ ለድህነተ አለም
ራሱን የተወደደ
መስዋዕት አድረጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ፡ የነፃነት ሐሙስ:-
ምክንያቱም
ለሀጢአትና ለዳቢሎስ ባሪያ መህን ማብቃቱንና የሰው ልጅ
ያጣውን፡ ክብር
መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡
፨፨፨ ዓርብ:-ጌታችን ከጲላጦስ አደባባይ እስከ ሊጦስጥራ
የተንገላታበት፣
ለአዳምና ለልጆቹ፡ በመልዕልተ መስቀል ለሞት፡ እራሱን
አሳልፎ የሰጠበት ቀን
ነው፡፡
፨፨፨ ቅዳሜ:-በዚች ዕለት የጌታችን መከራ በማሰብ በፆም
ታስባ ስለምትውል
ቅዳም ስዑር ወይም የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ ካህናቱም
ለምዕመናን
ልምላሜ ቄጤማን የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ ለምለም
ቅዳሜም ትባላለች፡፡
እንደዚሁም ልዑል እግዚአብሔርም በዚህ ቀን ፳፪ቱን ስነ
ፍጥረታት ፈጥሮ
ከሰራው ያረፈበት ዕለት ናት። መልካም የዖም ሳምብት፥
የስግደትና የእግዚኦታ
ሳምንት ይሁንልን አሜን ይቆየን።
እንዲሁ እንዳለን በሠላም በጤና ጠብቆ ለብረሃነ ትንሳኤው
በሠላም በፍቅር
ያድረሰን፡፡ አሜን።፨፨፨፨

Friday, April 22, 2016

የሕማማት ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የሕማማት ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
የሕማማት ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
1 በሕማማት ለምን መስቀል አንሳለምም ወይም
አናማትብም ?
የመስቀል ክብር እና ኃይል የታወቀው ጌታ በመስቀለ ከተሰቀለ
በኋላ ነው በሰሞነ ሕማማት ከሰኞ እስከ አርብ ያሉት ቀናት
የዓመተ ፍዳ መታሰቢያ ናቸው በነዚህ ዘመናት ሰዎች
የመስቀልን አገልገሎት እንዳልጀመሩ ለማሳየት በሰሞነ
ሕማማት በቤተክርስተያን ስርዓት መሰረት መስቀል
መሳለምም
ሆነ የማማተብ ስርዓት የለም
2 በሰሞነ ሕማማት ለምን አንንሳሳምም?
ይሁዳ ጌታውን በመሳም አሳልፎ ሰጥቶአል እኛም እንደ ይሁዳ
ክፋት ካለው መሳሳም መለየታችችንን ለማሰረዳት ከዚሀ
በተጨማሪም ፍፁም ሰላም በዘመነ ፍዳ እንዳልነበረ
ለማሳየት
በሰሞነ ሕማማት እሰከ ምሳሳም የደረሰ ጥብቅ ሰላምታ የለም
3 በሰሞነ ሕማማት የማይፈቀዱ ሌሎቸ ነገሮች ምን ምን
ናቸው ? ማንኛውም ለስጋ የሚያደሉ ተግባሮችን መቀነስ እና
ቢቻለን አበዛኛውን ጊዜአችንን በቤተ እግዚአብሔር የጌታን
መከራ ሕማም በማሰብ በፆም በስግደት በጸሎት ማሳለፍ
በትዳር ያሉ በመኝታ ከመተዋወቅ መታቀብ
ቢቻል አመጋገባችንን ከወትሮው መቀነስ
4 ስለ ሰሞነ ሕማማት በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈ አለን?
ነብዩ ኢሳይያስ "በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ ሕማማችንንም
ተሸክሞአል " ኢሳ53፤4 ይላል ሕማማት የሚለው ቃለ
በቀጥታ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ተወሰደ ሲሆን የጌታን መከራ የምናስብበት
ሳምንት ነው የጌታችንን ሞቱን ሕማሙን ማሰብ መዘከር
እንደሚገባ ቅዱስ ጳውሎስ እነዲህ ይላል
" ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና" 1ቆሮ11፤26
ይህ ሳምንት ለአይሁድና ለመሰሎቻቸው የደስታ ወቅት
ቢሆንም
ለክረስትያኖች በጥልቅ ኅዘን ውስጥ የሚገቡበት ሳምንት ነው
እንዲሀ ተብሎ እንደተጻፈ'' እናንተ ታለቅሳላችሁ ሙሾም
ታወጣላችሁ ዓለም ግን ደስ ይለዋል እናንተም ታዝናላችሁ ነገር
ግን ኃዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል'' ዮሐ16፤20
በእርግጥ ኃዘናችን ትንሳኤውን እሰክናይ ለጥቂት ጊዜ ቢሆንም
ግን እናዝናለን በትነሳኤው ደግሞ ደስታውን እንካፈላለን።
ሰኞ አይሁድ እንዴት እንደሚይዙት ለመማከር ክፉ
ጉባኤያቸውን
ጀመሩ
''በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ
በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ ጌታ ኢየሱስንም
በተንኮል ሊያስይዙት ሊገሉትም ተማከሩ" ማቴ26፡3_4
ይህንን ጉባዔ ቅዱሰ ዳዊት የከፉዎቸ ጉባዔ እያለ ይጠራዋል
"ብዙ ውሾች ከበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ"
መዝ21፤16
አይሁድ ሰኞ የጀመሩትን ዕረቡ ውሳኔአቸውን አጠናቀው
በምሴተ
ሐሙስ ከዕራትና ከቁርባን በኋላ ሰይፍና ጎመድ ይዘው መጡ
በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ሰጣቸው ያዙትም እስከ አርብ ስድስት
ሰአት ሲያንገላቱት ቆይተው ከበዙ መከራ በኋላ ሰቀሉት ዘጠኝ
ሰአት ላይ ቅድስት ነፍሱን በፈቃዱ ከቅዱስ ስጋው ለየ ከአሰራ
አንድ ሰአት በፊት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በምስጋና ገንዘው ቀበሩት

ከሕማሙ ከመከራው በረከት ያሳትፈን
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን

ሆሳዕና እና ምሳሌነቱ!

ሆሳዕና እና ምሳሌነቱ!
• ጌታችን የታሰሩ አህዮች ለምን መረጠ?
• ሃዋርያት ለምን ልብሳቸው አነጠፉለት ?
• ጌታ ለምን በፈረስ ላይ አልተቀመጠም?
• ዝንባባ የምን ምሳሌ ነው?
• በሆሣዕና በእጃችን እደ ቀለበት ማሰራችን የምን ምሳሌ
ነው?
ቤተ ፋጌ የድሆች መንደር ናት፡- ጌታ የድሆች መንደር ወደደ፡፡
እኛ ድሆቹን ባለ ፀጋ ሊያደርገን ስለኛ ብሎ ራሱን ድሃ ያደረገ
አምላክ ነውና፡፡ቤተ ፋጌ ለእየሩሳሌም በጣም ቅርብ ናት፡፡
እኛም ለቤተ ክርስትያን ቅርብ መሆን አለብን፡፡
እየሩ ሳሌም ቤተ ክርስትያን ናት እንቅረባት ፡፡እየሩ ሳሌም
እመቤታችን ናት እንቅረባት ፡፡ጌታ ቤተሳጌ በደረሰ ጊዜ
የተመሳቀለ መንገድ ቁሞ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱ ላከ *ሁሩ
ሃገረ ቅድመክሙ* ወደ ፊታችሁ ላለው ሃገር ሂዱ ወደ
መንደሪቱ ግቡ አላቸው፡፡
በተመሳቀለ ቦታ መቆሙ፡- ወደ ፊት በመስቀል ላይ
እሰቀላለሁ ሲል ነው፡፡
ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ሲልካቸው በፊታችሁ ላለው ሃገር ሂዱ
ያን ጊዜ አህያ ከውርንጭላዋ ጋር ታስራ ታገኛላችሁ ፈታችሁ
አምጡልኝ አላቸው፡፡
ጌታችን ብዙ ያልታሰሩ አህዮች እያሉ ለምን የታሰሩትን መረጠ?
አህዮቹ የታሰሩት ሌባ ሰርቆ ነው ያሰራቸው፡፡ ወንበዴ ሰርቆ
ነው ያሰራቸው
አህዮቹ ለጌታ ውለታ ሰርተዋል፡፡ ጌታ ሲወለድ
አሙቀውታልና፡፡ ለጌታ ውለታ ልንመልስ ያልቻልነው እኛ
ሰዎች ብቻ ነን፡፡
የታሰሩት እዲፈቱ የመረጠበት ሚስጥር፡-እኔ ከሃጥአታችሁ
ልፈታችሁ የመጣሁ ነኝ ሲል ነው፡፡
ወንበዴው አህዮቹን ሰርቆ በመንደር እንዳሰራቸው
ዲያብሎስም ለሰው ልጅ በሃጥአት ሰንሰለት ከሲኦል መንደር
አስራቸው ነበርና፡፡
ሃዋርያቱ ሲልካቸው ምን ታደርጋላችሁ የሚላችሁ ሰው ቢኖር
ጌታቸው ይሻቸዋል በልዋቸው አላቸው፡፡ የፈጠራቸው እሱ
ነውና፡፡
ከአህያዋ ጀርባ ሃዋርያት ልብሳቸው አነጠፉለት ለምን?
ለምንስ ኮርቻ አላደረጉለትም? ለምንስ ልብሳቸው መረጡ?
ለስላሳ ህግ የሰራህልን አንተ አባት ነህ ሲሉ ነው፡፡ለስላሳ ህግ
የተባለው ወንጌል ነው
ወንጌል ፍቅር ናት የሚረግማችሁ መርቁ ትላለችና፡፡ልብስ
የሰውነት ነውር ይሸፍናል፡፡ ነውረ ሃጥአታችን የምትሸፍንልን
አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡ እሱ ልብሳችን ነውና፡፡ ነውራችን
የሚሸፍንልን እሱ ነውና፡፡ችግሩ ግን ነውረ ሃጥአታችን
የሚሸፍንልን ልብስ እርሱ መሆኑን አለማወቃችን ነው፡፡
አብሮን እንዳለ አለማስተዋላችን ነው፡፡ስለዚ እንደ ሃዋርያት
ሃጥአታችንን አስቀድመህም የሸፈንክልን ዛሬም የምትሸፍንልን
ወደፊትም የምትሸፍንልን አምላክ አንተ ነህ ልንለው ይገባል፡፡
ጌታችን በሁለቱ አህያዎች በጥበብ ተቀመጠ፡- በሰው የማይቻል
በእግዚአብሔር ዘንድ ግን የሚቻል መሆኑ ጥበበኛ አባት ሁሉን
የሚችል አባት መሆኑ የሚገልጽ ነው፡፡ አንድም ወንጌልን
ኦሪትና ሃዲስን ሁለቱ አስታርቆ አስማምቶ አንዱን አንዱን
እየመገበ የሚሄድ መሆኑ የሚያመለክት ነው፡፡
ጌታ ለምን በፈረስ ላይ አልተቀመጠም?
ትንቢትና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ ት.ዘካ9፡9 ” አንቺ
የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ
ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም
ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ
ወደ አንቺ ይመጣል።”
በአህያ መቀመጡ
•ትህትናን ለማስተማር
•የሰላም ዘመን ነው ሲል
•ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና በየዋህነት
ለሚኖሩ መእመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል፡፡
•አህያዎች ትሁታን ናቸው ረጋ ብለው ነው የሚሄዱት፤በቀላሉ
ትወጣበታለህ፤በቀላሉ ትይዘዋለህ፤እንደፈለክም ታዝዋለህ፤እኛ
በትእቢት ተይዘን ነው እንጂ በየዋህነት ብንመላለስ እሱ
ያድርብን ነበር፡፡ እኛ የእግዚአብሔር ማደርያ ነንና፡፡
ትልቅዋ አህያ የኦሪት ምሳሌ ነው
1.ትልቅዋ አህያ ሸክም የለመደች ናት ህገ ኦሪትም የተለመደች
ህግ ናትና፡፡
2.የእስራኤል ምሳሌ ነው፡-ትልቅዋ አህያ ሸክም እንደለመደች
ሁሉ እስራኤልም ህግ ለመፈጸም በህግ ለመራመድ የለመዱ
ናቸው፡፡
3.የአዳም ምሳሌ ነው፡- አዳም ሸክም የበዛበት ነበርና
ውርጭላዋ
1.በህገ ወንጌል ትመሰላለች፡-ምክንያቱም ወንጌል ኢየሱስ
ክርስቶስ የመሰረታት የሰራት አዲስዋ ህግ ናትና፡፡
2.በአህዛብ ትመሰላለች፡-ትንሽዋ አህያ ሸክም የለመደች
አይደለችም እንዲሁም አህዛብም ህግህን የመቀበል የለመደ
አይደሉም፡፡ ለህግህ አዲስ ናቸውና፡፡
3.የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡- የዓለም ሸክም አቅልላለችና
በእመቤታችን ትመሰለላለች፡፡ እመቤታችን ድህነተ
ምክንያታችን ጌታን የተሸከመች ንጽህት እንከን የሌላት እናት
ናትና፡፡
ህዝቡም ልብሳቸው እያወለቁ በጎዳና አነጡፉለት ለምን?
እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያም ክብር ይገባታል ብለው
ነው፡፡እስራኤላውያን ጌታ የተቀመጠባት አህያ አከበሩ፡፡ ይህ
ትውልድ ግን ጌታ የተቀመጠባት እመቤታችን ማክበር
ተሳናቸው፡፡ልብሳቸው ማንጠፋቸው፡- ለክብሩ መግለጫ ነው፡፡
ሌሎችም ቅጠል አነጠፉለት፡ ሰስት አይነት ቅጠል አነጠፉለት
ዝንባባ፤የቴመር ዛፍ፤የወይራ ዛፍ አነጠፉለት፡፡
ዝንባባ
1.ዝንባባ፡- ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ ደስ ብሎት አብርሃምን
ዝንባባ ይዞ እግዚአብሔር አመስግነዋል፡፡
2.ዝንባባ ደርቆ እንደገና ሂወት ይዘራል፡- የደረቀ ሂወታችን
የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
3.ዝንባባ የሰላም ምልክት ነው፡- የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ
ነው
4.ዝንባባ የደስታ መግለጫ ነው፡- አንተ ደስ የምታሰኝ
ሃዘናችንም የምታርቅልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
5.ዝንባባ እሾሃማ ነው፡- አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ
ነው፡፡
6.ዝንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጂ፡፡ ጌታም
አንተ ባህሪህን የማይመረመር ነው ሲሉ ነው፡፡
ሆሣዕና በእጃችን እደ ቀለበት ማሰራችን የምን ምሳሌ ነው?
1.ጌታ ለአዳም የሰጠው ቃል ኪዳን ለማስታወስ፡-ከልጅ ልጅህ
ተወልጄ አድነሃለሁ ያለውን የተስፋ ቃል ለማስታወስ፡፡
2.ጌታ ለእመቤታችን የገባላትን ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው
3.ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው
4.ጌታ ለአዳም ከሰይጣን ግዛት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም
ከሰይጣን ግዛት ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከሃጥአት
አውጣን ማረን ለንስሃ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ
ቸርነትህ ይቅር በላን ስንል ከጌታ ደግመን ላናጠፋ ቃል
የምንገባበት ነው፡፡
ስለዚ እንደ ታሰሩ አህዮች መፈታት አለብን፡፡ ሁላችን ታስረናልና
ቤተ ክርስትያን በመሄድ እንድንፈታ እናድርግ፡፡ የታሰሩት ሁሉ
በካህናት አባቶቻችን አማካኝነት እዲፈቱ ልናድርግ ይገባናል፡፡
ለምን ቢባል አምላካችን ይፈልገናል አባታችን አማላካችን
ንጉሳችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈልገናል፡፡ ጌታ ጸጋውን አብዝቶ
ለዘላለሙ ከቤቱ አይለየን የነጻነት አባት ካለን ሱስና ልማድ ሁሉ
ነጻ አድርጎ ለሱ እንድንገዛ እርሱ ይርዳን
አሜን ተባረኩ መልካም በዓል፡፡

ሆሣዕና

።።።።።።ሆሳዕና።።።።። ።።
«ሆሳዕና» ቃሉ ከሁለት አረማይክ ቃላት የተሰራ ሲሆን
ትርጉም
«እባክህ እርዳ፣ አሁን አድን» ማለት ነው። እብራይስጡም
ይህንኑ ቃል ወርሶ « הושענא » ሆሻአና ሲል ይገኛል። አዎ
«አሁን አድን፣ እባክህ እርዳን» ብሎ የአዳም ዘር ያጣውን
ልጅነትና የደረሰበትን ሞት ለመላቀቅ የሚያሰማው የጩኸት
ድምጽ ነው፣ «ሆሳዕና»!!!
ዳዊት ነቢይ በመንፈስ ቅዱስ ተመልክቶ ማዳኑን ሲጣራና አሁን
ናልን ሲል ከዘመናት በፊት አድምጠነዋል። የውስጥ ዓይኖቹ
ሩቅ አይተዋል። ማዳኑንም ሽተው እንዲህ ሲል ዘምሮለታል።
«አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና»
መዝ ፻፲፰፣፳፭
ያ ማለት ደግሞ « אָנָּ֣א יְ֭הוָה הֹושִׁ֘יעָ֥ה נָּ֑א אָֽנָּ֥א
יְ֝הוָ֗ה הַצְלִ֘יחָ֥ה נָּֽא » አና ያኽዌ ሆሳአና አና ያኽዌ
ሆስሊኻ ና» የሚለው የእብራይስጡ ቃል ነው።
ሆሳዕና እና ምሳሌነቱ!
• ጌታችን የታሰሩ አህዮች ለምን መረጠ?
• ሃዋርያት ለምን ልብሳቸው አነጠፉለት ?
• ጌታ ለምን በፈረስ ላይ አልተቀመጠም?
• ዝንባባ የምን ምሳሌ ነው?
• በሆሣዕና በእጃችን እደ ቀለበት ማሰራችን የምን ምሳሌ
ነው?
ቤተ ፋጌ የድሆች መንደር ናት፡- ጌታ የድሆች መንደር ወደደ፡፡
እኛ ድሆቹን ባለ ፀጋ ሊያደርገን ስለኛ ብሎ ራሱን ድሃ ያደረገ
አምላክ ነውና፡፡ቤተ ፋጌ ለእየሩሳሌም በጣም ቅርብ ናት፡፡
እኛም
ለቤተ ክርስትያን ቅርብ መሆን አለብን፡፡
እየሩ ሳሌም ቤተ ክርስትያን ናት እንቅረባት ፡፡እየሩ ሳሌም
እመቤታችን ናት እንቅረባት ፡፡ጌታ ቤተሳጌ በደረሰ ጊዜ
የተመሳቀለ መንገድ ቁሞ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱ ላከ *ሁሩ
ሃገረ ቅድመክሙ* ወደ ፊታችሁ ላለው ሃገር ሂዱ ወደ
መንደሪቱ ግቡ አላቸው፡፡
በተመሳቀለ ቦታ መቆሙ፡- ወደ ፊት በመስቀል ላይ
እሰቀላለሁ ሲል ነው፡፡
ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ሲልካቸው በፊታችሁ ላለው ሃገር ሂዱ
ያን ጊዜ አህያ ከውርንጭላዋ ጋር ታስራ ታገኛላችሁ ፈታችሁ
አምጡልኝ አላቸው፡፡
ጌታችን ብዙ ያልታሰሩ አህዮች እያሉ ለምን የታሰሩትን መረጠ?
አህዮቹ የታሰሩት ሌባ ሰርቆ ነው ያሰራቸው፡፡ ወንበዴ ሰርቆ
ነው ያሰራቸው
አህዮቹ ለጌታ ውለታ ሰርተዋል፡፡ ጌታ ሲወለድ
አሙቀውታልና፡፡
ለጌታ ውለታ ልንመልስ ያልቻልነው እኛ ሰዎች ብቻ ነን፡፡
የታሰሩት እዲፈቱ የመረጠበት ሚስጥር፡-እኔ ከሃጥአታችሁ
ልፈታችሁ የመጣሁ ነኝ ሲል ነው፡፡
ወንበዴው አህዮቹን ሰርቆ በመንደር እንዳሰራቸው
ዲያብሎስም ለሰው ልጅ በሃጥአት ሰንሰለት ከሲኦል መንደር
አስራቸው
ነበርና፡፡
ሃዋርያቱ ሲልካቸው ምን ታደርጋላችሁ የሚላችሁ ሰው ቢኖር
ጌታቸው ይሻቸዋል በልዋቸው አላቸው፡፡ የፈጠራቸው እሱ
ነውና፡፡
ከአህያዋ ጀርባ ሃዋርያት ልብሳቸው አነጠፉለት ለምን?
ለምንስ ኮርቻ አላደረጉለትም? ለምንስ ልብሳቸው መረጡ?
ለስላሳ ህግ የሰራህልን አንተ አባት ነህ ሲሉ ነው፡፡ለስላሳ ህግ
የተባለው ወንጌል ነው
ወንጌል ፍቅር ናት የሚረግማችሁ መርቁ ትላለችና፡፡ ልብስ
የሰውነት ነውር ይሸፍናል፡፡ ነውረ ሃጥአታችን የምትሸፍንልን
አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡ እሱ ልብሳችን ነውና፡፡ ነውራችን
የሚሸፍንልን እሱ ነውና፡፡ችግሩ ግን ነውረ ሃጥአታችን
የሚሸፍንልን ልብስ እርሱ መሆኑን አለማወቃችን ነው፡፡
አብሮን
እንዳለ አለማስተዋላችን ነው፡፡ስለዚ እንደ ሃዋርያት
ሃጥአታችንን አስቀድመህም የሸፈንክልን ዛሬም የምትሸፍንልን
ወደፊትም
የምትሸፍንልን አምላክ አንተ ነህ ልንለው ይገባል፡፡ጌታችን
በሁለቱ አህያዎች በጥበብ ተቀመጠ፡- በሰው የማይቻል
በእግዚአብሔር ዘንድ ግን የሚቻል መሆኑ ጥበበኛ አባት ሁሉን
የሚችል አባት መሆኑ የሚገልጽ ነው፡፡ አንድም ወንጌልን
ኦሪትና
ሃዲስን ሁለቱ አስታርቆ አስማምቶ አንዱን አንዱን እየመገበ
የሚሄድ መሆኑ የሚያመለክት ነው፡፡
ጌታ ለምን በፈረስ ላይ አልተቀመጠም?
ትንቢትና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ ት.ዘካ9፡9 ” አንቺ
የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ
ሆይ፥
እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ
በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ
አንቺ ይመጣል።”
በአህያ መቀመጡ
•ትህትናን ለማስተማር
•የሰላም ዘመን ነው ሲል
•ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና በየዋህነት
ለሚኖሩ መእመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል፡፡
•አህያዎች ትሁታን ናቸው ረጋ ብለው ነው የሚሄዱት፤በቀላሉ
ትወጣበታለህ፤በቀላሉ ትይዘዋለህ፤እንደፈለክም ታዝዋለህ፤እኛ
በትእቢት ተይዘን ነው እንጂ በየዋህነት ብንመላለስ እሱ
ያድርብን ነበር፡፡ እኛ የእግዚአብሔር ማደርያ ነንና፡፡
ትልቅዋ አህያ የኦሪት ምሳሌ ነው
1.ትልቅዋ አህያ ሸክም የለመደች ናት ህገ ኦሪትም የተለመደች
ህግ ናትና፡፡
2.የእስራኤል ምሳሌ ነው፡-ትልቅዋ አህያ ሸክም እንደለመደች
ሁሉ እስራኤልም ህግ ለመፈጸም በህግ ለመራመድ የለመዱ
ናቸው፡፡
3.የአዳም ምሳሌ ነው፡- አዳም ሸክም የበዛበት ነበርና
ውርጭላዋ
1.በህገ ወንጌል ትመሰላለች፡-ምክንያቱም ወንጌል ኢየሱስ
ክርስቶስ የመሰረታት የሰራት አዲስዋ ህግ ናትና፡፡
2.በአህዛብ ትመሰላለች፡-ትንሽዋ አህያ ሸክም የለመደች
አይደለችም እንዲሁም አህዛብም ህግህን የመቀበል የለመደ
አይደሉም፡፡ ለህግህ አዲስ ናቸውና፡፡
3.የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡- የዓለም ሸክም አቅልላለችና
በእመቤታችን ትመሰለላለች፡፡ እመቤታችን ድህነተ
ምክንያታችን ጌታን የተሸከመች ንጽህት እንከን የሌላት እናት
ናትና፡፡
ህዝቡም ልብሳቸው እያወለቁ በጎዳና አነጡፉለት ለምን?
እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያም ክብር ይገባታል ብለው
ነው፡፡ እስራኤላውያን ጌታ የተቀመጠባት አህያ አከበሩ፡፡ ይህ
ትውልድ ግን ጌታ የተቀመጠባት እመቤታችን ማክበር
ተሳናቸው፡፡ ልብሳቸው ማንጠፋቸው፡- ለክብሩ መግለጫ ነው፡፡
ሌሎችም ቅጠል አነጠፉለት፡ ሰስት አይነት ቅጠል አነጠፉለት
ዘንባባ፤የቴመር ዛፍ፤የወይራ ዛፍ አነጠፉለት፡፡
ዘንባባ
1.ዘንባባ፡- ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ ደስ ብሎት አብርሃምን
ዝንባባ ይዞ እግዚአብሔር አመስግነዋል፡፡
2.ዝንባባ ደርቆ እንደገና ሂወት ይዘራል፡- የደረቀ ሂወታችን
የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
3.ዝንባባ የሰላም ምልክት ነው፡- የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ
ነው
4.ዝንባባ የደስታ መግለጫ ነው፡- አንተ ደስ የምታሰኝ
ሃዘናችንም የምታርቅልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
5.ዝንባባ እሾሃማ ነው፡- አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ
ነው፡፡
6.ዝንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጂ፡፡ ጌታም
አንተ ባህሪህን የማይመረመር ነው ሲሉ ነው፡፡
ሆሣዕና በእጃችን እደ ቀለበት ማሰራችን የምን ምሳሌ ነው?
1.ጌታ ለአዳም የሰጠው ቃል ኪዳን ለማስታወስ፡-ከልጅ ልጅህ
ተወልጄ አድነሃለሁ ያለውን የተስፋ ቃል ለማስታወስ፡፡
2.ጌታ ለእመቤታችን የገባላትን ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው
3.ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው
4.ጌታ ለአዳም ከሰይጣን ግዛት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም
ከሰይጣን ግዛት ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከሃጥአት
አውጣን ማረን ለንስሃ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ
ቸርነትህ ይቅር በላን ስንል ከጌታ ደግመን ላናጠፋ ቃል
የምንገባበት ነው፡፡
ስለዚ እንደ ታሰሩ አህዮች መፈታት አለብን፡፡ ሁላችን ታስረናልና
ቤተ ክርስትያን በመሄድ እንድንፈታ እናድርግ፡፡ የታሰሩት ሁሉ
በካህናት አባቶቻችን አማካኝነት እዲፈቱ ልናድርግ ይገባናል፡፡
ለምን ቢባል አምላካችን ይፈልገናል አባታችን አማላካችን
ንጉሳችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈልገናል፡፡ ጌታ ጸጋውን አብዝቶ
ለዘላለሙ ከቤቱ አይለየን የነጻነት አባት ካለን ሱስና ልማድ ሁሉ
ነጻ አድርጎ ለሱ እንድንገዛ የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል
ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን አበው ጥበቃ ይርዳን።

የዐቢይ ጾም 8ኛ ሳምንት ሆሣዕና

ሆሣዕና (የዐቢይ ጾም 8ኛ ሳምንት)
ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው
ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ
የሕማማት መገቢያ ዋዜማ ነው። ሆሣዕና አስቀድሞ ካለው
ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን
እንደሆነ ይታወቃል። ይህን ስም በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ
ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና
ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርዓየ… ‘ ወዘተ. በማለት
ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች
በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ
ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘምር
ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና
በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት
በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር
ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ
መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው።
አስቀድሞም በነቢየ እግዚአብሔር ዘካሪያስ እንደተነገረው
‘አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበለሽ ፣አንቺ የኢየሩሳሌም
ልጅ ሆይ እልል በይ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም
ሆኖ በአህያም በአህያያቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ
ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል… ሰላምን ይናገራል’’ ዘካ.9፣9።
በማለት እንደሚመጣና የሠላምንም ብሥራት እንደሚያበሥር
ተናገሮ ነበር። ሲመጣም ‘ሁሉም ፈጥነው ልብሳቸውን ወሰዱ
በሰገነቱም መሰላል እርከን ላይ ከእግሩ በታች አነጠፉት።’’
በማለት ሊደረግለት የሚገባውን ገልጿል። 2ኛ ነገ. 9፣13 ።
የሆሣዕና በዓል በቤተክርስቲያን ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ
ሕዝቡ ፀበርት ወይም ዘንባባ በመያዝ ‘ቡርክ ዘይመጽእ በስመ
እግዚአብሔር - በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረክ
ነው።’’ መዝ.117፣26 በማለት ስለተቀበሉት ይህን በማሰብና
በማድረግ ቤተክርስቲያናችን ዘንባባ ለሕዝበ ክርስቲያኑ
ይታደላል። በቤተክርስቲያን በአራቱም ማዕዘናት ይህን በዓል
የሚመለከቱ የቅዱስ ማቴዎስ (ማቴ. 21፣1-17)፤ የቅዱስ
ማርቆስ፣(ማር.11፣1-1 0)፤ የቅዱስ ሉቃስና
(ሉቃ.19፣29-38)፤ የቅዱስ ዮሐንስ (ዮሐ.12፣12-15)
ወንጌላት ይነበባሉ ። ታዲያ አኛ ይህን ዐቢይ በዓል
የምናከብረው እንዴት ነው? በነቢያቱ ከላይ እንደተገለጠው
በወንጌላቱም አንደተፈጸመው እርሱ ወደ እኛ የሚመጣበት ጊዜ
መቼ ነው? ሲመጣስ ምን እናድርግ? የእግዚአብሔርን
መምጫ ጊዜ ማሰብና መዘጋጀት ያለብን እንዴት ነው?
ምክንያቱም በዓሉ ከምንም በላይ የሚጠቅመን ለእኛ ነውና ።
ስለዚህ ይህን በዓል ስናከብር ሰላምንና ፍቅርን የእርሱን የክብር
አመጣጥ እያሰብን ልንተገብረው ይገባል።
ለጌታ የማያስፈልግ ፍጥረት የለም ይልቁንም የክብር ዘውድ
አድረጎ በመልኩ የፈጠረው ሰው ያስፈልገዋል።ያለ
እግዚአብሔር ፈቃድ የተፈጠረ ማንም የለም።እያንዳንዳችን
በእግዚአብሔር ዓላማና ዐቅድ የተፈጠርን እንደመሆናችን
መጠን እግዚአብሔር የሚከብርበትን ሥራ ልንሠራ
ይገባል።አህያ በሰው ሰውኛ ሲታይ የንቀትና የውርደት ሲመስል
ይችላል ።የአህያን ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ስንመለከት ግን
1. በለዓም በሥጋዊ ገንዘብ መንፈሳዊ ዓይኑ ታውሮ
እግዚአብሔር ያልረገማቸውን እስራኤላውያንን ሊራገም ሲሄድ
እስራኤላውያንን እንዳይራገም ለመንገር ከእግዚአብሔር ዘንድ
የተላከው መልአክ በሚሄድበት መንገድ ላይ ቆሞ ሳለ ከበለዓም
ይልቅ ያየችው የበለዓም አህያ ነበረች ። አህያይቱም መልአኩን
አክብራ መንገዱን እንደለቀቀችለት ቅዱስ መጽሐፍ
ይነግረናል። ዘኅ.22፣23።
2. በትንቢተ ኢሳያስ 1፣3 ‘ሰማይ ስሚ ምድርም አድምጪ በሬ
የገዢውን አህያም የጌታውን ጋጣ አወቀ እሥራኤል ግን
አላወቀም’’ እንደተባለው ጌታ በተወለደ ጊዜ ትንቢቱን
ምሳሌውን የሚያውቁ እሥራኤላውያን ባላወቁ ባለተቀበሉ
ሰዓት በዚያ በብርድ ወራት እናቱ የምታለብሰው ልብስ አጥታ
ቅጠል አልብሳው በነበረ ጊዜ ለጌታ ሙቀት የገበሩለት
እረኞቻቸውን ተከትለው የመጡ ከበቶች ላሞችና አህዮች
ናቸው። ‘ወአስተማወቅዎ አድግ ወላህም’’ እንዲል አባ
ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም።።
3. በሆሣዕና ዕለት ከሌሎች እንስሳት ይለቅ ጌታን ለመሸከም
ለከብር የተሸከመችው አህያ ናት። ጌታን የተሸከመችው አህያ
ከዚያ በፊት ያላየችውና ያልተደረገላት ክብር ተደርጉላታል።
አህያ ከዚህ በፊት ለኛ እህል ተሸክማ ስትሄድ ሂጂ እያልን በዱላ
እንደበድባት ነበር፡ ነውም። ነገር ግን በሆሣዕና ዕለት እንኳን
በዱላ ልትደበደብ ቀርቶ ሰዎች በእርሷ ላይ ለተቀመጠው ጌታ
ሲሉ ልብሳቸውን ሁሉ እያነጠፉላት በንጣፍ ላይ ተራምዳለች ።
ስለዚህ ክርስቶስ በአህያይቱ ላይ እንዲቀመጥባት ልብስም አንደ
ተጎዘጎዘላት እኛም ጌታ በፀጋውና በረድኤቱ እንዲያድርብን
ልባችንን ከኃጢአትና ከተንኮል አንጽተን ፍቅርንና ትሕትና
ልንጎዘጎዝ ይገባል።ጌታ በኛ ላይ በፀጋው ሲያድር በእርሱና
በቅዱሳኑ ዘንድ ያለን ክብርና ፀጋ ታላቅ ነው። በነገር ሁሉ
መከናወን ይሆንልናል።ክርስቶስን በመሸከሟ የአህያይቱ ታሪክ
እንደተለወጠ ሁሉ በክርስቶስ ማደሪያነታችን ያለፈው መጥፎ
ታሪካችን ይለወጣል።እንግዲህ በእለተ ሆሣዕና ወደ
ኢየሩሳሌም ሲሄድ ሕዝቡ ሁሉ በደስታ በዝማሬ እንደ ንጉሰ
እንደተቀበሉት እኛም ሀሴትን አድርገን ‘ሆሣዕና እምርት እንተ
አቡነ ዳዊት…’’ በማለት እናመሰግናለን። ከበዓሉ ረድኤት
በረከት ያሳትፈን።አሜን።
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ
ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ
ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት
እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ
ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ
ወሥልጣነ፡፡
ትርጉም: “በፋሲካ በዓል ሰሞን የእውነት አምላክ ደቀ
መዛሙርት ወደ ደብረ ዘይት ቀረቡ፤ በሀገረ እግዚአብሔር
(ኢየሩሳሌም) አቀበቱ ላይ ብዙ አረጋውያንና ሕፃናት የዘንባባ
ቅጠል ይዘው ሆሣዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት፣ በአህያ
ውርንጫ ላይ ተጭኖ በፍጹም ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።
ለእነዚህ ኃይልና ሥልጣንን ይሰጣቸዋል።

የዐቢይ ጾም 7ኛ ሳምንት ኒቆዲሞስ

ኒቆዲሞስ (የዐቢይ ጾም 7ኛ ሳምንት)
ዮሐ. 3÷1-11 ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ
ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ
ኢየሱስ መጥቶ። መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር
ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች
ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር
ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው። ኢየሱስም መልሶ።
እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር
የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።
ኒቆዲሞስም። ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል?
ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን?
አለው። ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል። እውነት እውነት
እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ
እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ
ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው። ዳግመኛ
ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁህ አታድንቅ። ነፋስ
ወደሚወደው ይነፍሳል፥ ድምፁንም ትሰማለህ፥ ነገር ግን
ከወዴት እንደ መጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ
የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው። ኒቆዲሞስ መልሶ። ይህ እንዴት
ሊሆን ይችላል? አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው።
አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን?
እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን
ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ምስክራችንንም አትቀበሉትም።
ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ
ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ? ከሰማይም ከወረደ
በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ
የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ሖረ ኀቤሁ ዘስሙ ኒቆዲሞስ ወይቤሎ ለኢየሱስ ረቢ ሊቅ ንሕነ
ነአምን ብከ ከመ እምኀበ አብ መጻእከ ከመ ትኩን መምህረ፤
ዕጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ አንሥአኒ በትንሣኤከ፡፡
ትርጉም: ስሙ ኒቆዲሞስ የተባለው ሰው ወደ ጌታችን ኢየሱስ
ሄደ፤ መምሕር ሆይ ልታስተምር ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ
እንደመጣህ እናምንብሃለን አለው። የአንበሳ ደቦል ተኛህ፣
አንቀላፋህም፤ በትንሣኤህ አንሣኝ።
እውነት እውነት እልሃለሁ፡- ሰው ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ
ካልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግሥት አያይም፡፡ ጌታችንና
መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን የተናገረው ለኒቆዲሞስ
ነው፡፡
ኒቆዲሞስ የሃይማኖት ሊቅ ነው፡፡ ብዙ የተማረ ብዙ ያወቀ
ሰው ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ ሊቅ - ምሁር - አለቃ ተብሎ
ተጠርቶአል፡፡ በጊዜው ከነበሩ ሰዎች ከፍ ያለና የላቀ ዕውቀት
የነበረው ሰው ነበር፡፡ በሌሊት ወደ ጌታ እየመጣ ይማር ነበር፡፡
የማታ ተማሪ ነበር፡፡ ቀን - ቀን የምኩራብ አስተማሪ ሆኖ ብዙ
ሰዎችን ያስተምር ስለ ነበረና እርሱ የሚያስተምራቸው አይሁድ
ጌታን ስላልተቀበሉ ቀን ለቀን መጥቶ የሚማርበት አመቺ ጊዜ
አልነበረውም፡፡
በአይሁድ ሕግ ጌታን የሚከተልና የሚቀበል ሰው ከምኲራብ
የሚባረር ስለሆነ እነርሱን ላላማስቀየም ማታ ነበር
የሚማረው፡፡ ኒቆዲሞስ ለጌታ ከሰው ችሎታ በላይ የሆኑ
ተአምራትን ስለምትሠራ እኛን ለማስተማርና ለመምከር
ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልከህ የመጣህ ነህ ብሎ
መስክሮለታል፡፡ ጌታም ለእናንተ ተልኬ የመጣሁ ከሆነና
እናንተን ለማስተማር እንደ መጣሁ ከተረዳህ ሰው ዳግመኛ
ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት
አይገባም አለው፡፡
ኒቆዲሞስ ስላልገባው እኔ አርጅቼአለሁ፤ እንዴት ነው ወደ እናቴ
ማኅጸን ተመልሼ የምገባውና ዳግም የምወለደው? ብሎ
ኢየሱስ ክርስቶስን ጠየቀው፡፡ ጌታም፡- ሰው ከሰው ከተወለደ
ሥጋዊ ነው፤ የሰው ልጅ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን
በመንፈስ መወለድ አለበት፡፡ ከእግዚአብሔር መወለድ ነፋስ
ከየት ተነሥቶ ወዴት እንደሚነፍስ እንደማይታወቅ ያለ ረቂቅ
ምሥጢር ነው አለው፡፡ አሁንም ያ ሊቅ፤ ያ አዋቂ አልገባኝም
አለ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስም፡- አንተ የእስራኤል ሊቅና አዋቂ
ሆነህ እንዴት ይህን አታውቅም አለው፡፡ ከሰማይ ከወረደው
በቀር ወደ ሰማይ የሚወጣ የለም፤ የምናውቀውንም
እንናገራለን ካለው በኋላ ጥያቄውን በዚህ ገታ፡፡
ኒቆዲሞስ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ መማሩ
የምያስመሰግነው ተግባር ነው፡፡ አይሁድ ወገኖቹ ጌታን
ሳይከተሉት እርሱ ጌታን መውደዱ የሚያስደንቅ ነው፡፡
ኒቆዲሞስ የሚያመሸው ከጌታ ጋር ነበር፡፡ ባለችው ትርፍ
ጊዜው ሁሉ ወደ ፈጣሪው ይሔድ ነበር፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል
ነው፡፡ ቀን ሲያስተምርና ሲደክም ስለሚውል ማታ - ማታ
ማረፍ ይገባው ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ ግን ቤቴ ገብቼ ልረፍ
አላለም፡፡ ባለ ሥልጣንና ባለጸጋ ስለ ነበር ደጅ የሚጠናው
ሕዝብና መሰል ባልንጀሮቹ ይፈልጉት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ
ከእነርሱ ጋር አላመሸም፡፡
ከዚህ አባት ታላቅ ትምህርት ልንማር ያስፈልጋል፡፡ እኛ ዛሬ
የምናመሸው የት ነው? የምናመሸውስ ከማን ጋር ነው? ምን
ስናደርግ ነው የምናመሸው? ኒቆዲሞስ ቤቱ አልነበረም
የሚያመሸው፤ ከእውነተኛው መምህር ጋር እንጂ፡፡ ኒቆዲሞስ
ጽድቁንና በረከቱን እየያዘ ነበር ወደ ቤቱ ይገባ የነበረው፡፡ እኛ
ወደ ቤታችን የምንገባው እየከበርን ነው ወይ? ጸድቀን ነው
የምንገባው ወይስ ጎስቁለን?
የዛሬው ሰው እየሰከረ፣ እየጨፈረ፣ እየደማ፣ እየቆሰለ አብዶ
ነው የሚመለሰው፡፡ በቤት ያሉትም እንቅፋት ያገኘው ይሆን?
ይሞት ይሁን? እያሉ እየተሳቀቁ ነው የሚያመሹት፡፡
የሚሞትም አለ፡፡ ማምሸት እንደ ኒቆዲሞስ ከጌታ ጋር ነው
እንጂ! ኒቆዲሞስ ከጌታ ጋር በማምሸቱ ፈጣሪውን አወቀ፡፡
ጌታን ማወቅ ብቻ ደግሞ አይበቃም፡፡ ማወቅማ አጋንንትም
ያውቁታል፡፡ ከመንፈስ መወለድ መወለድ ያስፈልጋል፡፡
ሰው ዕፀ በለስን በበላ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅነቱን ተነጥቆ
ነበር፡፡ ጌታ መጥቶ ዳግም ሰው እስከሚያደርገን ድረስ
የሰይጣል ልጆች ሆነን ነበር፡፡ ከዚያም በአርባና በሰማኒያ ቀን
ከአብራከ መንፈስ ቅዱስና ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ተወልደናል፡፡
አባታችን የምንለው ለዚህ ነው፡፡ ከእርሱ ከተወለድንና ልጅነትን
ካገኘን እንደገና ልጅነታችንን ካገኘን እንደገና ልጅነታችንን
እንዳናጣ አክብረን እንያዘው፡፡ መጀመሪያም አላወቅንበትም
ነበር፡፡ አዳም ከገነት የሚወጣ አልመሰለውም ነበር፡፡ ሰይጣን
አታሎታል፡፡ እኛም እንደገና እንዳንታለል ልጅነታችን
እንዳይሰረዝ እንጠንቀቅ፡፡
የብዙዎቻችን ልጅነት ዛሬ እየተወሰደ ነው፡፡ ልጅነታችንን
እያስነጠቅነው ነው፡፡ እነ ኤሳው እየነጠቁን ነው፡፡ ብዙዎች
እንደ ያዕቆብ ልጅነታችንን ሊወስዱብን አሰፍስፈዋል፡፡ ሰይጣን
እንደ አዳም ሊነጥቀን አሰፍስፏል፡፡ ዛሬ በጣም አርጅተናል፡፡
ኒቆዲሞስ አርጅቶ ነበር፡፡ በጥምቀትና በንስሓ ግን አዲስ
ሕይወት አግኝቶአል፤ ታድሷል፡፡ ያረጀው ሕይወቱ ለመለመ፡፡
ያረጀው ሰውነታችንን በሥጋውና በደሙ በንስሓ እናድሰው፡፡ ይህ
ከሆነ ነው የእግዚአብሔርን መንግሥት የምንወርሰው፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Saturday, April 9, 2016

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: የአብይ ፆም 6ኛ ሰንበት ገብርኄር!!!!!

የአብይ ፆም 6ኛ ሰንበት ገብርኄር!!!!!
+++++++++++++++ +++++++++++++++
+++++++++++++++ +++
ስያሜው የቅዱስ ያሬድ ሲሆን በዚህ ቀን ስለ ቅን አገልጋዮች ፤
ለአገልጋዮች የሚያገለግሉበት ፀጋ የሚሰጥ ፤አገልጋዮችን
‹ገብርኄር› እያለ ዋጋ የሚሰጥ አምላክ መሆኑ እየታሰበ
ይመለካል፡፡
1. የዕለቱ የቅዱስ ያሬድ መዝሙር ርዕስ
መኑ ውእቱ ገብርኄር
(ቸር አገልጋይ ማን ነው?)
2. የዕለቱ ቅዳሴ …የባስልዮስ
በቅዳሴ ሰዓት የሚነቡ የመፅሃፍ ቅዱስ ክፍሎች
1ኛ ጢሞ 2፡1-16(በዲያቆን)
1ኛ ጴጥ5፡1-12(በንፍቀ ዲያቆን)
ሀዋ 1፡6-9(በንፍቀ ካህን)
3. የዕለቱ ምስባክ
ከመ እግበር ፈቃድከ መከርኩ አምላኪየ
ወሕግከኒ በማእከለ ከርስየ
ዜኖኩ ጽድቅከ በማኅበር ዐቢይ
አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድኩ
ህግህም በልቤ ውስጥ ነው
በታላቁም ጉባኤም ጽድቅህን አወራለሁ፡፡ መዝ 39፡8
4. በዕለቱ የሚነበብ ወንጌል ማቴ 25፡14-31
5. የዕለቱ ትምህርት(ቸር አገልጋይ ማን ነው?)
ቸር አገልጋይ(ገብርኄር) ማቴ 25፡14-30 በዚህ ዕለት
በቅዳሴ ሰዓት የተነበበው ቃለ ወንጌል እንዳመለከተን
መድሃኒታችን የወንጌል አደራ በምሳሌ እናዳስተማረ
ተገንዝበናል፡፡ ትምህርቱም እንድ ባለፀጋ ሰው ነበር፡፡ ወደሩቅ
አገር ለመሄድ ባሰበ ጊዜ አገልጋዮችን ጠርቶ ከመንገዱ
እስኪመለስ ድረስ ይስራበት ዘንድ ለአንዱ አምስት መክሊት፤
ለሁለተኛው ሁለት ፡ ለሶስተኛው አንድ መክሊት ሰጣቸው፡፡
አምስት
መክሊት የተቀበለው ወጥቶ ወርዶ ሌላ አምስት መክሊት
በማትረፍ አስር መክሊት አደረገው፡፡ ሁለት መክሊት
የተቀበለውም ወጥቶ ወርዶ እጥፍ አትርፎ አራት መክሊት
አደረገው፡፡አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ወደ ስራ ከመግባቱ
በፊት በልቡ ውስጥ ስጋት ፤ጥርጥር ፤ፍርሃትንና አለማመንን
ስላነገሰ ስሰራበት ቢጠፋብኝስ ፤ ቢሰርቁኝስ
ቢቀሙኝስ እያለ በማሰብ እሰራለሁ ብዬ ያለኝን ከማጣ ለምን
ደብቄ አስቀምጬ በመቆየት ሲመጣ የሰጠኝን አልመልሰም
ብሎ መክሊቱን ቆፍሮ ቀበረው፡፡ ጊዜው ሲደርስ ባለንብረቱ
መጣና አገልጋዮቹን ይተሳሰባቸው ጀመር፡፡
በቅድሚያ አምስት የወሰደው መጣና ‹ጌታዬ ሆይ አምስት
መክሊት ሰጠኸኝ ነበር፡፡ ይኸውና ሌላ አምስት መክሊት
አትርፌያለሁ› ብሎ አስር መክሊት ለጌታው ሰጠ፡፡ ጌታውም
መልካም አደረክ አንተ መልካም አገልጋይ (ገብርኄር) በጥቂቱ
ስለታመንክ በብዙ ላይ እሾምሃለሁ› ተባለ፡፡
ሁለተኛው ‹ሁለት መክሊት ሰጠኸኝ ነበር እነሆ አራት መክሊት›
ብሎ እጥፍ ማትረፉን ገልፆ ለጌታው አስረከበ፡፡ እንደ ባለ
አምስቱ ‹መልካም አደረግህ ቸር አገልጋይ ነህ በጥቂቱ
ስለታመንክ በብዙ ላይ እሾምሃለሁ›› ተባለ
ሶስተኛው መጣ ሰነፍ ቃሉም መራራ ነው፡፡ የሰነፍ አካሉ ብቻ
ሳይሆኑ አእምሮውም ሰነፍ ነው፡፡ ጌታው ገንዘቡን ሲጠይቀው
‹ጌታ ሆይ አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ ፤ ካልበተንክበት
የምትሰበሰብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ
ፈራሁህ ሄጄም መሬት ቆፍሬ መክሊቴን ጉድጓድ ውስጥ
ቀበርኩ፡፡ ገንዘብህን ይኸውልህ ውስድ አለው፡፡ ጌታውም ይህን
ያህል ጨካኝ እንደሆንኩ ካወቅህ ንብረቴን ከነወለዱ
ልትመልስው ይገባህ ነበር፡፡ገንዘቤን ልትሰራበት ሲገባህ ለምን
ቀበርከው ብሎ መክሊቱን ወደ እርሱ ወስዶ ለባለ አምስቱ
ጨምሩለት ‹ላለው ይጨመርለታል ይትረፈረፍለታልም
ለሌላው ግን ያው ያለው ይወሰድበታል › ይህን የማይረባ
አገልጋይ ግን ልቅሶ ፤ጥርስ ማፏጨት ወዳለበት ጽኑ የፍርድ
ቦታ ውሰዱት አለ ይላል
በምሳሌ የተሰጠው የመድሃኒታችን ትምህርት፡፡ የትምህርቱም
ትርጉም
እንደሚከተለው ነው፡፡
የንብረቱ ባለቤት መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ሶስቱ
አገልጋዮች ልዩ ልዩ ፀጋ ተሰጥቶአቸው ያሉ ህዝበ ክርስቲያኖች
ምሳሌዎች ናቸው፡፡ስጦታው በአኃዝ ሲታይ ልዩነት መኖሩ አንዱ
ፀጋ ከሌላው የሚለይ መሆኑን ያሳያል፡፡
የአገልጋዮቹ ባህሪ
1. የመጀመሪያውና የሁለተኛው አገልጋዮች መንፈስ ሁለቱም
ሰርቶ ማግኘት እንደሚቻል የሚያምኑ ፤ ከጌታቸው ታማኞች ፤
በስራ ላይ የሚያጋጥማቸውን ችግር በማሰብ ጊዜያቸውን
የማያጠፉ ናቸው፡፡
ሁለተኛው አገልጋይም እንደ መጀመሪያው አገልጋይ ለምን
አምስት አልተሰጠኝም ብሎ ያለኩርፊያ በተሰጠው የሚሰራ
ነው፡፡ ባለ አምስቱ አምስት ሲያተርፍ ባለሁለቱም ሁለት
በማትረፍ ተመሳሳይ ትጋት የታየባቸው አገልጋዮች ናቸው፡፡
ዋጋቸው እኩል ነው ፤ለሁለቱም የተሰጠው የክብርም ስም
አንድ ነው፡፡ ገብርኄር የሚል የገቡበት የክብር ስፍራ አንድ
ነው፡፡ ያም ‹ጌታችን ደስታ ነው› ሁለቱም በጥቂት የታመኑ
ነበሩ፡፡ከሰጪው አንጻር ሲታይ የባለ አምስቱ እንደ ባለ ሁለቱም
፤ የባለ ሁለቱ እንደ ባለአምስቱ ጥቂት ነበር፡፡ ሰው በተሰጠው
ሳያንጎራጉር ፈጣሪውን ቢያገልግል ክብር ያገኛል፡፡ ለስው ልጅ
የሚጠቅመውን ችሎታውን ፤ፀጋውን መቁጠር ሳይሆን
በተሰተው ፀጋ ማገልገል ነው፡፡ እነዚህን አገልጋዮች በእውነት
በፍቅር በእምነት የሚያገለግሉ የቤተክርሰቲያን አገልጋዮች
ያመለክታሉ፡፡
2. የሶስተኛው አገልጋይ ባህሪ ፤ መልካም ጎኑ ስጦታው አነሰኝ
አለማለቱ ነው፡፡ በርግጥ ስንፍናውን ስለሚያውቅ ይሆናል፡፡
ይህ ሰው ከስራ ይልቅ በስጋ ጊዜ የሚፈጠረው ችግር አስቀድሞ
ይታየዋል፡፡አንዱን ሁለት ሲያደርግ ሳይሆን ያንኑ ያለውን
ሲቀማ ይታየዋል፡፡በጌታው ፊት እንደወንድሞቹ አይነቱን ትርፍ
ይዞ ቀርቦ ሲሸለም ሳይሆን ዓይነታውም ጠፍቶበት ለጌታው
የሚመልሰውን ሲያጣ ይታየዋል፡፡
በመሆኑም ምንም መስራት አልቻለም፡፡ የተሰጠውን መክሊት
ኪሱን አላምነው ብሎ መሬት ቆፍሮ ቀበረው፡፡‹ጨካኝ
መሆንህን ስላወቅሁ ይጠፋብኛል ብዬ ብርህን
አስቀምጬዋለሁ ይþውልህ ና ወሰድ› ነው ያለው፡፡ ሰነፍ
የሚናገረውም አያምርም ተቀምጦ መዐት ከማውራት ዝም
አይልም፡፡
ዛሬም ቢሆን ተቀምጠው መዐት የሚያወሩ የእግዚአብሄር ፀጋ
የቀበሩ ፤ ባስተምርና መናፍቅ ተከራክሮ ቢረታኝስ ?
የማውቀውን እውነት ለመስበክ ስጀምር ቢያሳስሩኝስ?
በቤተክርስቲያን ህዝብ በገበያ በልዩ ልዩ ቦታዎች ያሉትን
ሃጢያተኞች ብቃወም ጠላት ሆነው ቢነሱብኝ? ለምን ዝም
ብዬ ደመውዜን ሳልስራ አልበላም ብለው የሚኖሩ ስንት
አገልጋዮች አሉ፡፡ የዚህ ሰው ችግሩ መክሊቱ አንድ መሆኑ
ሳይሆን
በዚያው በተሰተው አለመስራቱ ነው፡፡ እያንዳንዱ አምኖ
በመቀበል ሊያገለግል ይገባዋል፡፡ ባለ ሁለት በባለ አምስቱ ፤
ባለ አንዱ በባለ ሁለቱ ሊቀና አይገባውም፡፡ ሁሉም ሊቀ ጳጳስ ፤
ጳጳስ ፤ ቄስ አይሆንም፡፡ ሁሉም ግን በተሰጠው ፀጋ ቢያገለግል
እውነተኞች ሊቃነ ጳጳሳት ፤ ጳጳሳት ፤ ቀሳውስት የሚያገኙትን
ዋጋ ያገኛል፡፡ ሁሉም ባለ ራዕይ ፤ ወንጌላዊ ፤ዘማሪ ፤ፈዋሽ
ሊሆን አይችልም፡፡ ለእያንዳንዱ ልዩ
ልዩ ፀጋ አለው፡፡ ሁሉም በፀጋው ቢያገለግል እኩል ዋጋ
ያገኛል፡፡
ወንድሜ አንተስ ፀጋህ ምንድን ነው? ፀጋህን ታውቀዋለህ?
ታገለግልበታለህን? አንቺስ እህቴ? መቼም ክርስቲያን ሁሉ
የክርስቶስ አካል ነው፡፡ የስራ ክፍል የሌለው የአካል ክፍል
ደግሞ የለም፡፡ አንተም/ አንቺም የክርሰቶስ አካል ነህ /ነሽ፡፡
ስለዚህ አካሉ በመሆንህ ደግሞፀጋ አለህ/አለሽ ፡፡ በመሆኑም
እንደ ፀጋችን እናገልግል፡ ፀጋውን እንቀበለው፤ ወንጌልን
በጊዜውም አለጊዜውም ሲሞላልንም ሲጎድልብንም እንስበክ
፤ ሀብታሙ ይመፅውት ፤ መምህሩ ያስተምር ፤ ዘማሪው
ይዘምር ፤ ፀሃፊው ይፃፍ ፤ ሁሉም በፀጋው ያገልግል፡፡እንድ
መክሊት እንደተቀበለው ሰው ነገ እንዲህ ብሆንስ ፤እንደዚያ
ቢፈጠርስ እያልን ባለማመን ዕለታችንን ጊዜአችንን አናባክን፡፡
መልካሙን እረኛም ያድለን! አሜን!
ወስብሃት ለእግዚአብሄር!!!!!!

Wednesday, April 6, 2016

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ:

።።ረቡዕ የሚፀለይ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል
ማርያም ምስጋና።።
፩የምድር ሁለተኛ የሆንሽ ሰማይ ሆይ የሰማያት ሰራዊት
(መላዕክት) ንዕፁ ነሽ ይላሉ ድንግል ማርያም የምስራቅ ደጅ
ናት ሙሽራዋ ንፁህ የሆነ ንፅህት የሰርግ ቤት ናት አብ በሰማይ
አይቶእንዳቺ ያለ አላግኝምና አንድ ልጁን ላከዉ በአንቺም ሰው
ሆነ ቅድስት ሆይ ልምኝልን
፪አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ትዉልድ ሁሉ አንቺን
ብቻ ያመሰግኑሻል
፫የእግዚአብሄር ሀገር ከተማ ሆይ ነበያት ድንቅ ድንቅ ነገርን
የተናገሩልሽ ደስ የተሰኙ የፅድቃን ማደሪያ ሆነሻል ና የምድር
ንግስታት ሁሉ በብርሀንሽ ይሄዳሉ ማርያም ሆይ ትውልድ ሁሉ
ያመሰግኑሻል ካንቺ ለተውለደውም ይስግዱለታል ያግኑታልም
ቅድስት ሆይ ለምኝልን
፬የዝናብ ዉሀ የታየብሽ የዕውነት ደመና አንቺ ነሽ አብ የልጁ
ምልክት አደረገሽ መንፈስ ቅዱስ አደረብሽ የልዑል ሀይል
ጋርደሽ ማርያም ሆይ ለዘላለም የሚኖር የአብን ልጅ ቃልን
የወለድሽልን መጥቶም ከሀጥያት አዳነን ደስ የተሰኘህ ሆነህ
ምስራችን ይተናገርክ መልአኩ ገብርኤል ሆይ የተሰጠህ ክብር
ታላቅ ንው ወደኛ ይመጣን የጌታን ልደት ንገርከን ልድንግል
ፀጋን የተመላሽ ሆይ እግዚእብሄር ካንቺ ጋርነውና ደስ ይበልሽ
ብለህ አበሰርካት ቅድስት ሆይ ለምኝልኝ
፭ፀጋን አገኘሽመንፈስ ቀዱስ አደረብሽ የልዑል ህይልም ጋረደሽ
(ፀለለብሽ) ማርያም ሆይ በዕውነት ቅዱሱን ወለድሽ ዐለምን
ሁሉ የሚያድን መጥቶአዳነን ቅድስት ሆይ ለምኝልን
፮አንደበታችን የድንግልን ስራ ያመሰግናል ጌታችንና
ምድሃኒታችን ኢይሱስ ክርስቶስ በዳዊት አገር ከእርስዋ
ስለተወለደ አምላክን የወለድች ማርያምን ዛሬ እናመስግናት
አሕዛብ ኑ ማርያምን እናመስግናት እናት እና ድንግል ሁለቱንም
ሁናልችና ርኩሰት የሌሌብሽ እና የአብ ቃል መጥቶ ካንቺ ሰው
ሆነ ንፅሕት ድንግል ሆይ ደስ ይብልሽ ነውር የሌለብሽ
ፍፅመትና ጉድፍ የሌለብሽ ሙዳይ ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ስለቀደመ
ሰው ሰው አዳም ሁለተኛ አዳም የሆነ የክርስቶስ ማደርያው
የምትናገሪ ገነት ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ከአባቱ ያልተለየ አንድ እሱን
የተሸከምሽ ሆይ ደስ ይበልሽ በክብር ጌጥ ሁሉ ያጌጠ እርሱ
መጥቶ ሰው የሆነብሽ ንፅሕት የሰርግ ቤት ሆይ ደስ ይበልሽ
እሳት ባህሪ ያላቃጠለሽ ዕፀ ጳጦስ ደስ ይበልሽ በኪሩቤል ላይ
የሚቀምጥዉ ሰማያዊ መልኮት በስጋ የተሽከምሽ ገረድ እና
እናት ድንግል እና ሰማይ ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ስለዚህ ንፁሀን
ከሆነ መላዕክት ጋር ብፍፁም ደስታ ደስ ተሰኝተን እናመስግን
በሰማይ ለእግዚእብሄር ምስጋና ይሁንብምድርም ዕርቅ ይሁን
እንበልክብርና ምስጋና ጌትንት ያለው እርሱ አንቺን ወድዋልና
ደስ ይበልሽ፡፡
፯ከቅዱሳን ክብር የማርያም ክብር ይበልጣል፣የአብን ቃል
ለመቀበል በተገባ ተገኝታለች እና፡፡መላዕክት የሚፈሩትን
ትጉሆች በሰማይ የሚያምሰግኑትን ድንግል ማርያም
በማህፀንዋ ተሸከመችው ፣ይህቺ ከኪሩቤል ትበልጣልች፤
ክሶስቱ አካል ለአንዱ ማድሪያ ሁናልችና፡፡የንቢያት ሀገራቸው
እየሩሳሌም ይህቺ ናት ፡፡ ለቅዱሳን ሁሉ የደስታቸው ማድርያ
ናት በጨለማ ና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ
ብርሀን ወጣላቸው፡፡ በቅዱሳን ላይ የሚያድር እግጻብሄር እኛን
ለማዳን ልዩከሆነች ድንግል ሰው ሆኗልና ኑ ይህን ድንቅ እዩ፡፡
ስለተግለጠልን ሚስጥር ምስጋና አቅርቡ፤ሰው የእምይሆን
ሰውሁኗልና፤ቃልተዋህዷልና ፤ጥንት የሌለው ስጋ ጥንታዊ
ቀዳማዊሆነ፡፡ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን
ተቆጠረለት፡፡የማይታወቅ ተገለጥ፤ የማይታይ ታየ፤የህያው
የእግዚአብሄር ልጅ በእርግጥ ሰው ሆነ፡፡ትላንት የነበረው፣
ዛሬም ያለው ፣መቼምየሚኖረው ኢየሱስ ክርስቶስ
አንሰግድለትና እናመስግነው ዘንድ አንድ ባህሪ ነው ቅድስት ሆይ
ለምኝልን፡፡
፰ ነብዩ ሕዝቀኤል ስለእርስዋ መስከረ፤ድንቅ በሆነ ታላቅ
ቁልፍ የተዘጋች ደጅ በምስራቅአየሁ አለ ከሀያላን ጌታ
በቀርውድ እርስዋ ገብቶ የወጣ የለምቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡
፱ኖሕትም ደጅም መድሀኒታችን የወለደች ደንግል ናት፡፡ እርሱን
ከወለደች በሃላ እንድ ቀድሞው ብድንግልና ኖራልችና፡፡ መጥቶ
ምህረት ከሌለው ጠላት እጅ ያዳነንጌታን የወለድሽ ሆይ ፤
የማህፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው አንቺ ፍፅመትና የተባረከሽ ነሽ
የዕወነት አምላክ በሆነ በክብር ባለቤት ዘንድ ባለሟልነትን
አግኝተሻልና በምድር ላይ ከሚኖር ሁሉ ይልቅ ገናንነትና ክብር
ላንቺ ይገባል፡፡ የአብ ቃል መጥቶ በአንቺ ሰው ሆነ፡፡ከሰውም
ጋር ተመላለሰ፡፡መሀሪ ይቅር ባይ ሰዉን ወዳጅ ነዉና በልዩ
አመጣጡ አዳነን ቅድስት ሆይ ልምኝልን፡፡
(ሼር በማድረግ ያካፍሉ)

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: መጋቢት 27

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: መጋቢት 27: አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን መጋቢት 27 ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ቸሩ አምላካችን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ያደረገው ድንቅ ተአምር ይህ ነው፡- በዚህች ዕለት ጌታችን በእ...

Monday, April 4, 2016

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: መጋቢት 27

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
አሜን
መጋቢት 27
ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ቸሩ አምላካችን
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ያደረገው ድንቅ ተአምር ይህ ነው፡-
በዚህች ዕለት ጌታችን በእስክንድርያ ባደረገው ታላቅ ተአምር
ብዙ አይሁድ በስሙ አምነው በአባ ቴዎፍሎስ እጅ
ተጠምቀዋል፡፡ ይኸውም እንዲህ ነው፡- በእስክንድርያ አገር
ስሙ ፈለስኪኖስ የሚባል አይሁዳዊ ባለጸጋ ሰው ነበር፡፡
እርሱም እንደ አባቶቹ የኦሪትን ሕግ ብቻ የሚጠብቅ ሰው
ነው፡፡ እንዲሁም ድሀ የሆኑ ሁለት ክርስቲኖች ነበሩ፡፡
በአንደኛው ላይ ሰይጣን የስድብ መንፈስ አሳድሮበት ጓደኛውን
‹‹ወንድሜ ሆይ ክርስቶስን ለምን እናመልከዋለን? እኛ ድኆች
ነን፡፡ ይህ ክርስቶስን የማያመልክ አይሁዳዊ ፈለስኪኖስ ግን
እጅግ ባለጸጋ ነው›› አለው፡፡ ጓደኛውም ‹‹ዕወቅ አስተውል፣
የዚህ ዓለም ገንዘብ ከእግዚአብሔር የሆነ አይደለም፤ ምንም
አይጠቅምም፡፡ ጥቅም ቢኖረው ጣዖትን ለሚያመልኩ፣
ለአምነዝራዎች፣ ለነፍሰ ገዳዮችና ለአመፀኞች ሁላ
ባልሰጣቸውም ነበር፡፡ አስተውም ነቢያትም ሆኑ ሐዋርያት
ድኆች ነበሩ ነገር ግን ጌታችን ‹ወንድሞቼ› ይላቸው እንደነበር
አስተውል…›› እያለ መከረው፡፡ ነገር ግን ጓደኛውን ሰይጣን
አድሮበታልና ምክሩን ሊሰማው አልቻለም፡፡
ከዚህም በኋላ ይህ ክፉ ሰው ወደ ባለጸጋው አይሁዳዊ ወደ
ፈለስኪኖስ ዘንድ ሄዶ ‹‹አንተን እንዳገለግል ተቀበለኝ›› አለው፡፡
ባለጸጋውም አይሁዳዊ ‹‹በሃይማኖቴ የማታምን አንተ
ልታገለግለኝ አይገባህም›› አለው፡፡ ዳግመኛም ያ ጎስቃቋላ
‹‹ተቀበለኝ እንጂ ወደ ሃይማኖትህ እገባለሁ፣ ያዘዝከኝንም ሁሉ
እፈጽማለሁ›› አለው፡፡ አይሄዳዊውም ‹‹ቆየኝ ከመምሀሬ ጋር
ልማከር›› አለው፡፡ መምህሩም ‹‹ክርስቶስን የሚክድ ከሆነ
ግረዘውና ተቀበለው›› አለው፡፡ አይዳዊውም ተመልሶ መጥቶ
መምህሩ እንደነገረው አድርጎ ተቀበለው፡፡ ከዚህመ በኋላ ወደ
ምኩራባቸው ወሰደው፡፡ የምኩራባቸውም አለቃ ‹‹ክርስቶስን
ክደህ አይሁዳዊ ትሆናለህን?›› አለው፡፡ እርሱም ‹‹አዎን
እክደዋለሁ›› አለው፡፡ የምኩራባቸውም አለቃ መስቀል
ሰርተው በላዩ የክርስቶስን ሥዕል እንዲያደርጉ መጻጻንም
የተመላች ሰፍነግ በዘንግ ላይ አሥረው ከጦር ጋር እንዲሰጡት
አዘዘ፡፡ ከዚያም ‹‹ከተሰቀለው ሥዕል ላይ ምራቅህን ትፋ፣
መጻጻውንም ወደ አፉ አቅርብለት፣ ክርስቶስ ሆይ ወጋሁህ
እያልክ በጦሩ ውጋው›› አሉት፡፡ እርሱም እንዳዘዙት አድርጎ
ሥዕሉን በጦር ወጋው፡፡ ወዲያውም የዕውነት ሆኖ በተደጋጋሚ
ውኃና ደም ከሥዕሉ ፈሰሰ፡፡ ለረጅም ጊዜም በድምድር ላይ
እየፈሰሰ ታየ፡፡ በዚያም ጊዜ ያ ከሃዲ ደርቆ እንደ ድንጋይ ሆነ፡፡
በአይድም ላይ ሁሉ ታላቅ ፍርሃት ወደቀባቸው፡፡ ‹‹እውነትም
የአብርሃም ፈጣሪ ስለእኛ ተሰቅሏል፤ እኛም ዓለምን ለማዳን
የመጣ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እርሱ እንደሆነ
አመንበት›› እያሉ ጮኹ፡፡
ከዚህም በኋለ አለቃቸው ከዚያ ከደሙ ወስዶ የአንዱን ዐይነ
ሥውር ዐይኖቹን አስነካው፡፡ ወዲያውም ዐይነ ሥውሩ ማየት
ቻለና ሁሉም አመኑ፡፡ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ቴዎፍሎስ ሄደው
የሆነውን ሁሉ ነገሩት፡፡ አቡነ ቴዎፍሎስም ከካህናቱ ሁሉ ጋር
ወደ አይሁድ ምኩራብ ሄዶ ውኃና ደም ከእርሱ ሲፈስ መስቀሉን
አገኘው፡፡ ከደሙም ወስዶ የራሱንና በዚያ ያሉትንም ሁሉ
ግንባራቸውን በመቀባት በረከትን ተቀበሉ፡፡ መስቀሉንም
በክብር ቀስደው በቤተ ክርስያን ውስጥ አስቀመጡት፡፡ ደሙ
የፈሰሰበትንም ምድር አፈሩን አስጠርጎ ለበረከትና ለሕሙማን
ፈውስ ሊሆን በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኖረው፡፡ ከዚህም በኋላ
አይዳዊው ፈለስኪኖስ ከነቤተሰቡ አቡነ ቴዎፍሎስን ተከተለው፡፡
ከአይሁድም ብዙዎቹ የቀደሙ አባቶቻቸው በሰቀሉት የክብር
ባለቤት በሆነ በመድኃኔዓለም ክርስቶስ አመኑ፡፡ አቡነ
ቴዎፍሎስም በስመ ሥላሴ አጥምቆ ሥጋ ወደሙን
አቀበላቸው፡፡ እነርሱም ጌታችንን እያመሰገኑና ክብሩን
እየመሰከሩ ኖሩ፡፡
/////////////// /////////////
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ኢትዮጵያዊው ሰማዕት ቅዱስ
ገላውዲዮስ ዐረፈ፡፡ ይኽም ቅዱስ አባቱ ልብነ ድንግል
ሃይማኖቱ የቀና ነበርና ልጁን ገላውዲዮስንም በሃይማኖት አንጾ
አሳደገው፡፡ በዘመኑም አህመድ ግራኝ ተነሥቶ አብያተ
ክርስቲያናትን አቃጠለ፣ ክርስቲያኖችን ፈጀ፡፡ ንጉሡ ልብነ
ድብግልም ሠራዊቱን እስኪያሰባስብ ድረስ ከእርሱ ሸሸ፡፡
በስደትም ላይ እንዳለ ድንገት ታሞ ሞተ፡፡ ግራኝም አብያተ
ክርስቲያናትን እያቃጠለና ክርስቲያኖችን እየፈጀ 15 ዓመት
ኖረ፡፡ ብዙዎችንም በኃይል አሰለማቸው፡፡ ‹‹የሚቃወመኝና
የሚችለኝ የለም›› እያለ ሲታበይ ቅዱስ ገላውዲዮስ ተነሣና
በየቦታው ያሉ የግራኝን መኳንንቶች አሸነፋቸው፡፡ ግራኝም
ይህን ሲሰማ ተቆጣና ከቱርክ አርበኞች ጋር ሆኖ ገላውዲዮስን
ገጠመው፡፡ ገላውዲዮስም ግራኝን ገደለው፡፡ አብያተ
ክርስቲያናትም መልሰው ታነጹ፣ የቀናች ሃይማኖትም
ተመለሰች፡፡
ቅዱስ ገላውዲዮስም በመጋቢት 27 ቀን የጌታችንን የስቅለቱን
በዓል እያከበረ እያለ የሙስሊሞች ወገን የሆኑ ብዙ ጭፍሮች
ድንገት ደርሰው ከበቡት፡፡ ከእርሱ ጋር የነበሩት ጥቂት ሰዎችም
ገላውዲዮስን ‹‹የጦር መኰንኖቻችን እስከሰበሰቡ ድረስ ፈቀቅ
እንበል›› ቢሉት ሰማዕትነቱን ተመኝቶት ነበርና እምቢ
አላቸው፡፡ እስላሞቹም በአንድነት ከበው በጦር ወግተው
ገደሉት፣ አንገቱንም ቆረጡትና የሰማዕትነትን አክሊል
ተቀዳጀ፡፡ ዳግመኛም በዚህች ዕለት ታላቁ አባት አባ መቃርስ
ዕረፍታቸው ነው፡፡ በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው
ይማረን፡፡
የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን በሠሩልን ሥርዓት መሠረት
የመጋቢት 27 የመድኃኔዓለም ክርስቶስ የስቅለቱን በዓል ወደ
ጥቅምት 27 ቀን መጥቶ እንዲከበር አባቶቻችን ወስነዋል፡፡
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ያበሠራትና
የጌታችንም ፅንሰት የተከናወነው በመጋቢት ወር በ29ኛው ቀን
በዕለተ እሁድ በ3 ሰዓት ነው፣ ነገር ግን ብሥራቱና ፅንሰቱ ግን
ታኅሣሥ 22 ቀን እንዲከበር ቅዱሳን አባቶች እነ ቅዱስ
ደቅስዮስ ወሰኑ፡፡ እነርሱም በዓሉን በዚሁ ዕለት
አክብረውታል፡፡ አንድም ነገረ ልደቱን ከማክበር አስቀድሞ
ነገረ ፅንሰቱን ማዘከር ማክበር ተገቢ ስለሆነ ነው፡፡ በዓቢይ
ጾም ወቅት ደግሞ ፍጹም ሐዘን ልቅሶ ጾም ጸሎት ይያዛል
እንጂ ደስታ ፌሽታ እልልታ ጭብጨባ የለም፡፡ ዓቢይ ጾም
ፍጹም የሐዘን ወራት ነው፡፡ ታቦት አውጥቶ በዓል ማክበር
ስህተት ነው፤ የአባቶችንም ሥርዓት ማፍረስ ነው፡፡ ምስጋና
ይድርሳቸውና ቅዱሳን አባቶቻችን ሁሉንም ነገር በሥርዓት
በሥርዓቱ አድርገው ሰፍረው ቆጥረው አስቀምጠውልናል፡፡
ከዓቢይ ጾም በኋላ ያሉትን 50 ቀናት ረቡዕና ዓርብንም
ጭምር ሥጋ እንኳን እንድንበላ ነው ሥርዓት የሠሩልን፡፡
አባቶቻችን የሠሯት ሕግ ፍጽምት ናት፡፡ በዚህም መሠረት
አባቶቻችን ሥርዓትን ሠሩልንና የመጋቢት 27 የጌታችንን
የስቅለቱን በዓል ወደ ጥቅምት 27 ቀን አምጥተው እንዲሁም
የመጋቢት 5 የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን የዕረፍት በዓል ወደ
ጥቅምት 5 ቀን አዙረው እንዲከበር አድርገዋል፡፡
በዚህ ታላቅ የዐቢይ ጾም ወቅት ለጾም፣ ጸሎት፣ ስግደታችን
ብዙ ጊዜ የምንሰጥበት ተጋድሎአችንን በእጅጉ በመጨመር
ከአምላካችን ሞት ጋር የምትተባበርበት ወቅት ነው፡፡
አባቶቻችን እንዳሉት ጌታችንን ‹‹ከእኛ ጋራ መከራን
ስለተቀበልክ እኛም ከአንተ ጋራ መከራን እንቀበላለን፡፡
በመስቀል ላይ የተቀበልከው የመከራህ ተሳታፊዎች
አድርገኸናልና በመከራ ስለመሰልንህ እንደዚሁ በጌትነትህ
በምትመጣበት ጊዜ በዕለተ ምጽዓት ከአገልጋዮችህ ከወዳጆችህ
ቅዱሳን ጋራ ክብርን አድለን›› እያልን ጾም ጸሎት ስግደት
ምጽዋት ተጋድሎአችን በመጨመር በእጅጉ የምንተጋበት
ወቅት ነው፡፡ ሞቱን በሚመስል ሞት ከመድኃኔዓለም ክርስቶስ
ጋር ተባብረን በኋላም ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ
ጋር ለመተባበር ዝግጁ የምንሆነበት ታላቅ ወቅት ነው፡፡ ሮሜ
6፡5፡፡ ስለዚህ እኔም ገድለ ቅዱሳኑንና ስንክሳሩን ሳላቋርጥ
በየቀኑ መጻፌን የምቀጥለው ዐቢይ ጾሙ እንዳለቀ ነው፡፡
አምላከ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ክርስቶስ መዋዕለ ጾሙን
በሰላም ያስፈጽመን!!!
እጅግ የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን እነ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ፣ እነ
አቡነ መብዓ ጽዮን ራሱ ጌታችን እንደነገራቸውና እነርሱም
ሲያደርጉት የነበረውን ነገር እንደነገሩን ‹‹የመድኃኔዓለምን
የሞቱን መታሰቢያ ያደረገ የተኮነኑ ነፍሳትን ከደይን ያወጣል፣
በሞቱም ጊዜ ሥቃይን አያያትም፡፡›› ስለዚህም የጥምቀት
ወገኖች የሆንን የተዋሕዶ ልጆች ሁላችን የመድኃኒታችንን
ሞቱን በአንክሮ እናዘክር ዘንድ የልቡናችን ዐይን ወደ ቀራንዮ
አደባባይ ይመልከት፡፡
እነሆ ክፉዎች አይሁድ ሰይጣን ልባቸውን አስቶታልና እንደ
ወረንጦና እንደ ወስፌ እንደመርፌም ያለ 300 እሾህ ያለው
ስረወጽ አድርገው አክሊል ሠርተው ከፍላት አግብተው በጉጠት
አንስተው ‹ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ነህ ዘውድ ይገባሃል› ብለው
በራሱ ላይ ደፉበት፡፡ ለአክሊለ ሦኩም 73 ስቁረት ነበረው፡፡
እራሳቸው እንደ መሮ፣ ወርዳቸው እንደ ሞረድ 4 ማዕዘን
አሠርተው ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸውን እንደ
ወስፌ አድርገው 73 ችንካር ሠርተው በ73ቱ ስቁረት
አግብተው በጌታችን በራሱ ላይ ቢመቱበት ሥጋ ለሥጋ ገብቶ
መሐል ልቡን ወጋው፡፡ አክሊለ ሦኩን በራሱ ላይ አድርገው
ሲያበቁ ከቤት ወደ አደባባይ እያመላለሱ ‹‹ንጉሥ ሆይ!...››
እያሉ ምራቃቸውን እየተፉበት ተዘባበቱበት፡፡ መስቀል
አሸክመው ከሊቶስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ እያዳፉ ሲወስዱት
136 ጊዜ በምድር ላይ ጣሉት፡፡ ከኋላ ያሉት ‹‹ፍጠን›› እያሉ
ገፍትረው ይጥሉታል፣ ከፊት ያሉት ደግሞ ‹‹ምን
ያስቸኩልሃል?›› እያሉ መልሰው ገፍትረው ይጥሉታል፡፡ ከዚህ
በኋላ ክፉዎች አይሁድ ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር ስለታቸው
ደግሞ እንደ ወስፌ የሆኑ 5 ችንካሮችን ሠርተው ሳዶር
በሚባለው ችንካር ቀኝ እጁን፣ በአላዶር ግራ እጁን፣ በዳናት
ሁለት እግሮቹን፣ በአዴራ መሐል ልቡንና በሮዳስ ደረቱን
ቸንክረው የአዳም ራስ ቅል ባለበት ቀራኒዮ አደባባይ ላይ
ሰቅለውታል፡፡
ክፉዎች አይሁድ መድኃኔዓለም ክርስቶስን እንደያዙት የኋሊት
አስረው አፍንጫውን 25 ጊዜ ቢመቱት ደሙ በመሬት ላይ
እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ ከጌቴሴማኒ እስከ ሐና ቤት ድረስ አስረው
የፊተኞቹ ሲጎትቱት የኋለኞቹ እየለቀቁት የኋለኞቹም በተራቸው
ሲጎትቱት የፊተኞቹ ይለቁታል፡፤ እንዲህ እያደረጉ 65 ጊዜ
ከመሬት ጋር አጋጭተውታል፡፡ ሳውል በእግሩ ሲረግጠው
ጌታችን ‹‹መመለስህ ላይቀር ለምን ትረግጠኛለህ?›› ቢለው
ስለዚህ ንግግርህ ብሎ ሳውል 440 ጊዜ አስገረፈው፡፡
ክፉዎች አይሁድ መድኃኒታችንን በሁለት ግንዶች መካከል
አድርገው 65 ጊዜ ከግንዱ ጋር አጋጩት፡፡ ቀያፋ
በሚመረምረው ጊዜ ጌታችን ‹‹አምላነቴን አንተው ራስህ
ተናገርኽ›› ቢለው አይሁድ በእጃቸው ሲመቱት እጃቸውን
ቢያማቸው ድንጋይ ጨብጠው 120 ጊዜ ፊቱን ጸፉት፡፡ አይሁድ
ወደ ጲላጦስ ዘንድ ሲወስዱት ‹‹ምናልባት ጲላጦስ ባይፈርድበት
እንኳ እንዳይቆጨን›› ብለው 305 ጊዜ በሽመል
ደብድበውታል፡፡ በአምላክነቱ ቻለው እንጂ የአንዱ ምት ብቻ
በገደለው ነበር፡፡ በርባን የይሁዳ የሚስቱ ወንድም (አማቹ)
ስለነበር እርሱ እንደፊታለትም ከዋጋው ከ30ው ብር ጋር አብሮ
ተደራድሮበት ነበር፡፡
ሰይጣን ልባቸውን ለክፋት ያስጨከናቸው ክፉዎች አይሁድ
በጲላጦስ አደባባይ የጌታችንን ፂሙን 80 ጊዜ ነጭተውታል፡፡
ጲላጦስ እንደ ሕጋቸው 41 ብቻ ገርፈው እንዲለቁት ቢያዝም
ክፉዎች አይሁድ ግን ጌታችንን ሲገርፉት ‹‹አሠቃቂ ግርፋቱን
አይተን ልባችን እንዳይራራ›› ብለው ሰንጠረዥ ገበጣ ሰርተው
ሲጫወቱ አንዱ ተነስቶ እስከ 60 እና 70 ድረስ ይገርፍና
ሲደክመው ‹‹ቆጠራችሁን?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡
‹‹አልቆጠርንም›› ሲሉት ከድካሙ የተነሣ ‹‹እኔው ልግረፍ
እንደገና እኔው ልቁጠር›› ብሎ ትቶት ሲቀመጥ ሌላኛው
ይነሣና እንደዛኛው ሁሉ በተራው 60 እና 70 ይገርፈዋል፡፡
ሁሉም እንዲህ እያሳሳቱ የራሳቸውን ሕግ እየተላለፉ አይሁድ
ጌታችንን ሥጋው አልቆ አጥንቱ እንደበረዶ ነጭ ሆኖ እስኪታይ
ድረስ 6666 ጊዜ ጽኑ ግርፋትን ገረፉት፡፡ በእነዚህ ሁሉ ግርፋቱ
ወቅት 366 ጊዜ ሥጋው ተቆርሶ መሬት ላይ ወድቋል፡፡
የመድኃኔዓለም ወገኖች ሆይ! የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ መሆኑንና
የትዕግሥቱን ብዛት አይተን እናደንቅ ዘንድ ከመጻሕፍት ጠቅሰን
እንነግራችኋለን፡፡ አይሁድ ጌታችን አብርሃም ሳይወለድ በፊት
እርሱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ
ጋር በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን አምላክ መሆኑን
ቢነግራቸው ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፡፡ እሱ ግን ጊዜው ገና
ነበርና ተሰውሮአቸው በመካከላቸው አልፎ ሲሄድ በፍጹም
አላዩትም ነበር፡፡ በቅዱስ ወንጌል ላይ እንዲህ ተብሎ
እንደተጻፈ፡- ‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት
አደረገ፥ አየም ደስም አለው። አይሁድም:- ገና አምሳ ዓመት
ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ኢየሱስም:- እውነት
እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው።
ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው
ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ፡፡›› ዮሐ 8፡
56-59፡፡
ዳግመኛም በዮሐንስ ወንጌል ላይ እንደተጻፈው አይሁድ
መድኃኔዓለምን ሊይዙት የጦር መሣሪያቸውን ሰብስበው ወደ
ጌቴሴማኒ በመጡ ጊዜ ‹‹ማንን ትፈለጋላችሁ?›› ቢላቸው
‹‹የናዝሬቱን ኢየሱስን እንፈልጋለን›› ሲሉት ‹‹እኔ ነኝ››
ቢላቸው ከአንደበቱ የወጣውን መለኮታዊ ቃል ብቻ መቋቋም
አቅቷቸው መሬት ላይ ወድቀው ተዘርረዋል፡፡ ይህም ክስተት
በተደጋጋሚ ተከስቷል፡፡ (ዮሐንስ ወንጌል ላይ ምዕራፍ 18
ከቁጥር አንድ ጀምሮ ይመለከቷል፡፡) እናም የጌታችን ሞቱ
በፍጹም ፈቃዱ ባይሆን ኖሮ በጌቴሴማኒ ሊይዙት የመጡት
ክፉዎች አይሁድን እንደመጀመሪያው ሁሉ በተሠወራቸው ነበር
አሊያም ከአንደበቱ በሚወጣው አምላካዊ ቃሉ ብቻ ባጠፋቸው
ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን ጌታችን ወደዚህች ምድር የመጣበትን
ዓላማ ይፈጽም ዘንድ እንዲገድሉት በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ
ቢሰጣቸው ያን ሁሉ እጅግ አሠቃቂ መከራ አደረሱበትና
ለመስቀል ሞት አበቁት፡፡
ወዮ ለዚህ ለመድኃኒዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል!
ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደሌባ ተያዘ፡፡
ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት
መድኃኔዓለም እርሱ ሊፈረድበት በፍርድ አደባባይ ቆመ፡፡
በእስራት ያሉትን የሚፈታ እርሱ በብረት ችንካር ተቸነከረ፡፡
ሰማይን በከዋክብት ምድርም በአበባ ያስጌጠ እርሱ ግን የእሾህ
አክሊል በራሱ ላይ ደፋ፡፡
ዓለሙን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብ እርሱ ተጠማሁ አለ፡፡
ወዮ የመድኃኔዓለም የማዳኑ ምሥጢር ምንኛ ድንቅ ነው!!!
ለዚህ ባሕርይው አንክሮ ይገባል፡፡
በመድኃኔዓለም ክርስቶስ ሞት በአንድነት እናለቅስ ዘንድ
ቅዱሳን ሁላችሁ ኑ! መድኃኒታችን ሙቷልና ፍጥረታት ሁሉ
ያለቅሳሉ፤ መያዝንና መታሠርን የተቀበለ መድኃኒታችን
ሙቷልና፡፡ ጥፊንና ግርፋትን የተቀበለ መድኃኒታችን ሞተ፡፡
መደብደብንና መመታትን የታገሰ መድኃኒታችን ሞተ፡፡ ሄኖክ
እግዚአብሔር ‹‹በሴም ቤት ይደር›› ብሎ አብ ስለራሱ
የተናገረለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ አብርሃም
ቃልኪዳን የገባልህን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡
ይስሐቅ ከሰይፍ ቤዛ የሆነህን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ
ዘንድ ና፡፡ ያዕቆብ በበረሃ የታገለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ
ዘንድ ና፡፡ ኢዮብ በደመና የታየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ
ዘንድ ና፡፡ ሙሴ ስለ እርሱ ‹እንደእኔ ያለ ነቢይ ይነሣል› ብለህ
የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳዊት
‹‹እነሆ በኤፍራታ ሰማነው፣ በበረሃ ዛፍም አገኘነው›› ብለህ
የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤርሚያስ
‹‹የክቡሩን ዋጋ ሠላሳ ብር ተቀበሉ›› ብለህ የተናገርኽለት
የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡
ኢሳይያስ ‹‹ወልድ ሰው ለመሆን ተገለጠልን፣ ሕፃን ተወለደልን፣
ድንቅ መካር ኃያል አምላክ›› ብለህ የተናገርኽለት
የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅኤል ‹‹አምላክ
ወደ ተዘጋች ደጃፍ ገባ፣ ከተዘጋች በርም ወጣ›› ብለህ
የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳንኤል ነጭ ሐር ለብሶ
ያየኸውን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤልያስ ከሞት
በፊት የሰወረህ በእሳት ፈረሶች ያሳረገህ የመድኃኒታችንን ሞቱን
ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅያስ የፀሐይ መግባቱን ያሳየህ
የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ምናሴ ችንካሮችህን
ከእግር ብረት የፈታ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡
ኢዮስያስ ፋሲካውን ያደረግህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ
ና፡፡ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል ከእሳት ምድጃ ያዳናች
የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ አብያና ሲላ ፌንቶስ
ከመወለዱ አስቀድሞ ያመናችሁበት የመድኃኒታችንን ሞቱን
ታይ ዘንድ ኑ፡፡ የቀድሞ አባቶች ነቢያት ሁላችሁ ከፋራን ተራራና
ከቴማን ይመጣል ያላችሁት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ
ኑ፡፡ አሞፅ በአድማስ ቅጥር ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን
ታይ ዘንድ ና፡፡ ዘካርያስ በተራራዎች መካከል ያየኸው
የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዕዝራ በአርፋድ በረሃ
ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡
ስምዖን በክንድህ የታቀፍከውን ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን
ታይ ዘንድ ና፡፡ ዮሴፍ እንደ አንተ የተሸጠ የመድኃኒታችንን
ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ጠራቢ ዮሴፍ በትከሻህ ያዘልከው በክንድህ
የተሸከምከው ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡
መጥምቁ ዮሐንስ ከሕፃንነትህ ጀምሮ በበረሃ ያለ እናት ያለ
አባት ያሳደገህ መንገዱንም እንድትጠርግለት ያዘጋጀህና
መለኮትን እንድታጠምቅ የመረጠህ የመድኃኒታችንን ሞቱን
ታይ ዘንድ ና፡፡
ኢያቄምና ሐና ሆይ የልጃችሁን ልቅሶዋን የልቧንም መዘንጋት
ታዩ ዘንድ ኑ፡፡ ከሔዋን እስከ ፋኑኤል ልጅ እስከ ሐና ያላችሁ
ሁላችሁ ቅዱሳት ሴቶች የድንግልን ልቅሶዋን ታዩ ዘንድ ኑ፣
አንድ ልጇ ሙቷልና፡፡ የለመለመ የሥጋ ሞት ሕንፃ
የተጀመረበት የአቤል ተከታዩ፣ ከጎኑ የፈሰሰው ደም ሔዋንን
ከጥፋት ያዳናት የተገደለ መድኃኒታችን ነው፡፡ የናቡቴ ጓደኛው
የተገፋው መድኃኒታችን ነው፡፡ አቤል ስለሚስቱ ሞተ፡፡ ናቡቴም
ስለ ወይኑ ቦታ ሞተ፡፡ መድኃኒታችን ግን በቀኙ ያነጻት ዘንድ
ስለቤተክርስቲያን ሞተ፡፡ ነፍሳችሁን ይወስዷታልና
መውረዱንም አላወቁምና ስለ ወገኖቹ ኃጢአት እስከ ሞት
ደረሰ ብሎ ስለ እርሱ የተናገረ አባቱን እንስማው፡፡ ሙሴም
እርሱን ያውቁት ዘንድ አላሰቡትም፣ በሚመጣበት ቀንም
አላወቁትም አለ፡፡ ዕዝራ በባሕር ጥልቅ ያለውን ማወቅ
እንዳይችሉ ወልድንም ማወቅ እንዲሁ ሆነባቸው አለ፡፡
ጳውሎስም ብታውቁትስ ኖሮ የክብርን ጌታ እግዚአብሔርን
ባልሰቀላችሁት ነበር አለ፡፡
በመሰደድ፣ ያለምንም በደልም በፍርድ አደባባይ በመቆም
መከራ መስቀልን በመሸከም አብነት የሆናችሁ ሰማዕታት
ሁላችሁ ኑ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት አስባችሁ በጋራ
አልቅሱለት፡፡ ሁሉ የእርሱ ከእርሱ ለእርሱ ተፈጥሮ ሳለ በምድር
ላይ ምንም ሳይኖረው ራሱን እንኳን የሚያስጠጋበት ቤት
ሳይኖረው አብነት የሆናችሁ ባሕታውያንና መነኮሳት ሁላችሁ ኑ
በዛሬዋ ዕለት ስለሞተው አምላካችሁ መሪር ዕንባን
አልቅሱለት፡፡ ሕግ ጠብቆ፣ ሥርዓት አክብሮ፣ ነዳያንን
በመመገብና ያዘኑትን በማጽናናት 33 ዓመት በምድር ላይ ኖሮ
አብነት የሆናችሁ እናንት በዓለም ሆናችሁ ሕግ ጠብቃችሁ፣
አሥራት በኩራቱን አውጥታችሁ፣ ድሆችን በመርዳት የምትኖሩ
ክርስቲያኖች ሁላችሁ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት ታስቡ ኑ፡፡
‹‹የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን
እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን
ተቀብሎአልና›› ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደጻፈልን (1ኛ ጴጥ
2፡21) እርሱ ንጹሕ ባሕርይ ሲሆን ወደ መጥምቁ ቅዱስ
ዮሐንስ ዘንድ ወደ ዮርዳኖስ በመሄድ ለተጠመቅን ለእኛ
ለተነሣሕያን ለሁላችን አብነት የሆነን መድኃኒታችን ስለእኛ
ሞቷልና ሞቱን እናስብ ዘንድ ኑ በቤቱ ተሰብስበን
እናልቅስለት፡፡ መታሰያውንም እናድርግለት፡፡ ጌታችን ሞቶ
ተቀብሮ ካረገ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳን አባቶቻችን
ለእነ አቡነ መባዓ ጽዮን፣ ለእነ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ እንደነገራቸው
የሞቱን መታሰቢያ የሚያደርግ ኃጠአተኛ እንኳ ቢሆን ሲኦልን
አያያትም፡፡ የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ የሚያድርግ
ቢኖር ሲኦል ራሷ አፍ አውጥታ ‹‹ይህችን ነፍስ ወደኔ
አታምጡብኝ›› ብላ ትጮሃለች እንጂ ችላ አትቀበለውም፡፡
የጌታችን ወዳጆቹ ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በድርብ በፍታና በመቶ
ወቄት ሽቱ ገንዘው በሐዲስ መቃብር ሊቀብሩት ቢሉ ጌታችን
ያን ጊዜ ዐይኑን ክፍቶ ‹‹በሰውነቴ መዋቲ ብሆን በመለኮቴ
ሕያው ነኝ እንጂ ምነው እንደ እሩቅ ብእሲ ዝም ብላችሁ
ትገንዙኛላችሁን?›› አላቸው፡፡ ይህን ጊዜም ዮሴፍ ኒቆዲሞስ
በታላቅ ድንዳጤ ሆነው ‹‹አቤቱ ጌታችን ሆይ! እንግዲያስ ምን
እያልን እንገንዝህ?›› አሉት፡፡ መድኃኒታችንም እንዲህ እያላችሁ
ገንዙኝ አላቸው፡- ‹‹ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ
ሕያው ዘኢይመውት ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል
ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ
ሕያው ዘኢይመውት ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ
መስቀል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል
ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት
ዕለት ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ
ዳግመ ይመጽእ በስብሐት ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ ተሣሃለነ
እግዚኦ› እያላችሁ ገንዛችሁ ቅበሩኝ አላቸው፡፡›› ከዚህም በኋላ
መድኃኒታችን ለወዳጆቹ ለ12ቱ ሐዋርያት፣ ለ72ቱ አርድእት፣
ለ36ቱ ቅዱሳት አንስት ‹‹እስከ ሦስት ቀን እነሣላችኋለሁ እዘኑ
አልቅሱ፣ እህል ውኃ አትቅመሱ በሏቸው›› ብሎ ለዮሴፍና
ለኒቆዲሞስ አክፍሎት አስተማራቸው፡፡
ዳግመኛም መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከዕርገቱ በኋላ ለቅዱሳን
ሐዋርያት የሞቱን መታሰቢያ እንዲያደርጉ ነግሯቸዋልና፡፡
ሕማሙንና ሞቱንም እንዲዘክሩ አዟቸዋልና አሁንም ያንን
ሁሉ የመድኃኔዓለምን ሞቱን ያላሰበና የሞቱን መታሰቢያ በዓል
ያላከበረና እርሱንም የማይወደው ቢኖር ዕድል ፈንታው ጽዋ
ተርታው ከአይሁድ ጋር ነው፡፡
የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ አድርገን ሞቱን
በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ተባብረን ትንሣኤውን በሚመስል
ትንሣኤ ከእርሱ ለመተባበር ያብቃን፡፡
ሰኞ የሚፀለይ አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ምስጋና
ጌታ በልቡ ያዘነና የተከዘ አዳምን ነፃ ያወጣውና ወደ ቀድሞው
ቦታው ይመልሰው ዘንድ ወደደ ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ከድንግል ያለወንድ ዘር በሥጋ ተወለደና አዳነን። ከይሲ
(ዲያብሎስ) ያሳታት ሔዋንን እግዚአብሔር ምጥሽንና ጻርሽን
አበዛዋለው ቢሎ ፈረደባት ሰውን ወደደና ነፃ አደረጋት። ቅድስት
ሆይ ለምኝልን።
ሰው የሆነና በኛ ያደረ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ክብሩንም
ለአባቱ አንደ እንደመሆኑ ክብር አየን። ይቅር ይለን ዘንድ
ወደደ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ነቢዩ ኢሳያስ በመንፈስ ቅዱስ የአማሩኤልን ምሥጢር አየ
ስለዚህም ሕፃን ተወለደልን ወልድም ተሰጠን ብሎ አሰምቶ
ተናገረ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ሰው ሆይ ፈጽመህ ደስ ይበልህ እግዚአብሔር ዓለሙን
ወዶታልና አንድ ልጁንም የሚያምንበት ሁሉ እስከ ዘለዓለም
ፈጽሞ ይድን ዘንድ አሳልፎ ሰጥቷልና ልዑል ክንዱን ሰደደልን።
ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
የተበረው የሚኖረው የመጣው ዳግመኛ የሚመጣውም ቃል
ኢየሱስ ክርስቶስ ያለመለወጥ ፍጹም ሰው ሆነ አንዱ ወልድ
በሥራው ሁሉ አልተለየም የእግዚአብሔር ቃል መልኮት አንድ
ነው እንጂ ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
የነቢያት ሀገራቸው ቤተልሔም ሆይ ደስ ይበልሽ ሁለተኛው
አዳም ክርስቶስ በአንቺ ዘንድ ተወልዷልና ከምድር (ከሲኦል)
ወደ ገነት ይመልሰው ዘንድ አዳም ሆይ መሬት ነበርክና ወደ
መሬት ትመለሳለህ ብሎ የፈረደበትንም የሞት ፍርድ ያጠፋለት
ዘንድ፤ ቡዙ ኃጢያት ባለችበት የእዚአብሔር ጸጋ ትበዛለች።
ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
የሰው ሁሉ ሰውነት ደስ ይላታል በሰማይ ለእግዚአብሔር
ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰውም እርሱ በሚፈቅደው
እያሉ አሰምተው ንጉሥ ክስርቶስን ከመላእክት ጋር
ያመስግኑታል። የቀድሞውን እርግማን አጥፍቷልና የጠላትን
ምክሩን አፈረሰበት ለአዳምና ለሔዋን የዕዳ ደብዳቤያቸውን
ቀደደላቸው በዳዊት ሀገር የተወለደ መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ አዳምና ሔዋንን ነፃ አደረጋቸው ።ቅድስት ሆይ
ለምኝልን።
በዚህ ዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምታበራ እውነትኛ ብርሃን
ስለሰው ፍቅር ወደ ዓለም የመጣው ፍጥረት ሁሉ በመጣትህ
ደስ አለው አዳምን ከስህተት አድረኸዋልና ሔዋንንም ከሞት
ጻዕረኝነት ነፃ አድርገኻታልና የምንወለድበትን መንፈስ (ረቂቁን
ልደት) ሰጠኸን ከመላእክት ጋርም አመስገንህ ቅድስት ሆይ
ለምኝልን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ

Sunday, April 3, 2016

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: የቤተ ክርስቲያን ደጃፉን ለምን እንደሚሳለሙ ያውቃሉ?

የቤተ ክርስቲያን ደጃፉን ለምን እንደሚሳለሙ ያውቃሉ?
በትእምርተ መስቀል ከአማትበን በኋላ የቤተ መቅደሱን ደጃፍ
በእምነት ስንሳለም ተመልክተው የሚገርማቸው አይጠፉም
እንዲህ ያሉ ሰዎች ዐጸዱን ደጃፉን በበሩን መስኮቱን
መሳለማችን እነርሱ እንደሚያስቡት ያለ ምክንያት አይደለም፡፡
ደጃፉን የምንሳለምበት የተለያየ ምክንያት አለን፡፡
፩. ቤተ መቅደሱን እንዲሁ በውስጡና በዙሪያው ያለውን የነካ
ስለሚቀደስበት
“የቅብዐት ዘይትን ወስደህ ማደሪያውን በእርሱም ያለውን ሁሉ
ትቀድሳለህ ቅዱስም ይሆናል” ሲል ለሙሴ አዞታል ኦሪ ዘፀ
፵፥፱/40፥9/
እግዚአብሔር ቤተ መቅደሱና በዙሪያው ያሉ ሁሉ እንዲቀደሱ
አዟል፡፡ደብተራ ኦሪት ሲተከል የሰሎሞን ቤተ መቅደስ ሲሰራ
ዙሪያው በቅብዓ ቅዱስ ተቀድሷል የቤተ መቅደሱ ደጃፍ
መሳለም መሳም የሚያስፈልገው ለዚህ ነው፡፡ሕንጻ ቤተ
ክርስቲያኑ ደጃፉ በቅብዓ ሜሮን የከበረ የተቀደሰ ስለሆነ
የሚሳለመው የሚስመው የሚተባበሰው ሁሉ ይቀደሳል፡፡
፪. ቤተ መቅደስ የክርስቶስ ማደሪያ ስለሆነ
በሌላ በኩል ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረ ቤተ ክርስቲያን
የክርስቶስ አካል ዘርፉ ልብሱ መቅደሱ ናት፡፡ ኤፌ
፭፥፳፫/5፥23/፡፡ አካል ከራስ ጠጉር እስከ እግር ጥፍር ያለውን
ሁሉ እንደሚይዝ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት ሲባል
የቤተ ክርስቲያኑ አካል ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ ስለዚህ አካሉ
የሆነችው ይህች ቤተ ክርስቲያን/ቤተ መቅደስ/ መሳለም
መተባበስ የጌታችንን የልብሱን ዘርፍ በመንካቷ አስራ ሁለት
በዓመት ሙሉ ደም ሲፈሳት ኖራ እንደተፈወሰችው ሴት
የእምነት ጥንካሬ ምልክት ነው ሉቃ ፰፥፵፫-፵፰ /8፥43-48/
፡፡በእምነት ለሚሳለም በእምነት ለሚኖር ሰው
የቤተክርስቲያን ደጃፎቿ ዐጸዱ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ያለው
ጠበል አጥሩ ቅጥሩ ውስጡ ውጪው ሁሉ ፈውስና መድኃኒት
ይሆነዋል፡፡
፫. ቤተ መቅደሱ የመለኮት ማደሪያ ስለሆነ
ቤተ ክርስቲያን/ቤተ መቅደሱ/ የመለኮት ማደሪያ ነው፡፡
በሰማይ በክብር የሚኖር እግዚአብሔር በቤተ መቅደሱን
በረድኤት ያድራል፡፡ ቤተ መቅደሱን የክብሩ
መገለጫ አድርጎታልና፡፡ “አሁንም ስሜ ለዘለዓለም በዚያ
ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለው ቀድሻለውም ዐይኖቼና
ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ” ፪/2/ ዜና፯፥፲፮ /7፥16/
“ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን” መዝ ፻፴፩፥፯/131፥7/ እንዲል
ቤተ መቅደሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ስለሆነ ደጃፉ አጥሩ
ቅጥሩ ሁሉ የተቀደሰ በበረከት የተሞላ ነው፡፡ ስለዚህ ወደ ቤተ
መቅደስ የሚቀርብ ሰው ይህን እያሰበ ይሳለማል፡፡
ስለዚህ ሰው ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ደጃፏን /ደጀ ሠላሟን/
“ሠላም ለኪ ቤተ ክርስቲያን አምሳለ ኢየሩሳሌም ቅድስት” /
ቅድስት የምትሆን የሰማያዊ ኢየሩሳሌም አምሳል የሆንሽ ቤተ
ክርስቲያን ሆይ
ሠላምታ ይገባሻል/ እያልን ደጃፏን አጥሯን እንሳለም::

Saturday, April 2, 2016

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: የዐቢይ ጾም አምስተኛ እሑድ ደብረ ዘይት

የዐቢይ ጾም አምስተኛ እሑድ ደብረ ዘይት
ተብሎ ይጠራል፡፡ የጌታችን ዳግም መምጣትና የዘመኑ
ምልክት የሚነገርበት ቀን በመሆኑ ዕለቱ ደብረ ዘይት
ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ጌታችን ስለ ዓለም መጨረሻና ስለ
መምጣቱ ምልክት የተናገረው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ
በመሆኑ ዕለቱ ደብረ ዘይት ተባለ (ማቴ. 24÷ 3)፡፡
ቅዱስ ያሬድ ዕለቱን ደብረ ዘይት ብሎ መሰየሙ ብቻ
ሳይሆን በዕለቱም ያቀረበው ዝማሬ እንዲህ የሚል
ነው፡-
“ወአመ ምጽአቱሰ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይትከወሰ ኲሉ
ኃይለ ሰማያት ወምድር አሜሃ ይበክዩ ኲሎሙ ኃጥአን ምድር
ወይወርድ እግዚእነ እምሰማይ ዲበ ምድር በትእዛዙ ወበቃሉ
ወበአእላፍ መላእክቲሁ በንፍሐተ ቀርን ዘእም ኀበ
እግዚአብሔር ይምሐረነ አብ በይእቲ ሰዓት እሞተ ኃጢአት
እስመ ገባሬ ሕይወት”
ትርጉም፡-
“የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ የሰማይና የምድር
ሠራዊት ሁሉ ይነቃነቃል። ያን ጊዜ በምድር የሚኖሩ
ኃጢአተኞች ሁሉ ያለቅሳሉ፡፡ ጌታችንም ከአእላፍ
መላእክት ጋር በትእዛዙና በቃሉ መሠረት ከሰማይ ወደ
ምድር ይወርዳል፡፡ የእግዚአብሔር መለከትም
ይሰማል፡፡ በዚያች ሰዓት እርሱ ያድነን። እርሱ የሕይወት
ባለቤት ነውና።”
ቅዱስ ያሬድ የዘመረው የማቴዎስ ወንጌል
ምዕራፍ 24ን ነው፡፡ ጌታችን ሲመጣ ፍጥረት
እንደማይፀና ኃጢአተኞች ደስታ እንደማይሰማቸው
ይገልጣል፡፡ በኃይሉ ፊት ፍጥረት፣ በፍርዱ ፊት ኃጥአን
መቆም አይችሉምና፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይመጣል። በብሉይ
ኪዳን እመጣለሁ ብሎ መጥቷል፡፡ በአዲስ ኪዳንም
እመጣለሁ ብሎ ቤተ ክርስቲያንን በተስፋ አስገዝቷታል፡፡
ፍጥረት ሁሉ የሚጠብቀው አንድ ታላቅ እንግዳ
ከፊታችን ባለው ባልራቀው ዘመን ይመጣል፡፡
የሚመጣው በትሕትና ሳይሆን በልዕልና ነው፡፡
በከብቶች በረት ሊጣል ሳይሆን በደመና በዙፋን
ተገልጦ ይመጣል፡፡ ስምዖን አረጋዊ እንደ ታቀፈው ሆኖ
አይመጣም፣ ሰማይና ምድር የማይችሉት ሆኖ
ይመጣል፡፡ ከእናቱ ጡትን እየለመነ አይመጣም፣
ለፍጥረት ሁሉ የሩጫውን ዋጋ ለመስጠት ይመጣል፡፡
ከሄሮድስ ፊት የሚሸሽ ሆኖ አይመጣም፡፡ ሰማይና
ምድር ሲያዩት ከፊቱ ይሰደዳሉ፡፡ ለእኛ ለክርስቲያኖች
መጣልን የምንለው እንግዳችን፣ ፈራጃችን እንጂ
መጣብኝ የምንለው አይደለም፡፡
የጌታችን ዳግም ምጽአት፡-
1. የጸሎታችን መልስ ነው።
2. የፍጥረት ምጥ ዕረፍት ነው።
3. የዘመናት ናፍቆት መልስ ነው።
4. የተስፋችን ፍጻሜ ነው።
5. የእምነታችን ክብር ነው።
6. የአዲስ ዓለም ጅማሬ ነው።
7. የዘላለም ሕይወት መክፈቻ ነው፡፡
የጸሎታችን መልስ ነው
ብዙ ሰዎች ክርስቶስ ዳግም ይመጣል ሲባሉ
ይፈራሉ፡፡ ፍርሃታቸው ግን ለንስሐ አያዘጋጃቸውም። ልበ
ሙሉ ሆነው ኃጢአት እንዳይሠሩ የመምጣቱ ዜና
ስለሚረብሻቸው ነው፡፡ የጌታችን ዳግም ምጽአት
በሚታሰብበት ቀን እንኳ ብዙ የኃጢአት መታሰቢያ
ሲደረግ ይውላል፡፡ ለብዙ ሰዎች እኩለ ጾም ከሥጋና
ከስካር ከተላቀቁ አንድ ወር መሆኑን ለመገናኘትም ወር
እንደሚቀራቸው የሚያስቡበት ቀን ነው፡፡ በጊዜያዊ
ጨዋነት የሰነበቱትም ሲሰክሩ የሚውሉበት የተውኔት
ቀናቸው ነው፡፡ ሃይማኖት የማይሞት ኃይል ነው፡፡ ከሰው
ልብ ግን ሊሞት የሚችለው ሰዎች እንደ ባሕል
ቆጥረውት ሲኖሩ ነው፡፡
የጌታችን መምጣት ግን የጸሎታችን መልስ
ነው፡፡ የምንፈራውና ያርቅልኝ የምንለው ሳይሆን
በየዕለቱ “መንግሥት ትምጣ” እያልን የምንጸልይበት
ትልቅ ርዕሳችን ነው፡፡ የዚህ ዓለም መንግሥት በግፍ
ተጀምሮ በግፍ የሚጠናቀቅ፣ በውሸትና በሐሰተኛ ተስፋ
ሰውን የሚያደክም፣ በጭካኔ ሲወዳደር የሚኖር፣ ደም
በደም የሆነ መንገድ ነው፡፡ በዚህ ክፉ ሥርዓት
የተጨነቁ ሁሉ ጽድቅና ሰላም የነገሠባትን የክርስቶስን
መንግሥት ይናፍቃሉ (ሮሜ. 14÷17)፡፡ የክርስቶስ
መንግሥቱ የምትገለጠው ጌታችን ምድራውያን
ነገሥታትን አሳልፎ ንጉሠ ነገሥት ሆኖ በሚነግሥበት
በዳግም ምጽአቱ ነው፡፡ ዳግም ምጽአቱ ምድራዊውን
ሥርዓት አሳልፎ አንድ መንግሥትን በሁሉ የሚያፀና
ነው፡፡
የፍጥረት ምጥ ዕረፍት ነው
ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “ የፍጥረት ናፍቆት
የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና” ይላል
(ሮሜ. 8÷19)፡፡ ዳግመኛም “ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን
ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን
እናውቃለንና” ይላል (ቁ.22)፡፡ በሰው ኃጢአት
የተጨነቀው ሰው ብቻ ሳይሆን ፍጥረት በሙሉ ነው፡፡
እንስሳቱ አራዊቱ ሁሉ የሰውን ኃጢአት ቅጣት
እየተካፈሉ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ የሚያርፉት ክርስቶስ
ልጆቹን በክብር በሚገልጥበት በምጽአቱ ቀን ነው፡፡
ስለዚህ ፍጥረት ሳይወድ በግድ የሰውን ማረፍ
ይናፍቃል፡፡ የራሱም ዕረፍት ነውና፡፡ ዛሬ በብዙ ነገር
እናለቅሳለን፡፡ ብዙ ጭንቀቶችም ከበውን እንኖራለን፡፡
የክርስቶስ መምጣት ግን የፍጥረት ምጥ ዕረፍት ነው፡፡
የዘመናት ናፍቆት እርካታ ነው
ማራናታ ማለት ጌታ ይመጣል ወይም ጌታ
መጣ ማለት ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት
ገጽ 609)፡፡ ይህ ቃል ዮሐንስ ራእዩን ሲዘጋ
ተጠቅሞታል፡- “ አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና” (ራእ.
22÷20)። ዮሐንስ በራእዩ ስለሚመጣው የዘመናት
ጣር ካየ በኋላ የዚህ ሁሉ ማብቂያው ምንድነው? ብሎ
ሲያስብ የጌታ መምጣት ነው፡፡ ስለዚህ ማራናታ አለ፡፡
የጌታችን መምጣት የመከራው ድንበር ነው፡፡
በመጀመሪያ ምጽአቱ ሞት ተገደበ፣ በዳግመኛ ምጽአቱ
መከራ ገደብ ያገኛል፡፡
የተስፋችን ፍጻሜ ነው
የምንጠባበቃቸው ብዙ ተስፋዎች ቢኖሩም
ትልቁ ተስፋችን ክርስቶስ ነው፡፡ የምንጠብቃቸው
ነገሮች ቢሆኑልን እንኳ ሌላ መመኘታችን አይቀርም፡፡
ክርስቶስ ከመጣልን ግን ምንም እስከማያምረን
ለዘላለም ያረካናል። ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “የተባረከው
ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና
የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክብር መገለጥ
እየጠበቅን ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ
እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር
ያስተምረናል” (ቲቶ. 2÷12-13) ይላል፡ ሰዎች ተስፋ
ካላቸው ራሳቸውን ከሚጎዳ ነገር ይከላከላሉ፡፡
እንዲሁም ክርስቶስ ተስፋቸው የሆነ ይቀደሳሉ፡፡
በኃጢአት መጫወት ተስፋ መቁረጥ ነው፡፡ የክርስቶስ
ምጽአት የተስፋችን ፍጻሜ ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን
የቀረላት ተስፋ የክርስቶስ መምጣት ነው፡፡
የእምነታችን ክብር ነው
ጌታችን ዳግመኛ የሚመጣው በናቀን ዓለም
ፊት እምነታችንን ሊያከብር ነው፡፡ የዘበቱብንና
ያስጨነቁን ለዘላለም ያፍራሉ፡፡ ዛሬ ቃሉን የረገጡ፣ ያን
ቀን ፍርዱን መርገጥ አይችሉም፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች
የሆንም በዚያን ቀን በዘላለም ክብር ተውበን በጉን
እረኛችን አድርገን ወደ ፍስሐ ዓለም እንገባለን፡፡
የአዲስ ዓለም ጅማሬ ነው
በዮሐንስ ራእይ ላይ እንደ ተጻፈው “አዲስ
ሰማይና አዲስ ምድርን አየሁ ፊተኛው ሰማይና
ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፤ ባሕርም ወደፊት የለም”
ይላል (ራእ. 21÷1)፡፡ አዲስ ነገር የሚያስፈልገው
ፊተኛው ሲያረጅ ነው። ያረጀ ነገር መልኩ የወየበ፣
ጉልበቱ ያለቀ፣ ወደፊት ሊጠቅም የማይችል ነው፡፡
አሁን ፍጥረት አርጅቷል፡፡ በረዶ እየቀለጠ፣ የምድር
ሙቀት እየጨመረ፣ መሬቱ ማዳበሪያ እየፈለገ፣ ሰውም
በብዙ መድኃኒት እየኖረ ነው። ይህ የማርጀት ምልክት
ነው፡፡ ይህን አዲስ የሚያደርገው የክርስቶስ መምጣት
ነው፡፡ ሰውም ሞት ላይዘው በትንሣኤ፣ የሚመጣው
ዓለምም ማርጀት ላያገኘው በአዲስነት ይኖራል፡፡
የዘላለም ሕይወት መክፈቻ ነው
ጌታችን ሲመጣ ዘላለማዊት የምትሆን
መንግሥተ ሰማያት ትከፈታለች፡፡ ዛሬ በክርስቶስ ያመኑ
በበጎ ሥራ የፀኑ አማንያን በጊዜያዊ ማረፊያቸው
በገነት ይኖራሉ፡፡ ገነት ጊዜያዊ የነፍሶች ማረፊያ ናት፡፡
ክርስቶስ ሲመጣ ገነትና ሲኦል ያልፋሉ፡፡ መንግሥተ
ሰማያትና ገሀነመ እሳት ይከፈታሉ (ማቴ.
25÷34.41)፡፡
የዘላለም ዘመንም ይከፈታል፡፡ ዘወትር አዲስ
የሆነውን ጌታ እያየን በዘላለም ደስታ እንኖራለን፡፡
የጌታችን መምጣት ብዙ ትርፎች ያሉት ወደማይነገርም
ክብር የምንገባበት ነው፡፡ ዛሬ በዓለም ላይ የምናየው
መከራና ሰቆቃ የምጽአቱ ዋዜማ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ጭንቅ
በክርስቶስ መምጣት ይጠናቀቃል፡፡ “አሜን፣ ጌታ
ኢየሱስ ሆይ፣ ቶሎ ና” /ራእ.22÷20/።

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: ደብረ ዘይት

3 እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ
ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል?
የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው?
አሉት።
4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። ማንም እንዳያስታችሁ
ተጠንቀቁ።
5 ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤
ብዙዎችንም ያስታሉ።
6 ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን
ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና
ነው።
7 ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ
ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ
ስፍራ ይሆናል፤
8 እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
9 በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል
ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ
ትሆናላችሁ።
10 በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም
አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤
11 ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤
12 ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር
ትቀዘቅዛለች።
13 እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
14 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት
ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው
ይመጣል።
15 እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት
በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥
16 በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥
17 በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፥
18 በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው
አይመለስ።
19 በዚያችም ወራት ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው።
20 ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን
ጸልዩ፤
21 በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ
ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና።
22 እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤
ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።
23 በዚያን ጊዜ ማንም። እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም።
ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤
24 ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥
ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ
ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።
25 እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ።
26 እንግዲህ። እነሆ፥ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥
በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤
27 መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥
የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና፤
28 በድን ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ።
29 ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ
ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም
ከሰማይ ይወድቃሉ፥
30 የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ
ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ
ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ
ደመና ሲመጣ ያዩታል፤
31 መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥
ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ
የተመረጡትን ይሰበስባሉ።
32 ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ
ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ
ታውቃላችሁ፤
33 እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደ ቀረበ
እወቁ።
34 እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ
አያልፍም።
35 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።
36 ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር
የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።
37 የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ
ይሆናልና።
38 በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ
እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ
ነበሩ፥
39 የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ
እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።
40 በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል
አንዱም ይቀራል፤
41 ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች
አንዲቱም ትቀራለች።
42 ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ
ንቁ።
43 ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ
እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም
ነበር።
44 ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ
በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።
የማቴዎስ ወንጌል 24 : 3-44