ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

Friday, March 17, 2017

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: =>+*"+<+>††መጋቢት ፯ (7)††

ስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡
አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖መጋቢት ፯ (7) ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
✞ ሰማዕትነት በቅዱስ ቴዎዶጦስ ሕይወት ✞
+*" ቅዱስ ቴዎዶጦስ "*+
=>በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ጊዜው ለክርስቲያኖች
ሁሉ ፍጹም የመከራ ከመሆኑ የተነሳ "ዘመነ-ሰማዕታት"
ሲባል በወቅቱ ከ47 ሚሊዎን በላይ ክርስቲያኖች
ተጨፍጭፈዋል::
+የዘመኑ ክርስቲያኖች ለመሞት የሚያደርጉትን
እሽቅድምድም እያዩ አሕዛብ "ወፈፌዎች" እያሉ
ይጠሯቸው ነበር:: (ዓለም እንዲህ ናትና!) እብዶቹ
ጤነኞችን "እብድ" ማለታቸውኮ ዛሬም አለ::
(ለነገሩ "ግደልና ጽደቅ" ከሚል መመሪያ በላይ ጤና
ማጣት አይኖርም)
=>ታዲያ በወቅቱ አንድ #ቴዎዶጦስ የሚሉት ወጣት
በምድረ ግብጽ ይኖር ነበር:: ወጣቱ እጅግ ብርቱ
ክርስቲያን ነበርና እንደ ዘመኑ ልማድ ተከሦ በነፍሰ
ገዳዮች ፊት ቀረ:: ክሱ አንድ ብቻ ነው:: "ክርስቶስን
አምልከሃል" የሚል::
+ከሥጋ ሞት ለማምለጥ ደግሞ መንገዱ ያው አንድ ብቻ
ነው:: ፈጣሪውን ክርስቶስን ክዶ ለአሕዛብ አማልክት
(አጋንንት) መገዛት:: #ቅዱስ_ቴዎዶጦስ በገዳዮቹ ፊት
ቆሞ ተናገረ:-
" #እኔ_ክርስቲያን_ክርስቶሳ ዊ_የክርስቶስ_ነኝ:: ምንም
ብታደርጉኝ ከክርስቶስ ፍቅር ልትለዩኝ አትችሉም"(ሮሜ.
8:35) አላቸው::
+እነሱ ግን ነገሩ እውነት አልመሰላቸውምና ሊያሰቃዩት
ጀመሩ::
*ገረፉት
*አቃጠሉት
*ደበደቡት
*ሌላም ሌላም ማሰቃያዎችን በእርሱ ላይ ተጠቀሙ::
የሚገርመው ግን እሱ ሁሉን ሲታገሥ ገዳዮቹ ግን
ደከሙ::
+በመጨረሻም ወደ ገዢው ዘንድ አቅርበው "ብዙ
አሰቃይተነዋል:: ግን ሊሳካልን አልቻለም" በሚል ሰይፍ
(ሞት) ተፈረደበት:: በአደባባይ ሊሰይፉት ሲወስዱት ግን
ትንሽ አዘኑለት መሰል ጨርቅ አምጥተው "ፊትህን ሸፍን"
አሉት:: (ያኔ ትንሽም ቢሆን ሰብአዊነት ሳይኖር አይቀርም)
+ቅዱስ ቴዎዶጦስ ግን ገዳዮቹን በመገረም
እየተመለከታቸው ተናገረ:- "እኛ ክርስቲያኖች ሞትን
አንፈራም:: ሞት ለእኛ ወደ ክርስቶስ መሸገጋገሪያ
ድልድያችን ነውና የምንፈራው ሳይሆን የምንናፍቀው
ነው::" "ኢትፍርሕዎሙ
(አትፍሯቸው)"
(ማቴ. 10:28)
+ይህን ብሎ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ጌታውን አመሰገነ::
ፊቱ ላይ ደስታ እየተነበበ ጨካኞቹ አንገቱን ሰየፉት::
በብርሃን አክሊልም ቅዱሳን መላእክት ከለሉት::
*መሠረታዊው ነገር ቅዱስ ቴዎዶጦስ ለምን አልፈራም?
ነው::
+አጭር መልስ ካስፈለገን ቅዱሱ ያልፈራው ከልቡ
ክርስቶሳዊ በመሆኑ ነው:: ትኩረት እንድንሰጠው
የሚያስፈልገው ግን የሰማዕታት ምስጢራቸው:-
1.በጽኑ የክርስትና መሠረት ላይ መመሥረታቸው
2.ዕለት ዕለት የክርስቶስን ፍቅር መለማመዳቸው
3.ከወሬ (ንግግር) ይልቅ ተግባርን መምረጣቸው
4.በንስሃ ሕይወት መመላለሳቸው
5.ሥጋ ወደሙን የሕይወታቸው ዋና አካል ማድረጋቸው
6.ከእነሱ የቀደሙ ቅዱሳንን ዜና ሕይወት ከልብ
ማንበባቸው
7.በቃለ እግዚአብሔር መታነጻቸው . . . መጠቀስ
የሚችሉ መገለጫዎቻቸው ናቸው::
<+>" ዛሬስ "<+>
=>ዓለማችን ከጠበቅነው በላይ ነፍሰ በላነቷ እየጨመረ
ነው:: ዛሬ የክርስትና ጠላቶች ከጉንዳን በዝተዋል::
*የራሳችን ማንነት
*ክርስትናችን በአፋችን ላይ ብቻ መሆኑ
*እረኞችና በጐች መለያየታቸው . . . ሁሉ እኛ ልናርማቸው
የሚገቡ ናቸው::
*አሸባሪዎች
*አሕዛብ
*የመዝናኛው ዓለም
*ሰይጣን አምላኪ ዝነኞች (Celebrities)
*ሚዲያው
*ማሕበራዊ ድረ ገጾችና መሰል ነገሮች ደግሞ
ልንጠነቀቅባቸው የሚገቡና እኛን ውስጥ ለውስጥ
በልተው የፈጁን የሰይጣን መሣሪያዎች ናቸው::
+ስለዚህም ከዛሬ ጀምረን ባለ መታወክ ክርስትናችንን
ከአፋችን ወደ ልባችን: ከብዕራችን ወደ አንጀታችን
እንድናወርደው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አደራ ትላለች::
+ዛሬ ነገሮችን ረስተን ሌሎች አላስፈላጊ ነገሮችን
ከጀመርን እጅግ አሳፋሪ መሆኑ አይቀርም:: በጐውን
ጐዳና ተከትለን በሃይማኖትና በፍቅረ ክርስቶስ ከጸናን ግን
ማንም ቢመጣም ፈጽሞ አንናወጥም::
+ይልቁኑ
"አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን:
ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው::
ስለዚህም ምድር ብትነዋወጥ: ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ
ቢወሰዱ አንፈራም::" (መዝ. 46:1) እያልን ከቅዱስ
ዳዊት ጋር እንዘምራለን::
<< ለዚህ ደግሞ ደመ ሰማዕታት ይርዳን:: በረከታቸው ይድረሰን:: የጌታ ፍቅርም አይለየን >>
+*" ጻድቁ ንጉሥ ቴዎድሮስ "*+
=>በሃገራችን ታሪክ በጣም ተወዳጅ ከነበሩ ነገሥታት
ጻድቁ ቴዎድሮስ ቅድሚያውን ይወስዳል:: በርግጥ
በርካቶቻችን የምናውቀው ስለ ሃገሩ ፍቅር ራሱን የሰዋውን
ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስን (1845-1860) ነው:: በበጎ
ሥራውና በቅድስና ሕይወቱ የተመሠከረለት ግን ዛሬ
የምናስበው ቀዳማዊው ነው::
+ቀዳማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ የደጉ ዐፄ ዳዊት (ግማደ
መስቀሉን ያመጡት) እና የተባረከችው ሚስታቸው ፅዮን
ሞገሳ ልጅና የጻድቁ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ታላቅ ወንድም
ነው:: በኢትዮዽያ ለ3 ዓመታት (ከ1396-1399) ብቻ
ነግሦ እያለ እንደ ንጉሥ ሳይሆን-
*ከጠዋት እስከ ማታ ድሃ እንዳይበደል ፍርድ
እንዳይጉዋደል ይታትር የነበር::
*ጾምና ጸሎትን የሚያዘወትር::
*ወገቡን ታጥቆ ነዳያንን የሚያበላ::
*ለአብያተ ክርስቲያናትም የሚጨነቅ ደግ ሰው ነበር::
+ስለዚህም በሕዝቡ እጅግ ተወዳጅ ነበር:: በነገሠ በ3
ዓመቱ ዐርፎ በዝማሬና በለቅሦ ሥጋውን ተሸክመው
ሲሔዱ ወንዝ ተከፍሎላቸዋል:: ከመቃብሩም ላይ ጸበል
ፈልቁዋል::
=>ዘለዓለም ሥላሴ ደግ መሪና ሰላማዊ ዘመንን ያድሉን::
=>መጋቢት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ጻድቁ ኢትዮዽያዊ ንጉሥ ዐፄ ቴዎድሮስ
2.ቅዱስ ቴዎዶጦስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ፊልሞን ሰማዕት
4.ቅዱስ አብላንዮስ ሰማዕት
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
=>+"+ ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ::
ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና::
ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው::
ስለዚህ ባ ለሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን
ሥርዓት ይቃወማል:: . . . ለሁሉ እንደሚገባው አስረክቡ::
ግብር ለሚገባው ግብርን: ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን:
መፈራት ለሚገባው መፈራትን: ክብር ለሚገባው ክብርን
ስጡ:: +"+ (ሮሜ. 13:1-8)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ:=>+*"+<+>††በቤተክርስቲያናችን ስርአት መሰረት 7 ጊዜ እንፀልያለን ። የእነሱም ትርጉም ††

~በቤተክርስቲያናችን ስርአት መሰረት 7 ጊዜ እንፀልያለን ።
የእነሱም ትርጉም
1= ጠዋት 12:00 ሰአት፡- አንድ ክርስቲያን እግዚአብሔርን
አምላክን በፀሎት የሚያመሰግንበት ምክንያት (ሚስጥር)
እግዚአብሔር አምላክ ሌሊቱንና ጨለማውን አሳልፎ ብርሀን
እንድናይ ስላበቃን በዚህ ሰአት እግዚአብሔር አምላካችንን
እንድናመሰግን ታዝዝዋል። አንድም በዚህ ሰአት ጌታችን
ለክስ ከጲላጦ ፊት ቆሞ የተወቀሰበት ሰአት ስለሆነ አንድም
በዚ ሰአት አባታችን አዳም ያልተፈቀደለትን እፅ በልቶ ከገነት
የተባረረበት ሰአት ስለሆነ ነው። አንድ ክርስቲያን ይህን ሁሉ
እያሰበ ወደ አምላኩ እንዲፀልይ ታዝዋል
2=ከጠዋቱ 3:00 ሰአት፡- አንድ ክርስቲያን እንዲፀልይ
የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር)
በዚህ ሰአት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብስራተ
ገብርኤልን የሰማችበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድም በዚህ
ሰአት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን
የፀነሰችበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድም ጌታችን መድሀኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ከ ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የተገረፈበት ሰአት
ስለሆነ ዮሐ 19 ፥1 ሐዋ ስራ 2፥15 እያንዳንዱ ክርስቲያን
ይሔንን የመሳሰሉ ሁሉ እያሰበ እግዚአብሔር አምላኩን
እንዲያመሰግን ታዝዋል
3= 6:00 ሰአት፡-አንድ ክርስቱያን እኩለ ቀን (ከ ቀኑ
6ሰአት) ሲሆን እንዲፀልይ የታዘዘበት ምክንያት ወይም
(ሚስጥር )
ጌታችን በቀራኔዎ አደባባይ በመስቀል ተሰቅሎበታልና
አንድም ልብሱን ተገፎበታል አንድም ሳዶር አላዶር ዳናት
ሮዳስ በተባሉ ችንካሮች ተቸንክሮበታል አንድ ክርስቲያን ይህን
ሁሉ እያሰበ በዚህ ሰአት እንዲፀልይ ታዞበታል
4= ከቀኑ 9:00 ሰአት፡- አንድ ክርስቲያን የሚፀልይበት
ምክንያት (ሚስጥር)
አይሁዶች ጌታችን መድሀኒታችን ኢየ�ሱስ ክርስቶስን መራራ
ሐሞት አጠጥተውበታል አንድም ቅድስት ነፍሱን ከ ክቡር
ስጋው የለየበት ሰአት ነውና አንድም በመስቀል እንዳለ 7ቱን
አፅርሀ መስቀል የተናገረበት ማር 15፥34 ማቴ 27፥50
አንድ በዚህ ሰአት ይህንን እያሰበ እንዲፀልይ ታዝዋል
5= ከቀኑ 11፡00 ሰአት፡- አንድ ክር�ቲያን እንዲፀልይበት
የታዘዘበት ምክንያት ወይም (ሚስጥር)
ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ወደ ከርሰ መቃብር
የወረደበት ሰአት ስለሆነ አንድም ቀኑን በሰላም አሳልፎ ወደ
ምሽት በሰላም ያደረሰን አምላክ ምስጋ ስለሚገባው ነው
ይህንን የመሳሰሉ ሁሉ ሕዝበ ክርስቲያን እንዲያስቡ ታዘዋል
6= ከምሽቱ 3:00 ሰአት፡- በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን
እንዲያመሰግን የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር)
በዚህ ሰአት እራሱ ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ
ስርአተ ፀሎት አሳይቶበታል አንድም በዚህ ሰአት ጌታችንን
አይሁድ በይሁዳ ጠቁዋሚነት ተረበርበው የያዙበት ሰአት
ስለሆነ ነው አንድም በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን ከመተኛቱ
በፊት በሰላም ያዋለንንና ያስመሸንን አምላክ አመስግኖ
መተኛት አለበት ይህን ሁሉ እያሰበ እንዲፀልይ ታዝዋል
7= መንፈቀ ሌሊት ከሌሊቱ 6 :00 ሰአት:- በዚህ ሰአት አንድ
ክርስቲያን እግዚአብሔር አምላኩን እንዲያመሰግንበት
የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር)
በዚህ ሰአት ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ተወልዶበታልና ነው አንድም ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ሙስና መቃብርን ድል አድርጎበታልና(ተነስቶበታ
ል) በመዝሙረ ዳዊት አመሰግንህ ዘንድ በመንፈቀ ሌሊት
እነሳለው ባለው መሰረት ጳውሎስ ሲላስ በእስር ቤት ሆነው
ወደ እግዚአብሔር የፀለዩበት ስለሆነ ነው አንድም የሰው ልጅ
የሚመጣበት ጊዜ ማታ ይሁን መንፈቀ ሌሊት ይሁን ዶሮ
ሲጮህም ይሁን ሲነጋም ቢሆን አይታወቅምና ባለው
አምላካዊ ቀል መሰረት በመንፈቀ ሌሊት አንድ ክርስቲያን
እንዲፀልይ ታዝዋል
የቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እና ምልጃ አክሊልና ጉልላት በሆነው
በእናታችን በወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም
ጸሎት ሁላችንንም ይማረን፡፡

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ:=>+*"+<+>††ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ††

ዮሐንስ ማለት ፍሰሓ ወሐሴት ሠላም ርህራሄ ወሳህል
ማለት ነው። ወልደ ነጎድጓድ፣ አቡቀለምሲስ፣ ነባቤ መለኮት፣
ታዖሎጎስ ይለዋል፡፡ “ቃዳሚሁ ቃል ውእቱ” ብሎ ምስጢረ
ሥላሴን አምልቶ አስፍቶ ይናገራልና፡፡ ፍቁረ እግዚእ
ይለዋል፡፡ “ዝኩ ካልዕ ረድዕ ዘያፈቅሮ እግዚእ ኢየሱስ”
ይለዋልና፡፡ ዮሐንስ 21፡7 መውደድንስ ሁሉንም ይወዳቸው
የለምን ቢሉ የርሱ የተለየ ነውና፡፡ ከቶማስም የሱ መወደድ
ይበልጣል፡፡ ቶማስ በጦር የተወጋ ጎኑን ቢዳስሰው እጁ ከእሳት
እንደገባ ጅማት ተኮማትሯል፡፡ እርሱን ግን በከናፍሩ ቢስመው
በጭኑ ቢያስቀምጠው ምንም ምን አልሆነም ::
ንጹህ ወድንግል ይለዋል፡፡ ጌታን ከመውደዱ የተነሳ ጌታም
እናቱን እነዃት እናትህ ሲል ድንግል ማርያምን በሱ በኩል
ተሰታናለች፡፡ እኛም ዛሬ ልጆቿ ነንና ደስ ይበለን ይበላችሁ
የድንግል ማርያም የአስራት፣ የተስፋና የስስት ልጆች፡፡ ዮሐንስ
19፡26፡፡ ዮሐንስ ሀገሩ ገሊላ አውራጃ ሲሆን ከታላቅ
ወንድሙ ከያዕቆብና ከአባቱ ከዘብድዮስ ጋር ዓሣ እያጠመደ
ይኖር ነበር። እናቱ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ስትሆን
ማርያም ትባላለች።
ዮሐንስ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን በሕይትም በኑሮም
ጌታ ስለሚመስል (ፍቁረ እግዚእ) ይባለል። ነገረ መለኮትን
በበለጠ ከሌሎች አምልቶ አስቶ በጥልቀት በማስተማሩ ነባቤ
መለኮት (ታዖሎጎስ)ተሰኝቷል። ስለጌታም ባለው ቅናት ባሳየው
የሀይል ሥራ በኦኔርጌስ (ወልደ ነጎድጓድም) ተብሏል። ፍጥሞ
በምትባል ደሴት በራዕይ መጻእያትን በመግለጡ ባለራዕይ
(በግሪክ አቡቀለምሲስ) ይባለል። በዕለተ ዓርብ በመስቀል ሥር
ተገኝቶ የጌታን መከራ መስቀል በማየቱ ፊቱ በሀዘን
ስለተቋጠረ ቁጽረ ገጽ (ፊቱ በሀዘነ የተቋጠረ) ስምም
ተሰቶታል። ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር የፋሲካን እራት ያዘጋጀ
አንካሳን የፈወሰ ታለቅ ሐዋርያ ነው። (ሊቃስ 22፡8) እስከ
መስቀል አምላኩን ተከትሎ እመቤታችንን በአደራ የተረከበ
ባለአደራ ሐዋርያ ሲሆን ከጰራቅሊጦስ በዓል በኋላ ከቅዱስ
ጴጥሮስ ጋራ በኢየሩሳሌም በአንጾኪያ በሎዶቅያ በእስያ
ከተሞች በተለይ በኤፌሶን በአሁኑ ቱርክ አስተምሯል።
(ዮሐ.19፡26) በወጣትነት ዕድሜው ተጠርቶ በዕለተ ዓርብ
የጌታን መከራ እያሰበ ያነባ የነበረ በፍቅር በታማኝነት
እስከመጨረሻ ድረስ የጸና ከጌታ ያልተለየ ወንጌላዊ ሲሆን
ወንጌልን ጨምሮ 3 መልዕክታትን የጻፈ እንዲሁም ሐዋርያው
ዩሐንስ በፍጥሞ ደሴት በዛሬቱ ቱርክ ለሰባት አመታት ታስሮ
በነበረበት ወቅት ወንጌሉንና ራዕዩን ጽፏል። አይገርምህም
ሐዋርያው ዩሐንስ በእስር እያለ ነው ራዕዩን የጻፈው!!!
ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ ደግሞ በቀዝቃዛ እስር ቤት እያለ ብዙ
መልእክታቱን ጻፈ!!! ሐዋርያቱ በእስር ቢሆኑ እንኳን
ስለቅድስት ቤተክርስቲያን አገልግሎት አብዝተው ያስቡ ነበር።
የሐዋርያቱ ብርታት ያበርታን።
ዩሐንስ ወንጌሉን በፍጥሞ ደሴት ሲጽፍ እንዲህ ብሎ ጀመረ፦
ዩሐንስ 1:1
+++ በመጀመሪያ ቃል ነበረ; ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ
ነበረ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።እኛም በቅዳሴ ላይ ሁሌ
የዩሐንስ ወንጌል ሲነበብ ቀዳሚሁ ቃል ሥጋ ኾነ ወሃደረ
ላዕሌነ ብለን እንቀበላለን። ግሩም ዜማ ከግሩም ሚስጢር
ጋር አባቶቻችን አወረሱን።
እስቲ ሚስጢሩን እንይ፦
በመጀመሪያ ቃል ነበረ፦ እንደምናውቀው ቃል ኢየሱስ
ክርስቶስ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ አልፋና ዖሜጋ መጀመሪያና
መጨረሻ ነውና ራዕ 22:12። ቃልም እግዚአብሔር ነበር፦
መጽሃፍ አንባቢው ያስተውል ይላል; ምን እንደሚል ልብ
እንበል “ቃልም እግዚአብሔር ነበር” ሐዋርያው በመጀመሪያ
ቃል ነበር ብሎን ነበር; ያ ቃል እግዚአሔር እንደሆነ
አስረዳን!!! በዚሁ ምዕራፍ ላይ ወረድ ብሎ /ዩሐንስ 1:14/
“ያ ቃል ሥጋ ሆነ ይለናል” እስቲ ጥያቄ እንጠያየቅ; ሐዋርያው
ያ ቃል ሥጋ ሆነ ብሏል ከማን? ከማን ሥጋን ነሳ?
ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ
ነፍስ ነስቶ በኤፍራታ በቤቴልሔም ተወለደ።
+++ የፍጥሞ ደሴት ታሪክ እነሆ፦ ሐዋርያው ዩሐንስ በፍጥሞ
ደሴት ወንጌሉን መጻፍ ሲጀምር የመለኮትን ነገር ጽፎ
የሚጨርስ መስሎት ብእሩን አነሳ። በመጀመሪያ ቃል ነበረ
አለና ሊጨርስ አሰበ፤ ያኔ መልአኩ ቅ/ሚካኤል ተገልጦ
በፍጥሞ ደሴት ያለችውን ባህር በእንቁላል ቅርፊት እየቀዳ
ወደ መሬት ሲያፈስ አየው; ሐዋርያው ዩሐንስም እንዴት ይህ
ታላቅ ባሕር በእንቁላል ቅርፊት ያልቃል ብሎ ጠየቀው;
መልአኩም እኔስ ብሞክር ፍጥረትን ነው አንተስ የፈጣሪን
ባሕርይ የሚያልቅ መስሎህ ትሞክር አይደለምን አለው። ያኔ
ሐዋርያው ዩሐንስ ይህን ተረድቶ ወዲያው ከእግዚአብሔር
የተላከ ስሙ ዩሐንስ የሚባል አንድ ሰው አውቃለሁ ብሎ
ስለመጥምቁ ዩሐንስ ታሪክ የቀጠለውም በዚሁ ምክንያት
ነበር። ዩሐንስ 1:19
ከሐዋርያው፣ ከዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ረድኤትና በረከት
ይክፈለን ምልጃና ጸሎት ከሁላች ጋር ይሁን አሜን !!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ
ክቡር ይቆየን አሜን።

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ:=>+*"+<+>††መጋቢት 5 ፃድቁ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ††

መጋቢት 5 ፃድቁ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ
በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ይውላል ።
በዚህ እለት እምናከብረው የእረፍት መታሰቢያቸውን ሲሆን
ከገድላቸውም እንዲህ ተፅፎ እናገኘዋለን ።
ፃድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የተወለዱት ግብፅ ንሂሳ
በምትባል ቦታ ከአባታቸው ስምዖን ከእናታው አቅሌስያ ነው።
በአጠቃላይ የኖሩበት ዕድሜ 562 አመት ሲሆን 300
ዓመቱን በግብጽ 262 ቱን በኢትዮጵያ 100 ዓመት በዝቋላ
በተጋድሎ ያሳለፉ ታላቅ አባት ናቸው።
መጋቢት 5 በገድለ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ
ዕለቱ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ሰዓቱ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት
ሆኗል፤ አሁንም ህማሙን እየታገለ እያላበው በድካም
ለፍጥረቱ ሁሉ ይለምናል፤ “አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህን
ኢትዮጰያንም ባርክ” ይላል። ህመም የጀመረው መጋቢት 3
ዓርብ ቀን ነው፤መታመሙን የሰሙ እንደርሱ ቅዱሳን የሆኑት
ዘርአ ቡሩክ፤ ፍሬ ቅዱስ፤ያዕቆብ፤ብንያምና ዮሴፍ እንዲሁም
በወቅቱ የኢትዮጰያ ንጉስ የነበረው እንድርያስ ሊጠይቁት
ተሰብስበዋል ወደ አጠገቡ መድረስ ግን አልተቻላቸውም
አባታችን ገብረመንፈስ ቅዱስ የሚጋርደው እንጨት ዛፍ
በሌለበት በርሃ እንደ አንበሳ ተኝቶ አዩት በላዩ ያረፈው
የእግዚያብሔር ጸጋ ከፊቱ የሚወጣው ብርሃን ቀይ መልኩ
ረዥም የራስ ጠጉሩ እንደ ነጭ ሐር የሚሆን ጽሕሙ
አስደነቃቸው። ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲሆን ከሰማይ ታላቅ
ነጎድጓድ ድምጽ ተሰማ ጌታችን መላአክትን አስከትሎ ወደ
አባታችን ወረደ፤ ከሰማይ ወደ ምድር ህብሩ አምሳያው ልዩ
ልዩ የሆነ እንደ ጸሐይና እንደ ጨረቃ የሚያበራ እንደ
ወንጪፍ ድንጋይ ይወረወር ነበር ከዚያ የነበሩ ሁሉ ፈሩ ወደ
ኃላም ሸሹ ምድር ራደች ተራሮች ኮረብቶች ተናወጡ ብርቱ
ጩኸት
ንውጽውጽታ ሆነ። “ወዳጄ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሰላም ላንተ
ይሁን” እነሆ የማይታበል ቃል ኪዳን እገባልኃለው ስምህን
የጠራ መታሰቢያህን ያደረገውን፤ እጣን ቋጥሮ ግብር ሰፍሮ
መባ ይዞ ቤትህ የመጣውን እምርልኃለው አንተ ከገባህበት
ገነት መንግስተ ሰማያት አገባዋለሁ አለው፤ አባታችንም
“አቤቱ ጌታ ሆይ የኢትዮጰያን ህዝብ ማርልኝ” አለው፤ እነሆ
ምሬልኃለው አስራት በኩራት አድርጌም ሰጥቼሃለው፤
ከመጋቢት አምስት ቀን ጀምሮ ዝክርህን ያድርጉ
በአማላጅነትህም ይማጸኑ አለው። ከዚህ በኃላ ሰባቱ ሊቃነ
መላእክት የአባታችንን ነፍስ ሊቀበሉ ወረዱ በታላቅ
ምስጋናም ወደ ሰማይ አሳረጉት ስጋውንም ይዘውት ሄዱ የት
እንደተቀበረ ግን እስካሁን አይታወቅም አንዳንዱ
በእየሩሳሌም ነው ይላሉ፤ ሌላው በምድረ ከብድ ነው ይላል
ግን እስካሁን ልክ እንደ ሊቀ ነብያት ሙሴ ስጋ የት
እንደተቀበረ አይታወቅም። ገድሉ ትሩፋቱ ከሰማይ ከዋክብት
ከምድር አሸዋ ይበዛል ኢትዮጰያን አብዝቶ ይወዳታል፤
ምድራዊ ምግብ አልተመገበም የእናቱን ጡት እንኳን
አልጠባም፤ ልብስ፤ መጠለያ አልፈለገም፤ የክረምት ቁር የበጋ
ሐሩር እየተፈራረቀበት በተጋድሎ 562 ዓመት ኖረ፤ በዛሬዋ
ቀን ሩጫውን ጨረሰ። ለእግዚያብሔር ምስጋና ይሁን
እኛንም ከአባታችን በረከት ያሳትፈን።
አምላከ ገ/መንፈስ ቅዱስ መንገዱን ያብራልን ። ገድሉንም
ሰሚወች ብቻ ሳንሆን እምንማርበት ያድርግልን ።

Friday, March 3, 2017

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ:=>+*"+<+>††የአብይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት ምኩራብ††+<+>

ምኩራብ (የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት)
(ዮሐ. 2÷12-ፍጻ.)፡- ከዚህም በኋላ እርሱና እናቱ÷
ወንድሞቹና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ቅፍርናሆም ወረዱ፤
በዚያም ብዙ ያይደለ ጥቂት ቀን ተቀመጡ፡፡ የአይሁድም
የፋሲካቸው በዓል ቀርቦ ነበር፤ ጌታችን ኢየሱስም ወደ
ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡ በቤተ መቅደስም በሬዎችንና በጎችን÷
ርግቦችንም የሚሸጡትን÷ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው
አገኘ፡፡ የገመድም ጅራፍ አበጀ፤ በጎችንና በሬዎችን÷ ሁሉንም
ከቤተ መቅደስ አስወጣ፤ የለዋጮችንም ገንዘብ በተነ፤
ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፡፡ ርግብ ሻጮችንም÷ “ይህን
ከዚህ አውጡ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉ”
አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም÷ “የቤትህ ቅናት በላኝ” የሚል
ቃል ተጽፎ እንዳለ ዐሰቡ፡፡ አይሁድም መልሰው÷ “ይህን
የምታደርግ ምን ምልክት ታሳያለህ?” አሉት፡፡ ጌታችን
ኢየሱስም÷ “ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ በሦስተኛውም
ቀን አነሣዋለሁ” ብሎ መለሰላቸው፡፡ አይሁድም÷ “ይህ ቤተ
መቅደስ በአርባ ስድስት ዓመት ተሠራ፤ አንተስ በሦስት ቀኖች
ውስጥ ታነሣዋለህን?” አሉት፡፡ እርሱ ግን ይህን የተናገረው
ቤተ መቅደስ ስለ ተባለ ሰውነቱ ነበር፡፡ ከሙታን በተነሣ
ጊዜም ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ እንደ ነገራቸው ዐሰቡ፤
በመጻሕፍት ቃልና ጌታችን ኢየሱስ በነገራቸውም ነገር
አመኑ፡፡ ጌታችን ኢየሱስም በፋሲካ በዓል በኢየሩሳለም ሳለ
ብዙ ሰዎች ያደረገውን ተአምራት ባዩ ጊዜ በስሙ አመኑ፡፡
እርሱ ጌታችን ኢየሱስ ግን አያምናቸውም ነበር፤ ሁሉን
እያንዳንዱን ያውቀዋልና፡፡ የሰውንም ግብሩን ሊነግሩት
አይሻም፤ እርሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና፡፡(ዮሐ. 2÷12-
ፍጻ.)
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት
ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት አነ ውእቱ እግዚኣ
ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ
እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ
ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠፆሙ ያርምሙ
አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፡፡
ትርጉም:- ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ፤
የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን
እወዳለሁ፤የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው
ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው ፡፡ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ
አታድርጉት፤ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል (እያለ የሃይማኖትን
ቃል አስተማራቸው፡)፡ ወደ ምኩራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ
ዘንድ ገሠፃቸው፤ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣
የአነጋገሩን ጣዕምና፣ የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነቁ።
እንደ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓትና ትውፊት መሠረት በዐቢይ
ጾም ስምንቱ ሰንበታት ሊዘመር የተዘጋጀው የጾመ ድጓው
መዝሙር ነው፡፡ በየሰንበቱ የሚነበቡት የመጽሐፍ ቅዱስ
ምንባባት ፣ የሚዘመረው የዳዊት መዝሙር (ምስባክ)
ከሰንበቱ ስያሜ ጋር የሚያያዙና የሚዛመዱ ናቸው፡፡
በሰንበታቱ ውስጥ የሚነበበውና የሚዘመረውም ጌታችን
በመዋዕለ ስብከቱ ያስተማራቸውን ትምህርቶችና የሠራቸውን
ዋና ዋና ተዓምራትና መንክራት የሚመለከቱ ናቸው፡፡ ጾሙ
የጌታ ጾም ስለሆነ ሁሉም መዝሙራትና ምንባባት ከጌታ
ትምህርትና ሥራ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ በዚህ መሠረት
ሦስተኛው ሰንበት ምኩራብ ተብሎ ተሰይሟል፡፡
ምኩራብ ማለት ሰቀላ መሰል አዳራሽ ማለት ነው። አይሁድ
ስግደትና መሥዋዕታቸውን የሚያቀርቡት በኢየሩሳሌም
ባለው መቅደስ ብቻ ነው ብለው ቢያምኑም (ዮሐ 4፥20)
፤በየተበተኑበት ቦታ ምኩራብ እየሠሩ ትምህርተ ኦሪትን
በመማር ሃይማኖታቸውን ያፀኑ ነበር። ምኲራብ የአይሁድ
የጸሎት ቤት ሲሆን በብሉይ ኪዳን ዘመን የአይሁድ አምልኮ
በኢየሩሳሌም በነበረው ቤተ መቅደስና በሥርዓቱ የተመሠረተ
ነበር፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት እንደሚገልጸው
ናቡከደነጾር የአይሁዳውያንን ቤተ መቅደሱን አፍርሶ
ሕዝቡንም ወደባቢሎን ካፈለሰ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ
በሚገኙባቸው ሥፍራዎች ሁሉ ለጸሎትና ለማኅበረተኛነት ልዩ
ቤት ሊሠሩ እንደጀመሩ ይገልጻል፡፡
አይሁድ በምኲራቦቻቸው የሕግንና የነቢያትን መጻሕፍት /
የብራና ጥቅሎች/ በአንድ ሣጥን ውስጥ ያስቀምጣሉ፡፡
በመሆኑ የጸሎት ሥፍራዎቻቸውን ለትምህርትና ለአምልኮ
ይጠቀሙባቸዋል፡፡ በሕገ ኦሪት የአይሁዳውያን ወደ ቤተ
መቅደስ መሄድ ሕግ ነበር፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ
ተግባራት ከሚሄዱበትም ይልቅ በዓመት አንዴ የሚቀርበውን
መሥዋዕትና መብዓ ለመስጠት ወደ ቤተ መቅደስ ይወጡ
ነበር፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሕግ ሊፈጽም ወደ ቤተ
መቅደስ ይሔድ ነበር፡፡ “ዐሥራ ሁለት ዓመትም በሞላው
ጊዜ እንዳስለመዱ ወደ ኢየሩሳሌም ለበዓል ወጡ” እንዲል /
ሉቃ.2፥42/ “ዕለት ዕለትም በቤተ መቅደስ /ምኩራብ/
ያስተምር ነበር፡፡” /ሉቃ.19፥47/ ፡፡
በዚሁ ዕለት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ
ሰላሙ ድረስ በዕለተ ሰንበት “ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ
ኢየሱስ በሰንበት ቀን ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ” እያለ
ኢየሱስ በአይሁድ ምኩራብ ማስተማሩን እያነሳ ስለሚዘምር
ይህን ሰንበት ለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ
እየገባ ለማስተማሩና በምኩራብ የሚሸጡ የሚለውጡ
ነጋዴዎችን ስለማስወጣቱ ቤተ መቅደሱን ስለማስከበሩ
መታሰቢያ ሆኖ ነው፡፡ማቴ21፡12
ጌታችን በምኩራብ እየተገኘ ሲያስተምር ትምህርቱን ሕግን
አውቆ እንደሚያሳውቅ ሠራዔ ሕግ ስለሆነ በሙሉ ሥልጣንና
ኃይል ያስተምር ነበር፡፡“ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ
ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር
እመሥዋዕትአነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት
እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያውኢትግበሩ ቤተ
አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ
ምኩራቦሙ ወገሠፆሙያርምሙ አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ
ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ወደ
አይሁድ ምኩራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን
አስተማረ፤ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤የሰንበት
ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅምየሰንበት
ጌታዋ ነው ፡፡ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት፤ቤቴስ
የጸሎት ቤት ይባላል (እያለየሃይማኖትን ቃል አስተማራቸው)
፤ ወደ ምኩራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ ዘንድ
ገሠፃቸው፤እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን
ጣዕምና፣ የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነቁ። የዕለተ ሰንበት
መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ቅዱስ ዳዊትም አስቀድሞ በተናረው ትንቢት መሠረት ጌታ
ለቤተመቅደሱ ቀንቶ አጽድቶት ነበር፡፡
መዝ 68፡9
እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡
ትርጉም፦የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና
ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፡፡
በነብዩ በኢሳይያስ እንደተጻፈ ጌታ በአይሁድ ምኩራብ ገብቶ
መጽሐፍ እንዲሰጡት ጠይቆ የሚሰሙት ቃል ዛሬ በጆሯቸው
እንደተፈጸመ እንዲህ ሲል እንደነገራቸው፡፡ “ኢየሱስም
በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ስለ እርሱም በዙሪያው
ባለችው አገር ሁሉ ዝና ወጣ። እርሱም በምኵራባቸው
ያስተምር ሁሉም ያመሰግኑት ነበር። ወዳደገበትም ወደ
ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ
ገባ ሊያነብም ተነሣ። የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት
መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ። “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው
ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና ለታሰሩትም
መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ የተጠቁትንም
ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ
ዘንድ ልኮኛል፡፡” ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ።
መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ
በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር።
እርሱም። “ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈጸመ ”ይላቸው
ጀመር። ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር ከአፉም ከሚወጣው
ከጸጋው ቃል የተነሣ እየተደነቁ። “ይህ የዮሴፍ ልጅ
አይደለምን? ”ይሉ ነበር። እርሱም። ያለ ጥርጥር ይህን
ምሳሌ። “ባለ መድኃኒት ሆይ ራስህን ፈውስ፤ በቅፍርናሆም
እንዳደረግኸው የሰማነውን ሁሉ በዚህ በገዛ አገርህ ደግሞ
አድርግ ትሉኛላችሁ” አላቸው። ሉቃ.4፡14
“ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀመዛሙርቱም ጋር
ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፣ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ፡፡ የአይሁድ
ፋሲካም ቀርቦ ነበር ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡ ወደ
መቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን
ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ የገመድም ጅራፍ
አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፣
የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ፣ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፣
ርግብ ሻጪዎችንም ይህን ከዚህ ውሰዱ፡፡ የአባቴን ቤት
የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም የቤትህ
ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደተጻፈ አሰቡ፡፡
አይሁድ መልሰው ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክ ት
ታሳየናለህ አሉት፡፡ ኢየሱስም መልሶ ይህን ቤተመቅደስ
አፍርሱት በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው ስለዚህ አይሁድ
ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፣
አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን አሉት፡፡ እርሱ ግን ስለ
ሰውነቱ ቤተመቅደስ ይል ነበር፡፡”ዮሐ 2፡12-25 ስለዚህ
ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ይህን እንደተናገረ
አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ፡፡
በፋሲካ በዓልም በኢየሩሳሌም ሳለ፣ ያደረገውን ምልክት ባዩ
ጊዜ ብዙ ሰዎች በስሙ አመኑ ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ
ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም
ነበርና አይተማመናቸውም ነበር፣ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ
ነበርና፡፡