ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

Friday, March 25, 2016

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: ምስጢረ ሥላሴ የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት ምስጢር

ምስጢረ ሥላሴ
የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት ምስጢር
ምስጢር የሚለው ቃል አመሰጠረ፣ ሰወረ፣ አረቀቀ ከሚለው
የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ፍቺውም ረቂቅ፣ ስውር፣ ኅቡዕ
ማለት ነው፡፡ ምስጢር መባሉም የሥላሴን ባሕርይ ፍጡር
መርምሮ የማይደርስበት በመሆኑ፣ በፍጡር ባሕርይ መወሰን፣
መጨረሻውን ማወቅ የማይቻልና ከፍጡር እውቀት አቅም
በላይ በመሆኑ ነው፡፡ ሥላሴ የሚለው ቃል ደግሞ ሠለሰ ሦስት
አደረገ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሦስትነት
ማለት ነው፡፡ ቅድስት ሥላሴ: - ለሥላሴ ቅድስት ብለን
እንቀጽላለን፡፡ ቅድስት ሥላሴ ማለት ልዩ ሦስትነት ማለት
ነው፡፡ ይህም ሦስት ሲሆን አንድ፣ አንድ ሲሆኑ ሦስት ስለሚሆኑ
ልዩ ሦስትነት ተብሏል፡፡
ስለዚህ ነገር መጽሐፈ ቅዳሴያችን ሥላሴ ሦስት ናቸው ስንል
እንደ አብርሃም እንደ ይስሐቅ እንደ ያዕቆብ ማለታችን
አይደለም ሦስት ሲሆኑ አንድ ናቸው እንጂ፣ አንድ ናቸውም
ስንል ቀዳሚ ሆኖ እንደተፈጠረው እንደ አዳም ማለታችን
አይደለም አንድ ሲሆኑ ሦስት ናቸው እንጂ፡፡ /ቅዳሴ
ማርያም/፡፡ ቅድስት ተብሎ በሴት አንቀጽ መጠራቱ ደግሞ
እናት ለልጇ ስለምታዝንና ስለምትራራ ሥላሴም ለፍጥረታቸው
ምሕረታቸው ዘለዓለማዊ ነውና ቅድስት ይባላሉ፡፡
በዚህ መሠረት ምሥጢረ ሥላሴ ማለት የአንድነት የሦስትነት
ምስጢር ማለት ነው፡፡
ይኸውም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም፣ በአካል፣ በግብር
ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ በሕልውና፣ በመለኮት ደግሞ አንድ
ናቸው፡፡ እንደዚህ ባለ ድንቅ ነገር አንድ ሲሆኑ ሦስት፣ ሦስት
ሲሆኑ አንድ ይባላሉና፣ ይህም ልዩ ሦስትነት ረቂቅ እና በሰው
አእምሮ የማይመረመር ስለሆነ ምስጢር ይባላል፡፡
የሰው ልጅ ሁሉን የመመርመርና የመረዳት መብትና ሥልጣን
ከአምላኩ የተሰጠው መሆኑ ቢታወቅም የፈጣሪን ባሕርይና
ጠባዮቹን ለመገንዘብ ውሱን ከሆነው አቅሙ በላይ
ስለሚሆንበት በእምነት ከመቀበል በቀር ሌላ አማራጭ
መንገድ ሊኖረውም አይችልም፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት በማድረግና ከቅዱሳን አባቶች
በተላለፈልን ትምህርት መሠረት ኃያሉ እግዚአብሔርን
በአንድነትና በሦስትነት እናምነዋለን፡፡ እግዚአብሔር አንድ
ሲሆን ሦስት፣ ሦስት ሲሆን አንድ መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት
ያስረዳሉ፡፡
የእግዚአብሔርን አንድነት የምናምነው፡- በፈጣሪነት፣
በአምላክነት፣ በአገዛዝ፣ በፈቃድ፣ በሥልጣን እነዚህን
በመሳሰሉት የመለኮት ባሕርያት ነው፡ /መለኮት ወይም
ማለኹት/ በዕብራይስጥ ቋንቋ መንግሥት ማለት ነው፡፡
በግዕዝ ግን ባሕርይ፣ አገዛዝ፣ ሥልጣን ማለት ነው፡፡ ሦስትነቱን
የምናምነው ደግሞ በስም፣ በግብር /በኩነት/ በአካል ነው፡፡
«እንዘ አሐዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ፣ ይሤለሱ በአካላት
ወይትዋሐዱ በመለኮት» እንዳለ /ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ/፡፡
ሀ/ እግዚአብሔር በአንድነቱ የሚታወቅበት ስሞች
1. ፈጣሪ
2. አምላክ
3. ጌታ
4. መለኮት
5. እግዚአብሔር
6. ጸባኦት
7. አዶናይ
8. ኤልሻዳይ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ለ/ እግዚአብሔር በሦስትነቱ የሚታወቅባቸው ስሞች ደግሞ
1. አብ
2. ወልድ
3.መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡
ሐ/ እግዚአብሔር በግብር ሦስትነቱ የሚታወቀው
1. አብ ወላዲ፣ አሥራፂ በመባል፣
2. ወልድ ተወላዲ በመባል፣
3. መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ በመባል ነው፡፡
የአብ ግብሩ መውለድ፣ ማስረጽ ሲሆን የወልድ ግብሩ መወለድ፣
የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መስረጽ ነው፡፡ አብ ወላዲ፣ ወልድ
ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ /የወጣ፣ የተገኘ/ ነው፡፡ አብ
አባት ነው፣ ወልድ ልጅ ነው፣ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ የሠረፀ
ነው፡፡ /ዮሐ.14-26/፡፡ ሦስቱ አካላት አንድ መለኮት ናቸው፡፡
ሠለስቱ ስም አሐዱ እግዚአብሔር እንዳለ /አባ ሕርያቆስ
በቅዳሴው/፡፡
የአካል ሦስትነታቸውም ለአብ ፍጹም አካል፣ ፍጹም መልክ፣
ፍጹም ገጽ አለው፤ ለወልድም ፍጹም አካል፣ ፍጹም መልክ፣
ፍጹም ገጽ አለው፤ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል፣ ፍጹም
መልክ፣ ፍጹም ገጽ አለው፡፡ እንዲህ ሲባል ግን የሥላሴ አካል
አንደ ሰው አካል ውሱን፣ ግዙፍ፣ ጠባብ አይደለም፡፡ ምሉዕ፣
ስፉሕ፣ ረቂቅ ነው እንጂ፡፡ ምሉዕነታቸውና ስፋታቸው እንዴት
ነው? ቢሉ ከአርያም በላይ ቁመቱ፣ ከበርባኖስ በታች መሠረቱ፣
ከአድማስ እስከ አድማስ ስፋቱ ተብሎ አይነገርም፣
አይመረመርም፡፡ ምክንያቱም ሥላሴ ዓለሙን ይወስኑታል
እንጂ ዓለሙ ሥላሴን አይወስናቸውምና፡፡
ርቀታቸውስ እንዴት ነው? ቢሉ ከሁሉ ነፋስ ይረቃል፡፡ ከነፋስ
መላእክት ይረቃሉ፡፡ ከነፍሳትና ከመላእክት ደግሞ ኅሊናቸው
ይረቃል፡፡ ይህ የኅሊናቸው ርቀት በሥላሴ ዘንድ እንደ አምባ
እንደ ተራራ ነው፡፡ በዚህም ርቀታቸው በፍጥረት ሁሉ ምሉዓን፣
ኅዱራን ናቸው፡፡ ባሕርያቸውም የማይራብ፣ የማይጠማ፣
የማይደክም፣ የማይታመም፣ የማይሞት ሕያው ነው፡፡ «ስምከ
ሕያው ዘኢይመውት ትጉህ ዘኢይዴቅስ ፈጣሪ ዘኢይደክም»
እንዳለ /ቅዲስ ባስልዮስ በማክሰኞ ሊጦን/፡፡
መ/ የኩነት /የሁኔታ/ ሦስትነት
ኩነት በህልውና /በአኗኗር/ እያገናዘቡ በአንድ መለኮት የነበሩ፣
ያሉ፣ የሚኖሩ ናቸው፡፡ እነርሱም፡-
1. ልብነት፡- በአብ መሠረትነት ለራሱ ለባዊ /አዋቂ/ ሆኖ
ለወልድ፣ ለመንፈስ ቅዱስ ልብ፣ ዕውቀት መሆን ነው፡፡
2. ቃልነት፡- በአብ መሠረትነት ለራሱ ነባቢ /ቃል/ ሆኖ ለአብ፣
ለመንፈስ ቅዱስ ቃል መሆን ነው፡፡
3. እስትንፋስነት፡- በአብ መሠረትነት ለራሱ ሕያው ሆኖ ለአብ፣
ለወልድ ሕይወት መሆን ነው፡፡
ስለዚህ በአብ ልብነት ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ህልዋን ናቸው
ያስቡበታል፤ በወልድ ቃልነት አብ፣ መንፈስ ቅዱስ ህልዋን
ናቸው ይናገሩበታል፤ በመንፈስ ቅዱስ አስትንፋስነት አብ፣ ወልድ
ህልዋን ናቸው ሕያዋን ሆነው ይኖሩበታል፡፡
ታላቁ ሐዋርያ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ 1ዐ-17
ላይ «እምነት ከመስማት ነው፣ መስማትም ከእግዚአብሔር
ቃል ነው» ብሎ እንደተናገረው ከላይ የተጠቀሱትን መጠነኛ
ማስረጃዎች በሙሉ ለመገንዘብ እንዲቻል የእግዚአብሔር
እስትንፋስ የሆኑትን የቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃዎችን
መመልከት ያስፈልጋል፡፡ ሥላሴ የሚለው ስም እንዲያው
የመጣ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በአንድነቱና በሦስትነቱ
የሚጠራበት የከበረና ከስም ሁሉ በላይ የሆነ ስም ነው፡፡
ለዚህም የመጽሐፍ ቅዱስ /ዐሥራው ቅዱሳት መጻሕፍት/
ማስረጃዎችን በዝርዝር እንመለከታለን፡፡
ምስጢረ ሥላሴ በብሉይ ኪዳን
1. እግዚአብሔርም አለ፡- «ሰውን በመልካችን
እንደምሳሌአችን እንፍጠር» ዘፍ.1-26 እዚህ ላይ
«እግዚአብሔርም አለ» ሲል አንድነቱ፣ «እንፍጠር» ሲል
ከአንድ በላይ መሆኑን ግሱ /ቃሉ/ ያመለክታል፡፡ ሦስት
መሆኑን ግን በዚህ ቃለ አልወሰነም፡፡
2. እግዚአብሔር አምላክ አለ፡- «እነሆ አዳም መልካሙንና
ክፉውን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ» ዘፍ.3-22 በማለት
ባለቤቱን አንቀጽን አንድ፣ አሳቡን ዝርዝሩን የብዙ አድርጐ
ይናገራል፡፡ «እግዚአብሔር አለ » ሲል አንድነቱን፣ «ከእኛ እንደ
አንዱ ሆነ» ሲል ደግሞ ከአንድ በላይ መሆኑን ያመለክታል፡፡
በዚህ ቃል ግን ሦስትነቱን አልወሰነም፡፡
3. እግዚአብሔርም አለ፡- «ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር
እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው፡፡»
ዘፍ.11.6-8፡፡ «እግዚአብሔር አለ» ብሎ አንድነቱ፣ «ኑ
እንውረድ» ብሎ ደግሞ ከአንድ በላይ መሆኑን ያመለክታል፡፡
4. «በቀትርም ጊዜ እግዚአብሔር ለአብርሃም ተገለጠለት
አብርሃም ሦስት ሰዎችን በፊቱ ቆመው አየ» ዘፍ.18.1-15
በማለት እግዚአብሔር አንድ መሆኑንና ሦስት አካል ያለው
መሆኑን ወስኖ ያስረዳናል፡፡
5. «እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅም አምላክ፣
የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር ነኝ» ዘጸ.3-6 ሲል
«አምላክ፣ አምላክ፣ አምላክ» ብሎ ሦስትነቱን፣ «እኔ
እግዚአብሔር ነኝ» ብሎ ደግሞ አንድነቱን ገልጾ ተናግሯል፡፡
6. «የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች፣
በእግዚአበሔርም ቃል ሰማዮች ጸኑ፣ ሠራዊታቸውም ሁሉ
በአፉ እስትንፋስ» መዝ.32-6፡፡
7. ነቢዩ ኢሳይያስም «ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት
እግዚአብሔርን በልዑል ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ አየሁት...
ሱራፌልም ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር
ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያሉ ይጨሁ ነበር፡፡»
ኢሳ.6.1-8 በማለት ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ብሎ ሦስትነቱን፣
የሠራዊት ጌታ እግዚአበሔር ብሎ ደግሞ አንድነቱን አይቶ
መስክሯል፡፡
ምስጢረ ሥላሴ በሐዲስ ኪዳን
በአዲስ ኪዳንም የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት /ምስጢረ
ሥላሴ/ በምስጢረ ሥጋዌ በሚገባ ታውቋል፡፡ ይኸውም
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተለየ አካሉ /ሰው
ሆኖ/ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ፣ አብ በደመና ሆኖ «የምወደው
ልጄ ይህ ነው የሚላችሁን ስሙት» ሲል፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ
በራሱ ላይ በርግብ አምሳል ሲወድቅበት ታይቶአል፡፡ /
ማቴ.3.16-17፣ ማር.1.9-11፣ ሉቃ.3.21-22፣
ሉቃ.1.32-34/ በዚህም እግዚአብሔር በአካል ሦስት
እንደሆነ ተገልጿል፡፡
መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤልም እመቤታችንን ባበሠራት
ጊዜ «መንፈስ ቅዱስ በአንች ላይ ይመጣለ፣ የልዑልም ኃይል
ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንች የሚለደው ቅዱሱ
የአግዚአብሔር ልጅ ይባላል፡፡» ብሎ የሥላሴን ሦስትነት
በግልጽ ተናግሯል፡፡ሉቃ.1-35፡ ፡
እራሱ ባለቤቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የማዳን ሥራውን
ፈጽሞ ከማረጉ በፊት ለደቀመዛሙርቱ ቋሚ ትዕዛዝ ሲሰጥ
«እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ
ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ... ደቀመዛሙርት አድርጓቸው»
ብሏል ማቴ.28.19-20፡፡
«ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ
የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለ እኔ
ይመሰክራል፡፡» ብሏል ዮሐ.15.26፣ 14.16-17፣ 25-26፡፡
ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች
በጻፈው መልእክቱ የሥላሴን ሦስትነት ገልጾ ተናግሮአል፡፡
«የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔርም ፍቅር፣
የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን» 2ኛ
ቆሮ.13-14፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በጻፈው መልእክቱ «በሰማይ
የሚመሰክሩ ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም አብ፣ ልጁም፣ መንፈስ
ቅዱስም ናቸው፡፡ 1ኛ.ዮሐ.5-7፡፡ እነዚህ ሦስቱም አንድ
ናቸው፡፡» በማለት የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት በግልጽ
ያስረዳናል፡፡ /ይህንን ቃለ በ1886 ዓ.ም ከታተመው
የአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ እትም ይመልከቱ/፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ ደግሞ የኪንግ ጀምስ የእንግሊዝኛውን መጽሐፍ
ቅዱስ እትም ብንመለከት ይህነን አማናዊ የሥላሴን ምስጢር
በትክክል ይመሰክራል/፡፡
ወንጌላዊው ቅድስ ዮሐንስም «በራእዩ እነሆም በጉ በጽዮን
ተራራ ቆሞ ነበር፣ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱም ስም
የመንፈስ ቅዱስም ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ
አርባ አራት ሺህ ነበሩ» ራእ.14-1፡፡ በማለት በገጸ-ልቡናቸው
ስመ ወላዲ፣ ስመ ሠራፂ የተጻፈባቸውን የሥላሴን ልጆች
አይቷል፡፡ በዚህም የሥላሴን ልዩ ሦስትነት በግልጽ መስክሯል፡፡
ከላይ በዝርዝር የተገለጹትና እነዚህን የመሳሰሉት ሁሉ
እግዚአብሔር አንድነቱንና ሦስትነቱን የገለጸባቸው ምስክሮች
ናቸው፡፡
የምስጢረ ሥላሴ ትምህርት/ምስክርነት በሊቃውንት
ምስጢረ ሥላሴ በሊቃውንትም ትምህርት የአብ መላዲነት፣
የወልድ ተወላዲነትና የመንፈስ ቅዱስ ሠራፂነት ነው፡፡ አብ
ተወላዲ አይባልም፣ ወልድ ወላዲ አይባልም፡፡ ወላዲ፣ ተወላዲ፣
ሠራፂ የሚባሉት ቃላት ሦስት አካላት ለየብቻ የሚታወቁባቸው
የግብር ስሞች ናቸው፡፡ ሊቃውንት አባቶቻችን በሃይማኖተ
አበው ምሳሌ ሲመስሉ ምሳሌ ሠይሐጽጽ /ጎደሎ ምሳሌ/
በማለት አንዳንድ ምሳሌዎችን ያቀርባሉ፡፡ ምሳሌውንም
ጎደሎ የሚሉበት ምክንያት ለምስጢረ ሥላሴ ሙሉ በሙሉ
ምሳሌ የሚሆን ሲያጡ ነው፡፡ ይህንንም የሥላሴን ሦስትነትና
አንድነት ሐዋርያት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በተማሩት
መሠረት በሚከተሉት ሦስት ምስሌዎች በሚገባ ገልጸውታል፡፡
የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በነፋስ፣ በፀሐይ፣ በአሳት
ይመሰላል፡፡
1. የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በሰው ምሳሌ ይገለጻል፡፡ ሰው
በነፍሱ ሦስትነት አለውና ነው፡፡ የኸውም ልብነት፣ ቃልነት፣
ሕይወትነት ነው፡፡
ስለዚህ በሰው ነፍስ፡- በልብነቷ አብ፣ በቃልነቷ ወልድ፣
በሕይወትነቷ መንፈስ ቅዱስ ይመስላሉ፡፡ የነፍስ ልብነቷ፣
ቃልነቷን፣ ሕይወትነቷን ከራሷ ታስገኛለችና፡፡ ቃልና ሕይወት
ከአንዷ ልብ ስለተገኙ በከዊን /በመሆን/ ልዩ እንደሆኑ
በመናገርም ይለያሉ፡፡ እንዲሁም አብ ወልድን በቃል አምሳል
ወለደው፣ መንፈስ ቅዱስንም በእስትንፋስ አንጻር አሰረጸው፡፡
ነፋስ ስትገኝ በሦስትነቷ በአንድ ጊዜ ተገኘች አንዷ ልብነቷ
ቀድሞ ቃልነቷና እስትንፋስነቷ በኋላ አልተገኙም፡፡ ሰው በዚህ
አኳኋን በነፍሱ የሚመስለው ስለሆነ እግዚአብሔር «ሰውን
በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር» ዘፍ.1-26 ብሎ
ተናገረ፡፡ ስለዚህ ነፍስ ልብ፣ ቃል፣ እስትንፋስ /ሕይወት/ መሆን
የከዊን /የመሆን/ ሦስትነትን ነገር በተናገረበት ድርሳን እንዲህ
አለ፡፡
«አምላክ ውእቱ አብ፣ ወአምላክ ውእቱ ወልድ፣ በአምላክ
ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ወኢትበሀሉ ሠለስተ አማልእክተ አላ
አሐዱ አምላክ ብሏል፡፡ ይህም ማለት አብ አምላክ ነው፣
ወልድም አምላክ ነው፣ መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው ነገር
ግን ሦስቱ አማልክት አይባሉም፣ አንድ አምላክ እንጂ፡፡»
ማለት ነው፡፡
ሥላሴ በፀሐይ ይመሰላሉ፣ ፀሐይ አንድ ሲሆን ሦስትነት
አለው፡፡ ይኼውም ክበቡ ብርሃኑ፣ ሙቀቱ ነው፡፡ ክበቡ አብ፣
ብርሃኑ ወልድ፣ ሙቀቱ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ «አብ
ፀሐይ፣ ወልድ ፀሐይ፣ መንፈስ ቅዱስ ፀሐይ አሐዱ ውእቱ ፀሐየ
ጽድቅ ዘላዕለ ኩሉ» እንዳለ /ቅዱስ አባ ሕርያቆስ/፡፡
ሥላሴ በእሳት ይመሰላሉ፡፡ እሳት አንድ ሲሆን ሦስትነት አለው፡፡
ይኼውም አካሉ፣ ብርሃኑ፣ ዋዕዩ /ሙቀቱ/ ነው፡፡ በአካሉ አብ፣
በብርሃኑ ወልድ፣ በዋዕዩ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ «አብ
እሳት ወልድ እሳት ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ እሳተ
ሕይወት ዘእምአርያም፡፡» እንዳለ /አባ ሕርያቆስ/ «አምላክህ
እግዚአብሔር የሚባላ እሳት ቀናተኛም አምላክ ነው፡፡» ዘዲ.
4-24፡፡
ሥላሴ በፀሐይና በእሳት መመሰላቸውንም ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ራሱ ለሐዋርያት «እኔና አባቴ መንፈስ ቅዱስም
እሳትና ነበልባል ፍሕምም ነን» በማለት አስተምሮአቸዋል፡፡
ሐዋርያትም ይህንን ጽፈውት ቀሌመንጦስ በተባለው መጽሐፍ
ይገኛል፡፡ /ቅዳሴ ሠለስቱ ምእትን/ ይመልከቱ፡፡ ነገር ግን
እነዚህ ሁሉ አንድ ነፍስ፣ አንድ ፀሐይ፣ አንድ እሳት፣ እንጂ ሦስት
ነፍስ፣ ሦስት እሳት፣ ሦስት ፀሐይ አይባሉም፡፡ ሥላሴም በአካል፣
በስም፣ በግብር ሦስት ቢባሉ በባሕርይ፣ በሕልውና፣ በፈቃድ፣
በመለኮት አንድ ናቸው አንጂ እማልክት አይባሉም፡፡
የቂሣርያው ሊጳጳስ ቅዱስ ባስልዮስ «እንዘ አሐዱ ሠለስቱ
ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ ይሤለሱ በአካላት ወይትዋሐዱ
በመለኮት» እንዳለ፡፡ ይህም ማለት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ
አንድ ሲሆኑ ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ ናቸው፡፡ በአካል ሦስት
ሲሆኑ በመለኮት አንድ ናቸው፡፡ ማለት ነው፡፡ ይህም ሰው
በሚረዳው መጠን ለመግለጽ ያህል ነው እንጂ ከፍጥረት ወገን
ለሥላሴ የሚሆን በቂ ምሳሌ የለም፡፡ የተመሰለ ቢመስል
ሕጸጽ /ጎደሎ/ ምሳሌ ነው፡፡

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ ያዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንታ መጻጒዕ

እንኳን አደረስቹ ያዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንታ መጻጒዕ
ለ 38 ዓመት በአልጋ ላይ ተኝቶ የምኖር አንደ ስው ነበረ
እርሱም መጾጒዕ ይበላል
((ዮሐ5፥1-11)) ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነብረ ኢየሱስም
ወደ አየሩሳሌም ወጣ በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ
በዕብራይስጥ " ቤተ ሳይዳ" የምትባል አንዲት መጠመቂያ
ነበሪች አምስትም መመላለሻ ነበረባት በእነዚህ ውስጥ
የወኃውን መንቀሳቀስ እያጠበቁ በሽተኞችና፣
ዕወሮች፣አንካሶችም ስውነታችውም የስለለ በዙ ሕዝብ ይተኙ
ነብር አንደንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂ ያይቱ ወርዶ
ውኃውን ያናውጥ ነበርና እንግዲህ ከወኃውን መናወጥ በኋላ
በመጀመሪያ የገቦ ከማናቸው ካላበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር
በዚያም። " ከሠላሳ ስምንት " ዓመት ጀምሮ ያተመም አንድ
ስው ነበረ ኢየሱስ ይህን ስው ተኝቶ በየ ጊዜ እስከ አሁን
ብዙዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ ልትደን ትወዳላህን?
አለው
ድውዮም፦ አዎ ጌታ ሆይ ውኃው በተናውጠ ጊዜ በመጠቂያይን
ወስጥ የሚያምኖሪኝ ስው የለኝም ነባር ግን እኔ ስመጣ ሳላሁ
ሌላው ቀድመኝ ይወርዳል ብሎ መለስለት፣
ኢየሱስ ፦ ተነሣና አልጋህን ተሽክመህ ሂድ አለው፣ወዲያውም
ስውዬው ዳነ አልጋውንም ተሽክመሞ ሄደ።
ያም ቀን " ስንበት" ቀን ነበረ ሰለዚህ አይሁድ የተፍወስውን
ስው " ስንበት" ነው
አልጋውን ልትሽከም አልተፍቀደልህም አሉት
እርሱ ግን ያደነኝ ያስው "አልጋውን ተሽክመህ ሂድ" አለኝ ብሎ
መላስላቸው።
((ማቴ9÷1)) በታንኳም ገብቶ ተሻገረና ወደ ገዛ ከተማው
መጣ እነሆም በአልጋ የተኝ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ ኢየሱስ
እምነታቸውን አይቶ ሽባውን አንተ ልጅ አይዛህ ኃጢአትህ
ተስረያችልህ አለው
((መዝ 40፥3)) እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳላ ይረዳዋል
መኝታውንም ሁሉ ከበሽታው የተነሣ ይለውጥለታል።
አቤቱ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ በየጸበሉ በሆስፒታሉ
የታመሙትን ምህረትህን ለሚናፍቁ የምህረት እጅህን
ዘርጋላቸው
የሐዋሪያት የነብያት የቅዱሳን አበው ጸሎት ልመና የተቀበለከ
አምላክ የእኛንም ተቀብለ ዘንድ አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር ይቆየን ኣሜን

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: እመቤታችን እና ሚሪና

እመቤታቸን እና ሚሪና፡፡
ይህ ደንገተኛ ተዓምር የተከሰተዉ በሶርያ ነዉ፡፡
ወይዘሮ ሚሪና ኦርቶዶክስ እና ጠንካራ ክርስትያን
ናት፡፡መጸለይ በጣም የምትወደዉ ነገር ነዉ
በጣም፡፡ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት መቆም
መጸለይ እንደዚሁም መዘመር ሁሌም
የምታደርገዉ ነገር ነዉ፡፡የምትጸልየዉ ለራሷ ብቻ
አይደለም ለሁሉ ሰዉ እንደዚሁም ለዓለም
ህዝቦች ነዉ በተለየይ ከእመቤታችን ሥዕል ፊት
መጸለይ ትወዳለች፡፡አንድ ቀን ግን ያልጠበቀችዉ
ነገር ተከሰተ ለታመመችዉ ጓደኛዋ ልትጸልይ ወደ
ከሌሎች ጓደኞቿ ጋር ሆና ወደ ታመመችዉ ቤት
ሄደች፡፡ከዚያም በእጇ ላይ ያልታበ ድንገተኛ
ብርሐን መታየት እና የዘይት መፍሰስ ተከሰተ
ስለሆነም የታመመችውን ጓደኛዋን ስትነካት
ተፈወሰች፡፡ሁሉም በጣም ተደነቁ፡፡ቀጥለውም
አጅበዋት ወደ ቤት ሄዱ ወደ ውስጥ እንደ ገቡ
ሁሌ ሚሪና የምትጸልይበት የእመቤታችን ሥዕል
ዘይት ማፍሰስ ጀመረ የሚፈሰውም ከእመቤታችን
አይኖች ነበር ደመና የከበበውም ይመስል
ነበር፤ሁሉም ከመደነቃቸዉ የተነሳ ለሚያውቋቸዉ
ሰዎች ሁሉ መናገር ጀመሩ ይህ ዜና ለሶርያ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትርያርክ እንደዚሁም
ለግሪክ ኦርቶዶክስ ጳጳስ ለካቶሊካውያን ጳጳሳት
እንደዚሁም የድንግል ማርያም አማላጅነት
ለሚቀበሉ ሁሉ ተዳረሰ፡፡ከዚያም ልክ ጌታ
ሲሰቀል እንደ ነበረዉ የስቃይ ምልከት መታየት
ጀመሩ ማለትም ግንባሩ ላይ የነበሩት ቁስሎች
እንደዚሁም እጆቹ እግሮቹ ላይ በሚስማር
የተወጉበት ጎኑ ላይ የተወጋበት አይነት በሚሪና
አካላት ላይ መታየት ጀመሩ፡፡እነዚህ ምልክቶች
ሲታዬ በጣም ትታመም ነበር ከዚያም በራዕይ
ጌታችንን እና እመቤታችንን ታይ ነበር፡፡
መልዕክትም ይነግሯት እና ሰዉ ሁሉ ወደ ንሰሐ
እና ወደ ቅዱስ ቁርባን እንዲቀርቡ ለሰዉ ሁሉ
ከሰማይ የመጣውን መልዕክት ትናገር ነበር፡፡
በሶርያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
ፓትርያርክ ትዕዛዝ መሰረት በሶርያ ወደ ሚገኘዉ
የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል
እንድትመጣ እና እዚያ ከዘይቷ ለሰዉ ሁሉ
እንድትሰጥ ተነገራት እርሷም መጣች ታላላቅ
ተዓምራትም ተፈጸሙ ከሰማይ የመጣላትን
መልዕክቶች ለሰዉ ሁሉ ተናገረች፡፡የአምላክ
እናት ተገልጣላት መልዕክት ነገረቻት ‹‹‹ልጄ
ሚሪና ዘይት በፈሰሰበት ሥዕሌ ፊት ሁሉም ሰዉ
ሻማ አብርቶ ይጸልይ ጸሎቱም ይሰማል
አባዝታችሁም ለሰዉ ሁሉ አዳረርሱ እኔ በተባዛዉ
ሥዕል ላይ ተዓምራትን አደርጋለሁ››› አለቻት
ይህንንም መልዕክት ለሰዎች ተነናገረች ድንግል
እንዳለችወው ብዙ እና ድንቅ ተዓምራት ተገለጡ
እመቤታችን በወይዘሮ ሚሪና ላይ የገለጠችዉ ተዓምር
ከሶርያ አልፎ በዓለም ሁሉ ተዳረሰ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ካቶሊኩ እንደዚሁም ሌሎች እምነት ተከታዮች በድንግል
ማርያም ሥዕል ፊት ከዓለም ተሰባስበዉ መዘመር መጸለይ
ጀመሩ፡፡እናታችን ድንግል ማርያም የፍቅር እናት ስለሆነች
ከማንኛውም ኃይማኖት የመጣውን ሰዉ በፍቅር ፈውሳ ወደ
ቤቱ ትሸኘዋለች፡፡በወይዘሮ ሚሪና ቤት ጠባብ ቢሆንም
በድንግል ተዓምር ለሁሉም በቃ፡፡ ጌታችን እና እመቤታችን
እንደ ገና መልዕክት በህልሟ ነገሯት፡፡‹‹ጌታችን በትልቅ
ተራራ እና በሚያምር ገነት በሆነ ቦታ ላይ ታያት ስለሆነም
ጌታ እንዲህ አላት ‹‹‹ልጄ የተባረክሽ ነሽ አኔ ሰማይን እና
ምድር የሰውን ልጆች ሁሉ የፈጠርኩ ጌታ አምላክ ነኝ
ለሰውም ልጆች መዳን መከራን የተቀበልኩ ነኝ በደሜ
ፈሳሽነት ዓለም ድኗል›››ብሏት ተሰወረ፡፡ከዚያም ከጥቂት
ደቂቃዎች በኋላ ነቃች እመቤታችን እንደገና ከቤቷ አጠገብ
ባለዉ ዛፍ ላይ እንደምትገለጥ በድምጽ ነገረቻት ወደ ዛፉ
ሄደች በሚያስደነግጥ አእነና በሚያስፈራ ግርማ እመቤታችን
ከሰማይ ወረደች ሚሪናም በጣም ደነገጠች ወዲያውኑ
እየሮጠች ወደ ቤቷ ገባች በሚቀጥለዉ ቀን የእግዚአብሔር
መልዓክ መጥቶ ‹‹‹የጌታ እናትን ለምን ታቃልያለሽ እርሷ
መልዕክት ልትነግርሽ እና ሰውንም ልትባርክ ነበር በዛፉ ላይ
የተገለጠችዉ››› አላት ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ እመቤታችን
በህልም ተገልጣላት ‹‹‹ለምን ያልኩሽን አላደረግሽም?
አይንሽን ብርሐን እወስደዋለሁ፡፡›››አለቻ ት በመሆኑም
ሚሪና አይኗን ስትገልጥ ታውራ ነበር በጣም ደንግጣ
በኃይለኛዉ ማልቀስ ጀመረች ነገር ግን በሰራችዉ ስራ
ስለሆነም እመቤታችን ይቅርታ ጠየቀቻት በመታወሯም
አላማረረችም ነበር፡፡በሶስተኛውም ቀን ነጭ ብርሐን ማየት
ጀመረች ፊቷ በወይራ ቅዱስ ዘይት መሞላት ጀመረ ከአፏም
ዘይት ይወጣ ነበር ምንጩ አይታወቅም ግን ሚሪና ባለቤቷን
‹‹‹አፌን አሽትልኝ››› አለችዉ እርሱም ሲያሸተዉ እንደ አበባ
አይነት ልዬ መዓዛ ያለዉ ነበር ከዚያም አይኗን የሆነ እጅ 3
ጊዜ ሲነካት ማስታወክ ጀመረች የምታስታውከዉ ቅዱስ
ዘይት ነበር ምግብም ((ለ3 ቀን አልበላችም ምግቧ ጸሎት
ነበር))ከዚያም አይኗ በራ እናቷ እና ባለቤቷ ተደሰቱ እልል
ብለዉ አመሰገኑ፡፡ወይዘሮ ሚሪና የምትኖርበት ቤት
ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳውሎስ ለ3 ቀን ታውሮ ለተቀመጠበት
ቤት ቅርብ ነዉ ይህን ነገር ከሚሪና ጋር በመገጣጠሙ ካህናቱ
ተደሰቱ፡፡እመቤታችንም ለሚሪና ተገልጣላት ‹‹‹ልጄ አሁን
ከስህተትሽ ተምረሻል ስለዚህ ስጦታ እሰጥሻለሁ››› አለቻት
ይህ ነገር ሚሪና አልገባትም ነበር ነገር ግን ከጥቂት ወራት
በኋላ የአንዲት ቆንጆ ሴት ልጅ እናት ሆነች፡፡ከቀን ወደ
ቀንም የወይዘሮ ሚሪና መልክ እያማረ መሄድ ጀመረ፡፡
በቀጣዩ ቀን በሰማዕታት አለቃ በቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል
የሶርያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያነን እንደምትመጣ
ተነገረ 10,000 ያህል ሰዉ ተሰበሰበ በዚህም ሁኔታ ላይ
እያለች ከፊቷ ከእጇ ከአይኗ ዘይት መውጣት ጀመረ ከዚያም
የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ተገለጠችላት መልዕክትም
ነገረቻት ‹‹‹‹‹‹‹‹ ቤተክርስትያን በምድር ላይ ያለች መንግስተ
ሰማያት ነች፡፡በህዝቡ መሰባሰብ ላይ አምላካችን
እግዚአብሔር በጣም ደስተኛ ነዉ በዚህ፡፡እኔም የኔ
ትውልዶች የሆኑትን ሁሉ ባንቺ ምሳሌነት
አስተምራቸዋለሁ፡፡›››› ›››› አለቻት ይህንን መልዕክት
ለሰዉ ሁሉ አባ ማሉሊ በተባለ ካህን አማካኝነት አስተላለፈች
ይህ አባት የምትናገራቸውንም መልዕክቶች በሙሉ ይጽፍ
ነበር፡፡ወይዘሮ ሚሪና ከንቱ ውዳሴ ስለመማትወድ ቶሎ ብላ
ወደ ቤቷ ትመለስ ነበር፡፡ከስር የምትመለከቱት ፎቶ የቅዱስ
ዘይቱ መፍሰስ ነዉ፡

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ: {መልክአ ኪዳነ ምህረት }

በስም ኣብ ወወልድ ወመንፍስ ቁዱስ ኣሃዱኣምላክ ኣሜን
እንኳን ኣደርሳቹሁ ኣደርስን ለእናታችን ለቅድስተ ቁዱሳን
ለኪዳን ምህርት ክብር በዓል ቀኑ የበርከት ቀን ይሁኑላቹ
ኣሜን።
{መልክአ ኪዳነ ምህረት }
፩ እግዚአብሔር ኣብ። እመቤቴ ኪዳን ምህርት ሆይ በአካል
ሦስት ሲሆን በመለኮታዊ ባሕርዩ በኣንድነቱ ጸንቶ የሚኖር
የብርሃን መገኛ እሱ እግዚአብሔር አብ ለቃል ኪዳንሽ
የተሰጠው ልዩ ክብር ብሩህ አድርጒ ያሳየኝ ዘንድ የቸርነቱ ጸዳለ
ብርሃን ዓይነ ልቡናዬን ያብራልኝ።
የቃል ኪዳኗ እመቤቴ ሆይ : ከእግዚአብሔር በታች በስማይም
በምድርም እንቺ የሁሉ እመቤት ነሽ እኮን።
፪ ለዝክረ ስምኪ። እመቤቴ ኪዳን ምህርት ሆይ በብርሃነዊው
ኮኮብ ለተመስለው ስም ኣጠራርሽ ስለምታ ይግባል ፤በጨለማ
ለሚኖሩ ሕዝቦች ብርሃኑን አብርቶላቸዋልና።
የቃል ኪዳኗ እመቤቴ ሆይ የኣምላክ ቃል ኪዳኑ መዛግብት
በዕለተ ዓርብ የተገኘውን የደኅንነታችን ተስፋ ያስገኘሽ ዕውነተኛ
መዝገብ ነሽ እኮን። ኣባታችን ቀዳማዊ ኣዳም በጭንቅና
በኀዘን ከገነት ወጥቶ በተስደደ ጊዜ ከልቡነው ኅዘን
ተረጋግቶብሻልና።
፫ ለስእርተ ርእስኪ ። እመቤቴ ኪዳን ምህርት ሆይ ያለ
ማቋረጥ ሰማያዊ ጠል ለረበረበበትና የሐር ጉንጉን
ለሚመስለው ስእርተ ርእስሽ ሰላምታ ይገባል ።
የቃል ኪዳኗ እመቤቴ ሆይ ሞትን የሚያስከትል ፤እንደ ኤልያስ
ሥጋዊ ሕይወት ያይደለ የነፍሴን ሕይወት ይስጠኝ ዘንድ በታላቅ
ጉባዔ ፊት የምሕረት ቃል ኪዳን በገባልሽ ልጅሽ ዘንድ አማልጅ
ኣሜን።
እመቤታችን ኪዳን ምህርት ሆይ እኛ ሃጥያቶኞች ከልጅሽ
ከወዳጅሽ ከእየሱስ ከርስቶስ ኣስታሬቂን ሃጥያታችን የበዛ
ግብራችን የከፊ በሃጥያት ለኣፍንጫ የሚከረፍፍ ነውና ልጅሽ
በቸርነቱ እና በይቅርባይኖቱ ያጥበን ዘንድ ኣማልጅን ጾማችን
ጾሎታችንም ይቀበልልን ኣሜን ።
ወስብሃት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ
ክብር ኣሜን ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣን እግዚአብሔር
ክብር ምስጋና ይግባው ለቅድስተ ሰላሴ ኣሜን
ኢትየጽያ ሃገራችን ኦርቶዶክስ ሃይማኖታችን እግዚአብሔር
ይጠብቅልን ኣሜን ።

#ኆኅተ_ብርሃን

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ
16 16 16 16 16
#ኆኅተ_ብርሃን
16 16 16 16 16
21
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ኆኅተ ብርሃን ማለት የብርሃን ደጅ፣ የብርሃን መውጫ
ማለት ነው፡፡ አማናዊውን ብርሃን ክርስቶስን ስላስገኘች ኆኅተ
ብርሃን የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፡፡ በዚህ
ጽሑፍ ብርሃን በቤተ ክርስቲያን አነጋገር ምን እንደ ሆነ
እመቤታችን ኆኅተ ብርሃን የመባሏን ምስጢር እግዚአብሔር
አምላክ በገለጠልን መጠን እንመለከታለን፡፡
በትውፊታችን ብርሃን የሚለውን ቃል በብዙ መልኩ
ተጠቅመንበታል፡፡ በዓላትን ስንጠራ ብርሃን የሚለውን ቅጽል
ከፊት አስቀድመን ብርሃነ ልደቱ፣ ብርሃኑ ጥምቀቱ፣ ብርሃነ
ትንሣኤው… ወዘተ እያልን እንጠራለን፡፡ የእግዚአብሔር
መላእክትን የብርሃን መላእክት (አጋንንትን የፅልመት/
የጨለማ
መላእክት) እንላለን፡፡ ክፉ ነገር የበዛበትን ዘመን የጨለማው
ዘመን፣ በስኬት የታጀበውን ደግሞ ወርቃማው /የብርሃን
ዘመን
(ዘመነ ብርሃን) በማለት እንሰይመዋለን፡፡ መልካም ሥራ
የሠሩ
ነገሥታትንና ሹማምንትን ስማቸው ላይ ‘ብርሃን’ን እንቀጽላለን
እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዚኢትዮጵያ እንድንል፡፡ ቀለምን
ለመቀበል
የፈጠነና የሚመረምር አእምሮ ያለውን ሰው ብሩህ (ብርሃናማ/
Bright) አእምሮ አለው እንላለን፡፡ ከብርሃን ጋር ባለው
ትውፊትና ሥርዓት የሰማይ ብሩህ ሕይወታችንን
እንዲመስልልን
ሻማን በፀሎት ጊዜ እናበራለን፡፡ በቅዱሳት ሥዕላት ላይ ቅዱሳን
ሲሣሉ በብርሃን ይከበባሉ፡፡ ወይም ብርሃን ከአካላቸው ሲወጣ
ይታያል፡፡ ‘ማኅቶቱ ለሥጋከ ዐይንከ ውእቱ’ (የሰውነትህ
መብራት ዐይንህ ናት) እንዲል ወንጌል (ማቴ.6፡22)፡፡ ዐይኑ
ማየት የተሳነውን ብርሃኑን አጣ እንለዋለን፡፡ ወላጆች ልጆችን
ሲወልዱ ስኬት ካገኛቸው ወይም በልጆቹ ይሳካልናል ብለው
ካሰቡ የልጆቹን ስም ብርሃኑ፣ ብርሃኔ….ወዘተ ብለው
ይሰይማሉ፡፡ ለመሆኑ ብርሃን ምንድን ነው?
21
ብርሃን በዕለተ እሑድ ከተፈጠሩ ከ8ቱ ፍጥረታት
አንዱ ነው፡፡ በዕለተ እሑድ መላእክትን ፈጥሮ ማን ፈጠረን
ብለው በተሸበሩበት ጊዜ ከበስተምስራቅ በኩል በብርሃን እንደ
ተገለጠላቸው መጽሐፈ አክሲማሮስ ዘኤጲፋንዮስ ይገልፃል፡፡
በዚህ የመጀመሪያ ዕለት ከተፈጠሩት መካከል እሳት አንዱ
ነው፡፡
ከላይ የተገለፀውን የብርሃን አፈጣጠር ስንመለከት
ከድኅነትና ከእውቀት ጋር ማዛመድ እንደሚቻል እንገነዘባለን፡፡
ለምሳሌ መላእክት የዕውቀት ገላጭ ፈጣሪን ሳያውቁት
ቆይተው በብርሃን ተገልፆ ዐወቁት፡፡ እነርሱ መርምረውት
ሳይሆን
እርሱ ተገልጦ አገኙት፡፡ ሳጥናኤል “እኔ ፈጠርኳችሁ” ብሎ
በኃጢአት ጨለማ ሊያጠፋቸው ሲፍጨረጨር ብርሃነ
መለኮቱን
ገልፆ አዳናቸው፡፡ ስለዚህ ብርሃን መጀመሪያ ሲፈጠር
ከማሳወቅና ከሃይማኖት (ከድኅነት) ጋር ነው፡፡ የእውቀት ሁሉ
መጀመሪያ እግዚአብሔርን ማወቅ፣ የሃይማኖት መጀመሪያ
በፈጣሪ፣ በቅድስት ሥላሴ ማመን ነውና ይህ ሆነ፡፡ ክርስትና
የመገለጥ ሃይማኖት ነው፡፡ ካለመገለጥ ክርስትና የለም፡፡
ምክንያቱም አምላክ ራሱን እንደ ችሎታችን ካልገለጠ በቀር
በምርምር፣ በሥጋዊ ጥበብ እርሱን ማወቅ አይቻልም፡፡ ለዚህ
ነው እንደ መላእክቱ፣ እንደነ ቅዱስ ገብርኤል መጀመሪያ
ማመን
ይቀድማል፣ ከዛ ዕውቀትን እርሱ ይገልጥልናል የምንለው፡፡
ከዚህ በመነሣት ምንም እንኳን በትውፊታችን ብርሃንን ለብዙ
በጎ ነገሮች እየቀጸልን ብንጠቀምም በዚህ ጽሑፍ የብርሃንን
ዕውቀትነትና ድኅነትነት ብቻ አንሥተን የእመቤታችንን ኆኅተ
ብርሃንነት በአጭሩ እናያለን፡፡
21
ሰው ዐውቆ እንዳይጸድቅ ዘወትር የሚታትረው
የድንቁርና አባት ዲያቢሎስ አዳም በዕፀ በለስ ላይ የነበረውን
ዕውቀት በማሳሳት ከነበረው ብርሃናማ ሕይወት እንደ እርሱ
በጨለማ እንዲኳትን አደረገው፡፡ የሰው ልጅም ከዚያ በኋላ
ባለማወቅና በኃጢአት ጨለማ ባዘነ፡፡ ‘ሕዝቤ ዕውቀትን
ከማጣት የተነሣ ጠፍቷል’ እንዲል ነቢዩ ሆሴዕ፡፡ (ሆሴ.4፡6)፡፡
የሰው ሕይወቱ የጨለማ ሕይወት (የጥፋት) ተባለ፡፡
እውነተኛው ብርሃን (አዳኝ) እስኪመጣ የሰው ልጅ ጽድቁ ሁሉ
እንደ መርገም ጨርቅ ሆነ፡፡ (ኢሳ.64፡6)፡፡ ነገር ግን
ንስሐውን
ዐይቶ ለአዳም እንደሚያድነው ቃል የገባለት ፈጣሪ፥ እንደ
ሚወርድ እንደሚወለድ ለነቢያቱ ገለፀላቸውና እነሱም ይህን
ተናገሩ፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ በጨለማ ውስጥና በሞት
ጥላ ያለ ሕዝብ ብርሃንን አየ ሲል ተነበየ፡፡ (ኢሳ.9፡2)፡፡
ሶሪያዊው ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬምም ‘ሕዝብ ዘይነብር ውስተ
ጽልመት ወጽላሎተ ሞት ርእየ ብርሃነ ዐቢየ’ ያለው ከዚህ
በመነሣት ነው፡፡ (ውዳሴ ማርያም ዘረቡዕ)፡፡
ጨለማ ውስጥ ያለውን የሰው ዘር ሊያድንና በታላቅ
መገለጥ ራሱን ሊገልጥ (ሊያሳውቅ) ለአዳም ቃል እንደገባ፣
ነቢያትን እንዳናገረ እውነተኛው ብርሃን እግዚአብሔር (ዮሐ.1፡
4፣ ዮሐ.1፡9፣ 1ኛ ዮሐ.1፡5) ወደ ዓለም መጣ፡፡ ለብርሃን
ጨለማ አይስማማውምና ከጨለማ ከተለየች ከድንግል
ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ሰው ሆነ፡፡ በወንጌልም
“እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” አለ (ዮሐ.8፡12)፤ ዓለምን
ከጨለማ
ጥፋት ሊያድን ተገልጧልና/ ታውቋልና፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም
በሰኞ ውዳሴ ማርያም ‘ብርሃን ዘበአማን ዘያበርህ ለኩሉ
ሰብእ’ (ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን) አለው፡፡
በኒቂያ የተሰበሰቡ 318ቱ ሊቃውንትም ፀሐየ ፅድቅ ክርስቶስን
‘ብርሃን ዘእምብርሃን’ (ከብርሃን የተገኘ ብርሃን) አሉት፡፡ ቅዱስ
ያሬድም “ ወካዕበ ይቤ በአፈ ዳዊት ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ
እግዚአብሔር ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም ዘያበርህ ላዕለ
ጻድቃን” (በዳዊት አፍ እንደ ተነገረ ብርሃን በሆነው
በእግዚአብሔር ስም የሚመጣና በጻድቃን ላይ የሚያበራ
የተባረከ ነው) ያለው ስለ ክርስቶስ በተናገረበት አንቀጽ ነው፡፡
ዳዊትም አስቀድሞ ‘ፈኑ ብርሃነከ’ ብርሃንህን ላክልኝ ብሎ
ዘምሮ ነበር፡፡ መዝ. 42/43፡3-4)፡፡
21
ከላይ ባየነው መልኩ መጻሕፍት ሁሉ ተባብረው
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን እውነተኛ ብርሃንነት
ይመሠክራሉ፡፡ እርሱን አምላክ ብለን ድንግልን ወላዲተ
አምላክ፣ እርሱን ጌታ እርሷን የጌታ እናት፣ እርሱን ጌታ እርሷን
እመቤት፣ እርሱን አምላክ ወሰብዕ እርሷን ድንግል ወእም
እንደምንለው እርሱን ብርሃን ብለን እርሷን እመ ብርሃን
እንላለን፡፡ እንደውም “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” (ዮሐ.8፡12)
እንዳለ ቅዱሳኑንም “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ” (ማቴ.5፡
14) ብሏልና እርሷንም ብርሃን እንላታለን፡፡ በነገረ ማርያም
ትምህርት ቴክታና ጴጥርቃ ስለተባሉ ከእመቤታችን ወደኋላ 7
ዘር ስንቆጥር ስለምናገኛቸው አያቶቿ በስፋት ይነገራል፡፡
ቴክታና
ጴጥርቃ ሳይወልዱ ብዙ ቆይተው በሕልም ቴክታ እንቦሳ
ስትወልድ፣ እንቦሳይቱ ሌላ እንቦሳ ስትወልድ፣ እንዲህ እያሉ
እስከ 6 ድረስ ይሔዱና ስድስተኛይቱ ጨረቃን፣ ጨረቃም
ፀሐይን ስትወልድ ያያሉ፡፡ ሕልም ፈቺም መልካም ሴት
እንደሚወልዱ፣ እርሷም ሌላ መልካም ሴት እንደምትወልድ፣
እንደዚሁ እስከ ስድስተኛዋ ደርሰው ከፍጥረታት ሁሉ
የምትበልጥ እንደምትወለድ ነግሯቸው የፀሐይ ነገርን ግን
አልተገለፀልኝም ይላቸዋል፡፡ ቴክታ ዴርዴን፣ ዴርዴ ሲካርን ፣
ሲካር ቶናን፣ ቶና ሔርሜላን፣ ሔርሜላ ሐናን ይወልዱና
ጨረቃ
የተባለችውን እመብርሃን ሐና ከኢያቄም ትወልዳለች፡፡ ጨረቃ
የተባለችው እመቤታችንም ዘእንበለ ዘርአ ብእሲ (ካለ ወንድ
ዘር) ፀሐይ የተባለውን እውነተኛውን ብርሃን ክርስቶስን
ወለደችው፡፡ እመቤታችን አማናዊ ፀሓይ ክርስቶስን በመውለዷ
ሊቃውንት አዲሲቷ ሰማይ ብለዋታል፡፡ ስለዚህ ድንግልን
የብርሃን መገኛ፣ የብርሃን ደጅ - ኆኅተ ብርሃን እንላታለን፡፡
21
ጠቢቡ ሰሎሞንም ስለ ጨረቃነቷ ስለ ብርሃንነቷ
ሲናገር “መኑ ይእቲ ዛቲ እንተ ትሔውጽ ከመ ጎሕ ሠናይት
ከመወርኅ ወብርህት ከመፀሐይ” (ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን
የምትጎበኝ እንደጨረቃ የተዋበች፣ እንደ ፀሐይም የጠራች
ዐላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማናት?) በማለት
ገልጿታል፡፡ (መኃ.6:10 )፡፡ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም
“ወአንሰ እትፌሣሕ በእንቲአኪ ኦ ሀገረ እግዚአብሔር
ወእትሐሰይ ብኪ ኦ ኤዶም ገነት ነባቢት እንተ ርእዩኪ ነቢያት
ከመጎሕ ድልው ለወሊደ ፀሓይ በከመ ይቤ ሰሎሞን አቡኪ አይ
ይእቲ ዛቲ እንተ ታስተርኢ ከመጎሕ” (እንደ ተዘጋጀ ወገግታ
ነቢያት ያዩሽ የምትናገሪ ኤዶም ገነት ሆይ ደስ እሰኝብሻለሁ፣
እንደ ማለዳ ብርሃን የምትታይ ይኽቺ ማን ናት? በማለት
አባትሽ
ሰሎሞን እንደተናገረ) በማለት አወድሷታል፡፡ (አርጋኖን
ዘሠሉስ
ምዕ. 5፡10-11)፡፡ አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ ፡
“ ዘካርያስ ርእየ ለወርኅ ሣባጥ በሠርቁ፤
ተአምረኪ ለዘይት ማእከለ ክልኤ አዕፁቁ፤
ማርያም ጽዮን ለብርሃን ትቅዋም ወርቁ፤
ዕዝራኒ በገዳም ከመ ወአለ ውዱቁ፤
ለሕብረ ገጽኪ ጽጌ ኅተወ መብረቁ፤”
(የብርሃን የወርቅ መቅረዙ ጽዮን ማርያም ነቢዩ
ዘካሪያስ በኹለቱ የወይራ አዕጹቅ መኻከል በየካቲት ወር
ምልክትሽን አየ፣ ዕዝራም በምድረ በዳ ወድቆ በዋለ ጊዜ
(ሱባኤ በገባ ጊዜ)፣ ጽጌ (አበባ) የፊትሽ ደም ግባት
ብልጭታው በፊቱ ብልጭ አለ (አንጸባረቀ)) ብሎ በብርሃን
እናትነቷ ማብራቷን መስክሯል፡፡ (ማኅሌተ ጽጌ ቁጥር 27)፡፡
ስለዚህ እመቤታችን ኆኅተ ብርሃን - የብርሃን መገኛ ናት፡፡
ዐይን መብራት እንደሚባል መጽሐፍ ቅዱስ
ያስረዳናል፡፡ (ማቴ.6፡22)፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊም
ሔዋንን
የታወረ የዓለም ግራ ዐይን ሲላት እመቤታችንን ደግሞ
በብርሃን
የተሞላ የዓለም ቀኝ ዐይን ይላታል፡፡ ሔዋን ወደ ጨለማ
ዓለምን ስትመራ ብርሃናማዋ ዐይን ድንግል ደርሳ ዓለምን
አዳነች፡፡ (Luminous eye, Sebastain Brock P.
70-73).
21
አስቀድመን የብርሃንን ድኅነትነትና ዕውቀትነት ብቻ
እንደምናይ ገልፀን ነበር፡፡ በአዳም ምክንያት ካገኘን ሞት
የመዳን ሥራ የተፈፀመልን በአምላካችን በክርስቶስ ሲሆን
ያዳነንም ከእመቤታችን ሰው በመሆን ነው፡፡ ስለዚህ
እመቤታችን አባቶች ምክንያተ ድኂን (የድኅነት/ የመዳን
ምክንያት) ይሏታል፡፡ አዳኙ ብርሃን ከእርሷ ተገኝቷልና ኆኅተ
ብርሃን መባሏም ለዚህ ነው፡፡ ከዕውቀት ጋር በተያያዘም
“በነገረ
መለኮት እንደ ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዐዋቂ የለም”
ይባላል፡፡ ይህ ሐዋርያ ዕውቀቱን ከየት እንዳገኘ አባቶች
ሲጠቁሙም “እነኋት እናትህ (ዮሐ.19፡20) ብሎ ጌታ
ድንግልን
በእናትነት ከሰጠው በኋላ ለ15 ዓመታት አስተምራው ነው”
ይላሉ፡፡ እመቤታችን ከዚህም በላይ ፍጡራን ሁሉ
የማያውቁትን
ምሥጢር ታውቃለች፡፡ በሠሉስ ትርጓሜ ውዳሴ ማርያም ላይ
እንደተጠቀሰው ከጌታ ዕርገት በኋላ እመቤታችንን ሐዋርያት
‘ጌታን እንዴት እንደወለድሽው ንገሪን’ ቢሏት እርሷ ግን ‘ይህ
ምስጢር ስንኳን ልናገረው ሳስበው ይጨንቀኛል፤ ተዉ፤
አይቻላችኹም፤ የረቀቀ ምስጢር ነው፤’ አለቻቸው፡፡ እነርሱ
ግን
“ግድ የለም ንገሪን” አሏት፡፡ እርሷም “ጊዜው ሠለስት ነበር
ቅጽረ ቤተ እግዚአብሔር ለሦስት ተከፈለ፤ ጉምና ካፊያ ኾነ፤
ወትሮ የማውቀው መልአክ ቀርቶ የማላውቀው መልአክ መጣ
“ወገሰሰ ዐጽፎ ዘየማን ወኮነ ኅብስተ ሕይወት ወገሰሰ ዐጽፎ
ዘፀጋም ወኮነ ጽዋዐ ሕይወት፤ ቀኝ ክንፉን ቢባርከው ኅብስተ
ሕይወት ሆነ በልቶ አበላኝ ግራ ክንፉን ቢባርከው ጽዋዐ
ሕይወት ሆነ ጠጥቶ አጠጣኝ ብላ ወደ ደገኛው ምሥጢር
ልትገባ ስትል መልአኩ መጥቶ ግሩም ድምጽ ቢያሰማቸው
ሁሉም ደንግጠው ወድቀዋል፡፡ “እርሷ ለበቃችው ምስጢር
እናንተ አልደረሳችሁም” ሲላቸው ነው፡፡ ስለዚህ እመቤታችን
ድኅነትና ዕውቀት የተገኙባት ብርሃን ናትና ኆኅተ ብርሃን
ትባላለች፡፡
21
ለዓለም የሚያበራውን እውነተኛውን ብርሃን ፀሐየ
ጽድቅ ክርስቶስን የሰጠችን እመ ብርሃን፣ ኆኅተ ብርሃን ድንግል
ማርያም በዓለም ጨለማ እንዳንዋጥ የምልጃዋን ጨረቃ
ታበራልን ዘንድ የእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ይሁን፡፡
21
ምንጭ:
† ይህ ጽሑፍ መታሰቢያነቱ ለውድ የመንፈስ እናቴ ለኆኅተ
ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤቴ ይሁንልኝ፡፡ †
በዲያቆን ሕሊና በለጠ ዘኆኅተ ብርሃን
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መስከረም 11 ቀን፣ 2008 ዓ.ም.)፡-
21
የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣
የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣
የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት
አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው
ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
†† † † ††
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት
ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን
፤ አሜን!!!
†† † † ††
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን
እንደገለጽክላቸው ለእኛም ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!!
†† † † ††
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክ ቡ ር

ሊቀ_ዲያቆናት_ቅ ዱስ_እስጢፋኖስ #መታሰቢያ

#እንኳን_ሊቀ_ዲያቆናት_ቅ ዱስ_እስጢፋኖስ #መታሰቢያ
ወርሃዊ በአል አደረሳችሁ አሜን
#እስጢፋኖስ፦የስሙ ትርጉም - በግሪክ ቋንቋ አክሊል ማለት
ነው፡፡ በግብሩ የቀን ሃሩር የሌሊት ቁር የማይለውጠው፣
መብራት ማለት ነው፡፡
አባቱ ስምኦን፣ እናቱ ሃና ይባላሉ፡፡
የተወለደው - ጥር 1 ቀን በእስራኤል ሃገር ውስጥ በብፅዓት /
በስለት/ ነው፡፡ ልዩ ስሟ ሐኖስ በተባለ ቦት ተወለደ
ከመጥምቁ ዮሐንስ እግር ሥር በመሆን ተምሯል፡፡
ጥቅምት 17 ቀን ሐዋርያት ሊቀ-ዲያቆናት አድርገው
ሾሙት፡፡
ወንጌልን በማስተማሩ አይሁድ በጠላልትነት ተነስተውበት
ጥር 1 ቀን በ34 ዓ.ም. በድንጋይ ተወግሮ በስማዕትነት
አረፈ፡፡ በዚህም ቀዳሚ-ሰማዕት ተሰኘ፡፡
ለአህዛብ ተአምራትን ያደርጉላቸው የነበረው ለምንድነው?
አህዛብ ያልተማሩ ስለነበሩ ልቡናቸውን ለመስበርና
የእግዚአብሔርን ኃይልነት ተረድተው እንዲገነዘቡ በማሰብ
ተአምራትን ያደርጉ ነበር፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስ በአህዛብ ፊት ያደረገው ተአምራት
ሊቀዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ በአህዛብ መካከል ቆሞ
ሲያስተምር ከቆየ በኋላ አንድ አንደበቱ ዲዳ የሆነ ሰው
አጠገቡ ቢመጣ በጆሮው የህይወት እስትንፋስ እፍ ቢልበት
መስማት የማይችለው መስማት ቻለ፡፡ በዚህም ጣኦት
አምላኪውን ናኦስ እና ተከታዮቹ ሁሉ ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ
ተመለሱ፡፡
ጣኦት አምላኪው ናኦስ በድርጊቱ በጣም በመናደዱ የተነሣ
በአጠገቡ የቆመውን በሬ ልክ ናኦስ በጆሮው ቢተነፍስበት
በሬው በምትሃት ለሁለት ተሰንጥቆ በመሞቱ ወደ ቅዱስ
እስጢፋኖስ የተመለሱት በናኦስ ምትሃታዊ ድርጊት
በመሣባቸው እንደገና ወደ ናኦስ ተመለሱ፡፡
የአህዛብ ልቡና ወላዋይ እንዳይሆንና እንዳይጠፉም በማሰብ
ናኦስ ለሁለት ሰንጥቆ የገደለውን በሬ በእግዚአብሔር ኃይልና
ድንቅ ሥራ ደግሞ ህይወት ዘርቶ ማስነሳት እንደማይችሉ
በማስተማር ልቦናቸው ወላውሎ ወደ ናኦስ የተመለሱትን
አህዛብ ገንዘቡ እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ኃይልነት እንዲያምኑ
አድርጓል፡፡
ናኦስ በአልሸነፍ ባይነትና በአጋንንት ረዳትነት ራሱን ወደ ላይ
እንዲንሣፈፍ አድርጎ በአየር ላይ ቢወጣ ቅዱስ እስጢፋኖስ
የእግዚአብሔርን ተአምር በማሳየት በትዕግስት ጠብቆ
በአጋንንት ረዳትነት ወደ ላይ የተነሳውን ናኦስ በትምዕርተ-
መስቀል ቢያማትብበት ይዘውት የነበሩት አጋንንት ሁሉ
ለቀውት ሲበተኑ ናኦስም ምድር ደርሶ ተንኮታኩቶ በመውደቁ
በጣኦት አምላኪነት የነበሩ ሁሉ ዳግም ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ
ተመልሰዋል፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስ አይሁድን መጀመሪያ ካስተማራቸው በኋላ
የዘለፋቸው ስለምንድነው
መጀመሪያ በዘለፋ ቢጀምር ይወግሩትና ይገድሉት ስለነበር
ምስጢሩን ይገልፅ ዘንድ ነው/ይህን የመሰለ ትምህርት
ባላስቀረልን ነበርና ነው/
አንድም ሰውን ከመዝለፍ በፊት መምከር ማስተማር
ይገባልና ነው
አንድም ከወደዱት ትምህርቱን ይቀበሉታልና ነው፡፡
***የአይሁድ ክስ ምክንያት***
የሙሴን ህግ በመሻር ኦሪት አትጠቅምም አትመግብም
አታድንም ሐዲስ ኪዳን/ወንጌል/ ግን ትመግባለች ታድናለች
በማለቱ፡፡ /የሐ.ሥራ. 6፤13-14/
እግዚአብሔርንም ይዘልፋል /ይሰድባል/ በማለት ነው፡፡
የሐ.ሥራ. 7፤50
አይሁድ እነዚህን ንግግሮች በእግዚአብሔር ላይ እንደተሰነዘሩ
ስድቦች በመቁጠር ነበር የወነጀሉት፡፡
የኦሪት የካህናት አለቃ እስጢፋኖስ ለተከሰሰበት መልስ ይሰጥ
ዘንድ ቢጠይቀው ... ለተከሰሰበት መልስ ከመስጠት ይልቅ
ከአብርሃም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ ያለውን የመጽሐፍ
ቅዱስ ጽሁፍ በሚገባ ተረከላቸው፡፡ በመጨረሻም
የተገለጠለትን ምሥጢር ‹‹... እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው
ልጅ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ተቀምጦ አያለሁ ...›› በማለቱ
ላለመስማት በታላቅ ጩኸት በመቃወም ከከተማ ውጪ
በማውጣት በድንጋይ ወገሩት፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስ በእርሱ ላይ እጃቸውን ላነሱበት ሁሉ ጸሎተ
ምህረት አድርሷል የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይህንን
ከኃጢአት አትቁጠርባቸው ሲል ነፍሱንም ለአምላክ አሳልፎ
በመስጠት በተወለደበት ዕለት ጥር 1 ቀን በ34 ዓ.ም.
በሰማዕትነት አልፏል፡፡ ይህም የመጀመሪያው /ቀዳሚ/
ሰማዕት አሰኝቶታል፡፡
ከአብርሃም መጀመሩ ነገረ ልደት/ግዝረት የተከናወነው/
የተጀመረው ከእርሱ ጀምሮ ነው፡፡
***የክርስቶስ አብነት የሆነበት ዓበይት ነጥቦች***
ጌታ ነፍሴን ተቀበላት እንዳለ ሁሉ እስጢፋኖስም አቤቱ ጌታ
ሆይ ነፍሴን ተቀበላት ብሏል፡፡
ጌታ አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው
እንዳለ እስጢፋኖስም ጌታ ሆይ ይህን ኃጥአት አትቁጠርባቸው
ሲል ጸልዮዋል፡፡
በጌታ ጸሎት ፊያታዊ ዘየማን ወደ ንስሐ በመምራት ገነት
መንግስተ ሰማያትን ወርሷል
የክርስቶስ መስቀል ሙት ያስነሣ ድውይ ይፈውስ እንደነበር
ሁሉ የቅዱስ እስጢፋኖስ አፅም ሙት ያስነሣ ድውይ ይፈውስ
ነበር፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስ የተወገረበት ድንጋይ ሰባት አብያተ
ክርስቲያናት ታንፆበታል፡፡ /ሰባት ቤተክርስቲያናትን አንጿል፡፡/
የቅዱሳን ሕይወት አብነታችን እንዲሆነን ታሪካቸውን
ተጋድሎዋቸውን ለእግዚአብሔር ያላቸውን ቅንአት መማር
ማወቅ ይገባናል
ኤዎስጣቲዮስ የሚባል ሊቅ-በቅዱስ እስጢፋኖስ ጸሎት
የጠፋውን ልጅ ሳኦል /ጳውሎስን/ ቤተክርስቲያን አስገኝታለች
ሲል ተናግሯል፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስ የተቀዳጀው ሦስቱ አክሊላት፡-
ስለንፅህናው ስለድንግልናው
ስለሰማዕትነቱ /ስለምስክሩ/ ስለተጋድሎው
ስለስብከቱ /ስለትምህርቱ/ ስለተአምራቱ
የቅዱስ እስጢፋኖስ ሁለቱ ስሞች፡-
ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ
ሐዋርያት በሰባቱ ዲያቆናት ላይ አለቃ አድርገው በሾሙት ጊዜ
የተሰጠው ስያሜ ነው፡፡
ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ
ከጌታ ቀጥሎ ከምእመናን የመከራውን ገፈት ከተቀበለ /
ሰማዕትነትን ከተቀበለ/ በኋላ የተሰጠው ስያሜ ነው፡፡
የቀዳሚ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ አፅሙ ሙትን ያስነሣ
ድውይን ይፈውስ ነበርና አይሁድ እንደ ክርስቶስ መከራ
መስቀል የቅዱስ እስጢፋኖስ አፅሙ አርቀው በመቆፈር
ቀብረው በላዩም ቆሻሻ በመጣል ለ300 ዓመት ያህል
ተቀብሮ እንደ ክርስቶስ መስቀል ተቆፍሮ በመውጣት
መስከረም 15 ቀን አፅሙ ወጥቶ በክብር በስሙ የታነፀው
ቤተክርስቲያን አርፏል፡፡
በቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ሞት ምክንያት ማኀበረ-
እስጢፋኖስ በመበተኑ ለአህዛብም ወንጌል መስበክ ተጀመረ፡፡
ወንድሞች መባላቸው ቀረና ክርስቲያን ተባሉ፡፡
የቤተክርስቲያን አባቶች የቀዳሜ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ
ሞት ለክርስትና እምነት መስፋፋት ዋነኛ ምክንያት መሆኑ
የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራውን እንድናይበት አድርጎናል ሲሉ
ይገልፁታል እውነት ነውና፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
#ረድኤት_በረከቱ_ይድርብን _አሜን!!

የከበሮ ክፍል ምሳሌያዊ ትርጉም

ተዋህዶ-ሀይማኖታችን: የከበሮ ክፍል ምሳሌያዊ ትርጉም: የከበሮ ክፍል ምሳሌያዊ ትርጉም አለው ምሳሌውን ግልጽ ለማድረግ የሚከተለውን ስዕላዊ መግለጫ እንመለከት እና ወደ ትንታኔው እንሂድ። ከበሮ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ...

ተዋህዶ-ሀይማኖታችን: መፃጉዕ (የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት)

ተዋህዶ-ሀይማኖታችን: መፃጉዕ (የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት): በ አባ ዘሚካኤል ደሬሳ «ተንሥዕ ንሣዕ ዓራተከ ወሑር፤ ተነስተህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ» /ዮሐ.5፡8/ የዐቢይ ፆም አራተኛው ሳምንት መጻጉዕ ይባላል፡፡ ይህ ዕለት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድ...